የጽርፈት አጋንንት ተዋርሶ ከ”Hara Tewahido ሐራ ተዋሕዶ” ወደ “ሐራ ዘተዋሕዶ”

በፊት ቃል በገባነው መሠረት ባነሳናቸው ርእሰ ጉዳዮች ላይ በመረጃና በማስረጃ ያልተደገፈ ጽሑፍ ላለመጻፍ በዚህ ገጽ አባላት ከተለያየ አቅጣጫ መረጃ የማሰባሰቡ ሂደት ስላልተጠናቀቀ በመዘግየታችን ይቅርታ እየጠየቅን ወደ አነሳናቸው ጉዳዮች አንድ በአንድ እንገባ፡፡

#ርእሰ ጉዳይ አንድ፡-የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ዛሬ ያለችበት አስተዳደራዊ እና መዋቅራዊ ልፍስፍስነት፣ ልሽቀትና ድክመት ላይ እንድትደረስ እነማን ምን ድርሻ ነበራቸው/አላቸው?

የማኅበራዊ ሚዲያ ጸሐፊዎች እና ገጾች

ይህን ርእሰ ጉዳይ የበለጠ ለመረዳትአንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍልን እናንሳ፡-

ይህቺ ሴት አገልግሎታቸውን፣ እውነትን ስለምትወድ፣ እነሱን ማሞገስ ፈልጋ ሳይሆን ሙገሳውን ቢቀበሉ ኖሮ ሄዳ ለማጭበርበሪያ እና ለገንዘብ መሰብሰቢያ ትጠቀምበት ነበር፡፡ በፍቅረ ነዋይ የታወረ ዓይነ ልቡናን እውነትን ከመቀበል ይልቅ ልብን በጥላቻ ይሞላል፡፡

#”ወደ ጸሎት ስፍራም ስንሄድ፥ የምዋርተኝነት መንፈስ የነበረባት ለጌቶችዋም እየጠነቈለች ብዙ ትርፍ ታመጣ የነበረች አንዲት ገረድ አገኘችን። እርስዋ ጳውሎስንና እኛን እየተከተለች፦ የመዳንን መንገድ የሚነግሩአችሁ እነዚህ ሰዎች የልዑል አምላክ ባሪያዎች ናቸው ብላ ትጮኽ ነበር። ይህንም እጅግ ቀን አደረገች። ጳውሎስ ግን ተቸገረና ዘወር ብሎ መንፈሱን፦ ከእርስዋ እንድትወጣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝሃለሁ አለው፤ በዚያም ሰዓት ወጣ።ጌቶችዋም የትርፋቸው ተስፋ እንደ ወጣ ባዩ ጊዜ ጳውሎስንና ሲላስን ይዘው ወደ ገበያ በሹማምት ፊት ጐተቱአቸው፤”ሐዋ.ሥራ 16:16-19

ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅ ይህን ክፍል በተረጎመበት “የገንዘብ ፍቅር ባለበት ቦታ ሁሉ ክፋት አለ፡፡ በጣም ክፉዎች ስለሆኑ እነሱ ገንዘብ ያግኙ እንጂ ልጅቷ በአጋንንት እስራት ብትኖር ጉዳያቸው አይደለም፡፡”

ዛሬም በማኅበራዊ ሚዲያ ገንዘብ ከፍለን ጻፉልኝ ካሏቸው፤ ወይም በዚህ ዘመን ላይክ፣ ሼር፣ ሰብስክራይብ፣ ኮፒ ሊንክ ገንዘብ የሚያመጣ ከሆነ ለምን ወንድማቸው አይሆንም፣ ለምን የትኛውም የአባቶች ወይም የቤተክርስቲያን ጉዳይ አይሆንም በርካታ እውነተኛ መሳይ ነገር ግን ርኩስ መንፈስ የሰፈራቸው አፈ ጻዲቆችን መበራከታቸው እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ነው፡፡

ሀ. የጽርፈት መንፈስ ተዋርሶ ያለባቸው/የነበረባቸው ጸሐፊዎችና ገጾች

#1. ደጀ ሰላም

የሐራ ተዋሕዶ የክፋት ወላጅ አባት የነበረው “ደጀ ሰላም” ይባል የነበረው ብሎግ ጸሐፊዎች የቤተክርስቲያ አባቶችን በተለይ ብጹአን አባቶችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ተላላኪ ለማድረግ ብቸኛ አማራጭ አድርገው ይዘውት የነበረው አባቶች የገጠማቸውንም ያልገጠማቸውንም ድቀት አደባባይ በማውጣት አባቶችን ማቃለልን፣ ማዋረድን እና የሞራል ገደላ(Character Assassination) ነው፡፡ በረከታቸው ይደርብንና ከፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ እና በርካታ ብጹአን አባቶችን በመርዛማ ብዕራቸው ወግተዋል፡፡ በኋላ ላይ የዚህ ብሎግ ባለቤት ማኅበረ ቅዱሳን ነው፤ እነ ኤፍሬም እሸቴ ናቸው የሚጽፉበት ተብሎ ስለነበር ማኅበሩ በስምዓ ጽድቅ ጋዜጣ 16ኛ ዓመት ቁጥር 21/ቅጽ 16 ቁጥር 182 ከሐምሌ 15-30 ቀን 2001 ዓ.ም ደጀ ሰላም የእኔ አይደለም ብሎ መግለጫ በማውጣቱ ተሳዳቢውም ጋኔንንም በዚያው ወጣ ብሎጉም ከነጸሐፊዎቹ ከሰመ ቤተክርስቲያንም ለጥቂት ጊዜ አረፈች፡፡

2. Hara Tewahido ሐራ ተዋሕዶ

ደጀ ሰላም ብሎግ ላይ አባቶችን በማዋረድ እና በማሸማቀቅ ከሚሰድቡቸውም ከሚያሰድቧቸውም የስድብ ገቢ የሚያገኙት ገንዘብ ስለነጠፈባቸው ማኅበሩ ደግሞ አላውቃችሁም ስላላቸው ለዳቦ የሚሆን ገንዘብ የሚያጡ መሆኑን ሲረዱ ከማኅበሩ መደበኛና ኢ-መደበኛ አገልግሎች ቀስ በቀስ ወጡ፡፡ በደጀ ሰላም ብሎግ ስለተነቃባቸው እንጂ ጋኔኑ ፈጽሞ ከውስጣቸው ተንቅሎ ስላልወጣ እነሱም ያ የሚያገኙት ገንዘብ አባቶችን ማዋረድ ቤተ ክርስቲያንን ማዋረድ መሆኑን ቢያውቁም በፍቅረ ነዋይ የገባባቸው ጋኔን ጥቅምት 12 ቀን 2005 ዓ.ም በታላቁ መልዐክ በቅዱስ ሚካኤል ቀን የያዛቸው ጋኔን Hara Tewahido ሐራ ተዋሕዶ (የተዋሕዶ ሠራዊት፣ የተዋሕዶ ወታደር) ብለው የበግ ለምድ ለብሰው ተኩላዎቹ ብቅ አሉ፡፡ ታዲያ እነዚህን ቡድኖች ከደጀ ሰላም ላይ ያካበቱት አባቶችን መዋረድና ማሸማቀቅ የስነ ልቡናና የሞራል ገደላ(Character Assassination) ተጨማሪ በጀት በመመደብ የጥቅምት እና የግንቦት የቅዱስ ሲኖዶስ ስበሰባ እያስቀረጹ በአባቶች መካከል ልዩነት እንዲሰፋ እና እርስ በእርስ እንዳይተማመኑ እያንዳንዱን ስበሰባ ቦታው ላይ ከብጹአን አባቶች ጋር እየተሰበሰቡ ያሉ በሚመስል መልኩ ወይም የቤተክርስቲያኒቱ ቃለ አቃባይ ተደርገው የተሾሙ በሚመስል ሁኔታ የጠዋት ፣የከሰዓት የቅዱስ ውሎ እያሉ የቤተክርስቲኒቱን የውስጥ ጉዳይ ዓይናቸው በፍቅረ ነዋይ ስለታወረ ለአደባባይ በማውጣት ለትዝብትና ለትችት አሳልፈው መስጠት ጀመሩ፡፡

እኛም የዚህ ገጽ እና ብሎግ አባላት ይህ ጉዳይ አደገኛና እና ቤተክርስቲያኒቱን ሰድቦ ለሰዳቢ የመስጠት የባንዳነት ተግባር በመሆኑ እነዚህ ጸሐፊዎች ማግኘት አለብን በማለት ብዙ ርቀት ተጓዝን፡፡ ጊዜ ቢፈጅብንም እልሃችንን ቢያስጨርሰንም እነዚህ በፍቅረ ነዋይ ያበዱ የጽርፈት መንፈስ ያደረባቸውን እኩያን ማወቅ ቻልን፡፡ በዚሁ አጋጣሚ ይህ አድካሚ ፍለጋ እና ማጋለጥ ከተጠናቀቀ በኋ የቤተክርስቲኒቱን ደመወዝ ከሁለትና ከሦስት ቦታ እየበሉ የነበሩ ያሉ “ታዋቂ እና አንቂ” ዘማርያ፣መምህራንና አገልጋዮች እኛ እኮ እነሱ እንደሆኑ እናውቅ ነበር እያሉ አፋቸውን ሞልተው ሲናገሩ በመስማታችን ያለንበትንና የደረስንበትን የመንፈሳዊ ሕይወት ዝለትና ዝቅጠት አሳይቶን አልፏል፡፡ በኋላ ላይ ብሎጉን በዋናነት ከሚዘውሩት መካከል እነ አሉላ ጥላሁን የፊተኛው መስመር ላይ ይኑሩ እንጂ ሰድቦ ማሰደቡ ላይ ግን ዛሬ በየደረጃው በመንግስት መዋቅር ያሉ ግለሰቦችና ብጹአን አባቶችን ጨምሮ በደንብ በቅንጅትና በመደራጀት ይሠሩ እንደነበር በጥናታችን ለማረጋገጥ ችልናል፡፡ ታዲያ ከጸሐፊዎች መካከል አንዳንዶቹ ልክ እንደ ቆሰለ አውሬ ማንነታቸው ስለተገለጠ ብቻ አጋልጠውናል በማለት የጠረጠሯቸውን ሰዎች ሁሉ ጋር እየሄዱ ለማስፈራራት እና ለማሸማቀቅ ቢሞክሩም አልተሳካም፡፡ የያዛቸው ጋኔን ለቋቸው ይሁን አይሁን እስከ ዛሬ ድረስ ማረጋገጥ ባንችልም ቡድኑ ከመጋቢት 28 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ መጻፍ አቆመ ቤተክርስቲያንም በድጋሜ አረፈች፡፡

ወደ ሚቀጥለው ከማለፋችን በፊት እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ እናንሳ፡፡ እነዚህ ሰዎች ለምን በዚህ እኩይ ተግባር ተሰማርተው ለሞኖር ፈለጉ? የሚለውን በስሱ መመለሱ ተገቢ ነው ብለን እናምናለን፡፡

አንድ አግልጋይም ይሁን አባት ራሱን ችሎ ጥረት የሚያደርግ እና ነገ ወደ ተሻለ ይደርሳል ብለው ከሰጉ የዚህ ቡድን አባላት እንደ አንድ መርህ የሚከተሉት ይሄ ሰውዬ ሊያመልጥ ስለሆነ #የመገደብ ዘመቻ ይከፈትበት በማለት ከአካላዊ ጥቃት እስከ ሕይወት ማጥፋት ድረስ ሊሄዱ እንደሚችሉ አመላካች ነገሮች እንዳሉ የሚያምኑ ብዙዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ ለምን? ለሚለው ጥያቄ ግን መልሱ በቃ ፍቅረ ነዋይ ነው፡፡

3. ሐራ ዘተዋሕዶ

ይህ ደግሞ ኅዳር 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ያንን የተላቀቅነውን የጽርፈት መንፈስ በግድ ካልተዋረስኩኝ ብሎ በትልቅ ድፍረትና የስድፍ አፍ የመጣ ነው፡፡ ከላይ እንደጠቀስነው ይህን ስም ይዞ ብቅ ማለት የተፈለገው ሐራ ተዋሕዶ በተሳዳቢነት እና የአባቶችን ክብር በማቃለል ያገኘውን ዝና በደንብ ስለሚያውቁ ከመሃል “ዘ”ን ጨምረው ብቅ አሉ፡፡

የዚህ ፌስቡክ ገጽ መሥራችና ባለቤት ዛሬ በሀገረ እንግሊዝ በስደት ያለና በአቡነ ሔኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዘመን ካህናትና አብያተ ክርስቲያናትን እንደ ላሜ ቦራ ያላበ የብዙ አገልጋይ ካህናት እንባና የግፍ ገንዘብ ከሀገር እንዲኮበልል ያደረገው የአቡኑ ልጅ የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ባለቤት የኤርምያስ ኪሮስ የግል ሀብትና ንብረት ነው፡፡

ለዛሬ አንድ ሁለት ማሳያ እናነሳና በቀጣይ ጽሑፍ እንግሊዝ ሀገር ከነማን ጋር ምን እየሠራ እንዳለና ከኢትዮጵያ ሲወጣ በየት በኩል ስንት ከፍሎ እንደወጣ በማስረጃ እንነግራችኋለን፡፡

#ማሳያ አንድ፡- ይህ ገጽ የኤርምያስ መሆኑን ለማወቅ ትንሽ ወደኋላ ሄደት ብሎ የለጠፋቸውን ጽሑፎች ማየት በቂ ነው፡፡ ይኸውም በሳዩት ደካማ አስተዳደርና በአስተዳደራቸው በነበረው ከፍተኛ የሆነ የሙስና መስፋፋት ምክንያት ለአንድ ብጹዕ አባት በማይገባ መልኩ ገንዘብ በግልጽ በፌስታል ይሰበስባሉ በማለት “አባ ኩርቱ” እስከ መባል የደረሱት አባቱ፣ አባታችን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥልጣን ዘመን ለማራዘም ካልተሳካም አጥፍቶ ለመጥፋት የተከፈተ የግል ገጹ ነው፡፡ በነገራችን ላይ ብዙ ወሬ ወዳጅ ሰው የበፊቱ የሐራ ገጽ መስሎት የተከላቸው ይመስለኛል፡፡ ነገር ግን የበፊቱ 101 ሺሕ ተከታይ ያለው ሲሆን ይሄኛው የኤርሚ ገጽ ግን 4.8 ሺህ ብቻ ተከታይ ያለው ነው፡፡ አጋንንታዊ ተዋርሶአቸውን ለማሳየት ስሙንና ሻማዋን ተጠቅሟታል፡፡ እናላችሁ በዚህ የፌስ ቡክ ገጽ የመጀመሪያ አፍ ማለቀቂያ የነበሩት የወቅቱ ጠቅላይ ሥራ አሥኪያጅ #አቡነ አብርሃም ነበሩ ከግንቦት 15 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ግንቦት 15 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ለሁለት ዓመታት ከጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ እስከሚወርዱ #ከ40 ጊዜ በላይ በዚህ የኤርሚ ገጽ ከፍ ዝቅ እየተደረጉ ተሰድበዋል በአንጻሩ አቡነ ሔኖክ ከንጉሥነት እስከ ቅዱስነት በሚደርስ ማንቆሎጳጰስ ተወድሰዋል፡፡

ይህ የፌስ ቡክ ገጽ በአባቶች መካከል ልዩነት እንዲሰፋ እና እርስ በእርስ እንዳይተማመኑ እና የትም ቦታ ተመድበው ቢሠሩ ሐዋርያዊ ግዴታቸውና የተሾሙበት አደራ ቢሆንም እሳቸውን ለመጠበቅ ተብሎ #መንግሥትን፣ #የደብር አሰተዳዳሪዎችን፣ #የመምሪያ ኃላፊዎች ሳይቀሩ #ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ፣#አቡነ ሳዊሮስ፣ #አቡነ ሩፋኤል፣ #አቡነ ፊልጰስ፣#አቡነ ዲዮስቆሪዮስ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ #አቡነ ያዕቆብ ከፍ ዝቅ ተደርገው ተብጠልጥለዋል፡፡

ቤተክርስቲያን ፈቃድ ራሷ ሰጥታ ራሷን እየሰደበና እያሰደባት ላለው የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል እና ባለቤቱ ኤርምያስ ኪሮስ በቀጣይ በስደት ባለበት ሀገረ እንግሊዝ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ ከማን ጋር ምን እኩይ ተግባር እየሠራ ነው የሚለውን እጃችን ላይ ስለገባ እንመለስበታለን::

ይቆየን!

Leave a Reply