ውድ አንባብያን እዚህ ገጽ ላይ የሚጻፉ ጽሑፎች ዓላማ የግለሰቦችን ስም ወይም ድርጊት በማንሳት ከዚህ በፊት ሌሎች በአባቶች ላይ የሞራል ገደላ እንዲሚያደርጉት አንዱን አባት አጉልቶ ሌላውን ለማኮሰስ ሳይሆን ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ “የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን” ዮሐ 3፡11 እንዲል መረጃና ማስረጃ ላይ ተደግፈን መጻፍ ነው፡፡ይሁን እንጂ ማንም ሰው ይሄ መረጃችሁ የተዛባ ነው፣ ሚዛናዊነት ይጎድለዋል ቢል ለማስተካከልና ለማረም ዝግጁዎች ነን፡፡ ዓላማችን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን የወንበዴዎች ዋሻ ያደረጓትን እና የሚያደርጉትን ለማረም ከጥፋታቸው እንዲመለሱ ለማደረግ እና ማንም በምንም ደረጃ ያለ ቢሆን በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እየቀለደ እንዳይኖር ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ገጽ የሚለቀቁ ጽሑፎችን በዚህ ዓውድ ሁናችሁ ታነቡ ዘንድ በቅድስት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስም ልመናቸንን እናቀርባለን፡፡
ከዚህ በፊት በጻፍነው ጽሑፍ ውስጥ የሐራ ዘተዋሕዶ የፌስቡክ ገጽ እና የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ፀሐፊ እና ባለቤት አንድ መሆኑን በአጭሩ ለማሳየት ሞክረናል፡፡ እንደሚታወቃው ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ከምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሚዲያነት የተቀየረ ሲሆን ባለቤትነቱ የብጹዕ አቡነ ሔኖክ ነው፡፡ጸሐፊው አጻፊው ዘዋሪውን ግን ኤርምያስ ኪሮስ መሐሪ ነው፡፡ ይህን ለማረጋገጥ ብዙ ቦታ መሄድ ላያስፈልግ ይችላል፡፡ ሚዲያው ሲቋቋም ዓላማ አድርጎ የነበረው ሚዛናዊ ቤተክርስቲያንን የሚበጅ መረጃ ለማካፈልና ለትምህርት ነበር፡፡
ይሁን እንጂ በዚህ ዓላማ ጸንተው ለመጓዝ ችግር ገጠማቸው፡፡ ይኸውም አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በወቅቱ በከፍተኛ ብልሹ አሠራር እና ሙስና እየተጨማለቀ በመምጣቱ ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውስጥ ያሉ አብያተ ክርስቲያናትን የልማት ሥራ መጎብኘት በሚል ሰበብ በእነ ኤርምስ እና ዮሐንስ ቀኖ ፕሮግራም አውጪነት በኩርቱ ፌስታል የሚሰበሰበው ብር በማኅበራዊ ሚዲያ መውጣት እየተበራከተ በመምጣቱ የስድብ አፍ የሚሆናቸውን የፌስቡክ ገጽ መክፈት ግድ አላቸው፡፡ በዋናው ገጽ(በተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል) ዜና ቤተክርስቲያን በጭብብሉ ገጽ(ሐራ ዘተዋሕዶ) ገድለ ዲያብሎስ እና ዜና ዲያብሎስ ወሳጥናኤል ማስተላለፍ ጀመሩ፡፡
ታዲያ ጊዜው በብዙ አቅጣጫ ቤተክርስቲያንና አገልግሎታን በአጠቃላይ ሕልውናዋን የሚፈታተን ሁነቶች የተከሰቱበት ወቅት ነበር፡፡ እናላችሁ በወቅቱ ይህን በይሁዳ ከረጢት(በኩርቱ ፌስታል) የሚሰበሰብ ከደሀ መቀነት ተጠራቅሞ በዕንባ ታብሶ ወደ ሙዳየ ምጽዋት የሚገባ ገንዘብ ዝርፊያ እንዲቆም ጥረት ምክርና የሀገረ ስብከቱ ሕገ ወጥ አካሄድ ይስተካከል ብለው ሲታገሉ የነበሩት የወቅቱ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ላይ ዘመቻ ተከፈተ፡፡ በባለፈው ጽሑፍ እንዳስነበብናችሁ ከግንቦት 15 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ግንቦት 15 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ለሁለት ዓመታት ከጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ እስከሚወርዱ #ከ40 ጊዜ በላይ በዚህ የኤርሚ ገጽ ከፍ ዝቅ እየተደረጉ ተሰድበዋል በአንጻሩ አቡነ ሔኖክ ከንጉሥነት እስከ ቅዱስነት በሚደርስ ማንቆሎጳጰስ ተወድሰዋል፡፡ ስለዚህ ማንም ብዙ የጠለቀ ዕውቀት ሳይፈልገው የሐራ ተዋሕዶን ገጽ ልጥፎች(ፖስቶች) ቢመለከት የአቡነ ሔኖክ ጠላቶች ወይም ተቃራኒ ሀሳብ የሚያቀርቡ አልያም ነገ ሊሄዱበት ላቀዱት እንቅፋት ይሆናሉ ተብለው በሚታሰቡት ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ እና በየሀገረ ስብከታቸው ለአድማ ማስነሺያ የሚጠቀሙበት ነው፡፡ መጽሐፍ እግዚአብሔር ከሚጠላቸውና ከሚጸየፋቸው ስድስት ነገሮች መካከል “…በወንድሞች መካከል ጠብን የሚዘራ” ምሳ 6፡-19 እንዲል ልብ ይሏል፡፡
የሆነ ሆነና እስቲ ቀጠሮ ወደ ያዝነው የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል እና የሐራ ዘተዋሕዶ ፌስ ቡክ ገጽ ባለቤቱ ኤርምያስ አለነ (ኪሮስ) በስደት ባለበት ሀገረ እንግሊዝ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ ከማን ጋር ምን እኩይ ተግባር እየሠራ ነው? ወደ ሚለው እንዝለቅ፡፡
#ለመሆኑ ኤርምያስ አለነ ማነው? ኤርምያስ ኪሮስ ማነው?
ኤርምያስ ሽሮ ሜዳ ተወልዶ ያደገ እና ለትምህርት ያልተፈጠረ መሆኑን በጊዜ አውቆ አባቶችን በመጠጋት ሥጋዊ ሕይወቱ እንደሚለወጥ በማመን ለዚህም በዓላማ ሲሠራ የነበረ ወንድም ነው፡፡ ስለ ሽሮሜዳ ሥላሴ ሕይወቱና ቆይታው መዘርዘር ለያዝነው ዓላማ ስለማይጠቅመን እንተወው እና ቀጥታ ከምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት እስከ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ፤ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እስከ ሀገረ እንግሊዝ እንጓዝ ፤ ከብጹዕ አቡነ ሔኖክ ጋር ያለውን ዝምድና እና ግኙነት እንመልከት፡፡ ሠናይ ንባብ…
#የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
ይህ ሚዲያ ሲቋቋም በጎ ዓላማ ይዞ አማራጭ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ድምጽ ለመሆን ነበር፡፡ የስቱዲዮ ምርቃቱ የአንድ ቤተክርስቲያን ያህል የተዳነቀ፣ ግርግር የበዛበት እና ብጹአን አባቶች የተገኙበት ነበር፡፡ በዋናነት ይህ ሚዲያ የምዕመናን ቀልብ እንዲይዝና ትኩረት እንዲያገኝ ያደረገው በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስበከት የደረሰው አሰቃቂ የምዕመናን እና የካህናት(የሰማዕታት) እልቂት እንጂ የኤርሚ የሚዲያ ዕውቀት ወይም የአባቶች ጸሎት እንዳልሆነ እሙን ነው፡፡ ልክ ሚዲያው እንደተቋቋመ የዚህ ሚዲያ የፊት መስመር አጥቂና ተሰላፊው የነበረው በቅጡ እንኳ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ያላጠናቀቀው ምናልባት ልክ እንደ ፓስፖርቱ የትምህርት ማስረጃውን ፎርጅድ ካላሰራ በስተቀር የአባቱንና የአያቱን ስም ያስቀየረው የቀድሞው ኤርምያስ አለነ ወይም የዛሬው ኤርምያስ ኪሮስ ነበር፡፡
በዚህ ሚዲያ ስም የዋሑን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ምዕምን ዛሬ የወደቁበትን ያሉበትን እንኳን ለአንድ ቀን ተዘክሮላቸው የማያውቁ የሰማዕታቱን ምስል ወድምጽ በማቅረብ በሰማዕታቱ ደም ላይ በመረማመድ ከኢትዮጵያ ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት እስከ አሜሪካ፣ አውሮፓ፣የዓለም ሀገራት ሁሉ የሚደርስ የገንዘብ መቀፈያ መረብ ተዘረጋ አይተውትም ሰምተውትም ያማያውቁት ፈራንካ ለእነ ገንዘብ ብርቁ ይጎርፍ ጀመር፡፡ ወራት ባለሞላ ጊዜ ውስጥ ሰማዕታቱን ተረሱ ስለ ተጠቃሚነት ማሰብ ተጀመረ፡፡ በኋላ ላይ ኤርሚ በእግርና በራይድ እየተንከራተተባቸው ስለተቸገሩ ከተሰበሰበው ገንዘብ ላይ ቦጨቅ በማድረግ ለኤርሚ ቅንጡ መኪና እና ሌሎች ነገሮች ተሟሉለት ከዚያማ ኪሱም ልቡም ማበጥ ጀመረ፡፡ ይህን ተከትሎ እነ መ/ር ዘመድኩን የተዘረፈው ብር እንዲመለስ ጥያቄ ማንሳት ጀመሩ፡፡
ይህን ድንገተኛ ዓለም አቀፍ ውርደት ለማለፍ ሁለት ነገር ማድረግ ነበረባቸው አንደኛው ገንዘቡን ማጠብ(Money laundary) ማድረግ ፣ ሁለተኛ ምንም እንኳን ጠቅላይ ቤተክህነት የሚዲያ ፈቃድ የሰጠው ለምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ቢሆንም ማንም ወደ ኋላ ሄዶ ሰለማያጣራ(ፈቃድ መስጠት እንጂ ኦዲት የሚያደርግ እንደሌለ ስለሚያውቁ ቢመጣም አፉን በፍራካ ስለሚይዙ) የሚዲያውን ስም መቀየር አንዱ የገንዘብ ማጠቢያ መንገድ በመሆኑ በፍጥነት ወደ ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከልነት ተቀየረ፡፡ በዚህ መንገድ ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ተደራጀ ኤርሚም ይህንን የድፍረት ኃጢአት በአሸናፊነት ስለተወጣ በኋላ ላይ እንደምናየው እኩይ ተግባሩን አጠናክሮ ቀጠለ፡፡
#ኤርምያስ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት
አቡነ ሔኖክ ከዚህ በፊት በአገለገሉባቸው ቦታዎች ስማቸው ይህን ያህል በክፉ አይነሳም ነበር፡፡ ነገር ግን ምዕራብ አርሲን ለቀው ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስነት ከመጡ በኋላ በሰማዕታት ደም በመነገድ የድፍረት ኃጢአትን ገንዘብ ባደረጉ በእነ ኤርምያስ እና ዮሐንስ ቀኖ በመሰሉ አማካሪነትና መርሐ ግብር አውጪነት ቅድመ ቅዳሴ ፣ ጊዜ ቅዳሴ እና ድኅረ ቅዳሴ ፣ ቅድመ ንግሥ እና ድኅረ ንግሥና የመሳሰሉ የገንዘብ መቀፈያ መርሐ ግብር እያወጡ ስማቸውን አባ ኩርቱ ተብሎ እንዲነሳ የዋሁን አባትገፍተው አስገቡአቸው የእነሱን ድፍረት አለማመዷቸው፡፡ እጅግ ያሳዝናል፡፡ ይህ ሁኔታ አሁን ባለቡትም የደቡብ እና ምዕራብ አፍሪካ ተከትሏቸው እንደሄደ አንድ በደቡብ አፍሪቃ የሚኖር የዚህ ገጽ አባል “በበፊቶቹ ብጹአን አባቶች የማናውቀውን አንድ ቤተክርስቲያን መጥተው እንዲጎበኙ ከተፈለገ በቅድሚያ 5ሺ ራንድ የጉብኝት አበል አዘጋጁ መባሉ ለጊዜው መደናገጥን ቢፈጥርም ዛሬ ላይ ግን ስለለመድነው እየፈጸምነው እንገኛለን” ማለቱን አስታወሳለሁ፡፡ አሁን ደግሞ ዮሐንስ ቀኖ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ባካበተው የዘረፋ ልምድ የበለጠ እንደሚያሳልጠው ይጠበቃል፡፡ ደቡብ አፍሪካዎች እግዚአብሔር ይሁናችሁ፡፡
ወደቀደመ ነገር እንመለስና ኤርሚ የአዲስ አበባ ጉዳይ ማክተሙን ሲያውቅ ከመሞት መሰንበት በሚል ቡድን አደራጅቶ አስቀድሞ ከዚህ ክፍል በፊት እንደተጻፈው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጉዳይን ያነሱ ይሁኑ የጠረጠራቸውን በሙሉ ሐራ ዘተዋሕዶ የሚባል ገጽ ከፍቶ መዋጋት ጀመረ ለሁለት ዓመታት በተከታታይ እንደ እነ ብጹዕ አብርሃም የመሳሰሉት ስም በማጥፋት የአልሞት ባይ ተጋዳይ ትግል አደረገ፡፡ ግን ምን ያደርጋል አልተሳክቶም!!!
ልብ አይሞት አይደል ሌላ መፍትሔ ማፈላለግ ጀመረ…አቡነ ሔኖክ ሲወርዱ ሙስና የተቀበላቸው ቃል የገባላቸው አገልጋዮች እንደማይለቁት ያውቃል…ስለዚህ ለአቡኑም ይሁን ለራሱ ማረፊያ ቦታ መፈለግ ጀመረ…ያለውን ጥሪት ሁሉ ሰበሰበ መኪናውም ተሸጠ፡፡ አሜሪካ መሄድ ከባድ ነው በወቅቱ፡፡ ስለዚህ እንግሊዝ ሀገር ወደ አክስቶቹ ጋር በስደት መሄድ አለበት፡፡ አቡነ ሔኖክ ደግሞ ተገፍተዋል በሚል ከቻለ ገንጥሎ የራሳቸው ቤተክርስቲያን እንዲኖራቸው አሊያም …ብቻ በእንግሊዝ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ስም የጳውሎስ፣ የኬፋ፣ የአጵሎስ ብሎ ማቋቋም እንደሚቻል ካህናቱም እርስ በእርሱ የተከፋፈለና ለበርካታ ዓመታት ሲነታረኩ የኖሩ መሆኑን አጠና ስለዚህ ስደት ተጀመረ፡፡
#ኤርምያስ በዩጋንዳ ካምፓላ
ቀጥታ እንግሊዝ መግባት ከባድ በመሆኑ በሰማዕታት ደም ላይ ተረማምዶ እና ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የዘረፈውን የግፍ ገንዘብ በመሰብሰብ ዕድሜውን ከ30 ወደ 20 በመቀነስ፣ ስሙን ከኤርምያስ አለነ ወደ ኤርምያስ ኪሮስ በመለወጥ፣ ዜግነቱን ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ በመለወጥ፤ ልጅነቱን ከእናቱ ወደ አክስቱ በመቀየር ስደተኛ ካምፕ ዩጋንዳ ካምፓላ ገባ፡፡ ኤርምያስ ይሄን ሁሉ ነገር ማድረጉ ምናልባት እዚህ ሀገር መኖሩ ለሕይወቱ ሥጋት ፈጥሮበት ሊሆን ስለሚችል እና ሌሎችም የሚያደርጉት በመሆኑ ብዙም ከዚህ ጋር ተያይዞ ለሚነሱ ጉዳዮች ትኩረት አንሰጠውም፡፡ የእኛ የትኩረት አቅጣጫ ግን በዚህ ሁኔታ እንግሊዝ ሀገር ከገባ በኋላ የፈጸማቸው እና ያስፈጸማቸው እኩይ ተግባራት ናቸው፡፡
#ኤርምያስ በሀገረ እንግሊዝ
ከዚህ በኋላ ያለው ጉዳይ ብዙ ሰዎችን ሊነካ ቢችልም አስቀድመን እንግሊዝ ሀገር ባሉ ወዳጆቻችን አርፎ የስደት ወረቀቱን እንዲያስተካክል መክረናል አስመክረናል፡፡ ግን ምንም አታመጡም ባይ ሆነ፡፡ በነገራችን ላይ ኤርምያስ በእንግሊዝ ሀገረ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ያደረሰውን ግፍ፣ ጥላቻና የማን አለብኝነት ተግባር በውል መረዳት ለሌሎችም በውጪ ያሉ የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናትን ችግር ለመቅረፍ እንደመፍትሔ አመላካች ይሆናልና በትኩረት ይታይ እንላለን፡፡
በሀገረ እንግሊዝ ካሉ የዚህ ገጽ አባላት መረዳት እንደቻልነው፡፡ ኤርሚ መጀመሪያ አከባቢ የበግ ለምድ ለባሹ ተኩላ ማንነቱ በፍጥነት እንዳይታወቅ የወቅቱ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ያዕቆብ ጋር ወደጅ እና የቅርብ ሰው እንደሆነ በመስበክ በቃልም በተግባርም ይንቀሳቀስ ነበር፡፡ በኋላ ላይ ግን አቡነ ሔኖክን ይመራበት በነበረው መልክ የማይሄዱ የአፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩ፣የራሳቸው የአስተዳደር ዕውቀትና ችሎታ ያላቸው በቀላሉ አባ አባታችን..አቦ አቦ በማለት የማይሸነፉ መሆናቸውን ሲረዳ ከእሳቸው መራቅ ጀመረ፡፡ በውስጡ ተቀበሮ ልፈንዳ ልፈንዳ እያለ የነበረውን ኢትዮጵያም እያለ እኔማ እንደ እነ አባ እገሌ በውጪ ሀገር የግል ቤተ ክርስቲያን ሊኖረኝ ይገባል የሚል ቁጭትና ተስፋ ስለነበረው ብጹዕነታቸው ለዚህ ደግሞ እንደማይመቹ ሲገባው የራሱን ቡድን በመመስረት በየአጥቢው በመሄድ ሀገረ ስብከቱን የማወክ ተግባር ጀመረ፡፡ በሁሉም ዘንድ ከሚታወቁ እኩይ ተግባሮቹ መካከል በጣም ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል፡-
- ስቶክ ኦን ትረንት ደብረ ሃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ምዕመናንን የመከፋፈል ሥራ መሥራት፤የደብሩ አስተዳዳሪን ሳያሳውቅ በሌሉበት የሰበካ ጉባኤ አስተዳደር ምርጫ በማድረግ ምዕመናኑ ላይ መለያየት እንዱፈጠር ማድረግ
- የድንች ወይም የውሸት ማኅተምና የደብዳቤ ራስጌ በመጠቀም በየደብሩ አስተዳዳር የማይታወቁና ያልተፈቀዱ ደብዳቤዎችን መጻፍ
- በቤተ ክርስቲያን አውደ ምሕረት በእራሱ ቡድን በአስነሳው ጸብ አጫሪነት፥ ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ሕፃናት ልጆች ፊት አካላዊ ግጭት ማስነሳት
የመሳሰሉት ተግባራትን እየፈጸመ ሲሆን ይህ ሁሉ ግን ግርግር ለሌባ ያመቻል እንዲሉ መጀመሪያም አንግሊዝ ሀገር ሲመጣ ግቡ በእርሱና በአባቱ ስም የግል ቤተክርስቲያን ባለቤት መሆን በመሆኑ በዚያ መንገድ ላይ ያገኛቸውንና እንቅፋት ይሆናሉ ሊሆኑ ይችላሉ ብሎ ያሰባቸውን በሙሉ ልክ እንደቆሰለ አውሬ መናከስ ጀመረ፡፡
#የአቡነ ሔኖክና የኤርምያስ የግል አብያተ ክርስቲያናት በሀገረ እንግሊዝ
በቀደመው ዘመን የሲኖዶስን ከሁለት መከፈል እንደምቹ አጋጣሚ በመጠቀም ስሙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ንብረትነቱ ግን የአቡነ እገሌ፣ የመምህር እገሌ…የሆነ ቤተክርስቲያን ተመሠረተ እየተባለ እንሰማ ነበር፡፡ በኋላ ላይ ባለን መረጃ መሠረት ይህንን ጉዳይ ወደፊት በስፋት የምናየው ቢሆንም የአባቶች አንድነት ሲፈጸም አብያተ ክርስቲያናት ይዞታ ውኅደት ግን አልተደረገም፡፡ እስካሁንም በሀገረ አሜሪካ በአንድ ጳጳስ፣ ወይም በቦርድ አሊያም በሆነ ማኅበር አባላት ስም የተመዘገቡ አብያተ ክርስቲያናት፣ አሁን ደግሞ በትግራይ ስም ያሉ አያሌ ናቸው፡፡ ነገ ጊዜው ሲደረስ ሁሉም ወደ አንድ ባለቤትነት ይካተታሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ የሆነ ሆነና ኤርምያስ ሆዬ ምንም እንኳን ምንም ዓይነት የቤተክርስቲኒቱ ትምህርት ቤት ገብቶ የቀለም ጠብታ ባይነካው በእንግሊዝ ሀገር የግል ቤተክርስቲያን መመሥረት የሚያመጣውን መዘዝ ቢያውቅም በጎን የሀገረ ስብከቱን ኃላፊዎችና ሊቀጳጳሱን በደብዳቤ የመሠረትኩትን ቤተክረስቲያን አጽድቁልኝ እያለ ከዓመት በፊት ግን ቅደመ ዝግጅት በማድረግ አቡነ ሔኖክን ከውስጥ አዋቂ ምንጮች የክፍሉ ሊቀጳጳስ እንግሊዝ የማይኖሩበትን ጊዜ በማጥናት በተዋሕዶ ሚደዲያ ማዕከል ““አጼ ኃ/ሥላሴ በስደት ወቅት የኖሩበትን ታሪካዊ ቤት ጎበኙ” እያለ በሌላ በኩል በተመሳሳይ ቀን በራሱና ፌስ ቡክ ገጽ እና በግሉ ቤተክርስቲያን ገጽ ግን ወደ ሀገረ እንግሊዝ የመጡበትን ዋና አላማቸው የሆነውን ካህን ያለ ሀገረ ስብከታቸው ሾሙ ይልልሃል፡፡ ይህ ተሿሚ ከዚህ በፊት በእንግሊዝ መንግሥት ሀገረ ስብከቱ ባልፈጸመው ገንዘቡን ማጠብ(Money laundary) አድርጋችኋል በሚል ከስድስት ሰዓት በላይ የፈጀ አላስፈላጊ ምርመራ ውስጥ እንዲገቡ ያደረገውን ባለውለታቸውን እና በዩኬ “ማኅበረ ካህናት” በሚል ከምዕመናን በምዕራብ አርሲ ሰማዕታት ስም ተሰብስቦ ለግል ፍጆቷ የዋለውን ብር ሲያስተባበር ከነበሩት መካከል ዲ/ን ዳግማዊ ወርቁን ቅስና ያለ ሀገረ ስብከታቸው በመሾም የሐዋርያት ቀኖና ጥሰት በመፈጸም ጳጳሱ፣ ኤርምያስና ለእኩይ ተልእኮ የሾሙትን ቄስ ለሦስት በመሆን የግል ቤተክርስቲያን መሠረቱ::
በውጪ የግል ቤተክርስቲን ለመመሠረት ዋናኛው መንገድ በበጎ አድራጎት ድርጅት ማስመዝገብ ነው፡፡ ሕጋዊ እና የሚታወቁትም የኢ በዚህ ሥር ተመዝግበው እንደሚገኙ ልብ ይሏል፡፡ታዲያ የዚህ የእነ አቡነ ሔኖክ የበጎ አድራጎት ድርጅት( የግል ቤተክርስቲያን) መቼ ተመሠረ?
- የበጎ አድራጎቱ ስም፡ ተዋሕዶ ትረስት( Tewahedo Trust)
የበጎ አድራጎቱ የምዘገባ ቁጥር፡-1215254
Activities – how the charity spends its money
The Tewahedo Trust provides Oriental Orthodox theological courses for clergy and members of the Oriental Orthodox Church, supports youth spiritual development, and carries out charitable activities to assist those in need within the community.
ተግባራት
ተዋሕዶ ተረስት የኦሬንታል ኦርቶዶክ የሥነ መለኮት ትምህርት ለአገልጋዮችና ለአባላቶቹ ያስተምራል፤የወጣቶች መንፈሳዊ ዕድገትን ይደግፋል እና እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች እርዳታ ያደርጋል፡፡ የተለያዩ የእርዳታ ተግ
Charitable objects
TO ADVANCE THE CHRISTIAN RELIGION IN ACCORDANCE WITH THE TENETS AND DOCTRINES OF THE ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHEDO CHURCH
የበጎ እድራጎት ድርጅቱ ዓላማዎች
“በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ትምህርቶችና ዶግማዎች መሠረት የክርስቲያን ሃይማኖትን ማስፋፋትና ማጎልበት ነው።”
CIO(Charitable Incorporated Organisation) – FOUNDATION Registered 06 Oct 2025
በበጎ አድራጎት ድርጅትነት የተመዘገበው፡- እ.ኤ.አ 06 ኦክቶበር 2025(26/01/2018 ዓ.ም)
ሙሉ መረጃውን ገብተው ለማየት ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ
TEWAHEDO TRUST – 1215254
2. STOKE-ON-TRENT ST RUFAEL AND ST ABUNE ECHEGE YOHANNES ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHEDO CHURCH
የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ስም፡- በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የስቶክ ኦን ትሬንት ምዕራፈ ቅዱሳን ቅዱሰ ሩፋኤል ወእጨጌ አቡነ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን
የበጎ አድራጎቱ የምዘገባ ቁጥር፡-1213122
CIO(Charitable Incorporated Organisation) – FOUNDATION Registered 29 April 2025
በበጎ አድራጎት ድርጅትነት የተመዘገበው፡- እ.ኤ.አ 29 አፕሪል 2025(21/08/2018 ዓ.ም)
Activities – how the charity spends its money
We focuses on promoting the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church faith through worship and religious ceremonies. We conduct Twice a month services, provide religious education to children, and offer tailored services for Ethiopian, British and Eritrean communities. Additionally, we assist new migrants in settling in the UK while ensuring compliance with UK law and religious regulations.
ተግባራት
እኛ “በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት መሠረት በአምልኮና በሀይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች የሃይማኖቱን ማስፋፋት እንሰራለን፤ በወር ሁለት ጊዜ የአምልኮ አገልግሎት እናካሂዳለን፣ ለህፃናት ሀይማኖታዊ ትምህርት እንሰጣለን፣ እንዲሁም ለኢትዮጵያውያን፣ ለብሪታንያውያንና ለኤርትራውያን ማህበረሰቦች ተስማሚ አገልግሎቶችን እንሰጣለን፤ በተጨማሪም የአገሪቱን ሕግና የሀይማኖት መመሪያዎች በመጠበቅ አዲስ ስደተኞች በዩኬ እንዲደራጁ እገዛ እናደርጋለን ።”
Charitable objects
THE ADVANCEMENT OF THE ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHEDO FAITH AND TO PROPAGATE THE GOSPEL OF CHRIST IN ACCORDANCE WITH THE BASIS OF FAITH AS SET OUT IN THE PROVISIONS OF THE FTHA NEGEST AND IN ACCORDANCE WITH THE PRINCIPLES AND REGULATIONS OF THE ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHEDO CHURCH AS SET OUT IN THE QALE AWADEE THROUGHOUT ENGLAND THROUGH THE HOLDING OF RELIGIOUS SERVICES AND PRAYER MEETINGS, RELIGIOUS EDUCATION, CONDUCTING RELIGIOUS CEREMONIES, INTERFAITH ACTIVITIES, OUTREACH AND PASTORAL CARE IN THE COMMUNITY.
የበጎ እድራጎት ድርጅቱ ዓላማዎች
“የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነትን ማስፋፋትና መጠናከር፣ እንዲሁም በፍትሐ ነገሥት የተገለጹ የእምነት መሠረቶች መሠረት እና በቃለ ዓዋዲ ውስጥ የተወሰኑ መርሆዎችና ደንቦች መሠረት የክርስቶስን ወንጌል ማስፋፋት በእንግሊዝ ዙሪያ በሀይማኖታዊ አገልግሎቶችና የጸሎት ስብሰባዎች መካሄድ፣ ሀይማኖታዊ ትምህርት መስጠት፣ ሀይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች መፈጸም፣ ከሌሎች ሀይማኖቶች ጋር የጋራ እንቅስቃሴዎች ማካሄድ፣ ማህበረሰብ ውስጥ የውጭ እንቅስቃሴ ማድረግ እና መንፈሳዊ እንክብካቤና ድጋፍመስጠት ነው።”
ማስታወሻ፡- ይሄንን ቤተክርስቲያን ኤርምያስና ቀድሞ ከጁቢቲ በትልቅ ውንብድና የተባረሩት ፣ ኋላም ጣሊያን ሀገር አቡነ ሕርያቆስን ሲያውኩ የነበሩ፤ ያለ ሀገረ ስብከቱ ፈቃድና እውቅና ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጽ/ቤት የተመደቡት አባ ዮናስ መልከጼዴቅ ናቸው፡፡ የጥፋት ሰንሰለቱን ለቡ!
በነገራችን ላይ ስለ አባ ዮናስ እኩይ ግብር እንጻፍ ቢባል የቱን ትተን የትኛውን እንጻፍ? ነው የሚያስብል፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ ጊዜም ገጽም ስለማይበቃን እንደው እንደ መግቢያ እንዲሆን ይቺን ሊንክ ይጫኑ፡፡
ምዝበራ ያዳከመው የጅቡቲ ቅ/ገብርኤል ደብር: በህልውና ስጋት ውስጥ ነው፤ “አማሳኞቹ በሕግ ይጠየቁ፤ በልኡካን ምደባ ጥንቃቄ ይደረግ”/ምእመናን/ | ሐራ ዘተዋሕዶ
ስለ ብጹዕ አቡነ ሔኖክ ልጅ፣ ስለ ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከሉ እና ስለ ሐራ ዘተዋሕዶ መሳደቢያ የፌስ ቡክ ገጽ ባለቤት ሁለተኛ የግል ቤተክርስቲያን ሙሉ መረጃውን ገብተው ለማየት ይህንን ሊንክ ይጫኑ
STOKE-ON-TRENT ST RUFAEL AND ST ABUNE ECHEGE YOHANNES ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHEDO CHURCH – 1213122
ኤርሚ ታዲያ ሌላውን ወደ ማጣራት ሳንገባ የሁለት አብያተ ክርስቲያናት ባለቤት ሆነ ሕልሙም ተሳካ!
ሁለቱ ጉዳዮች የበጎ አድራጎት ምዝገባዎች በመከናወናቸው ምክንያት ሁለት ብጹን አባቶች ሆዴ ይሙላ ደረቴ ይቅላ ብለው በሚጓዙ ኤርምያስነ በመሳሰሉ የቤተክርስቲያን መዥገር እና ነቀርሳዎች ስህተት ውስጥ ገብተዋል::
- አቡነ ሄኖክ ፡- በሕክምና እና በጉብኝት ሰበብ ያለ ሀገረ ስብከታቸው በራሳቸውና በልጃቸው ስም ሁለት የግል ቤተክርስቲያናትን አቋቁመዋል፣ ሥልጣነ ክህነት ሰጥተዋል
- አቡነ ኤልያስ፡- እሊህን ብጹዕ አባት በስቶክ ኦን ትሬንት ያለሀገረ ስበከታቸው በመገኘት ሦስት ዲያቆናትን ሾመዋል፡፡ ሰሞኑን በግሪክ ጉዳይ የገጠማቸውን ሳስብ እና ከዚህ በፊት ቤተክርስቲያን በሁለት በተከፈለችበት ወቅት በፌስታል ብቻቸውን ዘመዳቸውን ጳጳስ አድረገው መሾማቸውን ባሰብን ጊዜ ከእሳቸው ምን እንማር ?እላለን
የሐዋርያት ቀኖና በእነዚህ ጉዳዮች
ቀኖና 1፡ ጳጳስ መጰጰስ ያለበት ከሁለት በላይ በሆኑ ጳጳሳት ነው፡፡
ቀኖና 14 አንድ ኤጲስ ቆጶስ ከራሱ ሀገረ ስብከት ውጭ ጣልቃ ለመግባት ቢሞክር፤ ይህን እንዲያደርግ በሌሎች እንኳን ቢጠየቅ፤ ይህን በማድረጉ ለበጎ ነገር መሆኑ ቢረጋገጥም እሱ በራሱ ፈቃድ እንኳን ቢሆን አያድርግ፡፡ ነገር ግን በሌሎች ጳጳሳት ፈቃድና ትእዛዝ እንዲሁም በነሱ ጥያቄ ካልሆነ በቀር፡፡
ቀኖና 31:አንድ ቄስ ጳጳሱን ንቆና አቃሎ ሕዝብ ሰብስቦና አስከድቶ ያለ ጳጳሱ ፈቃድ ሌላ ቤተ ክርስቲያን ቢያቋቁም! በጳጳሱ ላይ ምንም የሃይማኖት ጉድለት ሳይኖርበት ነውና ነቀፋ ሳይገኝበት ይህን ፈጽሞ ቢገኝ ከሹመቱ ይሻር፡፡ ምክንያቱም ቄሱ ሥልጣን ፈላጊ በመሆኑ በተመሳሳይ ሁኔታ ሌሎችን ካህናት በማሳሳቱ የተባበሩት ሁሉ ከሹመታቸው ይሻሩ፡፡ ምእመን ከሆነ ከቤተ ክርስቲያን ይለይ፤ ይህ ውሳኔ ካንድ ሁለት ጊዜ ተደግሞ በሦስተኛ ጊዜ ጳጳሱ ለመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ይሰጠው፡፡
ቀኖና 35፡ አንድ ኤጲስ ቆጶስ ከሀገረ ስብከቱ ውጭ በእሱ ክልል (ወሰን) ውስጥ በማይገኙ መንደሮች ከተሞች ሥልጣነ ክህነት መስጠት የለበትም፡፡ ከእሱ ሀገረ ስብከት ውጭ ሥልጣነ ከህነት መስጠቱ ከተረጋገጠበትና ይህንንም የፈጸመው ሥልጣኑ ከሚመለከተው ጳጳስ ፈቃድና ፍላጎት ውጭ ሆኖ ከተገኘ ከሹመቱ ይሻር፡፡እንዲሁም ሥልጣነ ክህነት ከእሱ የተቀበሉም ከሹመታቸው ይሻሩ፡፡
ቀኖና 36፡ አንድ ጳጳስ ጵጵስና ከተቀበለ በኋላ በተመደበበት ቦታ ለማገልገል ፈቃደኛ ሁኖ ካልተገኘና የእግዚአብሔርን መንጋ ለመጠበቅ ፈቃደኛ ካልሆነ ከሹመቱ ይሻር፤ ከሥልጣኑ ይወገድ፡፡ ግዴታውን ለመወጣት ፈቃደኛ እስኪሆን ድረስ እገዳው አይነሣለት፡፡ እንዲሁም ቄስና ዲያቆን በተመደቡበት ቦታ ለመሥራት ፈቃደኛ ካልሆኑ ከሥልጣናቸው ይታገዱ፡፡ ነገር ግን አንድ ጳጳስ ከተመደበበት ቦታ ሒዶ በምእመናኑ እምቢተኝነት ምክንያት ተቀባይ ቢያጣ የጵጵስና ሥልጣኑ አይያዝም፤ አይታገድም፡፡ ነገር ግን የዚያች ከተማ ካህናትና ምእመናኑ የተወዝዙ ይሁኑ፣ ከስህተታቸው ተመልሰው አቋማቸውን እስከሚያስተካከሉ ድረስ፡፡
በነገራችን ላይ ኤርምያስ እነዚህ ቀኖናዎች በፌስ ቡክ ገጾቻችን ላይ ከለጠፍን በኋላ የፌስ ቡክ ገጹን(Ermias Ze Anathot(@ermia23)) ወይ አጥፍቶታል አሊያም የተወሰኑ ሰዎች ብቻ እንዲያዩት እድርጓል፡፡ አይዞን ወንድሜ ሰው እንደሆነ የዘራውን ሳያጭድ አይቀርም፡፡ እዚህ ምድር ላይ እንኳን የክርስቶስ አካሉ የሆነች ቤተክርስቲያን ላይ አይደለም አንድ ግለሰብ ላይ የሠራነውን ግፍ የሰማይ ቅጣቱ እንዳለ ሆኖ ከፍለን ነው የምንሄድ፡፡ለቡ!
ታዲያ የተዋሕዶ ሚዲያና የሐራ ተዋሕዶ ባለቤቱ ኤርምያስ አለነ(ኪሮስ) የእንግሊዝና አየር ላንድ ሀገረ ስብከትና ሊቀ ጳጳሱ ላይ ዘመቻ ጀመሩ?
ለሀገረ ስብከቱ ከሚቀርቡ ምንጮች ለመረዳት አንደቻልነው በደቡብ አፍሪካ ለማኅበረሰቡ ባበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አማካኝነት በደቡብ አፍሪካ ታላቁ ዩኒቨርሲቲ የተሰጣቸውን የክበር ዶክትሬትና በቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ ምክንያት የተሰጣቸውን ዕውቅና ሳንቆጥር ብጹዕ አቡነ ያዕቆብ ከበርካታ ዓለማቀፍ ሰዎች ጋር የመሥራትና የመላው አፍሪካ፣ የደቡብ እና ምዕራብ አፍሪካ፣ እና የምሥራቅ አፍሪካ ሊቀጳጳስ ሆነው የመላው አፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ምክትል ፕሬዝደንት በመሆን ያገለገሉ፣ ማስተርሳቸውን በሊደርሽፕ ሠርተው ሦስተኛ ዲግሪያቸውን በመሥራት ላይ የሚገኙ፤ የዓለም የሰላም ፌዴሬሽን የሰላም አምባሳደር፤ በተለይ ደግሞ የደቡብ አፍሪካና የእንግሊዝ ሀገር ሕግ ተወራራሽነት ያላቸው በመሆኑ ደቡብ እና ምዕራብ አፍሪካ ላይ ቃለ አዋዲውን እና ሕገ ቤተክርስቲንን መነሻ በማድረግ ቤተክርስቲያን በሀገሪቱ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሕጋዊ ዕውቅና እንዲኖራት በማድረግ የቅዱስ ያሬድን ገዳምን ጨምሮ ሁሉን አብያተ ክርስቲያናት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሥር አስመዝግበዋል፡፡
ይህንኑ ተሞክሮአቸውን በመጠቀም ከኮቪድ በኋላ ባሉት ሁለት ዓመታት ሀገረ ስብከቱ ግማሽ ምእተ ዓመት የሞላው ቢሆንም በሀገሪቱ ያልተመዘገበ ሲሆን ከልጆቻቸው ጋር በመሆን ሕግ አጸድቀዋል፡፡ ከ50 ዓመት በላይ የሆነው ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስናም ይሁን ጽ/ቤት የሌለው በመሆኑ ይህን የሚያጠናና የሚሠራ ኮሚቴ አቋቁመዋል፤ ሀገረ ስብከቱ እንዲደራጅ ኮሚቴ መርጠው አጽድቀዋል፡፡
ታዲያ ማነው እየተቃወማቸው ያለው? ለምንስ ነው የሚቃወሟቸው ? አሁን የትና በምን ሁኔታ ላይ ናቸው? ያሉት ብለን ለጠየቅናቸው የመረጃ ምንጮቻችን እንዲሁ ብለውናል፡፡
1.ማነው እየተቃወማቸው ያለው? ወደ እንግሊዝ መመደብ ፍላጎት ያላቸው ብጹዓን አባቶች፣ በቀጣይ በዝርዝ የምንመለከታቸው በጣት የሚቆጠሩ ካህናት እና የግል ቤተ ክርስቲያን ያቋቋሙ ስግብግብ ግለሰቦች
2. ለምንስ ነው የሚቃወሟቸው? ብጹዕነታቸው የሀገረ ስበከቱን ሕግ አስጸድቀው ሀገረ ስብከቱ ካስመዘገቡ በኋላ አለን ለሚሉ አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ ሕጋቸሁን በጸደቀው መሠረት አድርጉ፣ ፈቃዳችሁን አምጡ፣ ቤተ ክርስቲያን ለውጪ አብያተ ክርስቲያናት ያጸደቀችውን ሕግ ተግባራዊ አድርጉ ብለው አባታዊ መመሪያ አስተላለፉ፡፡ እነ ኤርምያስና ግብር አበሮቻቸው የግል ቤተክርስቲያን ባለቤት የመሆን የልጅነት ሕልማቸው ሊጨነግፍ ሆነ ስለዚህ የበሬ ወለደ መረጃ ፈጥረው እሳቸውን አሳደው እነ አቡነ ሔኖክን ለማስመደብ ነው የሚል መረጃ ነው ሰማነው፡፡ ድሮም የእንግሊዝ ችግር በአብዛኛው ከጥቂት ነፍሰ በላ አገልጋዮች የሚመነጭ እንጂ ምዕመኑ አባቶቹን ወደጅና አክባሪ ነው ተብለናል፡፡ በተለያየ ጊዜ አባቶችን በማሰቃየት እና የሞራል ገደላ በማድረግ ግማሹን በብስጭት ሌላው በማባረር የተካኑና በሚቀጥለው ጽሑፍ በስፋት የምንዳስሳቸው እኩይ ተግባር ነው ተብለናል፡፡
3. ብጹዕ አቡነ ያዕቆብ የትና በምን ሁኔታ ላይ ናቸው?
ብጹዕ አቡነ ያዕቆብ ወደ እንግሊዝ ኅዳር 2018 ዓ.ም በመሄድ ቤተክርስቲያ የመረቁ ሲሆን፤ እስከ ሚያዝያ ደረስ አንግሊዝ ሀገር ቆይተው ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል፡፡ የመረጃ ምንጮቻችን ባስረዱን መሠረት በእንግሊዝ ሀገረ ብጹዕነታቸው የሄዱበት ወቅት ከፍተኛ ቅዝቃዜ የነበረበትና ሱፐር ፍሉ የሚባል አደገኛ በሽታ የነበረበት ጊዜ በመሆኑ እንዲሁም ሀገረ ስብከቱ ለአባቶች የሚሆን ቋሚ ማረፊያ ስሌለው በጣም ታመው በሕክምና ሲታገዙ የነበረ ሲሆን በዚህ ሕመም ውስጥ ሆነው ከ20 ዓመታት በላይ የዘለቀውን የደብረ ጽዮን ግጭት ለምፈታት ጥረት አድርገዋል:: ለመጀመሪያ ጊዜም ተቀራርበው እንዲነጋገሩ አድርገዋል፡፡ የገጠማቸውን የጤና እክል በተመለከተ ከፍተኛ የነርቭ ችግር የገጠማቸው ሲሆን ከዚህ በታች በፎቶው ላይ እንደሚታየው ክራንች እስከመያዝ ደርሰው ጤናቸውና የመንቀሳቀስ ሁኔታቸው አሳሳቢ ስለነበር እሳቸውን ለማድረስ ብቻ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ አብረው እንደመጡ ኢትዮጵያ በደረሱ ወቅት መንፈሳዊ ልጆቻቸው ላንድ ማርክ ሆስፒታል በመውሰድ በተመረመሩበት ወቅት ከፍተኛ የነርቭ ጉዳት ገጥሟቸው አንደነበርና የዚህን ዓይነት በሽታ በትንሹ እስከ 6 ወር የሚደርስ የሕክምና ክትትል ድጋፍ የሚጠይቅ ቢሆንም የብጹዕነታቸው ሁኔታ ግን ሰውነታቸው በራሱ ጊዜ እያገገመ መምጣቱን በመግለጽ ለሐኪሞችም ከፍተኛ ግርምትን እንደፈጠረ እና አሁን ግን ከክራንችና ከሰው ድጋፍ ተላቀው ፊዚዮ ቴራፒ እያደረጉና እያገገሙ መሆኑን ለመረዳት ችለናል፡፡ የዝግጅት ክፍላችንም በቶሎ አገግመው ወደ ተለመደው ሐዋርያዊ አገልግሎት እንዲመለሱ ምኞታችንና ጸሎታችን ነው፡፡
ማጠቃለያ
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ችግር የሚመነጨው ከአስተምሮዋ ማለትም ከዶግማ ከቀኖናዋና ከቅዱስ ትውፊቷ ሳይሆን ሆድ አድር በሆኑ ለአፍታ እንኳ ዕለተ ሙታቸውን በማያስቡ የእናት ጡት ነካሽ በሆኑ ልጆቿ ነው ብለን እናምናለን፡፡የዚህ ገጽ አባላት እዚህ ላይ የተነካኩ ጉዳዮችን ማስተማሪያ ይሆኑ ዘንድ በዝርዝር የምንሄድበት ሲሆን የእንግሊዝና የአየር ላንድ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ከመረጃ እጥረት አንጻር በዝርዝር መሄድ ያልቻልናቸውን ጉዳይ በማስተዋልና ጥበብ በተሞላበት መንገድ በመሄድ ቤተ ክርስቲያን የግል ጥቅማቸው እንዳይነካ በማሰብ ብቻ ጥቅምትና ግንቦት ሲኖዶስ ስብሰባ ሲመጣ የሚፍጨረጨሩ አካላት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማስተማር ይገባል፡፡ በርግጥ ኤርምያስን በተመለከተ በእንግሊዝ ሀገር የምትገኙ አንዳንድ የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች በእንግሊዝ ሀገር ሆም ኦፊስ የኢሚግሬሽን ኢንፎርሰመንት (UK Home Office – Immigration Enforcement) አባላት ጋር እያደረጋችሁ ያላችሁትን ጥረት ብናደንቅም ማስተካከያ እርምጃውን አንድ ግለሰብ ላይ ትኩረት በማድረግ ባይሆን እንላለን፡፡
ሌላው በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ያላችሁ የብጹዕ አቡነ ያዕቆብ ልጆችና ወዳጆች ብጹዓን አባቶች(በተለይ የቋሚ ሲኖዶስ አባላት) ይህ መረጃ እንዲደርሳቸው በማድረግ ቤተክርስቲያንን ከእኩያን ልንታደግ ይገባል እንላለን፡፡
የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ጭንብልን በመግለጥ በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅ ያለበለዚያ የተሰጠው የሚዲያ ፈቃድ ካለ እንዲሰረዝ ማድረግ ጊዜያዊ መፍትሔ ሊሆን ይችላል በማለት የዛሬውን እዚህ ላይ እናብቃ፡፡
በቀጣይ
- የእንግሊዝና አየርላንድ ሀገረ ስብከት የሁል ጊዜ ነቀርሳ የሆኑ አባቶችን በማሰቃየት የሚታወቁ አገልጋዮችን እንቃኛልን
- የእንግሊዝና አየርላንድ ሀገረ ስብከት 50 ዓመታት ጉዞ
- የደብረ ጽዮን ከ20 ዓመታት በላይ የዘለቀ መለያየት ምንጭ እና የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ከባለታሪኮቹ እንሰማለን
ይቆየን!