What is the fault of His Grace #Abune Fanuel?

Of the 85 Apostolic Canons, the #40th says:

“Let the private goods of the Bishop, if he have any such, and those of the Lord, be clearly distinguished, that the Bishop may have the power of leaving his own goods, when he dies, to whom he will, and how he will, and that the Bishop’s own property may not be lost under pretence of its being the property of the Church: for it may be that he has a wife, or children, or relations, or servants; and it is just before God and man, that neither should the Church suffer any loss through ignorance of the Bishop’s own property, nor the bishop or his relations be injured under pretext of the Church: nor that those who belong to him should be involved in contests, and cast reproaches upon his death.”

In this regard, what is the fault of His Grace #Abune Fanuel, who had donated his residential building which is registered by His own name to #Mekdonia Helping Center For The Elderly & Mentaly Disoredered? If there is something we have not understood or seen, please explain to us

የብጹዕ #አቡነ ፋኑኤል ጥፋት ምኑ ላይ ነው?

ከ85ቱ የሐዋርያት ቀኖና መሐል #40ኛው እንዲህ ይላል ፡-

“ጳጳስ (ለግል ጉዳዩ ካስፈለገው) ንብረት ሃብት ይኑረው:: የግል ንብረቱ በግልጽ ለሕዝብ ይታወቅ፡፡ የቤተ ክርስቲያኑም ንብረት ከጳጳሱ ንብረት ተለይቶ ለሕዝብ ይገለጽ፡፡ ጳጳስ ሲሞት ንብረቱን ለፈለገው የመስጠት የማውረስ መብት ስለ አለው ነው፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ንብረት ጋር እንዳይቀላቀልና የቤተ ክርስቲያን ንብረት በማስመሰል የግል ገንዘቡ እንዳይወሰድና የመውረስ መብት ያላቸው ሚስትና ልጆች ወይም የቅርብ ዘመዶች፣ የወንድ አሽከር፣ የቤት ገረድ ተገቢ ድርሻቸውን እንዳያጡ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ባወቀ ገንዘብ የቤተ ክርስቲያኑም ያለአግባብ እንዳይባክን፣ የጳጳሱም ለተገቢው ባለመብት እንዲደርስ፣ በገንዘቡ የተነሣ ሰዎች እርስ በራሳቸው እንዳይጋጩና ሙት ወቃሽ ሁኔታ እንዳይፈጠር ተገቢ ነው፡፡”

ከዚህ አንጻር ብጹዕ አቡነ ፋኑኤል በስማቸው ተመዝግቦ የነበረውን ቤታቸውን #ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በስጦታ ማበርከታቸው  ጥፋቱ ምኑ ላይ ነው? እስቲ ያልተረዳነው ወይም ያላየነው ነገር ካለ አስረዱን፡፡

ሐራ ዘተዋሕዶ በተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ጭምብል ውስጥ… ያለ ሀገረ ስብከታቸው የግል ቤተክርስቲያን የተከሉ ጳጳስና ልጃቸው….

ውድ አንባብያን እዚህ ገጽ ላይ የሚጻፉ ጽሑፎች ዓላማ የግለሰቦችን ስም ወይም ድርጊት በማንሳት ከዚህ በፊት ሌሎች በአባቶች ላይ የሞራል ገደላ እንዲሚያደርጉት አንዱን አባት አጉልቶ ሌላውን ለማኮሰስ ሳይሆን ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ “የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን” ዮሐ 3፡11 እንዲል መረጃና ማስረጃ ላይ ተደግፈን መጻፍ ነው፡፡ይሁን እንጂ ማንም ሰው ይሄ መረጃችሁ የተዛባ ነው፣ ሚዛናዊነት ይጎድለዋል ቢል ለማስተካከልና ለማረም ዝግጁዎች ነን፡፡ ዓላማችን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን የወንበዴዎች ዋሻ ያደረጓትን እና የሚያደርጉትን ለማረም ከጥፋታቸው እንዲመለሱ ለማደረግ እና ማንም በምንም ደረጃ ያለ ቢሆን በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እየቀለደ እንዳይኖር ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ገጽ የሚለቀቁ ጽሑፎችን በዚህ ዓውድ ሁናችሁ ታነቡ ዘንድ በቅድስት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስም ልመናቸንን እናቀርባለን፡፡

ከዚህ በፊት በጻፍነው ጽሑፍ ውስጥ የሐራ ዘተዋሕዶ የፌስቡክ ገጽ እና የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ፀሐፊ እና ባለቤት አንድ መሆኑን በአጭሩ ለማሳየት ሞክረናል፡፡ እንደሚታወቃው ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ከምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሚዲያነት የተቀየረ ሲሆን ባለቤትነቱ የብጹዕ አቡነ ሔኖክ ነው፡፡ጸሐፊው አጻፊው ዘዋሪውን ግን ኤርምያስ ኪሮስ መሐሪ ነው፡፡ ይህን ለማረጋገጥ ብዙ ቦታ መሄድ ላያስፈልግ ይችላል፡፡ ሚዲያው ሲቋቋም ዓላማ አድርጎ የነበረው ሚዛናዊ ቤተክርስቲያንን የሚበጅ መረጃ ለማካፈልና ለትምህርት ነበር፡፡

ይሁን እንጂ በዚህ ዓላማ ጸንተው ለመጓዝ ችግር ገጠማቸው፡፡ ይኸውም አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በወቅቱ በከፍተኛ ብልሹ አሠራር እና ሙስና እየተጨማለቀ በመምጣቱ ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውስጥ ያሉ አብያተ ክርስቲያናትን የልማት ሥራ መጎብኘት በሚል ሰበብ በእነ ኤርምስ እና ዮሐንስ ቀኖ ፕሮግራም አውጪነት በኩርቱ ፌስታል የሚሰበሰበው ብር በማኅበራዊ ሚዲያ መውጣት እየተበራከተ በመምጣቱ የስድብ አፍ የሚሆናቸውን የፌስቡክ ገጽ መክፈት ግድ አላቸው፡፡ በዋናው ገጽ(በተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል) ዜና ቤተክርስቲያን በጭብብሉ ገጽ(ሐራ ዘተዋሕዶ) ገድለ ዲያብሎስ እና ዜና ዲያብሎስ ወሳጥናኤል ማስተላለፍ ጀመሩ፡፡

ታዲያ ጊዜው በብዙ አቅጣጫ ቤተክርስቲያንና አገልግሎታን በአጠቃላይ ሕልውናዋን የሚፈታተን ሁነቶች የተከሰቱበት ወቅት ነበር፡፡ እናላችሁ በወቅቱ ይህን በይሁዳ ከረጢት(በኩርቱ ፌስታል) የሚሰበሰብ ከደሀ መቀነት ተጠራቅሞ በዕንባ ታብሶ ወደ ሙዳየ ምጽዋት የሚገባ ገንዘብ ዝርፊያ እንዲቆም ጥረት ምክርና የሀገረ ስብከቱ ሕገ ወጥ አካሄድ ይስተካከል ብለው ሲታገሉ የነበሩት የወቅቱ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ላይ ዘመቻ ተከፈተ፡፡ በባለፈው ጽሑፍ እንዳስነበብናችሁ ከግንቦት 15 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ግንቦት 15 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ለሁለት ዓመታት ከጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ እስከሚወርዱ #ከ40 ጊዜ በላይ በዚህ የኤርሚ ገጽ ከፍ ዝቅ እየተደረጉ ተሰድበዋል በአንጻሩ አቡነ ሔኖክ ከንጉሥነት እስከ ቅዱስነት በሚደርስ ማንቆሎጳጰስ ተወድሰዋል፡፡ ስለዚህ ማንም ብዙ የጠለቀ ዕውቀት ሳይፈልገው የሐራ ተዋሕዶን ገጽ ልጥፎች(ፖስቶች) ቢመለከት የአቡነ ሔኖክ ጠላቶች ወይም ተቃራኒ ሀሳብ የሚያቀርቡ አልያም ነገ ሊሄዱበት ላቀዱት እንቅፋት ይሆናሉ ተብለው በሚታሰቡት ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ እና በየሀገረ ስብከታቸው ለአድማ ማስነሺያ የሚጠቀሙበት ነው፡፡ መጽሐፍ እግዚአብሔር ከሚጠላቸውና ከሚጸየፋቸው ስድስት ነገሮች መካከል “…በወንድሞች መካከል ጠብን የሚዘራ” ምሳ 6፡-19 እንዲል ልብ ይሏል፡፡

የሆነ ሆነና እስቲ  ቀጠሮ ወደ ያዝነው የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል እና የሐራ ዘተዋሕዶ ፌስ ቡክ ገጽ ባለቤቱ ኤርምያስ አለነ (ኪሮስ) በስደት ባለበት ሀገረ እንግሊዝ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ ከማን ጋር ምን እኩይ ተግባር እየሠራ ነው? ወደ ሚለው እንዝለቅ፡፡

#ለመሆኑ ኤርምያስ አለነ ማነው? ኤርምያስ ኪሮስ ማነው?

ኤርምያስ ሽሮ ሜዳ ተወልዶ ያደገ እና ለትምህርት ያልተፈጠረ መሆኑን በጊዜ አውቆ አባቶችን በመጠጋት ሥጋዊ ሕይወቱ እንደሚለወጥ በማመን ለዚህም በዓላማ ሲሠራ የነበረ ወንድም ነው፡፡ ስለ ሽሮሜዳ ሥላሴ ሕይወቱና ቆይታው መዘርዘር ለያዝነው ዓላማ ስለማይጠቅመን እንተወው እና ቀጥታ ከምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት እስከ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ፤ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እስከ ሀገረ እንግሊዝ እንጓዝ ፤ ከብጹዕ አቡነ ሔኖክ ጋር ያለውን ዝምድና እና ግኙነት እንመልከት፡፡ ሠናይ ንባብ…

#የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

ይህ ሚዲያ ሲቋቋም በጎ ዓላማ ይዞ አማራጭ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ድምጽ ለመሆን ነበር፡፡ የስቱዲዮ ምርቃቱ የአንድ ቤተክርስቲያን ያህል የተዳነቀ፣  ግርግር የበዛበት እና ብጹአን አባቶች የተገኙበት ነበር፡፡ በዋናነት ይህ ሚዲያ የምዕመናን ቀልብ እንዲይዝና ትኩረት እንዲያገኝ ያደረገው በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስበከት የደረሰው አሰቃቂ የምዕመናን እና የካህናት(የሰማዕታት) እልቂት እንጂ የኤርሚ የሚዲያ ዕውቀት ወይም የአባቶች ጸሎት እንዳልሆነ እሙን ነው፡፡ ልክ ሚዲያው እንደተቋቋመ የዚህ ሚዲያ የፊት መስመር አጥቂና ተሰላፊው የነበረው  በቅጡ እንኳ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ያላጠናቀቀው ምናልባት ልክ እንደ ፓስፖርቱ የትምህርት ማስረጃውን ፎርጅድ ካላሰራ በስተቀር የአባቱንና የአያቱን ስም ያስቀየረው የቀድሞው ኤርምያስ አለነ ወይም የዛሬው ኤርምያስ ኪሮስ ነበር፡፡

በዚህ ሚዲያ ስም የዋሑን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ምዕምን ዛሬ የወደቁበትን ያሉበትን እንኳን ለአንድ ቀን ተዘክሮላቸው የማያውቁ የሰማዕታቱን ምስል ወድምጽ በማቅረብ በሰማዕታቱ ደም ላይ በመረማመድ ከኢትዮጵያ ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት  እስከ አሜሪካ፣ አውሮፓ፣የዓለም ሀገራት ሁሉ የሚደርስ የገንዘብ መቀፈያ መረብ ተዘረጋ አይተውትም ሰምተውትም ያማያውቁት ፈራንካ ለእነ ገንዘብ ብርቁ ይጎርፍ ጀመር፡፡ ወራት ባለሞላ ጊዜ ውስጥ ሰማዕታቱን ተረሱ ስለ ተጠቃሚነት ማሰብ ተጀመረ፡፡ በኋላ ላይ ኤርሚ በእግርና በራይድ እየተንከራተተባቸው ስለተቸገሩ ከተሰበሰበው ገንዘብ ላይ ቦጨቅ በማድረግ ለኤርሚ ቅንጡ መኪና እና ሌሎች ነገሮች ተሟሉለት ከዚያማ ኪሱም ልቡም ማበጥ ጀመረ፡፡ ይህን ተከትሎ እነ መ/ር ዘመድኩን የተዘረፈው ብር እንዲመለስ ጥያቄ ማንሳት ጀመሩ፡፡

ይህን ድንገተኛ ዓለም አቀፍ ውርደት ለማለፍ ሁለት ነገር ማድረግ ነበረባቸው አንደኛው ገንዘቡን ማጠብ(Money laundary) ማድረግ ፣ ሁለተኛ ምንም እንኳን ጠቅላይ ቤተክህነት የሚዲያ ፈቃድ የሰጠው ለምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ቢሆንም ማንም ወደ ኋላ ሄዶ ሰለማያጣራ(ፈቃድ መስጠት እንጂ ኦዲት የሚያደርግ እንደሌለ ስለሚያውቁ ቢመጣም አፉን በፍራካ ስለሚይዙ) የሚዲያውን ስም መቀየር አንዱ የገንዘብ ማጠቢያ መንገድ በመሆኑ በፍጥነት ወደ ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከልነት ተቀየረ፡፡ በዚህ መንገድ ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ተደራጀ ኤርሚም ይህንን የድፍረት ኃጢአት በአሸናፊነት ስለተወጣ በኋላ ላይ እንደምናየው እኩይ ተግባሩን አጠናክሮ ቀጠለ፡፡

#ኤርምያስ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት

አቡነ ሔኖክ ከዚህ በፊት በአገለገሉባቸው ቦታዎች ስማቸው ይህን ያህል በክፉ አይነሳም ነበር፡፡ ነገር ግን ምዕራብ አርሲን ለቀው ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስነት ከመጡ በኋላ በሰማዕታት ደም በመነገድ የድፍረት ኃጢአትን ገንዘብ ባደረጉ በእነ ኤርምያስ እና ዮሐንስ ቀኖ በመሰሉ አማካሪነትና መርሐ ግብር አውጪነት ቅድመ ቅዳሴ ፣ ጊዜ ቅዳሴ እና ድኅረ ቅዳሴ ፣ ቅድመ ንግሥ እና ድኅረ ንግሥና የመሳሰሉ የገንዘብ መቀፈያ መርሐ ግብር እያወጡ ስማቸውን አባ ኩርቱ ተብሎ እንዲነሳ የዋሁን አባትገፍተው አስገቡአቸው የእነሱን ድፍረት አለማመዷቸው፡፡ እጅግ ያሳዝናል፡፡ ይህ ሁኔታ አሁን ባለቡትም የደቡብ እና ምዕራብ አፍሪካ ተከትሏቸው እንደሄደ አንድ በደቡብ አፍሪቃ የሚኖር የዚህ ገጽ አባል “በበፊቶቹ ብጹአን አባቶች የማናውቀውን አንድ ቤተክርስቲያን መጥተው እንዲጎበኙ ከተፈለገ በቅድሚያ 5ሺ ራንድ የጉብኝት አበል አዘጋጁ መባሉ ለጊዜው መደናገጥን ቢፈጥርም ዛሬ ላይ ግን ስለለመድነው እየፈጸምነው እንገኛለን” ማለቱን አስታወሳለሁ፡፡ አሁን ደግሞ ዮሐንስ ቀኖ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ባካበተው የዘረፋ ልምድ የበለጠ እንደሚያሳልጠው ይጠበቃል፡፡ ደቡብ አፍሪካዎች እግዚአብሔር ይሁናችሁ፡፡

ወደቀደመ ነገር እንመለስና ኤርሚ የአዲስ አበባ ጉዳይ ማክተሙን ሲያውቅ ከመሞት መሰንበት በሚል ቡድን አደራጅቶ አስቀድሞ ከዚህ ክፍል በፊት እንደተጻፈው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጉዳይን ያነሱ ይሁኑ የጠረጠራቸውን በሙሉ ሐራ ዘተዋሕዶ የሚባል ገጽ ከፍቶ መዋጋት ጀመረ ለሁለት ዓመታት በተከታታይ እንደ እነ ብጹዕ አብርሃም የመሳሰሉት ስም በማጥፋት የአልሞት ባይ ተጋዳይ ትግል አደረገ፡፡ ግን ምን ያደርጋል አልተሳክቶም!!!

ልብ አይሞት አይደል ሌላ መፍትሔ ማፈላለግ ጀመረ…አቡነ ሔኖክ ሲወርዱ ሙስና የተቀበላቸው ቃል የገባላቸው አገልጋዮች እንደማይለቁት ያውቃል…ስለዚህ ለአቡኑም ይሁን ለራሱ ማረፊያ ቦታ መፈለግ ጀመረ…ያለውን ጥሪት ሁሉ ሰበሰበ መኪናውም ተሸጠ፡፡ አሜሪካ መሄድ ከባድ ነው በወቅቱ፡፡ ስለዚህ እንግሊዝ ሀገር ወደ አክስቶቹ ጋር በስደት መሄድ አለበት፡፡ አቡነ ሔኖክ ደግሞ ተገፍተዋል በሚል ከቻለ ገንጥሎ የራሳቸው ቤተክርስቲያን እንዲኖራቸው አሊያም …ብቻ በእንግሊዝ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ስም የጳውሎስ፣ የኬፋ፣ የአጵሎስ ብሎ ማቋቋም እንደሚቻል ካህናቱም እርስ በእርሱ የተከፋፈለና ለበርካታ ዓመታት ሲነታረኩ የኖሩ መሆኑን አጠና ስለዚህ ስደት ተጀመረ፡፡

#ኤርምያስ በዩጋንዳ ካምፓላ

ቀጥታ እንግሊዝ መግባት ከባድ በመሆኑ በሰማዕታት ደም ላይ ተረማምዶ እና ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የዘረፈውን የግፍ ገንዘብ በመሰብሰብ ዕድሜውን ከ30 ወደ 20 በመቀነስ፣ ስሙን ከኤርምያስ አለነ ወደ ኤርምያስ ኪሮስ በመለወጥ፣ ዜግነቱን ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ በመለወጥ፤ ልጅነቱን ከእናቱ ወደ አክስቱ በመቀየር ስደተኛ ካምፕ ዩጋንዳ ካምፓላ ገባ፡፡ ኤርምያስ ይሄን ሁሉ ነገር ማድረጉ ምናልባት እዚህ ሀገር መኖሩ ለሕይወቱ ሥጋት ፈጥሮበት ሊሆን ስለሚችል እና ሌሎችም የሚያደርጉት በመሆኑ ብዙም ከዚህ ጋር ተያይዞ ለሚነሱ ጉዳዮች ትኩረት አንሰጠውም፡፡ የእኛ የትኩረት አቅጣጫ ግን በዚህ ሁኔታ እንግሊዝ ሀገር ከገባ በኋላ የፈጸማቸው እና ያስፈጸማቸው እኩይ ተግባራት ናቸው፡፡

#ኤርምያስ በሀገረ እንግሊዝ

ከዚህ በኋላ ያለው ጉዳይ ብዙ ሰዎችን ሊነካ ቢችልም አስቀድመን እንግሊዝ ሀገር ባሉ ወዳጆቻችን አርፎ የስደት ወረቀቱን እንዲያስተካክል መክረናል አስመክረናል፡፡ ግን ምንም አታመጡም ባይ ሆነ፡፡ በነገራችን ላይ ኤርምያስ በእንግሊዝ ሀገረ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ያደረሰውን ግፍ፣ ጥላቻና የማን አለብኝነት ተግባር በውል መረዳት ለሌሎችም በውጪ ያሉ የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናትን ችግር ለመቅረፍ እንደመፍትሔ አመላካች ይሆናልና በትኩረት ይታይ እንላለን፡፡

በሀገረ እንግሊዝ ካሉ የዚህ ገጽ አባላት መረዳት እንደቻልነው፡፡ ኤርሚ መጀመሪያ አከባቢ የበግ ለምድ ለባሹ ተኩላ ማንነቱ በፍጥነት እንዳይታወቅ የወቅቱ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ያዕቆብ ጋር ወደጅ እና የቅርብ ሰው እንደሆነ በመስበክ በቃልም በተግባርም ይንቀሳቀስ ነበር፡፡ በኋላ ላይ ግን አቡነ ሔኖክን ይመራበት በነበረው መልክ የማይሄዱ የአፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩ፣የራሳቸው  የአስተዳደር ዕውቀትና ችሎታ ያላቸው በቀላሉ አባ አባታችን..አቦ አቦ በማለት የማይሸነፉ መሆናቸውን ሲረዳ ከእሳቸው መራቅ ጀመረ፡፡ በውስጡ ተቀበሮ ልፈንዳ ልፈንዳ እያለ የነበረውን ኢትዮጵያም እያለ እኔማ እንደ እነ አባ እገሌ በውጪ ሀገር የግል ቤተ ክርስቲያን ሊኖረኝ ይገባል የሚል ቁጭትና ተስፋ ስለነበረው ብጹዕነታቸው ለዚህ ደግሞ እንደማይመቹ ሲገባው የራሱን ቡድን በመመስረት በየአጥቢው በመሄድ ሀገረ ስብከቱን የማወክ ተግባር ጀመረ፡፡ በሁሉም ዘንድ ከሚታወቁ እኩይ ተግባሮቹ መካከል በጣም ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል፡-

  • ስቶክ ኦን ትረንት ደብረ ሃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ምዕመናንን የመከፋፈል ሥራ መሥራት፤የደብሩ አስተዳዳሪን ሳያሳውቅ በሌሉበት የሰበካ ጉባኤ አስተዳደር ምርጫ በማድረግ ምዕመናኑ ላይ መለያየት እንዱፈጠር ማድረግ
  • የድንች ወይም የውሸት ማኅተምና የደብዳቤ ራስጌ በመጠቀም በየደብሩ አስተዳዳር የማይታወቁና ያልተፈቀዱ ደብዳቤዎችን መጻፍ
  • በቤተ ክርስቲያን አውደ ምሕረት በእራሱ ቡድን በአስነሳው ጸብ አጫሪነት፥ ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ሕፃናት ልጆች ፊት አካላዊ ግጭት ማስነሳት

የመሳሰሉት ተግባራትን እየፈጸመ ሲሆን ይህ ሁሉ ግን ግርግር ለሌባ ያመቻል እንዲሉ መጀመሪያም አንግሊዝ ሀገር ሲመጣ ግቡ በእርሱና በአባቱ ስም የግል ቤተክርስቲያን ባለቤት መሆን በመሆኑ በዚያ መንገድ ላይ ያገኛቸውንና እንቅፋት ይሆናሉ ሊሆኑ ይችላሉ ብሎ ያሰባቸውን በሙሉ ልክ እንደቆሰለ አውሬ መናከስ ጀመረ፡፡

#የአቡነ ሔኖክና የኤርምያስ የግል አብያተ ክርስቲያናት በሀገረ እንግሊዝ

በቀደመው ዘመን የሲኖዶስን ከሁለት መከፈል እንደምቹ አጋጣሚ በመጠቀም ስሙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ንብረትነቱ ግን የአቡነ እገሌ፣ የመምህር እገሌ…የሆነ ቤተክርስቲያን ተመሠረተ እየተባለ እንሰማ ነበር፡፡ በኋላ ላይ ባለን መረጃ መሠረት ይህንን ጉዳይ ወደፊት በስፋት የምናየው ቢሆንም የአባቶች አንድነት ሲፈጸም አብያተ ክርስቲያናት ይዞታ ውኅደት ግን አልተደረገም፡፡ እስካሁንም በሀገረ አሜሪካ በአንድ ጳጳስ፣ ወይም በቦርድ አሊያም በሆነ ማኅበር አባላት ስም የተመዘገቡ አብያተ ክርስቲያናት፣ አሁን ደግሞ በትግራይ ስም ያሉ አያሌ ናቸው፡፡ ነገ ጊዜው ሲደረስ ሁሉም ወደ አንድ ባለቤትነት ይካተታሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ የሆነ ሆነና ኤርምያስ ሆዬ ምንም እንኳን ምንም ዓይነት የቤተክርስቲኒቱ ትምህርት ቤት ገብቶ የቀለም ጠብታ ባይነካው በእንግሊዝ ሀገር የግል ቤተክርስቲያን መመሥረት የሚያመጣውን መዘዝ ቢያውቅም በጎን የሀገረ ስብከቱን ኃላፊዎችና ሊቀጳጳሱን በደብዳቤ የመሠረትኩትን ቤተክረስቲያን አጽድቁልኝ እያለ ከዓመት በፊት ግን ቅደመ ዝግጅት በማድረግ አቡነ ሔኖክን ከውስጥ አዋቂ ምንጮች የክፍሉ ሊቀጳጳስ እንግሊዝ የማይኖሩበትን ጊዜ በማጥናት በተዋሕዶ ሚደዲያ ማዕከል ““አጼ ኃ/ሥላሴ በስደት ወቅት የኖሩበትን ታሪካዊ ቤት ጎበኙ” እያለ በሌላ በኩል በተመሳሳይ ቀን በራሱና ፌስ ቡክ ገጽ እና በግሉ ቤተክርስቲያን ገጽ ግን ወደ ሀገረ እንግሊዝ የመጡበትን ዋና አላማቸው የሆነውን ካህን ያለ ሀገረ ስብከታቸው ሾሙ ይልልሃል፡፡ ይህ ተሿሚ ከዚህ በፊት በእንግሊዝ መንግሥት ሀገረ ስብከቱ ባልፈጸመው ገንዘቡን ማጠብ(Money laundary) አድርጋችኋል በሚል ከስድስት ሰዓት በላይ የፈጀ አላስፈላጊ ምርመራ ውስጥ እንዲገቡ ያደረገውን ባለውለታቸውን እና በዩኬ “ማኅበረ ካህናት” በሚል ከምዕመናን በምዕራብ አርሲ ሰማዕታት ስም ተሰብስቦ ለግል ፍጆቷ የዋለውን ብር ሲያስተባበር ከነበሩት መካከል ዲ/ን ዳግማዊ ወርቁን ቅስና ያለ ሀገረ ስብከታቸው በመሾም የሐዋርያት ቀኖና ጥሰት በመፈጸም ጳጳሱ፣ ኤርምያስና ለእኩይ ተልእኮ የሾሙትን ቄስ ለሦስት በመሆን የግል ቤተክርስቲያን መሠረቱ::

በውጪ የግል ቤተክርስቲን ለመመሠረት ዋናኛው መንገድ በበጎ አድራጎት ድርጅት ማስመዝገብ ነው፡፡ ሕጋዊ እና የሚታወቁትም የኢ በዚህ ሥር ተመዝግበው እንደሚገኙ ልብ ይሏል፡፡ታዲያ የዚህ የእነ አቡነ ሔኖክ የበጎ አድራጎት ድርጅት( የግል ቤተክርስቲያን) መቼ ተመሠረ?

  1. የበጎ አድራጎቱ ስም፡ ተዋሕዶ ትረስት( Tewahedo Trust)

የበጎ አድራጎቱ የምዘገባ ቁጥር፡-1215254

Activities – how the charity spends its money

The Tewahedo Trust provides Oriental Orthodox theological courses for clergy and members of the Oriental Orthodox Church, supports youth spiritual development, and carries out charitable activities to assist those in need within the community.

ተግባራት

ተዋሕዶ ተረስት የኦሬንታል ኦርቶዶክ የሥነ መለኮት ትምህርት ለአገልጋዮችና ለአባላቶቹ ያስተምራል፤የወጣቶች መንፈሳዊ ዕድገትን ይደግፋል እና እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች እርዳታ ያደርጋል፡፡ የተለያዩ  የእርዳታ ተግ

Charitable objects

TO ADVANCE THE CHRISTIAN RELIGION IN ACCORDANCE WITH THE TENETS AND DOCTRINES OF THE ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHEDO CHURCH

የበጎ እድራጎት ድርጅቱ ዓላማዎች

 “በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ትምህርቶችና ዶግማዎች መሠረት የክርስቲያን ሃይማኖትን ማስፋፋትና ማጎልበት ነው።

CIO(Charitable Incorporated Organisation) – FOUNDATION Registered 06 Oct 2025

በበጎ አድራጎት ድርጅትነት የተመዘገበው፡- እ.ኤ.አ 06 ኦክቶበር 2025(26/01/2018 ዓ.ም)

ሙሉ መረጃውን ገብተው ለማየት ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ

TEWAHEDO TRUST – 1215254

2. STOKE-ON-TRENT ST RUFAEL AND ST ABUNE ECHEGE YOHANNES ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHEDO CHURCH

የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ስም፡- በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የስቶክ ኦን ትሬንት ምዕራፈ ቅዱሳን ቅዱሰ ሩፋኤል ወእጨጌ አቡነ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን

የበጎ አድራጎቱ የምዘገባ ቁጥር፡-1213122

CIO(Charitable Incorporated Organisation) – FOUNDATION Registered 29 April 2025

በበጎ አድራጎት ድርጅትነት የተመዘገበው፡- እ.ኤ.አ 29 አፕሪል 2025(21/08/2018 ዓ.ም)

Activities – how the charity spends its money

We focuses on promoting the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church faith through worship and religious ceremonies. We conduct Twice a month services, provide religious education to children, and offer tailored services for Ethiopian, British and Eritrean communities. Additionally, we assist new migrants in settling in the UK while ensuring compliance with UK law and religious regulations.

ተግባራት

እኛ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት መሠረት በአምልኮና በሀይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች የሃይማኖቱን ማስፋፋት እንሰራለን፤ በወር ሁለት ጊዜ የአምልኮ አገልግሎት እናካሂዳለን፣ ለህፃናት ሀይማኖታዊ ትምህርት እንሰጣለን፣ እንዲሁም ለኢትዮጵያውያን፣ ለብሪታንያውያንና ለኤርትራውያን ማህበረሰቦች ተስማሚ አገልግሎቶችን እንሰጣለን፤ በተጨማሪም የአገሪቱን ሕግና የሀይማኖት መመሪያዎች በመጠበቅ አዲስ ስደተኞች በዩኬ እንዲደራጁ እገዛ እናደርጋለን ።”

Charitable objects

THE ADVANCEMENT OF THE ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHEDO FAITH AND TO PROPAGATE THE GOSPEL OF CHRIST IN ACCORDANCE WITH THE BASIS OF FAITH AS SET OUT IN THE PROVISIONS OF THE FTHA NEGEST AND IN ACCORDANCE WITH THE PRINCIPLES AND REGULATIONS OF THE ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHEDO CHURCH AS SET OUT IN THE QALE AWADEE THROUGHOUT ENGLAND THROUGH THE HOLDING OF RELIGIOUS SERVICES AND PRAYER MEETINGS, RELIGIOUS EDUCATION, CONDUCTING RELIGIOUS CEREMONIES, INTERFAITH ACTIVITIES, OUTREACH AND PASTORAL CARE IN THE COMMUNITY.

የበጎ እድራጎት ድርጅቱ ዓላማዎች

“የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነትን ማስፋፋትና መጠናከር፣ እንዲሁም በፍትሐ ነገሥት የተገለጹ የእምነት መሠረቶች መሠረት እና በቃለ ዓዋዲ ውስጥ የተወሰኑ መርሆዎችና ደንቦች መሠረት የክርስቶስን ወንጌል ማስፋፋት በእንግሊዝ ዙሪያ በሀይማኖታዊ አገልግሎቶችና የጸሎት ስብሰባዎች መካሄድ፣ ሀይማኖታዊ ትምህርት መስጠት፣ ሀይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች መፈጸም፣ ከሌሎች ሀይማኖቶች ጋር የጋራ እንቅስቃሴዎች ማካሄድ፣ ማህበረሰብ ውስጥ የውጭ እንቅስቃሴ ማድረግ እና መንፈሳዊ እንክብካቤና ድጋፍመስጠት ነው።”

ማስታወሻ፡- ይሄንን ቤተክርስቲያን ኤርምያስና ቀድሞ ከጁቢቲ በትልቅ ውንብድና የተባረሩት ፣ ኋላም ጣሊያን ሀገር አቡነ ሕርያቆስን ሲያውኩ የነበሩ፤ ያለ ሀገረ ስብከቱ ፈቃድና እውቅና ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጽ/ቤት የተመደቡት አባ ዮናስ መልከጼዴቅ ናቸው፡፡ የጥፋት ሰንሰለቱን ለቡ!

በነገራችን ላይ ስለ አባ ዮናስ እኩይ ግብር እንጻፍ ቢባል የቱን ትተን የትኛውን እንጻፍ? ነው የሚያስብል፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ  ጊዜም ገጽም  ስለማይበቃን እንደው እንደ መግቢያ እንዲሆን ይቺን ሊንክ ይጫኑ፡፡

ምዝበራ ያዳከመው የጅቡቲ ቅ/ገብርኤል ደብር: በህልውና ስጋት ውስጥ ነው፤ “አማሳኞቹ በሕግ ይጠየቁ፤ በልኡካን ምደባ ጥንቃቄ ይደረግ”/ምእመናን/ | ሐራ ዘተዋሕዶ

ስለ ብጹዕ  አቡነ ሔኖክ ልጅ፣ ስለ ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከሉ እና ስለ ሐራ ዘተዋሕዶ መሳደቢያ የፌስ ቡክ ገጽ ባለቤት ሁለተኛ የግል ቤተክርስቲያን ሙሉ መረጃውን ገብተው ለማየት ይህንን ሊንክ ይጫኑ

STOKE-ON-TRENT ST RUFAEL AND ST ABUNE ECHEGE YOHANNES ETHIOPIAN ORTHODOX TEWAHEDO CHURCH – 1213122

ኤርሚ ታዲያ ሌላውን ወደ ማጣራት ሳንገባ የሁለት አብያተ ክርስቲያናት ባለቤት ሆነ ሕልሙም ተሳካ!

ሁለቱ ጉዳዮች የበጎ አድራጎት ምዝገባዎች በመከናወናቸው ምክንያት ሁለት ብጹን አባቶች ሆዴ ይሙላ ደረቴ ይቅላ ብለው በሚጓዙ ኤርምያስነ በመሳሰሉ የቤተክርስቲያን መዥገር እና ነቀርሳዎች ስህተት ውስጥ ገብተዋል::

  1. አቡነ ሄኖክ ፡- በሕክምና እና በጉብኝት ሰበብ ያለ ሀገረ ስብከታቸው በራሳቸውና በልጃቸው ስም ሁለት የግል ቤተክርስቲያናትን አቋቁመዋል፣ ሥልጣነ ክህነት ሰጥተዋል
  2. አቡነ ኤልያስ፡- እሊህን ብጹዕ አባት በስቶክ ኦን ትሬንት ያለሀገረ ስበከታቸው በመገኘት ሦስት ዲያቆናትን ሾመዋል፡፡ ሰሞኑን በግሪክ ጉዳይ የገጠማቸውን ሳስብ እና ከዚህ በፊት ቤተክርስቲያን በሁለት በተከፈለችበት ወቅት በፌስታል ብቻቸውን ዘመዳቸውን ጳጳስ አድረገው መሾማቸውን ባሰብን ጊዜ ከእሳቸው ምን እንማር ?እላለን

የሐዋርያት ቀኖና በእነዚህ ጉዳዮች

በነገራችን ላይ ኤርምያስ እነዚህ ቀኖናዎች በፌስ ቡክ ገጾቻችን ላይ ከለጠፍን በኋላ የፌስ ቡክ ገጹን(Ermias Ze Anathot(@ermia23)) ወይ አጥፍቶታል አሊያም የተወሰኑ ሰዎች ብቻ እንዲያዩት እድርጓል፡፡ አይዞን ወንድሜ ሰው እንደሆነ የዘራውን ሳያጭድ አይቀርም፡፡ እዚህ ምድር ላይ እንኳን የክርስቶስ አካሉ የሆነች ቤተክርስቲያን ላይ አይደለም አንድ ግለሰብ ላይ የሠራነውን ግፍ የሰማይ ቅጣቱ እንዳለ ሆኖ ከፍለን ነው የምንሄድ፡፡ለቡ!

ታዲያ የተዋሕዶ ሚዲያና የሐራ ተዋሕዶ ባለቤቱ ኤርምያስ አለነ(ኪሮስ) የእንግሊዝና አየር ላንድ ሀገረ ስብከትና ሊቀ ጳጳሱ ላይ ዘመቻ ጀመሩ?

ለሀገረ ስብከቱ ከሚቀርቡ ምንጮች ለመረዳት አንደቻልነው በደቡብ አፍሪካ ለማኅበረሰቡ ባበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አማካኝነት በደቡብ አፍሪካ ታላቁ ዩኒቨርሲቲ የተሰጣቸውን የክበር ዶክትሬትና በቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ ምክንያት የተሰጣቸውን ዕውቅና ሳንቆጥር ብጹዕ አቡነ ያዕቆብ ከበርካታ ዓለማቀፍ ሰዎች ጋር የመሥራትና የመላው አፍሪካ፣ የደቡብ እና ምዕራብ አፍሪካ፣ እና የምሥራቅ አፍሪካ ሊቀጳጳስ ሆነው የመላው አፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ምክትል ፕሬዝደንት በመሆን ያገለገሉ፣ ማስተርሳቸውን በሊደርሽፕ ሠርተው ሦስተኛ ዲግሪያቸውን በመሥራት ላይ የሚገኙ፤ የዓለም የሰላም ፌዴሬሽን የሰላም አምባሳደር፤ በተለይ ደግሞ የደቡብ አፍሪካና የእንግሊዝ ሀገር ሕግ ተወራራሽነት ያላቸው በመሆኑ ደቡብ እና ምዕራብ አፍሪካ ላይ ቃለ አዋዲውን እና ሕገ ቤተክርስቲንን መነሻ በማድረግ ቤተክርስቲያን በሀገሪቱ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሕጋዊ ዕውቅና እንዲኖራት በማድረግ የቅዱስ ያሬድን ገዳምን ጨምሮ ሁሉን አብያተ ክርስቲያናት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሥር አስመዝግበዋል፡፡

ይህንኑ ተሞክሮአቸውን በመጠቀም ከኮቪድ በኋላ ባሉት ሁለት ዓመታት ሀገረ ስብከቱ ግማሽ ምእተ ዓመት የሞላው ቢሆንም በሀገሪቱ ያልተመዘገበ ሲሆን ከልጆቻቸው ጋር በመሆን ሕግ አጸድቀዋል፡፡ ከ50 ዓመት በላይ የሆነው ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስናም ይሁን ጽ/ቤት የሌለው በመሆኑ ይህን የሚያጠናና የሚሠራ ኮሚቴ አቋቁመዋል፤ ሀገረ ስብከቱ እንዲደራጅ ኮሚቴ መርጠው አጽድቀዋል፡፡

ታዲያ ማነው እየተቃወማቸው ያለው? ለምንስ ነው የሚቃወሟቸው ? አሁን የትና በምን ሁኔታ ላይ ናቸው? ያሉት ብለን ለጠየቅናቸው የመረጃ ምንጮቻችን እንዲሁ ብለውናል፡፡

1.ማነው እየተቃወማቸው ያለው? ወደ እንግሊዝ መመደብ ፍላጎት ያላቸው ብጹዓን አባቶች፣ በቀጣይ በዝርዝ የምንመለከታቸው በጣት የሚቆጠሩ ካህናት እና የግል ቤተ ክርስቲያን ያቋቋሙ ስግብግብ ግለሰቦች

2. ለምንስ ነው የሚቃወሟቸው? ብጹዕነታቸው የሀገረ ስበከቱን ሕግ አስጸድቀው ሀገረ ስብከቱ ካስመዘገቡ በኋላ አለን ለሚሉ አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ ሕጋቸሁን በጸደቀው መሠረት አድርጉ፣ ፈቃዳችሁን አምጡ፣ ቤተ ክርስቲያን ለውጪ አብያተ ክርስቲያናት ያጸደቀችውን ሕግ ተግባራዊ አድርጉ ብለው አባታዊ መመሪያ አስተላለፉ፡፡ እነ ኤርምያስና ግብር አበሮቻቸው የግል ቤተክርስቲያን ባለቤት የመሆን የልጅነት ሕልማቸው ሊጨነግፍ ሆነ ስለዚህ የበሬ ወለደ መረጃ ፈጥረው እሳቸውን አሳደው እነ አቡነ ሔኖክን ለማስመደብ ነው የሚል መረጃ ነው ሰማነው፡፡ ድሮም የእንግሊዝ ችግር በአብዛኛው ከጥቂት ነፍሰ በላ አገልጋዮች የሚመነጭ እንጂ ምዕመኑ አባቶቹን ወደጅና አክባሪ ነው ተብለናል፡፡ በተለያየ ጊዜ አባቶችን በማሰቃየት እና የሞራል ገደላ በማድረግ ግማሹን በብስጭት ሌላው በማባረር የተካኑና በሚቀጥለው ጽሑፍ በስፋት የምንዳስሳቸው እኩይ ተግባር ነው ተብለናል፡፡

3. ብጹዕ አቡነ ያዕቆብ የትና በምን ሁኔታ ላይ ናቸው?

ብጹዕ አቡነ ያዕቆብ ወደ እንግሊዝ ኅዳር 2018 ዓ.ም በመሄድ ቤተክርስቲያ የመረቁ ሲሆን፤ እስከ ሚያዝያ ደረስ አንግሊዝ ሀገር ቆይተው ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል፡፡ የመረጃ ምንጮቻችን ባስረዱን መሠረት በእንግሊዝ ሀገረ ብጹዕነታቸው የሄዱበት ወቅት ከፍተኛ ቅዝቃዜ የነበረበትና ሱፐር ፍሉ የሚባል አደገኛ በሽታ የነበረበት ጊዜ በመሆኑ እንዲሁም ሀገረ ስብከቱ ለአባቶች የሚሆን ቋሚ ማረፊያ ስሌለው በጣም ታመው በሕክምና ሲታገዙ የነበረ ሲሆን በዚህ ሕመም ውስጥ ሆነው ከ20 ዓመታት በላይ የዘለቀውን የደብረ ጽዮን ግጭት ለምፈታት ጥረት አድርገዋል:: ለመጀመሪያ ጊዜም ተቀራርበው እንዲነጋገሩ አድርገዋል፡፡ የገጠማቸውን የጤና እክል በተመለከተ ከፍተኛ የነርቭ ችግር የገጠማቸው ሲሆን ከዚህ በታች በፎቶው ላይ እንደሚታየው ክራንች እስከመያዝ ደርሰው ጤናቸውና የመንቀሳቀስ ሁኔታቸው አሳሳቢ ስለነበር እሳቸውን ለማድረስ ብቻ የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ አብረው እንደመጡ ኢትዮጵያ በደረሱ ወቅት መንፈሳዊ ልጆቻቸው ላንድ ማርክ ሆስፒታል በመውሰድ በተመረመሩበት  ወቅት ከፍተኛ የነርቭ ጉዳት ገጥሟቸው አንደነበርና የዚህን ዓይነት በሽታ በትንሹ እስከ 6 ወር የሚደርስ የሕክምና ክትትል ድጋፍ የሚጠይቅ ቢሆንም የብጹዕነታቸው ሁኔታ ግን ሰውነታቸው በራሱ ጊዜ እያገገመ መምጣቱን በመግለጽ ለሐኪሞችም ከፍተኛ ግርምትን እንደፈጠረ እና አሁን ግን ከክራንችና ከሰው ድጋፍ ተላቀው ፊዚዮ ቴራፒ እያደረጉና እያገገሙ መሆኑን ለመረዳት ችለናል፡፡ የዝግጅት ክፍላችንም በቶሎ አገግመው ወደ ተለመደው ሐዋርያዊ አገልግሎት እንዲመለሱ ምኞታችንና ጸሎታችን ነው፡፡

ማጠቃለያ

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ችግር የሚመነጨው ከአስተምሮዋ ማለትም ከዶግማ ከቀኖናዋና ከቅዱስ ትውፊቷ ሳይሆን ሆድ አድር በሆኑ ለአፍታ እንኳ ዕለተ ሙታቸውን በማያስቡ የእናት ጡት ነካሽ በሆኑ ልጆቿ ነው ብለን እናምናለን፡፡የዚህ ገጽ አባላት እዚህ ላይ የተነካኩ ጉዳዮችን ማስተማሪያ ይሆኑ ዘንድ በዝርዝር የምንሄድበት ሲሆን የእንግሊዝና የአየር ላንድ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ከመረጃ እጥረት አንጻር በዝርዝር መሄድ ያልቻልናቸውን ጉዳይ በማስተዋልና ጥበብ በተሞላበት መንገድ በመሄድ ቤተ ክርስቲያን የግል ጥቅማቸው እንዳይነካ በማሰብ ብቻ ጥቅምትና ግንቦት ሲኖዶስ ስብሰባ ሲመጣ የሚፍጨረጨሩ አካላት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማስተማር ይገባል፡፡ በርግጥ ኤርምያስን በተመለከተ በእንግሊዝ ሀገር የምትገኙ አንዳንድ የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች  በእንግሊዝ ሀገር ሆም ኦፊስ የኢሚግሬሽን ኢንፎርሰመንት (UK Home Office – Immigration Enforcement) አባላት ጋር እያደረጋችሁ ያላችሁትን ጥረት ብናደንቅም ማስተካከያ እርምጃውን አንድ ግለሰብ ላይ ትኩረት በማድረግ ባይሆን እንላለን፡፡

ሌላው በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ያላችሁ የብጹዕ አቡነ ያዕቆብ ልጆችና ወዳጆች ብጹዓን አባቶች(በተለይ የቋሚ ሲኖዶስ አባላት) ይህ መረጃ እንዲደርሳቸው በማድረግ ቤተክርስቲያንን ከእኩያን ልንታደግ ይገባል እንላለን፡፡

የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ጭንብልን በመግለጥ በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅ ያለበለዚያ የተሰጠው የሚዲያ ፈቃድ ካለ እንዲሰረዝ ማድረግ ጊዜያዊ መፍትሔ ሊሆን ይችላል በማለት የዛሬውን እዚህ ላይ እናብቃ፡፡

በቀጣይ

  1. የእንግሊዝና አየርላንድ ሀገረ ስብከት የሁል ጊዜ ነቀርሳ የሆኑ አባቶችን በማሰቃየት የሚታወቁ አገልጋዮችን እንቃኛልን
  2. የእንግሊዝና አየርላንድ ሀገረ ስብከት 50 ዓመታት ጉዞ
  3. የደብረ ጽዮን ከ20 ዓመታት በላይ የዘለቀ መለያየት ምንጭ እና የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ከባለታሪኮቹ እንሰማለን

ይቆየን!

የጽርፈት አጋንንት ተዋርሶ ከ”Hara Tewahido ሐራ ተዋሕዶ” ወደ “ሐራ ዘተዋሕዶ”

በፊት ቃል በገባነው መሠረት ባነሳናቸው ርእሰ ጉዳዮች ላይ በመረጃና በማስረጃ ያልተደገፈ ጽሑፍ ላለመጻፍ በዚህ ገጽ አባላት ከተለያየ አቅጣጫ መረጃ የማሰባሰቡ ሂደት ስላልተጠናቀቀ በመዘግየታችን ይቅርታ እየጠየቅን ወደ አነሳናቸው ጉዳዮች አንድ በአንድ እንገባ፡፡

#ርእሰ ጉዳይ አንድ፡-የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ዛሬ ያለችበት አስተዳደራዊ እና መዋቅራዊ ልፍስፍስነት፣ ልሽቀትና ድክመት ላይ እንድትደረስ እነማን ምን ድርሻ ነበራቸው/አላቸው?

የማኅበራዊ ሚዲያ ጸሐፊዎች እና ገጾች

ይህን ርእሰ ጉዳይ የበለጠ ለመረዳትአንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍልን እናንሳ፡-

ይህቺ ሴት አገልግሎታቸውን፣ እውነትን ስለምትወድ፣ እነሱን ማሞገስ ፈልጋ ሳይሆን ሙገሳውን ቢቀበሉ ኖሮ ሄዳ ለማጭበርበሪያ እና ለገንዘብ መሰብሰቢያ ትጠቀምበት ነበር፡፡ በፍቅረ ነዋይ የታወረ ዓይነ ልቡናን እውነትን ከመቀበል ይልቅ ልብን በጥላቻ ይሞላል፡፡

#”ወደ ጸሎት ስፍራም ስንሄድ፥ የምዋርተኝነት መንፈስ የነበረባት ለጌቶችዋም እየጠነቈለች ብዙ ትርፍ ታመጣ የነበረች አንዲት ገረድ አገኘችን። እርስዋ ጳውሎስንና እኛን እየተከተለች፦ የመዳንን መንገድ የሚነግሩአችሁ እነዚህ ሰዎች የልዑል አምላክ ባሪያዎች ናቸው ብላ ትጮኽ ነበር። ይህንም እጅግ ቀን አደረገች። ጳውሎስ ግን ተቸገረና ዘወር ብሎ መንፈሱን፦ ከእርስዋ እንድትወጣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝሃለሁ አለው፤ በዚያም ሰዓት ወጣ።ጌቶችዋም የትርፋቸው ተስፋ እንደ ወጣ ባዩ ጊዜ ጳውሎስንና ሲላስን ይዘው ወደ ገበያ በሹማምት ፊት ጐተቱአቸው፤”ሐዋ.ሥራ 16:16-19

ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅ ይህን ክፍል በተረጎመበት “የገንዘብ ፍቅር ባለበት ቦታ ሁሉ ክፋት አለ፡፡ በጣም ክፉዎች ስለሆኑ እነሱ ገንዘብ ያግኙ እንጂ ልጅቷ በአጋንንት እስራት ብትኖር ጉዳያቸው አይደለም፡፡”

ዛሬም በማኅበራዊ ሚዲያ ገንዘብ ከፍለን ጻፉልኝ ካሏቸው፤ ወይም በዚህ ዘመን ላይክ፣ ሼር፣ ሰብስክራይብ፣ ኮፒ ሊንክ ገንዘብ የሚያመጣ ከሆነ ለምን ወንድማቸው አይሆንም፣ ለምን የትኛውም የአባቶች ወይም የቤተክርስቲያን ጉዳይ አይሆንም በርካታ እውነተኛ መሳይ ነገር ግን ርኩስ መንፈስ የሰፈራቸው አፈ ጻዲቆችን መበራከታቸው እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ነው፡፡

ሀ. የጽርፈት መንፈስ ተዋርሶ ያለባቸው/የነበረባቸው ጸሐፊዎችና ገጾች

#1. ደጀ ሰላም

የሐራ ተዋሕዶ የክፋት ወላጅ አባት የነበረው “ደጀ ሰላም” ይባል የነበረው ብሎግ ጸሐፊዎች የቤተክርስቲያ አባቶችን በተለይ ብጹአን አባቶችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ተላላኪ ለማድረግ ብቸኛ አማራጭ አድርገው ይዘውት የነበረው አባቶች የገጠማቸውንም ያልገጠማቸውንም ድቀት አደባባይ በማውጣት አባቶችን ማቃለልን፣ ማዋረድን እና የሞራል ገደላ(Character Assassination) ነው፡፡ በረከታቸው ይደርብንና ከፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ እና በርካታ ብጹአን አባቶችን በመርዛማ ብዕራቸው ወግተዋል፡፡ በኋላ ላይ የዚህ ብሎግ ባለቤት ማኅበረ ቅዱሳን ነው፤ እነ ኤፍሬም እሸቴ ናቸው የሚጽፉበት ተብሎ ስለነበር ማኅበሩ በስምዓ ጽድቅ ጋዜጣ 16ኛ ዓመት ቁጥር 21/ቅጽ 16 ቁጥር 182 ከሐምሌ 15-30 ቀን 2001 ዓ.ም ደጀ ሰላም የእኔ አይደለም ብሎ መግለጫ በማውጣቱ ተሳዳቢውም ጋኔንንም በዚያው ወጣ ብሎጉም ከነጸሐፊዎቹ ከሰመ ቤተክርስቲያንም ለጥቂት ጊዜ አረፈች፡፡

2. Hara Tewahido ሐራ ተዋሕዶ

ደጀ ሰላም ብሎግ ላይ አባቶችን በማዋረድ እና በማሸማቀቅ ከሚሰድቡቸውም ከሚያሰድቧቸውም የስድብ ገቢ የሚያገኙት ገንዘብ ስለነጠፈባቸው ማኅበሩ ደግሞ አላውቃችሁም ስላላቸው ለዳቦ የሚሆን ገንዘብ የሚያጡ መሆኑን ሲረዱ ከማኅበሩ መደበኛና ኢ-መደበኛ አገልግሎች ቀስ በቀስ ወጡ፡፡ በደጀ ሰላም ብሎግ ስለተነቃባቸው እንጂ ጋኔኑ ፈጽሞ ከውስጣቸው ተንቅሎ ስላልወጣ እነሱም ያ የሚያገኙት ገንዘብ አባቶችን ማዋረድ ቤተ ክርስቲያንን ማዋረድ መሆኑን ቢያውቁም በፍቅረ ነዋይ የገባባቸው ጋኔን ጥቅምት 12 ቀን 2005 ዓ.ም በታላቁ መልዐክ በቅዱስ ሚካኤል ቀን የያዛቸው ጋኔን Hara Tewahido ሐራ ተዋሕዶ (የተዋሕዶ ሠራዊት፣ የተዋሕዶ ወታደር) ብለው የበግ ለምድ ለብሰው ተኩላዎቹ ብቅ አሉ፡፡ ታዲያ እነዚህን ቡድኖች ከደጀ ሰላም ላይ ያካበቱት አባቶችን መዋረድና ማሸማቀቅ የስነ ልቡናና የሞራል ገደላ(Character Assassination) ተጨማሪ በጀት በመመደብ የጥቅምት እና የግንቦት የቅዱስ ሲኖዶስ ስበሰባ እያስቀረጹ በአባቶች መካከል ልዩነት እንዲሰፋ እና እርስ በእርስ እንዳይተማመኑ እያንዳንዱን ስበሰባ ቦታው ላይ ከብጹአን አባቶች ጋር እየተሰበሰቡ ያሉ በሚመስል መልኩ ወይም የቤተክርስቲያኒቱ ቃለ አቃባይ ተደርገው የተሾሙ በሚመስል ሁኔታ የጠዋት ፣የከሰዓት የቅዱስ ውሎ እያሉ የቤተክርስቲኒቱን የውስጥ ጉዳይ ዓይናቸው በፍቅረ ነዋይ ስለታወረ ለአደባባይ በማውጣት ለትዝብትና ለትችት አሳልፈው መስጠት ጀመሩ፡፡

እኛም የዚህ ገጽ እና ብሎግ አባላት ይህ ጉዳይ አደገኛና እና ቤተክርስቲያኒቱን ሰድቦ ለሰዳቢ የመስጠት የባንዳነት ተግባር በመሆኑ እነዚህ ጸሐፊዎች ማግኘት አለብን በማለት ብዙ ርቀት ተጓዝን፡፡ ጊዜ ቢፈጅብንም እልሃችንን ቢያስጨርሰንም እነዚህ በፍቅረ ነዋይ ያበዱ የጽርፈት መንፈስ ያደረባቸውን እኩያን ማወቅ ቻልን፡፡ በዚሁ አጋጣሚ ይህ አድካሚ ፍለጋ እና ማጋለጥ ከተጠናቀቀ በኋ የቤተክርስቲኒቱን ደመወዝ ከሁለትና ከሦስት ቦታ እየበሉ የነበሩ ያሉ “ታዋቂ እና አንቂ” ዘማርያ፣መምህራንና አገልጋዮች እኛ እኮ እነሱ እንደሆኑ እናውቅ ነበር እያሉ አፋቸውን ሞልተው ሲናገሩ በመስማታችን ያለንበትንና የደረስንበትን የመንፈሳዊ ሕይወት ዝለትና ዝቅጠት አሳይቶን አልፏል፡፡ በኋላ ላይ ብሎጉን በዋናነት ከሚዘውሩት መካከል እነ አሉላ ጥላሁን የፊተኛው መስመር ላይ ይኑሩ እንጂ ሰድቦ ማሰደቡ ላይ ግን ዛሬ በየደረጃው በመንግስት መዋቅር ያሉ ግለሰቦችና ብጹአን አባቶችን ጨምሮ በደንብ በቅንጅትና በመደራጀት ይሠሩ እንደነበር በጥናታችን ለማረጋገጥ ችልናል፡፡ ታዲያ ከጸሐፊዎች መካከል አንዳንዶቹ ልክ እንደ ቆሰለ አውሬ ማንነታቸው ስለተገለጠ ብቻ አጋልጠውናል በማለት የጠረጠሯቸውን ሰዎች ሁሉ ጋር እየሄዱ ለማስፈራራት እና ለማሸማቀቅ ቢሞክሩም አልተሳካም፡፡ የያዛቸው ጋኔን ለቋቸው ይሁን አይሁን እስከ ዛሬ ድረስ ማረጋገጥ ባንችልም ቡድኑ ከመጋቢት 28 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ መጻፍ አቆመ ቤተክርስቲያንም በድጋሜ አረፈች፡፡

ወደ ሚቀጥለው ከማለፋችን በፊት እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ እናንሳ፡፡ እነዚህ ሰዎች ለምን በዚህ እኩይ ተግባር ተሰማርተው ለሞኖር ፈለጉ? የሚለውን በስሱ መመለሱ ተገቢ ነው ብለን እናምናለን፡፡

አንድ አግልጋይም ይሁን አባት ራሱን ችሎ ጥረት የሚያደርግ እና ነገ ወደ ተሻለ ይደርሳል ብለው ከሰጉ የዚህ ቡድን አባላት እንደ አንድ መርህ የሚከተሉት ይሄ ሰውዬ ሊያመልጥ ስለሆነ #የመገደብ ዘመቻ ይከፈትበት በማለት ከአካላዊ ጥቃት እስከ ሕይወት ማጥፋት ድረስ ሊሄዱ እንደሚችሉ አመላካች ነገሮች እንዳሉ የሚያምኑ ብዙዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ ለምን? ለሚለው ጥያቄ ግን መልሱ በቃ ፍቅረ ነዋይ ነው፡፡

3. ሐራ ዘተዋሕዶ

ይህ ደግሞ ኅዳር 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ያንን የተላቀቅነውን የጽርፈት መንፈስ በግድ ካልተዋረስኩኝ ብሎ በትልቅ ድፍረትና የስድፍ አፍ የመጣ ነው፡፡ ከላይ እንደጠቀስነው ይህን ስም ይዞ ብቅ ማለት የተፈለገው ሐራ ተዋሕዶ በተሳዳቢነት እና የአባቶችን ክብር በማቃለል ያገኘውን ዝና በደንብ ስለሚያውቁ ከመሃል “ዘ”ን ጨምረው ብቅ አሉ፡፡

የዚህ ፌስቡክ ገጽ መሥራችና ባለቤት ዛሬ በሀገረ እንግሊዝ በስደት ያለና በአቡነ ሔኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዘመን ካህናትና አብያተ ክርስቲያናትን እንደ ላሜ ቦራ ያላበ የብዙ አገልጋይ ካህናት እንባና የግፍ ገንዘብ ከሀገር እንዲኮበልል ያደረገው የአቡኑ ልጅ የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ባለቤት የኤርምያስ ኪሮስ የግል ሀብትና ንብረት ነው፡፡

ለዛሬ አንድ ሁለት ማሳያ እናነሳና በቀጣይ ጽሑፍ እንግሊዝ ሀገር ከነማን ጋር ምን እየሠራ እንዳለና ከኢትዮጵያ ሲወጣ በየት በኩል ስንት ከፍሎ እንደወጣ በማስረጃ እንነግራችኋለን፡፡

#ማሳያ አንድ፡- ይህ ገጽ የኤርምያስ መሆኑን ለማወቅ ትንሽ ወደኋላ ሄደት ብሎ የለጠፋቸውን ጽሑፎች ማየት በቂ ነው፡፡ ይኸውም በሳዩት ደካማ አስተዳደርና በአስተዳደራቸው በነበረው ከፍተኛ የሆነ የሙስና መስፋፋት ምክንያት ለአንድ ብጹዕ አባት በማይገባ መልኩ ገንዘብ በግልጽ በፌስታል ይሰበስባሉ በማለት “አባ ኩርቱ” እስከ መባል የደረሱት አባቱ፣ አባታችን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥልጣን ዘመን ለማራዘም ካልተሳካም አጥፍቶ ለመጥፋት የተከፈተ የግል ገጹ ነው፡፡ በነገራችን ላይ ብዙ ወሬ ወዳጅ ሰው የበፊቱ የሐራ ገጽ መስሎት የተከላቸው ይመስለኛል፡፡ ነገር ግን የበፊቱ 101 ሺሕ ተከታይ ያለው ሲሆን ይሄኛው የኤርሚ ገጽ ግን 4.8 ሺህ ብቻ ተከታይ ያለው ነው፡፡ አጋንንታዊ ተዋርሶአቸውን ለማሳየት ስሙንና ሻማዋን ተጠቅሟታል፡፡ እናላችሁ በዚህ የፌስ ቡክ ገጽ የመጀመሪያ አፍ ማለቀቂያ የነበሩት የወቅቱ ጠቅላይ ሥራ አሥኪያጅ #አቡነ አብርሃም ነበሩ ከግንቦት 15 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ግንቦት 15 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ለሁለት ዓመታት ከጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ እስከሚወርዱ #ከ40 ጊዜ በላይ በዚህ የኤርሚ ገጽ ከፍ ዝቅ እየተደረጉ ተሰድበዋል በአንጻሩ አቡነ ሔኖክ ከንጉሥነት እስከ ቅዱስነት በሚደርስ ማንቆሎጳጰስ ተወድሰዋል፡፡

ይህ የፌስ ቡክ ገጽ በአባቶች መካከል ልዩነት እንዲሰፋ እና እርስ በእርስ እንዳይተማመኑ እና የትም ቦታ ተመድበው ቢሠሩ ሐዋርያዊ ግዴታቸውና የተሾሙበት አደራ ቢሆንም እሳቸውን ለመጠበቅ ተብሎ #መንግሥትን፣ #የደብር አሰተዳዳሪዎችን፣ #የመምሪያ ኃላፊዎች ሳይቀሩ #ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ፣#አቡነ ሳዊሮስ፣ #አቡነ ሩፋኤል፣ #አቡነ ፊልጰስ፣#አቡነ ዲዮስቆሪዮስ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ #አቡነ ያዕቆብ ከፍ ዝቅ ተደርገው ተብጠልጥለዋል፡፡

ቤተክርስቲያን ፈቃድ ራሷ ሰጥታ ራሷን እየሰደበና እያሰደባት ላለው የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል እና ባለቤቱ ኤርምያስ ኪሮስ በቀጣይ በስደት ባለበት ሀገረ እንግሊዝ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ ከማን ጋር ምን እኩይ ተግባር እየሠራ ነው የሚለውን እጃችን ላይ ስለገባ እንመለስበታለን::

ይቆየን!

#እርማችንን ማን ከመካከላችን ያጥፋልን?

አንኳን ለሆሳዕና በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

#እርማችንን ማን ከመካከላችን ያጥፋልን?

#የቤተ መቅድሱን ወንበዴዎች፣ ሻጭ ሸቃጭ ለዋጮችን ማን ያጽዳልን?

በዓለ ሆሳዕናን ባሰብኩ ቁጥር ሦስት ጥያቄዎች (ጉዳዮች) እዕምሮዬ ላይ ይመላለሳሉ:-

1. እኛ ብቻ አናውቅላችኋለን፣ የቤተ መቅደሱ(ሙኩራቡ) ጠባቂዎች የእግዚአብሔር እና የሕጉ አክባሪ አስከባሪ ጠበቆች እኛ ብቻ ነን የሚሉ ጸሐፍት እና ፈሪሳውያን ክርስቶስን ለመቀበል፣ ከእውነት ጎን ለመቆም፤ ስለ እውነት ለመመስከር ለምን አልቻሉም ?

2. መቅደሱን መሽጫ መሸቀጫ የወንበዴዎች ዋሻ እስከማድረግ ያደረሳቸውን ድፍረት ከየት አገኙ? ከላይ የተጠቀሱት የመቅደሱ ጠበቆች፣ የሕግ አክባሪና አስክባሪዎች ነን ባዮች ለምን የመቅደሱን የጸሎት ቤትነት ማስከበር(መጠበቅ) አልቻሉም?

3. የበዓለ ሆሳዕና ድምቀት ለሆኑ ሕጻናት(ተተኪ ትውልድ) የምናወርሳቸው ምንድነው? የሚሉት ናቸው።

እነዚህን ሦስት ጥያቄዎች (ጉዳዮች) አፍታቶ ማየት ለዛሬዬቱ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የአማኞቿ የሞራል ልዕልና ማጣት፣ በማኅበራዊ ሕይወት እና በኢኮኖሚያዊ ይዞታ የበታችነት አመክንዮ ለመረዳት ከማስቻሉ በላይ ለነገዪቱ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ እድገት ለመሥራት ያነሳሳል ብለን እናምለን።

የዚህ ገጽ አባላት ከረጅም ጊዜ በኋላ ወደዚህ መንደር ብቅ ብለን ለመጻፍ የተመለስነው ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና የማይቀብሉ ካህናት(አገልጋዮች) እና ምዕመናን ፣ ለውጥ ፈላጊ እና ተራማጅ የሆኑ አባቶችንና የቤተክርስቲያኒቱን አገልጋዮች ላይ ያነጣጠረ የሞራል ገድላ(Character Assassination) በማድረግ የማዳክም ሥራ፤ በዕቅድ(በዓላማ) ኃላፊነት እና ሥልጣን የተሰጣቸውን የመንጋው ጠባቂዎችን ተቀባይነት ለማሳጣት ”እረኛውን ምታ በጎቹም ይበተናሉ” የሚል መርህ በመያዝ ያለ እረፍት እና ያለ መታከት አጽራረ ተዋሕዶዎች ከውስጥም ከውጪም እየሠሩ መሆኑን በመገንዘባችን ነው፡፡

እሊህ አጽራረ ተዋሕዶዎች ቤተክርስቲያናችንና መዋቅሯን ለመናድ በሚናበቡ ነገር ግን የተለያዩ በሚመስሉ ቡድኖች የሚንቀሳቀሱ ናቸው፡፡ ይኸውም፡-

#የጥቅምትና የግንቦት ሲኖዶስ ስብሰባ በመጣ ቁጥር አባቶች አንድ ቦታ ተረጋግተው ከሠሩ እኩይ ተግባራቸው ስለሚነቃ እና ጥቅማቸው ስለሚቀርባቸው አጀንዳ የሚፈበርክ ቡድን፤

#ለቤተክርስቲያን መዋቅር የማይገዙ የካህናት፣ የአብያተ ክርስቲያናት፣ የአካባቢ ወጣቶች እና የምዕመናን ኅብረት በማቋቋም(በተለይ በውጪው ዓለም) ምዕመናን እና አባቶችን በጊዜያዊ አጀንዳ ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ የሚያደርግ ቡድን፤

#በአባቶች መካከል፣ በአባቶች እና ምዕመናን መካከል አለመተማመን ፣ አለመከባበር እንዲኖርና እና በአባቶቹ ተስፋ እንዲቆርጥ በማኅበራዊ ሚዲያ የሞራል ገደላ(Character Assassination) በመፈጸም ተግቶ የሚሠራ ቡድን፤

#የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን ምዕመናን ከማኅበራዊና ከፖለቲካዊ ሱታፌ እንዲሁም ከኦኮኖሚያዊ ተጽእኖ ፈጣሪነት ውጪ ማድረግን አሳክተናል ብለው ስለሚያስቡ ምዕመናን ከሱታፌ ቤተክርስቲያን(ከአገልግሎት) ውጪ ማድረግን በሰበካ ጉባኤ እና በሰ/ትቤት አመራርነት፣ በቤተክርስቲያኒ የአስተዳደር መዋቅር ውስጥ መሳተፍን እንደ ኮረንቲ እንዲፈራው በማድረግ ቤተክርስቲኒቱ ሰው ያጣች ይመስል በሥነ ምግባር ጉድለት የሚታወቁና ከአንድ መደብ በወንብድና በዝርፊያ የተነሱ የራሳቸውን አባላትን በማስመደብ በየደረጃው ያለውን የሥልጣን ተዋረድ ጠቅልሎ የሚይዝ የሚያስዝ ቡድን፤

ማደራጀት ጥቂቶቹ ሲሆን ወደ ፊት እያንዳንዱን በዝርዝር የምንሄድበት ይሆናል፡፡ በዚህ መሠረት በቀጣይ ጽሑፎቻችን፡

1. የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ዛሬ ያለችበት አስተዳደራዊ እና መዋቅራዊ ልፍስፍስነት፣ ልሽቀትና ድክመት ላይ እንድትደረስ እነማን ምን ድርሻ ነበራቸው/አላቸው?

2. እነማን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን ለማድክም ብሎም ለማጥፋት በዕቅድ እየሠሩ ነው/ነበሩ?

3. ሕገ ቤተክርስቲያን ስለነማን ምን ይላል እያንዳንዳችን ድርሻችን ምን ድረስ ነው?

4. ለሚቀጥለው ትውልድ በሰፊው ተዘፍቀንበት ያለውን አባቶችን ማቃለልን፣ ማዋረድን እና የሞራል ገደላ(Character Assassination) ነው የምናስተላልፈው?

እና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች ላይ በመወያየት፣ ጥያቄዎችን በመመለስ ፣ አስተያየት በመስጠት እና በመቀበል የቱንም ያህል ጊዜ ቢፈጅ አጽራረ ተዋሕዶን ለማስታገስ በዓላማ በእቅድ እየሠሩብን እንዳሉ ሁሉ እኛ እንዲሁ ለመሥራት ቃል እንገባለን፡፡

#ለዛሬ ግን

እርማችንን ማን ከመካከላችን ያጥፋልን?

በእስራኤል ዘሥጋ ታሪክ ውስጥ ሙሴንና አሮንን ጨምሮ ከግብጽ የተነሣው ማርና ወተት ወደ ምታፈሰው ወደ ተስፋይቱ ምድር እንዲገባ ተስፋ ተስጥቶት የነበረውን #ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በምድረ በዳ መክኖ ተንከራቶ እንዲቀር እንዲሞት ያደሩጉት እና ለሽንፈት ምክንያት የሆኑት ሁለት ዋንኛ ታሪኮችና ክስተቶች በስሱ እናነሳለን፡፡

1. በኦሪ.ዘኁ 13 እና 14 ከ12ቱ ሰላዮች መካከል አሥሩ #ክፉ ወሬ በማውራት ራሳቸውንም ሆነ ሕዝቡን(600 ሺህ ሕዝብ) በበረሃ እንዲጠፋ ያደረጉበትንና

2.በ መ. ኢያ 7 እስራኤል በጋይ ሰዎች እንዲሸነፉ እና በመጨረሻ ለመላ ቤተሰቡ መሞት ምክንያት የሆነውን ያልተፈቀደ ተግባር በመፈጸም በእስራኤል መካከል እርም የሆነውን ነገር የደበቀው የዛራ ልጅ አካን ታሪክ ማየት ለወደፊት ለምናነሳቸው ጉዳዮች እጅግ ጠቃሚ ታሪኮች ናቸው፡፡

በእኛ እምነት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ዛሬ ላለችበት ደረጃ ያደረሷት እና ልጆችዋም በማያቋርጥ መጠላላት፣ መነቃቀፍ እና መጠፋፋት ውስጥ እንዲጓዙ እያደረጉ ያሉት እነዚህ ጉዳዮች ናቸው ብለን በብርቱ ስለምናም በማያቋርጥ ጥረትና ትግል በእግዚአብሔር ፈቃድ፣ በቅዱሳን ምልጃና ጸሎት ልንፈታቸው ከሚገቡ ጉዳዮች መካከል፡-

1. #ክፉ ወሬ እንደ ማውራት ማኅበራዊ ሚዲያዎቻችን ቤተክርስቲያንና አገልጋዮችን በመተቸት በማሸማቀቅ የተሙሉ በመሆናቸው

2. #እርም ነገርን እንደ ዛራ ልጅ አካን እንደ መደበቅ ነውር የሆነ ዘረኝነትን፣ የግል ጥቅምን ብቻ ማሳደድን፣ እኔ ብቻ አውቅላችኋለሁ ባይነትን እና ለመንጋው አለመጨነቅን ፣የመድረክ ብቻ(የታይታ) ክርስቲያንነት ማስወገድ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት

ከነዓን መንግሥተ ሰማያት ከመግባት እንዳያስቀረን፤ የመከነና የባከነ አማኞችን ቁጥር ቀንሶ እንደ ጌታ እግዚአብሔር ፈቃድ የሚኖር ምዕመናን ለማብዛት የሚረዳን በመሆኑ እግዚአብሔር ቢያደርሰን ቢያቆየንና ቢፈቅድ ከትንሣኤ በዓል በኋላ ከላይ ያነሳናቸውን ጉዳዮች በዝርዝር እንሄድበታለን፡፡

ይቆየን

ተጻፈ መጋቢት 27 ቀን 2018 ዓ.ም፡፡

በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በየቀኑ እየተፈለፈሉ ያሉ ሉተራዊና ምዕራባዊ አካሄድን የሚከተሉ ማኅበራት የት ያደርሱን ይሆን?

አስቀድመን በፌስ ቡክ ገጻችን ላይ አንድ ጥያቄ ጠይቀን ነበር፡፡ ይኸውም የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ወደ ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ለምን ተቀየረ? የሚል ጥያቄ ጠይቀን በጣም የሚገርማችሁ ማን መልስ ቢሰጥ ጥሩ ነው? ሞዐ ተዋሕዶ ነበር!!!ለቡ!!!

ለማንኛውም ከላይ ወደ አነሳሁት ርዕስ ልመለስ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚፈጠሩ ችግሮችን እንደ መልካምና ምቹ አጋጣሚ የሚጠቀሙ አሊያም ከችግሩ ፈጣሪዎች ጋር ቀድመው የተወያዩ በሚመስል መልኩ ችግር በተፈጠረ ማግስት የሚፈጠሩ ማኅበራትና ግበረ ኃይሎች ወይም ኅብረቶች(በነገራን ላይ #ኅብረት ዓይነተኛዋ የማጭበርበሪያ የዳቦ ስም ናት) በአብዛኛው ኢ-መዋቅራዊ ከመሆናቸው ባሻገር ከአብዛኛዎቹ ጀርባ ያሉት ግለሰቦች ተመሳሳይ መሆናቸው ከላይ ያነሳሁን ጥያቄ እንደጠይቅ አስገድዶኛል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ “ሕጋዊ በሆነ መንገድ የቤተ ክርስቲያንን መብት ለማስከበር ይሠራል፡፡” ብሎ ቃል እየገባ

እንዴት ልደግፍ? የእኔ ድርሻ ምንድነው? ምንተ ንግበር? ብሎ ከመጠየቅ ይልቅ ኃያላችንን ለማዳከም፣ የትኩረት አቅጣጫችን የተበታተነና ልክ እንደ ሉተራውያን በተለያየ ስም (መካነ ኢየሱስ፣ሙሉ ወንጌል፣ ቃለ ሕይወት፣ ጌጃ…) አንድ ሆነው ሲያበቁ ራሳቸውን በተለያየ ስያሜ እየሰየሙ የዋሕኑና ደጉን ምዕመን ማሰናከል ምን ይሉታል? እስካሁን ከዚህ በታች ከዘረዘርናቸው ማኅበራት፣ ኅብረት፣ ግብረ ኃይል ሂደት ሁላችንም መረዳት እንደምንችለው የስበት ማዕከላቸውና መዳረሻቸው  ገንዘብ መሰብሰብና የግል ተከታይ(ቲፎዞ) ማፍራት ነው፡፡ ያለ ቅዱስ ሲኖስ ዕውቅናና ፈቃድ ማኅበራት፣ ኅብረት፣ ግብረ ኃይል እያሉ ማቋቋም ለቤተ ክርስቲያነቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳያል፡፡ እንዲሁም እኔ አውቅላችኋለሁ በሚል የትዕቢት ስሜት አንዱን አባት ተቆርቋሪ፤ ሌላው ለዘብተኛ፤ የተቀረውን ደግሞ ደንታ ቢስ ለማስመሰል የሚሠራውን እያንዳንዱን ሸፍጥ ታሪክ የመዘገበው ስለሆነ ዋጋ ሳያስከፍለን አይቀርም፡፡ በብፁዓን አባቶችም መካከል መለያያት ለመፍጠር የሚጠቀሙበት እንዲህ ዓይነቱ ስልት ያረጀ ያፈጀ ከመሆኑም ባሻገር የእግዚአብሔር ቃል ግን በመ. ምሳሌ 6፡ 16-19 “እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው ፤ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፤…በወንድማማች መካከል ጠብን የሚዘራ፤” እንዲል በዚህ መንገድ የሚጓዙ በአባታችን በእግዚአብሔር ዘንድ ጽዩፍ ስለሆኑ የ10፣ የ20፣ የ100 ዓመት ደረጃውን የጠበቀ ስልታዊ ዕቅድ ቢያቅዱ፤ ቀን ከሌሊት በትጋት ቢሠሩ እንኳ ወጤቱ ፍሬ አልባ መሆን ወይም መራራ ፍሬ ማፍራት ነው፡፡

ለምሳሌ የሕዝቡን ትኩሳት ተጠቅሞ ለምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ተብሎ የተቋቋመውን ሚዲያ ግለሰቦች እንደፈለጋቸው እንዲሆኑበት በላይክ፣ በሰብስክራይብ እና በሼር እንዲጠቀሙበት ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ብለው ሲሰይሙ ዝም ስላል ዛሬ ደግሞ ራሱን ልክ የቤተ ክርስቲያኒቱ ዋንኛ ተጠሪ አካል አድርጎ የምክክርና የጥናታዊ ጽሑፍ መድረክ ለመላው ኦርቶዶክሳውያን ማለት ምን ማለት ነው? ማነው መላ ኦርቶዶክሳዊያንን ጠሪ ያደረጋችሁ ? ማነው በእኛ ላይ የሾማችሁ? መድረኩ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችን የመመለስ ሓላፊነት አላችሁ? ለእናንተ ሲሆን ቀኖና ቤተ ክርስቲያን አይሠራም እንዴ? ጉባኤው በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት፣በጠቅላይ ቤተ ክህነት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፤በጠቅላይ ቤተ ክህነት እውቅና አለው? ፈቃድ ያለውን የቤተ ክርስቲያኒቱን ሚዲያ መጠቀም ለምን አልቻላችሁም? ዙሮ ዙሮ ከዩቲዩብ ለሚገኝ ድቃቂ ሳንቲም ብሎ ኢ-መዋቅራዊና ሁሉን አቀፍ ያልሆነው #ሞዐ ተዋሕዶ ላይ ከፊት የተሰለፉ ሰዎችን ለመስበርና ለማሰበር የሚደረገው ሩጫና ጥድፊያ ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝን ማስተዋል ይጠቅማል፡፡

በአጠቃላይ ባለፉት ሁለት እና ሦስት ዓመታት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ የተፈጠሩ መጠነ ሰፊ  ችግሩችን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ለግለሰቦች የዕለት ጉርስ የዓመት ልብስ  ከመጥቀም ባሻገር ይሄ ነው የሚባል ሁለንተናዊ ጥቅምና ለውጥ ያላመጡ ማኅበራት፤ኅብረት እና ግበረ ኃይሎች መካከል፡-

  1. ፈለገ ባኮስ የሰባክያን እና ዘማርያን ኅብረት
  2. የአዕላፋት ድምፅ የካህናትና ምዕመናን ተናሥዖት ኅብረት
  3. ሠለስቱ ምዕት የመንፈሳዊያን ማኅበራት ኅብረት
  4. የአስተዳዳሪዎች ኅብረት
  5. የወጣቶችና ጎልማሶች ማኅበራት ኅብረት
  6. የነገረ መለኮት ምሩቃን ማኅበር
  7. የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
  8. ጴጥሮሳውያን የቤተ ክርስቲያን መብትና ክብር አስጠባቂ ማኅበራት ኅብረት
  9. ማኅበረ ካህናት ዘሰሜን አሜሪካ
  10. ማኅበረ ካህናት ዘዩኬና አየር ላንድ ሲሆኑ
  11. አሁን ደግሞ #ሞዐ ተዋሕዶ
  12. …ነገ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ችግር ሲፈጠር የሚፈጠሩ ይቀጥላሉ…

ከላይ የተዘረዘሩት እጅግ ጥቂቶቹ ሲሆኑ እነዚህ 99% እርስ በእርሳቸው በስውር መረብ የተሳሰሩ ናቸው፡፡ በእነዚህ ውስጥ ዋና ዋኛዎቹ ተዋንያን የራሳቸው ቋሚ ገቢ የሌላቸው፤ አለን የሚሉት ደግሞ በቃኝ የማያውቁ ሆድ አምላኩዎች ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የሁሉም መርሕ “የቤተ ክርስቲያንን መብት እናስከብራለን” ነው፡፡ የሚገርመው ነገር ደግሞ ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ማኅበር(ኅብረት) አንዲት ነገር ከለጠፈ ሳይጣራ፣ ሊሰጥ የሚችለው ጥቅም ፣ሊያስከትል የሚችለው ጉዳት ሳይጤን የእግር ኳስ ደጋፊ ይመስል እየተቀባበለ ይለጥፋል፡፡ ይሄ ከንቱነት ነው!!!

ሌላኛው ስጋቴ ማኅበረ ቅዱሳን እየቆየ ሲሄድ ዳንኤልና ግብረ አበሮቹ በሠሩት ሴራ ደመወዝዝ ከሚከፈላቸው መደበኛ የአድባራትና የገዳማት አገልጋዮች፣ ከሰባክያና ከሰ/ት/ቤት ጋር የመለያያት፣ያለመናበብ ብሎም የጥላቻ ስሜት እንደገጠመውና እንደተጋረጠበት ሁሉ የሞዐ ተዋሕዶ አጀማመርና አካሄድም ይሄንን ልዩነት የበለጠ የሚያሰፋው ካልሆነ በስተቀር የሚያጠብ ስላልሆነ ከተሳፈርንበት ጋላቢ ፈረስ ወረድ፤ ቆም ብለን ማሰብ አለብን!

በመጨረሻም በርካታ ተከታይ ያላቸው ሁለቱ ታላላቅ መምህራኖቻችን መ/ር ሰሎሞን ተስፋዬ እና ፍሬው አራት ዐይና የለጠፉትን በአጽንኦት ማየት የበርካታ ሰዎችን ስሜት ለመረዳት ይጠቅማልና ከታች ለጥፌዋለሁ፡፡

ስለ “ሞዐ ተዋሕዶ”ቆም! በደንብ ቆም! በትክክል ቆም! ተብሎ ይታሰብ!!!

ተጻፈ የካቲት 2014 ዓ.ም

“ሞዐ ተዋሕዶ ግብረ ኃይል” ከድጡ ወደ ማጡ…

ሰላም ተወዳጆች!

ይህን ጦማር እሰከምጽፍበት ቀን ድረስ የ”ሞዐ ተዋሕዶ” የምሥረታ ዜና ድንጋጤን፣ ግርምትንና ግራ መጋባትን ፈጥሮብኝ ከመሥራች ጉባኤ ተሳታፊ እስከ ጽንፍ ተቃዋሚ ሰዎችን ሀሳብ ለመረዳት ሞከርኩ ነገር ግን አሁን ድንጋጤዬ፤ ግርምቴና ግራ መጋባቴ ቀጥሏል፡፡

ድንጋጤዬ፡- በማስተዋልና በብስለታቸው የማከብራቸውና ተስፋ የምጥልባቸው መ/ር ፋንታሁን ዋቄ፣ ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ፣ ዶ/ር ዘርዓየሁ ስሜን የመሳሰሉ ሰዎች አልፎ አልፎ በፈቃደኝነት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን አሰስተወዋጽኦ ሲያደርጉ አእነንደነበረሩ በቢተታወቀቅመም በሚጠሉትና በሚኮንኑት በሆቴል መስብሰብን ተግባራዊ አድርገው ኢ-መዋቅራዊ፣ አደገኛ፣ ከፋፋይ፣ ሌላውን ያገለለ የተነናጥል የቡድንና የሸፍጥ አሠራር አሁን ግን አእነሰሱ ራሳቸው ተዘፍቀው መገኘታቸው ይገርማል! ከድጡ ወደ ማጡ ይልሃል ይሄ ነው!ሎቱ ስብሐት!

ግርምቴ፡- መድረኩን ሲመሩ የነበሩ አባቶች ጴንጤያዊ የማስፎከርና ዘመንኛና አስጨብጫቢ ቲፎዞ ፈላጊ ሰባክያን የሚጠቀሙበትን መንገድ እጅግ የተከበሩ ሰዎች በተሰበሰቡበት ጉባኤ በባዶ ፉከራ ሲያስጨበጭቡ መዋላቸው ይገርማል!፤ ለምሳሌ ይሄንን ለመረዳት ይቺን ያዳምጧት https://youtu.be/vLMPonfS5fk

ግራ መጋባቴ፡- ፍሬ አልባ ሆነው እንደመከኑ በርካታ ጥቅመኛ ማኅበራትና ግብረ ኃይሎች ስብስብ መሥራቾች  እና የቤተ ክርስቲያን መጠቃትና ተቆርቋሪነት መነሻ አድርጎ፣ ብዙ ተወርቶለት፣ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ሸክም የሚጋራ ተቋም ተመሠረተልን ብለን ተስፋ አድርገን ሳለ ለመሪዎቹ(ኮሚቴዎች) ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤትና የጥቅማ ጥቅም ስጦታ እነሆ ተብሎ እንዲመክንና የቴሌቪዥን መስኮት አዳማቂ ብቻ ሆኖ እንዲቀር የሆነውን የ”ጴጥሮሳውያን የቤተ ክርስቲያን ክብርና መብት አስጠባቂ ኅብረት” መስራቾች ዛሬ ደግሞ “ተዋሕዶ ታሸንፋለች!” ብለው በሌላ ገጽ፤ በሌላ መሠረት መምጣት ለምን ፈለጉ? መልስ የለም! ግራ መጋባቴ ቀጥሏል…

“የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት፣ በፍቅርና በመተሳሰብ ያሸንፋል! ከማለት ይልቅ “ኢትዮጵያ ታሸንፋለች” ሲሉ ምን እያሉ እንደሆኑ የሚያውቁት አይመስለኝም፡፡ በየጊዜው የሚነሱ ተዋንያን እንድናተርፍ ያደረጉን ረሀብ፣ማኅበራዊ ኢኮኖሚያዊ የሥነ መንግሥት የአመራር ችግር ነው፡፡ ነጻ ማውጣት የሚቻለው በልዑል እግዚአብሔር መሪነት በቃልም በሥራም እንጂየጭድ እሳት ይመስል በፍከራና በመንቦግቦግ አይደለም፡፡ ማሸነፍ የሚገኘው በጥበብ በማስተዋልና ሁሉን ተረድቶና አሳትፎ በመጓዝ ነው፡፡ታዲያ ኢትዮጵያ አሸንፋለች?

አሁንም ሁሉን አቀፍ ያልሆነ፣ኢ-መዋቅራዊና ከአባቶች ጋር መግባባትና ይሁኝታ ያላገኘ አካሄድ ይዞ ተዋሕዶ ታሸንፋለች ማለት ከድጡ ወደ ማጡ ይከተን ካልሆነ በቀር መፍትሔ ያመጣል የሚል ግምት የለኝም፡፡

ይሄንን ለማሳየት አንድ ምሳሌ ላንሳ በትግራይ ክልል የነበረውን ችግር ለመፍታት ከቱርክ ተሞክሮ ተወስዶ በዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም ተቋም ተጠንቶ በወቅቱ የነበረውን የእስላሞች እንቅስቃሴ ለማስተንፈስ ተብሎ የተቋቋመው “የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ” እና የሰላም ሚኒስቴር ማንንም ሳያማክሩ አንድ ውሳኔ ይወስናሉ፡፡ ይኸውም 95% የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኝ ባለበት ክልል የቅዱስ ሲኖዶስን አባላትን ሳያማክሩና የመፍትሔው አካል እንዲሆኑ ሳያደርጉ ቢያንስ እንኳን ዛሬ ራሳችንን ችለናል ብለው መግለጫ እስከ ማውጣት የደረሱ የትግራዋይ 4/5 ጳጳሳትን ሳያካትቱ ለሥልጣን የሚሻኮቱ የፓለቲካ ኃይሎችን ኩርፊያ ለማስማማት የተደረገው እንቅስቃሴ ተቃባይነትን ካለማግኘቱ ባሻገር አድርገናል ለማለት ያህል ለፖለቲካ ፍጆታ ዋለ እንጂ መፍትሔ እንደማያመጣ እየታወቀ የተዋቀረ ግብረ ኃይልና ስብስብ ነበር፡፡

ሞዐ ተዋሕዶ ግብረ ኃይል ከድጡ ወደ ማጡ ወሳጅ ጎዳና የሚሆነው ለምንድነው

ሀ. ማኅበሩ በርካታ የሠራቸው ፍሬያማ ሥራዎች፣ እንዲጫጩና ልክ ማደበሪያ እንደለመደ መሬት እንዲመክኑ ትልቁን ሚና ሲጫወት የቆየው በውጪ የስለላ ድርጅት ተላላኪነቱን በመጠቀም አቅም ያላቸውንና እውነተኛ የተዋሕዶ ልጆችን በማሳደድና ብፁዓን አባቶችን እንዲከፋፈሉና አንድነት እንዳይኖራቸው እንደ አይጥ በፁዓን አባቶች ቤት እየተሹለኮለካና ድብቅ ካሜራ ጭምር በማስቀመጥ ሲያተራምሰንየኖረው፤ ቀድሞ ከቁልፍ የሕወሐት ሰዎች ጋር ጥብቅ ቁርኝነት የነበረው፤ በኋላ ግን ጥቡዓን በሆኑ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ሁላችንም በተገኘንበት ደባውና ሴራው በማጋለጥ አንተ ሰላይ እጅህን ከቤተ ክርስቲያን ላይ አንሳ ስለተባለና ስለተነቃበት እናቱ እንሞተችበት  በአንድ ጉባኤ ስቅስቅ ብሎ ያለቀሰው እና ዛሬ ደግሞ የተጋለጠውንና ያልተሳካውን ካባውን ቀይሮ የአዲሱ ፓርቲ አባል ሁኖ በልጽጎ ፓርላማ ገብቶ ያለው ባያብል ሙላቴን የመሳሰሉ መሰሪዎችና ዲቃላዎችነቀርሳዎች ከጀርባ መኖራቸው ነው፡፡

  • ለ. በስልክና በትስስር መስመር ላይ ብቻ ያሉትን ብቻ ያካተተ መሆኑ ነው፡፡ ይህም ማለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ጉዳት፣ ስደት፣ መከራ እየደረሰባት ያለው ከየትኛውም ጊዜ ይልቅ በዚህ ዘመን መሆኑ እሙን ነው፡፡ ተዋሕዶ ማሸነፍ የምትችለው በቅዱስ ሲኖዶስ ምክርና ውሳኔ፤ በሊቃውንትና በገዳማውያን ጸሎትና ግሳጼ፣ በእውነተኛ ሰባክያን መሰጠትና ትምህርት፤ በሰ/ት/ቤት ተማሪዎች አገልግሎትና ትጋት እንጂ 90% የማኅበሩ ደጋፊ በሆኑበት ግብረ ኃይል ሊሆን አይችልም፡፡

ሐ. ማሸነፍ የምንችለው ችግር በተከሰተ ቁጥር ገንዘብና እርዳታ ሰብሳቢና አሰባሳቢ በመሆንና እዚህም እዚያም ግብረ ኃያልና ማኅበር በማቋቋም ሳይሆን ሕጻናት እየተጫወቱበት ያለውን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየደረጃው ያሉ መዋቅር ውስጥ ገብቶ በማገልገልና በማጠናከር እንጂ ምንም እንኳ ጠቃሚ ሀሳብ ብንይዝም የቤተ ክርስቲያኒቱ የበላይና ወሳኝ አካላት ምንም አያመጡም ወይም አቅም የላቸውም በሚመስል እሳቤ ወደ ጎን በማለትና እንደ አሜባ በማባዛት አይደለም፡፡ ስማቸው ሊወድቅ ወይም ገቢያቸው ሊቀንስ ሲጀምር በድርድ ያስቀመጧትን መረጃ ብቅ እያደረጉ ወሳኝ አካላት ናቸው ብለን እንድናስብ በይሉኝታ ላም እሳት ወልዳ ዓይነት የሆኑ ያሉን ማኅበራትና ግብረ ኃይሎች ይበቁናል፡፡

መ. የሞ ተዋሕዶ ባለ ሰባት ነጥቡ የአቋም መግለጫ ሲጠቃለል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ራሷን የቻለች፣ ተደማጭነት ያላት፣ ማንም እንደፈለገ የማያሽከረክራት ተቋም ሁና ማየት ነው ብዬ ወስጄዋለሁ፡፡ ይህ ከሆነ ቤተ ክርስቲያን ማሸነፍ የምትችለው ሁለንተናዊ በሆነ መንገድ ራሷን ስትችል እንደሆነ አምናለሁ፡፡

ነገር ግን በታሪካችን ውስጥ ይህ ጉዳይ ያልተሳካበትን መንገድ ማየቱ ለዛሬ ከጠቀመን እነሆ፡-

1ኛ. ደጃዝማች ወልደ ሰማዕት ገብረ ወልድ “ሕይወቴ” በሚለው መጽሐፋቸው ከገጽ 522-24 ላይ እንዳሠፈሩት በንጉሡ ጊዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ራሷን ችላ እንድትተዳደር ለማድረግ ማለትም ሀብቷ ባንድ ላይ ተጠቃሎ ቤተ ክርስቲያኗ በምታዘጋጀው በጀት መሠረት አብያተ ክርስቲያናት እንዲተዳደሩበት በሚል በአቶ ከበደ አበበ ሰብሳቢነት የተቋቋመው ሰባት ታላላቅ ሰዎች ያሉበት ግብረ ኃይል ዕቅድ እንዳይሳካ ያደረገው በረከታቸው ትድረሰንና መቼም ከሰው ስህተት ከብረት ዝገት አይጠፋምና በግፍ በሰማዕትነት ያለፉት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ በሚያስተምሯቸውና በሚረዷቸው ሰዎች ምክንያት የቤተ ክርስቲያኒቱ ተቋማት ሆነው ነገር ግን ጠቀም ያለ የሆነ የኪራይ ገንዘብ የሚያስገኙ ለግላቸው የሚውሉ ተቋማት ገቢ ወደ አንድ ቋት እንዲገባና ከዚያ እንዲጠቀሙ ሲነገራቸው ፈቃደኛ ባለመሆናቸው መሆኑን ጽፈዋል፡፡

2ኛ. ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ “አንድ አፍታ ላውጋችሁ” በሚለው መጽሐፋቸው ገጽ  246-47 በደርግ ዘመን ከንጉሡ ዘመን ግብረ ኃይል አባላት መካከል ሁለቱን በማካተት በኮሎኔል አጥናፉ አደራጅነት ቤተ ክርስቲያን ከመንግሥት ድጋፍ ወጥታ ራሷን የምትችልበት መንገድ እንዲፈጠር በዶ/ር ክነፈ ርግብ ዘለቀ ሰብሳቢነት የሚመራ ሰባት አባላት ያሉት ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ነበር፡፡ ነገር ግን በእነ ሊቀ ማእምራን አበባው ይግዛው ጠንሳሽነት ያልተሰጣቸውን አጀንዳ ፓትርያርኩ ለመንግሥት ሳያሳውቁ አቡነ ጳውሎስን ጨምሮ ሦስት ጳጳሳትን ሾመዋልና ከፕትርክና ይነሱ ብለው ሰበር የሆነ ሰባሪ አጀንዳና መለያየት ምክንያት ይሄኛውም ግብረ ኃይል ውጤታማ ሳይሆን እንደቀረ ጽፈዋል፡፡

3ኛ. በዚሁ በቅርብ ጊዜ ደግሞ በብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ መሪነት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ወቅት ቤተ ክርስቲያን ዘመኑን በዋጀ የአሠራር መንገድ እንድትጓዝና ራሷን እንድትችል ታቅዶ ጥልቅ የጥናት ሰነዶች ተዘጋጅተው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አድባራት ፭ቱ ከለባት ማኅበረ ቅዱሳን ቦታህን ሊቀማህ መጣብህ በሚል ውክቢያ እንዲዳፈን የተደረገው እንዲሁም የመከነውና በሞዐ ተዋሕዶ ሊዋጥ ሊሰለቀጥ በመንገድ ላይ ያለው ጴጥሮሳውያን የቤተ ክርስቲያን ክብርና መብት አስጠባቂ ኅብረት ለምን የተመሠረቱት አላማ ሊያሳኩ አቃታቸው? ብሎ ገምግሞ ያለውን ፈትሾ አጥርቶ የተነሳ ባለመሆኑ ነው፡፡(በፎቶ የቀረበውን የሁለቱን  መመሳሰልና አንዱ ሌላውን ይውጠው ዘንድ እንዲገባ ለቡ!)

በርግጥ ኢ-መዋቅራዊ አደረጃጀት እሳት ለማጥፋት፣ የሕዝብን ሥልጣን ይዞ ሕዝብ ላይ የሚያላግጥን ባለሥልጣን ለማስደንገጥና አደብ ለማስያዝ ጠቃሚ ቢሆንም ይህ ዓይነቱ አካሄድ አስተዳደሯ ክህነታዊ ለሆነው ለታላቋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካለመመጠኑም በላይ በማኅበሩ ውስጥ የተሰገሰጉ በጣት የሚቆጠሩ ለቅዱስ ሲኖዶስና ብፁዓን አባቶች ክብር የሌላቸውና ንቀትን የተለማመዱ አካላት አነሳሽነትና ገፋፊነት እየተደረገ ያለ  አካሄድ በመሆኑ አደጋው ከባድ ነው፡፡ አንዱ ማሳያ ገና ሲጀምር የፌስ ቡክ ገጹን ከቨር ፎቶ እንኳ የብፁዓን አባቶች ማድረግ ሲገባው የአንድ ሊቀ ጳጳስ ማድረጉ ትዝብት ውስጥ የሚከትና ለጥርጣሬ የሚጋብዝ ነው፡፡

ስለዚህ  “ሞዐ ተዋሕዶ ግብረ ኃይል” ከድጡ ወደ ማጡ የሚከተን እንዳይሆን ከሆቴል ወጥቶ ወደ ቤተ ክርስቲያን፤ ለቤተ ክርስቲያን የማውቅላት እኔ ብቻ ነኝ ከሚለው ግንጥል አካሄድ ወጥቶ ሁሉን አቀፍ እና በቤተ ክርሰቲያን መዋቅር ሥር ሆኖ ተጠያቂነትና ኃላፊነት በሚሰማው መንገድ ለመጓዝ ራሱን ቢያርም መልካም ነው እላለሁ፡፡

ይቆየን!

የካቲት 2014 ዓ.ም

በአቋም መግለጫ ጋጋታ ሀገርንም ሆነ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መታደግ አይቻልም!!!

ተወዳጆች እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የእረፍቷ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን!!!

በአቋም መግለጫ አወጣጥ ቅደም ትከተል ካልሆነ በስተቀር በቃል የቤተ ክርስቲያኒቱ ተቆርቋሪ መሳዮች በተግባር ግን ጥቅማቸው እስካልተነካ ጆሮ ዳባ ብለው ከኖሩ፥ አብዛኞቹ ለሠሩትና ወደፊት ለሚሠሩት የኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችን ወኔና ሥነ ልቡና የመስለብና የማምከን ሥራ ቤትና ዳጎስ ያለ ገንዘብ ከከተማ አስተዳደሩ በሽልማት መልክ የተቸራቸው፥ ሌሎቹ ድግሞ በማኅበራት ስም ተሰባስበው የቀድሞውን ሥርዓት ነቃፊ መስለው በስውር ግን አሽከርና ተላላኪ ሁነው በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ ደባ ሲፍጽሙ የኖሩ ለአቋም መግለጫ ሲራወጡ ስመለከት ግራ በተጋባ ስሜት ውስጥ ሆኜ ይህችን መጣጥፍ ጣፍኩኝ።

ከፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ጋር የማልስማማባቸው አንዳንድ ነገሮች ቢኖሩኝም ለዛሬ “አንዳፍታ ላውጋችሁ” ከሚለው መጽሐፋቸው ገጽ 368-9 ላይ የሰፈረ ሀሳባቸውን ተዋስኩኝ።  ምንም እንኳን የእምነቱ ተከታይ ባይሆኑም የፕሮቴስታንት ሚሲዮናውያን በሀገርና በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚፍጽሙትን ደባ “አድናቃፊና ደንቃራዎች” በሚል ንዑስ ርእስ ሥር እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል፦

“ወንጌላውያን ነን የሚሉ ሚሽኔሪዎች—የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን፥ በጠቅላላው የኦርቶዶክስን ሃይማኖት የሚጠሉ ወገኖች ኢትዮጵያ የመጡት ችግረኞችን ለመርዳት ወይም ያላመነውን ለማሳመን፥ ወይም የስዊዲን ሚሽኔሪዎች እንደሚሉት  የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ለመርዳት ሳይሆን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን አፍርሶ አዲስ ቤተ ክርስቲያን ለመሥራት መሆኑን ከነሱው ውስጥ አንዱ በሕልሙ ያየላትን አፍርሶ አዲስ ቤተ ክርስቲያን መሥራት በግላጭ ተናግሯል። ዝርዝሩን እኔና ሌሎች “The Missionary Factor in Ethiopia” በሚል ርዕስ ባሳተምነው መጽሐፍ ውስጥ ማየት ይቻላል። “

እነሱ በግላጭ እንዲህ እያሉ የኛዎቹ ግርግርን እየጠበቁ ውርውር የሚሉ ጥቅመኞችና ቲፎዞ አሰባሳቢዎች ራሳቸው አቋም አልባ ሆነው የሚወጡትም “የአቋም መግልጫ/ማሳወቂያ” ከቤተ ክህነት ቅርጫት ላያልፍ እንዲህ ማዳነቅ መቀባበል ምን የሚሉት ነው??? ምናልባት ይሄ አቋም አልባ መግልጫቸው የዘመናዊ ሙዳየ ምጽዋት ለቃቃሚዎች(youtubers) ፍጆታ ማሟያና ማስተዋወቂያ፥ ሰብስክራይብ ፥ ሼር አድርጉ እያሉ ቁም ስቅላችንን ለሚያበሉን አስተዋጾ እንዲያብረክት ካልሆነ በስተቀር ሀገርንም ሆነ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን  አስቦና አቅዶ ሊያጠፋ የተነሳ አካልን በብጣሽ ወረቀት ጋጋታ ማሸነፍ አይቻልም።

እዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባው ዛሬ ላይ በመናፍቃን እየተፈጸመ ያለው ግፍ እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ የመጣ አይደለም። ኦነግም በለው ሸኔ የግብር አባታቸውን ጸር ክርስቶሰ አቋም ያለውን ሉተርን መስለውና አህለው እንዲብቅሉ ትልቁን ሚና እየተጫወተች ያለችው ብዙም ያልተወራላትና አድፍጣ የጥፋት ሠራዊቶችን ያሰማራችብን የሉተር እናት ጀርመን ናት። እስቲ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ እንፈልግ!!!

  1. ለምን አውሮጳዊቷ ሀገር ወለጋ ላይ ከዛሬ 100 ዓመት በፊት ሆስፒታል ገነባች?
  2. ኦነጎችና ጀርመኖች ምን አዛመዳቸው?
  3. ዛሬ በየደረጃው ያሉ ኢትዮጵያን የሚያስተዳድሯት አብዛኛው መሪዎች በኢትዮጵያ የሉተራን ቤተ ክርስቲያን ክንፍ የሆንችው መካነ ኢየሱስ አባላት የሆኑት በአጋጣሚ ይሆን?
  4. ኤርትራ ከኢትዮጵያ ስትገነጠል የሚሽኔሪዎች ድርሻ ምን ነበር?
  5. የአናሲሞስ ነሲቡን በግእዝ ፊደላት የተጻፈውን የመጀመሪያውን መጽሐፍ ቅዱስ ማን በላቲን ብቻ ወደ ሚል መርሕ ወሰደው?
  6. ??? እያላቸሁ ቀጥሉበት

ደጃዝማች ወልደ ሰማዕት ገብረ ወልድ “ሕይወቴ” በሚል ድንቅ መጽሐፋቸው ገጽ 474-5 በ1966 ዓ/ም የነበረውን ሁኔታ እንዲህ ይገልጹታል፥-

“ የጊምቢ አውራጃ ቀደም ብለው ሚሲዮኖቸ የገቡበት ስለሆነ ከቀሩት አውራጃዎች ሁሉ ይብልጥ የሚሲዮን ትምህርት ቤቶችና የጤና አገልግሎት ያገኛል።———–በአይራ ጉሊሶ ወረዳ በአይራ መንደር በጀርመናውያን ሚሲዮናውያን የሚካሄደው ሆስፒታል ይገኛል። ጀርመናውያኑ የጤና አገልግሎት ብቻ ሳይሆን ሕዝቡ በእናት አገሩ ላይ እንዲያምጽ፣ ኢትዮጵያዊነቱን በሚያስክድ ፖለቲካ ይመርዙታል። ኦነግ ተጠንስሶ ወደ ቀሪዎቹ የአውራጃው ክፍሎች እንዲዛመት በማድረግ ላይ እንዳተኮሩ ደረስኩብት።—-“ ይላሉ።

ጉሊሶ ማለት የዛሬዋ የሰማዕታት መንደር ናት! ለቡ!!!

ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ በ”መድሎተ ጽድቅ ቁጥር ፫” ገጽ 275-6 ይህንኑ እንዲህ በማለት ገልጦታል፦

“ወደ እኛ ሀገር የመጡ የጀርመን ፕሮቴስታንት ሚሲዮናውያን በዋናነት የሰበኩትም ስለ “ኢየሱስ” ሳይሆን ኦርቶዶክስ ጠል እና ሴማዊ ሕዝብ ጠል የሆነ አስተሳሰብን ማሥረጽ ነበር። ከ100 ዓመታት ኦርቶዶክሳዊነትን  እና ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰብን የማስጠላት ዘመቻ በኃላም ውጤቱን አሁን በሀገራችን እየተመለከትን ነው።—-ሉተራውያን  የጀርመን ፕሮቴስታንቶች በኢትዮጵያ ላይ ያስቡትን የረጂም ዘመን ዕቅድ ይዘው ወደ ኢትዮጵያ ይዘመቱበት ሃኖቨር የተባለውን ቦታ የዚህ መጽሐፍ ጸሐፊ በዓይኑ ለማየት ችሏል። እንደዚሁም እነዚያው የጀርመን ሚሲዮናውያን ከእኛው ቤተ ክርስቲያን ካህናትና አገልጋዮች መካከል በስውር እየመለመሉ   ኦርቶዶክሳዊነትንና ኢትዮጵያዊ ማንነትን የሚጸየፍና እንደ ጭቋኝ እንዲመለከት እያደረጉ የሚቀርጹብትን የፕሮቴስታንት ስብከት የጀመሩበትን ቦታም እንዲሁ በምዕራብ ወለጋ ላይ  በዓይኑ  አይቷል።“

እንግዲህ ኦነግ በዳቦ ስሙ በሸኔ የሚፈጽመው እጅግ ዘግናኝ ጭፍጨፋ በማን ትምህርት እና ሥልጠና እንደሆነና ጀርመኖቹ ከአንድ ምዕተ ዓምት በላይ የመካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያንን እንዴት እንደተጠቀሙባት ሳሰብ ለእነዚህ ሰዎች የአቋም መግልጫ ምናቸው ነው??? ምንተ ንግበር??? እላለሁ።

አሁን በሥልጣን ላይ በየደረጃው ያሉት ዋንኞቹ መሪዎች ለማስመሰልና ለማደናገር ያህል ዛሬ ላይ የሆነ የጴንጤ ድርጅት ላይ አምልኮአቸውን ይፈጽሙ እኝጂ ዓላማ አንግበው የተነሱት የሉተራን ክንፍ ከሆነችው ከመካነ ኢየሱስ ነው። ያ ማለት የመሥራቾቻው ዓላማና ግብ የሆነው ሕዝቡ በእናት አገሩ ላይ እንዲያምጽና ኢትዮጵያዊነቱን በሚያስክድ ፖለቲካ እንዲመራና እንዲመራ መፈጸም ትይዩ ዓላማቸው ነው ማለት ነው።

ለሁላችንም የሚበጀን ግን ይህንን የክፋት አሠራር አስወግደን ለሁላችንም ማዕከላችን የሰላምና ፍቅር ባለቤት የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አርአያ ተከትለንና ተመልክተን መከባበር፣ መደማመጥና መከባበር እንጂ ሃይማኖተኛ መስሎ ሊያጠፉን የተነሱት የምዕራባውያንን እኩይ ተልዕኮ ተሸክሞ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ለመምራት መሞከር ሩቅ የማያደርስ ጎዳና ከመሆኑ ባሻገር ኦርቶዶክሳዊነትና ኢትዮጵያዊ ማንነትን እየተሠራ ያለውን ግፍ ታሪክና የታሪክ ጸሐፍት በአግባቡ እየመዘገቡት በመሆኑ በደም የጨቀየ የግፍ ታሪክ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ባንትጋ መልካም ነው።

ሌላው ጉዳይ ታላላቅ የኦሮሞ፣ የአማራ፥ የደቡብ እና ከሌሎችም ብሄር የተውጣጡ አርበኞች የገነቧትን ኢትዮጵያ በጽንፈኞች አንድነታችን፣ የህዝብ አብሮነት እንዲፈርስ መንቀሳቀስና ደጉን የኦሮሞ ሕዝብ ከለላ አድርጎ በከፋፍለህ ግዛው መርሕ አማራንና ትግራዋይን እንደ ሕዝብ ደም እንዲቃቡ እንደተደረገ ሁሉ፤ የጀርመኖቹ ምልምል በሆኑ ባለሥልጣናትና የኦነግ( ሸኔ) ሠራዊት የኦሮሞና የአማራ ሕዝብን እንደ ሕዝብ ደም ለማቃባት የሚደረገው ደባና ሩጫ እንዲቆም በጸሎት እየተጉ ቆም ብሎ ማሰብ፣ ማቀድ እንጂ የአቋም መግለጫ ጋጋታ ምን ያህል እንደ አሜባ እንደተበጣጠስን እንጂ ቆራጥንታችንና የዓላማ ሰዎች መሆናችንን የማያሳይ በመሆኑ በአስተውሎት ብንጓዝ እላላሁ።

ይቀጥላል+++

ተጻፈ ጥር 2014

እንኳን በሰላምና በጤና ለብርሃነ መስቀሉ አደረሰን! አደረሳችሁ!

ባይ ባይ ኢ-አማኒው  አሥር አለቃ ፋንታሁን ሙጬ!!!

የዘንድሮው የደመራ በዓል አከባበር ሀገራችንና ወገኖቻችን በጣም በከባድና በአሳዛኝ ሁኔታ ላይ ሁነው ብናከብርም ዳሩ #በመስቀል አደባባይ እጅግ ደስ የሚል የበረከት በዓል አክብረናል፡፡ ብዙዎቻችን ከረካንበት ነገር አንዱ በዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል ላይ ከ the…the…the…is… is…was…ነጻ የሆነ ተገቢው የሆነ የመድረክ መሪ አግኝተን እነ ሙጬን ከመሳሰሉ ደፋሮች ተላቀን በተገቢው ቦታ ተገቢውን ሰው በማየታችን ነው፡፡

ከመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ጋር በተያያዘ በአማኙም ይሁን በኢ-አማንያን ዘንድ ተደጋግሞ ከሚሰነዘሩ ትችቶች አንዱ ምነው ቤተክርስቲያኒቱ ሰው የላትም እንዴ? ምነው ሌላው ቢቀር present, past and future tense ለይቶ በማይናገር ሰው መድረኩን የምትጫወቱበት ይባል ነበር፡፡

ዘንድሮ እግዚአብሔር ይመስገን መድረኩ ለሚገባ ሰው በመሰጠቱ መምህራችን ቀሲስ ዳንኤል ይደልዎ! ብለናል፡፡ ለዚህ ትልቁን ድርሻ የተወጡት አድርባይነት የሌለባቸው ባሕታዊና የልማት አባት የሆኑት ብጹዕ አቡነ ያሬድ የጠቅላይ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ እንደሚሆኑ ጥርጥር የለንም፡፡ ምክንያቱም ልክ ወደ ኃላፊነት እንደመጡ የመጀመሪያ ሥራ ያደረጉት ለረጅም አመታት አንደ መዥገር ተጣብቆ ሲጫወትበት ከኖረበት የሰበካ ኩባኤ ማደራጃ መመሪያ ኃላፊነት በማስወገድ ነው፡፡ በዚህም ከአድርባይነት የጸዱ እውነተኛ የቤተክርስቲያኒቱ አባት መሆናቸውን በተግባር አስመስክረዋል፡፡

በምትኩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጪ ግንኙነት የበላይ ኃላፊ፣ የነገረ መለኮት ሊቅ፣ መምህር፣ ተመራማሪ፣የሃይማኖት፣ የታሪክ፣ የባህልና የሥነ ጥበብ ባለሙያና ፀሐፊ የሆኑት የቤተክርስቲያናችን ዕንቁ ልጅ ለሆኑት ለመምህር ቀሲስ ዳንኤል ሰይፈሚካኤል መስጠቱ ይበል ያሰኛል፡፡ ቅድስት ቤተክርስቲያን ብዙ ጊዜ የምትሰደበው እነ ሙጬ የመሳሰሉ መንገደኛና የምንግዜም ደም መጣጭ ሰዎች ሳይገባቸው ቦታ ይዘው ነው፡፡ ይህ የማስተካከያ እርምጃ በሌሎችም ዘርፎች እንደሚቀጥሉ ተስፋ አለን!!!

ባይ ባይ ኢ-አማኒው  አሥር አለቃ ፋንታሁን ሙጬ!!!

መልካም በዓል!

ይቆየን  

ጳጉሜን ለሁሉም፣ የሁሉም፣በሁሉም

ሰላም!ሰላም!ወዳጆች

ዛሬ ላካፍላችሁ የወደድኩት ርእሰ ጉዳይ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሀገር አቀፍ የአምስት ቀናት ጸሎት፣ ጾምና ምህላ ማወጁን ተከትሎ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ

  • ምን አገባውና ለምን ያውጃል?
  • ስለ ምህላውና ጾሙ አፈጻጸምና ጥቅም ከማውራት ይልቅ ፓትርያርኩ ለምን መግለጫው ላይ አልተገኙም?
  • ጳጉሜን 1፣2…የእንትን ቀን የእንትን ቀን እያልን ከማክበር በጾም በጸሎት ማሳለፍ ይሻላል ከሚሉ አስተሳሰቦችና አስተያየቶችን ጀምሮ  የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የወሰነው ውሳኔ ጊዜውን የዋጀ መልካም ተግባር ነው እስከሚሉት ዋልታ ረገጥ ሀሳቦች ሲንሰራሸሩ በማየቴ ጥቂት ለማለት ነው፡፡

በእኔ እምነት የሃይማኖት ተቋማትም ይሁኑ ሀገር ከገቡበት ቅርቃር መውጫ ብቸኛ መንገድ የቤተክርስቲያን ጸሎትና ጥበብ በመታመን ነው፡፡ ምክንያቱም ኢትዮጵያ የመዳኛና ከችግር የመውጫ ተስፋና መንገዷ እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ቅዱስ ዳዊት ‹‹ኢትዮጵያ ታበጽእ እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር ›› መዝ 67፡31 ፤‹‹ይገንዩ ቅድሜሁ ኢትዮጵያ ወጸላእቱሂ ሐመደ ይቀምሑ፤በፊቱም ኢትዮጵያ ይሰግዳሉ፣ ጠላቶቹም አፈር ይልሳሉ›› መዝ 71፡9  እንዲል ጠላት ከወረወረው ጦር ከክፉዎች ሴራና ከአባር፣ቸነፈር፣ከወረርሽኝ…መዳን የምንችለው በአግዚአብሔር ታምነን በምናደርገው ጸሎት ነው፡፡ በኮቪድ 19 ምክንያት ከ28 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ያልቃሉ ተብሎ ቢሟረትብንም ኢትዮጵያውያን ወደ ተስፋችን ወደ እግዚአብሔር ተግተን በመማጸናችን ሕዝበ ነነዌን ያሰበ አስቦ አድኖናል፡፡

ምንም እንኳን ቢዘገይም ዛሬም በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አነሳሽነት ለሀገር ሰላምና አንድነት ጾም፣ ጸሎትና ምህላ  መታወጁ መልካም ነው፡፡ ለዚህም የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን በመወከል በብዙ ድካም የሚወጡ የሚወርዱ የጉባኤው ዋና ጸሐፊ ሊ/ትጉሃን ቀሲስ ተጋይ ታደለ የመሳሰሉ ትጉኃን ምስጋና ይገባዋቸል፡፡

የዘንድሮውን የጳጉሜን የጾም፣ ጸሎትና ምህላ መርሐግብር አስመልክቶ ቢስተካከሉ የምንሻቸውን ሀሳቦች  ላጋራችሁ ፡፡

እንዲህ ዓይነት መርሐግብሮች ሲዘጋጁ ብዙ ጊዜ ለኢትዮጵያውያን በሙሉ እንደተዘጋጁ ቢነገርም እውነታው ግን መርሐ ግብሮቹ በደበዘዘ መልኩም ቢሆን ተፈጻሚ የሚሆኑት በከተሞችና ቴሌቪዥን ባላቸው ሰዎች ቤት በከፊል ነው፡፡ ስለዚህ ተፈጻሚ ሆነው ውጤት ማስገኘት እንዲችሉ መርሐ ግብሮቹ ለሁሉም፣ የሁሉም፣በሁሉም መሆን አለባቸው፡፡

  • ለሁሉም፡- ይህ ማለት አብዛኛው የሀገሪቱ ሕዝብ ማለት 80 በመቶው በገጠር ከመኖሩ አንጻር ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን ታስቦ ሊሆን ይገባዋል፡፡ በጦርነት ወቅት የመጀመሪያው ተጠቂና አገር ጠባቂ ይሄው ከግምት ውስጥ የማናስገባው 80 በመቶው በገጠር የሚኖረው ማኅበረሰብ በመሆኑ ወደ አዋጅ ከመገባቱ በፊት ዛሬም ነገም ቢሆን የምናዘጋጃቸው መርሐ ግብሮቻችን ሁሉ እነዚህን ወገኖች ታሳቢ ማድረጉን በቅድሚያ ማረጋገጥ ይገባል ማለት ነው፡፡
    • የሁሉም፡- ብዙ ጊዜ በቤተክርስቲያናችንም ይሁን በሀገራችን የሚታዩ ችግሮች ምንጭ እኔ ላስብልህ፣ላውራልህ፣ልስራልህ፣ልኑርልህ፣ላስተዳድርህ እና የመሳሰሉ ጽንፍ የወጡ የራስ ወዳድነት መገለጫ ጠባያት ናቸው፡፡ ስለዚህ የምናከናውናቸው የትኛውም ሀገራዊ ጉዳዮችና መርሐ ግብሮች ኅብረተሰቡ የእኔ ብሎ ተቀብሎ ያለነቀፋ በደስታ እንዲተገብራቸውና የሁሉ እንዲሆኑ ቀደሞ አቅዶ መሥራት ይገባል እንጂ ዋዜማ ላይ ደርሶ እኔ ባወጣሁሉህ መርሐ ግብር ተመራ ማለት ወደ ውጤት ከማደረስ ይልቅ የእነሱ እንጂ የእኛ ብሎ ተቀብሎ እንዳይተገብረው ያደርጋልና ለቡ፡፡
    • በሁሉም፡- ካልተሳሳትኩኝ የአሁኑም መርሐ ግብርም ሊከናወን የታሰበው ቴሌቪዥን ላላቸውና የከተማ ሰዎች ሥራ ጨርሰው ሲመለሱ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ነው፡፡ ይሄም እቅዱ ወጤታማ እንዳይሆን ያደርገዋል፡፡ ቴሌቪዥን ያለው ምን ያህሉ የኅብረተሰብ ክፍል ነው? 3ት ሰዓት ላይ ምን ያህሉ የኅብረተሰብ ክፍል ይመቸዋል? ለሚሉ መሰል በርካታ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የጾም፣ ጸሎትና ምህላ መርሐግብሮቻችን በሁሉም የሀገሪቱ ጫፎች ተደራሽ ሆነው መልስ ማምጣት የሚችሉ መሆን እንዲችሉ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ትሁን የሀገሪቱ የተለያዩ ተቋማት በሬድዮና በቀላሉ ተደራሽ የሆኑ የመገናኛ ብዙኃን እንደየቦታውና ሁኔታው አመቺ የሆነ ሰዓት በመጠቀም ይህ ታላቅ ሕዝብ በጋራ ወደ ጌታ፣ አምላኩና የፍጥረት ሁሉ ፈጣሪ ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔር እንዲጸልይ ሁኔታዎች ማመቻቸት ቀዳሚ ተግባር ቢሆን መልካም ነው፡፡

በአጠቃላይ ይህ ሕዝብ በት. አሞጽ 9፡7 ላይ ‹‹ የእስራኤል ልጆች ሆይ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ›› ቅዱስ ዳዊት በመዝ 86፡4 ‹‹… የኢትዮጵያም ሕዝብ እነዚያ በዚያ ተወለዱ›› ተብሎ የተመሰከረለት ታላቅ ሕዝብ በመሆኑ የምናዘጋጃቸው መርሐ ግብሮች ከ20 በመቶ የማይበልጠውን የከተማውን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ከ80 በመቶ በላይ የሆነውን የገጠሪቱ ሕዝባችንን ብዙኃኑን ያማከለ እንዲሆን በትኩረት መሥራት ይፈልጋል፡፡ በኢትዮጵያዊነቱ ከማይደራደረው የአፋር፣የሶማሌና የጋምቤላ ሕዝብ ጀምሮ የቤተክርስቲያናችንም ይሁን የሀገራችን ገጽታና ጸጋ ለማጠልሸት ከሚሠሩ ጥቂት ምግባረ ብልሹ ሰዎች በቀር አብዛኛው የሀገራችን ሕዝብ በእግዚአብሔር የሚያምን ሰለራሱ ሳይሆን ስለጎረቤቱና ስለወገኑ የሚያለቅስ ደግ ሕዝብ በመሆኑ አስፈሪውን ዘመነ ኮቪድ ጠብቆ እያሻገረን ያለው ጌታ አምላክ የሁሉ ፈጣሪ እግዚአብሔር አምላክ ሰላሙን፣ ፍቅሩን፣ አንድነቱን ያድለን ዘንድ፤

ተንሥኡ ለሰላም!

ተንሥኡ ለፍቅር!

ተንሥኡ ለጸሎት!

ነሐሴ 30 ቀን 2013 ዓ.ም