
4. በደቡብ አፍሪካ አጣሪ ሆነው ተመደበው ስለነበሩ ግለሰቦች ማንነት
በመሠረቱ በመጀመሪያ አጣሪ ሁነው የተመደቡት ሦስት ልዑካን ሲሆኑ እሊህም አቡነ ማቴዎስ የመገናኛ ብዙሃን የበላይ ጠባቂ፣ ሊ/ማ ፋንታሁን ሙጬ እና መ/ሃ አብርሃም ገረመው ናቸው፡፡ ብጹዕ አቡነ ማቴዎስ ከልዑካኑ ጋር ከተጓዙ ነገሩ ስለሚበላሽ አስቀድሞም ብጹዕነታቸው የተመረጡት በዓላማ ስለነበረ ማለት ቲም ዲዮስቆሪዮስ ስለሆኑ ከተመረጡ በኋላ ምክንያት ፈጥሮ ማስቀረት ስለሚቻል ማለቴ ነው፡፡ ከደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ ቪዛ ከተመታላቸው በኋላ ጥሩ ህልም አላየሁም፣ሊቀ ጳጳሱ ስልክ አላነሱልኝም እዚያ ሄጄ የማንም ዱርዬ መጫወቻ መሆን አልፈልግም ፣ቪዛ ቶሎ ስላልደረሰከአሜሪካ ጉዞዬ ጋር ስለተጋጨብኝ በሚል ተልካሻ ምክንያት ሆን ብለው ከአጣሪ ቡድኑ ጋር ሳይሄዱ ቀርተዋል፡፡ በመሠረቱ አቡነ ማቴዎስ ከተወለዱበት የምንጃር ሾንኮራዋ ምንታምር ቀበሌ ጀምሮ ከቤተሰባቸው ጋር የነበራቸው ያለመስማማት ጠባይ፣በመናገሻ አምባ ማርያም እያሉ የፈጸሙት ተግባር፣ ጳጳስ ከሆኑ በኋላ በመከራ ከታረቋቸው ለቤተሰቦቻቸው በገዙት የFSR አይሱዚ በንግድ ሥራ መሠማራታቸው፣አቧሬ አከባቢ በገነቡት ቤት የሚያስተዳድሩትን ‹‹የግል ቤተሰብ›› እንዲሁም ከሱማሌው የቤተክርስቲያንና የምዕመናን ቃጠሎና ስደት በኋላ አሞኛል በሚል ሰበብ ከሀገረ ስበከቱ ሸሽተው አዲስ አበባ የኢኦተቤ የመገናኛ ብዙኃን የበላይ ጠባቂ በብዙ ልመና ከሆኑ በኋላ የሚፈጽሟቸውን ተግባራት ስለማውቅ ብዙም አልገረመኝም፡፡ብጹዕነታቸው የሱማሌው ድንጋጤ አስካሁን ስላልለቀቃቸው እሳቸው ያላሳዩንን ጥብአት በቴሌቪዥን መስኮት እየቀረቡ ዘራፍ! ማለት ዋና ሥራቸው ሁኗል፡፡ ታዲያ የብጹዕነታቸውን መቅረት በፈጠረላቸው ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ደፋሮቹና ጅቦቹም ግብዣው የተላካላቸው አቡነ ያዕቆብ ከሚመሩበት ሀገረ ስብከት ቢሆንም ሁሉም እንደሚያውቀው የሄዱበትን የተንኮል(የሴራ) ድርጊት ለማከናወን በመሆኑ ማለትም ከኢትዮጵያው ሲኖዶስ ከእነ አቡነ ሳዊሮስ ከአሜሪካ ደግሞ ከእነ አቡነ ቴዎፍሎስ ጋር ነገር ለመተብተብ ስለማይመቻቸው ያረፉት እነ አባ አእምሮ ባዘጋጁላቸው ቦታ ነበር፡፡ እነዚህ ሁለቱ አጣሪዎች ምቹ የሰይጣን ፈረስነታቸውን ለመረዳት ማንነታቸውን ማወቁ አስፈላጊ በመሆኑ እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ፡-
ሀ. ሊቀ ማዕምራን ፋንታሁን ሙጬ
ከዚህ በፊት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በፈጸመ ታሪክ የማይረሳው እኩይ ተግባር ምክንያት በሐራውያን ‹‹መስኪድ አልባው እስላም›› ተብሎ የነበረው አሥር አለቃ ፋንታሁን ሙጬ በጥቅምት 2002 ዓ.ም በጊዜያዊነት የአዲስ አበባ ሥራ አስኪያጅ ሆኖ ተመርጦ ከገባ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ አብያተክርስቲያናት ሲሞናዊነት መደብ ይዞ እንዲሰራበት ሕጋዊ እውቅና የሰጠ የቤተክርስቲያን የምንጊዜም ጠላትና የተራቡና የማይጠግቡ የቤተክህነቱ ጅቦች ራስ ነው፡፡ እኔ ሰለ ፋንታሁን ብዙ ከማወራ የአሁኑ ሊቀጠበብት ዘሪሁን ሙላቱ(ዶ/ር) ፈታሒ በጽድቅ በሚል የብዕር ስም ባዘጋጃት ‹‹የሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች›› ተብላ በተሰራጨችው እና እስከ እስር በዳረገችው አነስተኛ ባለ 50 ገጽ መጽሐፍ ከገጽ 9-23 ላይ አሥር አለቃ ፋንታሁን ሙጬን በአግባቡ ስለገለጠው ሙሉ ንባቡን ለእናንተ ትቼ በወፍ በረር ሙጬን(በነገራችን ላይ ቤተክህነት ውስጥ የእርሱን ስም መጥራት ያረክሰናል በሚል የሚጠሩት በአባቱ ስም ነው) ላስተዋውቃችሁ፡-

ዳሰሳ ዘአሥር አለቃ ፋንታሁን ሙጬ

‹‹ይህ ሥነ ምግባሩ የተበላሸ፣ ቀኖና ቤ/ክን ያፈረሰ፣ በወሲብ ቅሌትና በዝሙት ኃጢአት እግዚአብሔር ለማይድን በሽታ አሳልፎ የሰጠው ሲሆን …ይህ ግለሰብ ለዚህ የዋና ሥራ አስኪያጅነት ሥልጣን የሚያበቃው መንፈሳዊ ሕይወትም ይሁን ሥጋዊ ጤንነት እንዲሁም የስራ ልምድ የሌለው በመሆኑ ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን በሚሊንየሙ ድፍን አንደ ሺህ ዓመት ያላጋጠማትን ፈተና አሁን እየተጋፈጠች ትገኛለችና ብጹአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ካህናትና ምዕመናን በጸሎትና በጾም ሊያስወግዱት የሚገባ ልቡሰ ሥጋ ሰይጣን ነው፡፡…..››
- የትምህርት ችሎታውም..‹‹..አቶ ፋንታሁን ሙጬ በቅድስት ሥላሴ በነበረው የትምህርት ቤት ቆይታው በጣም ሰነፍ ከመሆኑ የተነሳ 3ኤፍ የሚል ቅጽል ስም ወጥቶለት እንደነበር ..እስከ ዛሬ ድረስ በቅጽል ስምነት ይጠቀሙበታል፡፡…ሌሎች ነጻ የትምህርት ዕድል ማግኘት ሲገባቸው በኦስትርያ ቬና ያለች የሮም ካቶሊክ ቤ/ክን ት/ቱን ብትፈቅድለትም መማር ስላቃተው ይኸው ከ10 ዓመት ያላነሰ ት/ቱን መጨረስ አቅቶት እስከ ዛሬ ድረስ ሲዳክር ይገኛል….አቶ ፋንታሁን ሙጬም በኦስትርያ ቬና የካቶሊክ ቤ/ክን ዩኒቨርስቲ ሲቀላቀል የፈረመው ፎርም በካቶሊክ ቀኖና መሠረት ሚስት እንደሌለው ወደ ፊትም እንደማያገባ ውሉ ላይ በጣት አሻራው ፈርሞ ነበር ት/ቱን የጀመረው፡፡ ይሁንና እውነትና ንጋት እያደረ መጥራቱ አይቀርምና የኋላ ኋላ ሚስት እንዳለው የሚያውቁ ኢትዮጵያውያን መረጃውን ለካቶሊክ ቤ/ክን በፎቶ አስደግፈው አቀረቡ፡፡ እርሱም በግንባር ቀርቦ ሲጠየቅ ሚስቴ አይደለችም ወደ ፊት እኔም ማግባት አልፈልግም ይልቁንም የካቶሊክ ቄስ ነው መሆን የምፈልገው በማለት መሀላውን አጸናው፡፡….የእሱ ማምታታትና ማጭበርበር ያበሳጫቸው ምዕመናን ሚስቱ ኦስትርያ ቬና የምትመጣበትን መንገድ አመቻችተው እንድትመጣ አደረጉ…በነበራት የጉብኝት ጊዜ የህግ ባለቤቱ መሆኗን ገልጻለች የጉብኝት ጊዜዋን ጨርሳ ወደ ሀገሯ በመጣች ጊዜ እርሱም አብሯት መጥቷል፡፡ ከዚህ በኋላ ወዲያውኑ መርዝ በጥብጦ ስላጠጣት የሞቷ ቀን ተፋጥኗል፡፡…››
- ‹‹…ሰብአዊነት የሌለው አቶ ፋንታሁን ሙጬ ሰብአዊ መብት የሚባል ነገር አላውቅም እስከ ማለት መድረሱ ድፍረት ቢሆንም እስከ አሁን ድረስ በዚህ ጨካኝና ደርግ ሰው ንጹሐን የቤተክርስቲያን አባቶች በረሀብ በእንግልት በመሰቃየታቸው…መቼም ሰውን በተግባሩ መሰየምና መግለጽ ስድብ ሳይሆን ባህርይውን ማብራራት እንደሆነ በተለይ በስነ ጽሑፍ የተሰማሩ ሁሉ የሚያውቁት የአገላለጽ ስታይል ነው፡፡አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ጴጥሮስን በአንድ ወቅት ሰይጣን ብሎ ገስጾታል፡፡የገሊላውን ሄሮድስን ደግሞ ቀበሮ ብሎታል፡፡ይህ ማለት በእንስሳቱ መመሰል ሳይሆን በእንስሳቱ ባሕርይ ሰዎቹን መግለጽ ነው፡፡…ስለሆነም መቼም ቅዱስ ሚካኤል የረገጠው ዲያብሎስ በአካል ገዝፎ በመልክ መስሎ በባህርይ ተስተካክሎ ሊመሰልልን ብቻ ሳይሆን ወክሎ ሰይጣንን ሊሰራ የሚችልም ተዋናይ ሰው ብንፈልግ ‹ሁሉም ሰው እረ ፋንታሁን ሙጬ አለልን› እንደሚል እርግጠኛ ነን፡፡…የላሜህ መንፈስ የተጸናወተው አቶ ፋንታሁን በነበረው ቆይታ ወለተ ገብርኤልና ወለተ ሚካኤል የተባሉ ሁለት እህትማማቾችን አገባችኋለሁ በማለት በሩካቤ እንደተገናኛቸው እርሱ ራሱ አንዳንዴ እየቃዠ የሚያወራ ሲሆን…››
- ሥጋዊ ጤንነቱን በተመለከተ…አቶ ፋንታሁን ሙጬ ተስፋ የቆረጠ ስለተያዘበት በሽታ እንኳን ዛሬ ድረስ በቂ መረጃ የሌለው አጥፍቶ ጠፊ ነው፡፡ …አቶ ፋንሁን ሙጬ በትዳሩ ላይ ባደረሰው ከፍተኛ ደባ፣ ቅሌትና የወሲብ መዘዝ ብዙዎችን ወደ መቃብር አሳዷል፡፡ የዚሁ ክፉ ተግባሩ ዋንኛ ተጠቂ ደግሞ በባለቤትነት አግብቷት የነበረችው ባለቤቱ ወ/ሮ ሠናይት ነበረች ነፍሷን ይማረውና አሁንም በሕይወት የለችም፡፡ ሌሎች ከአራት ያላነሱ ጓደኞቹ ደግሞ ማለትም እንድን ሴት ለአራት ለአምስት እየሆኑ ይተኙ ስለነበረ…››
- ይህም በእጅጉ የሚያሳየው ነገር ቢኖር አቶ ፋንታሁን ሙጬ ታዲያ እንኳን የቅድስት ቤተክርስቲያን ጉዳይ ሊያሳስበው ቀርቶ የራሱ ጉዳይና ጤንነት የማያሳስበው ተስፋ የቆረጠ ሰው መሆኑን ብቻ እንረዳለን፡፡
- የኢኮኖሚ አቅሙ …ይህ ሰው በላ አጥፍቶ ጠፊ ግለሰብ ከዚህ በፊት አይሰርቅም አይዋሽም እንድንል የሚያስችለን የኢኮኖሚ መሠረትም ሆነ አቅም አልነበረውም ዳሩ ግን አሁን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ጥሬ ገንዘብ ያለው ያለ አግባብ ብልጽግናን በአቋራጭ የተቆናጠጠ ወቅታዊ ባለጸጋ ሆኗል፡፡ ይህንንም የባለጸግነት መንገድ ያገኘው ባለው የስራ ልምድና የትምህርት ችሎታ ሳይሆን በዘረፋና በሙስና ነው፡፡
- ፖለቲካዊ ሕይወቱ…አቶ ፋንታሁን ሙጬ የፖለቲካ ሕይወቱን የጀመረው እንዲህ በቀላሉ በቅርብ የሚገመት አይደለም በደርግ ዘመን ብላቴን ሄዶ የውትድርና ሳይንስ በመማር ከሰለጠነ በኋላ በሱሉልታ ከተማ መሳሪያ ታጣቂ ሆኖ ደርግን አገልግሏል፡፡ በኋላም የተጠቀሰውን ክላሽ መምሬ ጥበቡ ለተባሉ ቄስ ጎፋ ገብርኤል ቤ/ክን ወስዶ አስረክቧል፡፡ አቶ ፋንታሁን ሙጬ በደርግ ዘመን በነበረው ንቁ እግዚአብሔር የለሽ የፖለቲካ ምልከታው የሃምሳ አለቃነት ማዕረግን የተቀበለ ጨካኝ የደርግ ሰው ነው፡፡ ይህ ሰው በደርግ ዘመነ መንግሥት የእግዚአብሔርን ስም እንዳይጠራ ሰዎች ክርስትና እንዳያስነሱ በየቀበሌውና በየሰፈሩ ቤት ለቤት እየዞረ እግዚአብሔር የለም በሚል እወጃው ብዙዎችን አስክዷል፡፡ ለዚሁ ሥራው ከፍተኛ ተባባሪው ከነበረው በዚያን ጊዜው ጓድ ጌታቸው ጓዴ በአሁኑ ሊቀ ኅሩያን ጌታቸው ጓዴ ጋር የእግዚአብሔርን ስም ካህናት እንዳይጠሩ በስመ አብ …ቀርቶ በስመ ሌኒን ወማርክስ እክህደከ ኢምፔሪያሊዝም በማለት…ካህናት መስቀላቸውን እየጣሉ ሽጉጥ እንዲጨብጡ ቤ/ክንን እየዘጉ ቤተመንግሥት እንዲገቡ የወንጌል አገልግሎን እየናቁ የፖቲካው ባራኪና ተንታኝ እንዲሆኑ የበኩሉን ጥረት በማድረግ በተሰለፈበት የውትድርና መስኩ የ50 ዓለቅነትን ማዕረግ ከደርግ ተቀብሏል፡፡ በማለት ይገልጠዋል ሊቀ ጠበብት ዘሪሁን ሙላት(ዶ/ር)
ከጥቂት ጊዜ ወዲህ በተለይ ደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያን ላይ ከፈጸመው ደባ በኋላ
- በብጹዕ አቡነ ማቴዎስ የኢኦተቤ የመገናኛ ብዙሃን የበላይ ኃላፊ ቀድሞ ቃል የተገባለት ይሁን አይሁን ባላውቅም አዲስ ገንዘብ መብያ መስክ ይሆንልኛል ብሎ የቋመጠበትንና መልሼ አገኘዋለሁ በሚመስል ሁኔታ የኢኦተቤ የመገናኛ ብዙሃን ሥራ አስኪያጅነት ለማግኘት ከደቡብ አፍሪካ በሰበሰበው ዳጎስ ያለ ገንዘብ እየረጨ እንዳለ ለማረጋገጥ ችያለሁ፡፡
- እጅግ በጣም ያስደነቀኝ ሌላው ጉዳይ ደግሞ መጽሐፍ ‹‹ዮሴፍን የማያውቅ ንጉሥ ተነሣ›› እንዲል…እሱና ሎሎች የቤተክርስቲያን አይጦች በማኅበረ ቅዱሳን የሐመር መጽሔትና ቴሌቪዥን የተከበረ እንግዳ እየሆኑ የመቅረባቸው ጉዳይ ነው፡፡ ቤተክርስቲያንና አገልጋዮቿ ላይ ላይ ድብደባ፣ ቃጠሎና ሰይጣናዊ ፈተና ከሚያደርሱባት አክራሪ እስላሞች በላይ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትንና ጠቅላይ ቤተክህነትን በሙስና በዘረኝነት እነዲጨማለቅ በር ከፋች የሆነውን በልቶ የማይጠግበውን ጅብ አስር አለቃ ፋንታሁን ሙጬን ስለ ቤተክርስቲያን ተናጋሪ ማድረግ ምዕመናን ላይ ማሾፍ ይመስለኛል፡፡ በዚያ ላይ እርም ያለባቸውን እነ ፋንታሁን ሙጬ፣ የአዲስ ዘመኑ ሽጉጥ ታጣቂ፣ጫት ቃሚና አፋር ላይ የመኪና አድርሶ በገንዘብ ኃይል እስር ቤት ከመማቀቅ የተረፈውን ‹‹አፈ መምህር›› ተብዬውን ስለ ቤተክርስቲያን ተናጋሪ አድርጎ ማቅረብ እርም ስለሆነ ለውጥ ያመጣል ብዬ አላስብም፡፡ ሙጬን የመጋበዙ ትልቁ ምክንያት የቆሸሸ ማንንቱን ለማጠብ የታቀደ እንጂ ስለ ቤተክርስያን ለመናገር ምንም ዓይነት ተነሳሽነት ብቃትና ቁመና ስላለው እንዳልሆነ ቀደምቱ የማቅ አባላት በደንብ ያውቃሉ፡፡ በዚህ ተከታታይ ክፍል እየቀረበ ባለው የማኅበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ መንግሥት ሊሰማን ይገባል! ሕዝቡ ሊነሳ ይገባል! እያሉ መንጫጫት ከንቱ ጩኸት ነው ባይ ነኝ፡፡ ምክንያቱም ከተናገሪዎቹ መካከል ጥቂቶቹ እጅግ የቆሸሸ ስብእና ያላቸው ተረፈ አካናውያን ናቸውና ነው፡፡ሰውን ልናታልል እንችላለን የቤተክርስቲያን ራስ ክርስቶስን ግን ማታለል አይቻልም፡፡ በኤር 40፡3‹‹…በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርታችኋልና ቃሉን አልሰማችሁምና ይህ ነገር ሆነባችሁ፡፡›› እንዲል በማስተዋል ሆነን ይሄ ሁሉ ፈተና በእኛ ኃጢአት፣ በደልና ክፋት እንዲሁም መለያየትና ዘረኝነት መጣብን! ብለን ንስሐ ከመግባት ጋር የተቀናጀ የመፍትሔ ሥራ መሥራት ይገባል እላለሁ፡፡






ማስታወሻ፡-ስለዚህ የመጽሔት፣የጋዜጣ፣የሬድዮና የቴሌቪዥን አዘጋጆች እባካችሁ! እባካችሁ! እባካችሁ!…የምትጋብዟቸው ሰዎች መለፍለፍ ስለሚችሉ ብቻ ነገር ግን ለቤተክርስቲን አንዳች የማይጨነቁ፤ ለመንጋውን ምንም ዓይነት ርኅራኄ የሌላቸውን የዘመናችን ፀሐፍት ፈሪሳውያን ከመጋበዛችን በፊት ከፍተኛ ጥንቃቄ ካላደረጋችሁ በርካታ እርም የሆነ ነገር አዝለው ስለሚዞሩ ከመፍትሔና ከማሸነፍ ይልቅ የበለጠ ውድቀትን ለቤተክርስቲያን የሚያመጣ በመሆኑ ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን ጉዳይ በሙስና፣በዘረኝነትና በክፋት የሰለጠኑትን ሳይሆን እውነተኛ የቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ሰዎች መጋበዝ እንዲገባ መረዳት አለብን፡፡በመጽሐፈ ኢያሱ የተጠቀሰው በእኛም እንዳይደርስብን ማለቴ ነው፡፡
ኢያ 7፡11-12 ‹‹…ሕዝቡ በደሉ ከእነሱ ጋር የተማማልኩት መሓላዬን አፍርሰው እርም ካሉት ገንዘብ ወሰዱ ሰርቀውም ከገንዘባቸው ጋር ጨመሩ፡፡ እንግዲህ ወዲህ የእስራኤል ልጆች በጠላቶቻቸው ፊት ቆመው መዋጋት አይችሉም፤የተረገሙ ሆነዋልና ጀርባቸውን መልሰው ይሸሻሉ አሁንም የተረገመውን ሰው ከእናንተ ለይታችሁ ካላወጣችሁ እንግዲህ ወዲህ ከእናንተ ጋር በረድኤት አልኖርም፡፡››
በርግጥ በማኅበሩ ቴሌቪዥን የተነሳው ርእሰ ጉዳይ አጅግ አስፈላጊ፣ ጊዜውን የጠበቀና በደንብ የተጠናና የተደራጀ መፍትሔ የሚፈልግ እንደሆነ እሙን ነው፡፡ ዛሬ ዛሬ እንዲያውም ቅድስት ቤተክርስቲያንን ከውጪው ፈተና ይልቅ ከውስጥ በሰው አሳማዎችና ጅቦች እየገጠማት ያለው ፈተና እጅግ የበረታ ነው፡፡ የውጪውንስ አውግዘን፣ ጽፈን፣ ሲብስ ደግሞ ተዋግተንም ቢሆን ድል እናደርጋለን የውስጡን ግን ለመዋጋት እልህ አስጨራሽ ነው፡፡ አሁን ለምሳሌ ፋንታሁን ሙጬ ብንወስደው ብዙ ተስፋ የቆረጠበት ነገር ስላለ ሰለምንም ነገር ተናገር ብትሉት በጣም ደፋር ስለሆነ የሐሰት ካባውን ግጥም አድሮጎ ለብሶ ማውራት ይችላል፡፡ እንዲህ ዓይነት ሰዎች ደግሞ አጥፍቶ ጠፊዎች ስለሆኑ ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን የትኛውንም መስዋዕትነት ሊከፍሉ የሚችሉ ክርስቲያኖችን ጥበብ በጎደለው መልኩ እንዲጓዙና ያልተገባ መስዋዕትነት እንዲከፍሉ ሰለሚያደርጉ እንጠንቀቅ የታናሽነት ምክሬ ነው!!!
ዳሰሳ ዘሐዲስ ሃሳማ አብርሃም ገረመው
ከእድገቱ ከ‹‹ሎኮ›› የገጠር መንደር ጀምሮ የሚያውቁት አንዳንድ ወንድሞች እንዲሁም ከየኔቢጤነት የማይተናነስ የአምስት ኪሎ ቅድስት ማርያም ደጅ ጠኚነት ሕይወቱን የሚያውቁት አባቶች ሁሉም በአንድ ቃል የነገሩኝ አዲሱ አሳማ አንዳንዶች ደግሞ ሲራመድ ሲገላበጥ ሲያዩት ዶልፊኑ እያሉ የሚጠሩት አብርሃም እንዴት ከትህትና ወደ አሳማነትና ወደ ጅብነት እንደተሸጋገረ እንደሚያደንቁ ነው የሚነግሩኝ፡፡ እኔም ቅድስት ሥላሴ ከመግባቱ በፊት ስለማውቀው ምንም እንኳን ደቡብ አፍሪካ ለመሄድ ሲል ራሱን የሆሳዕና ሰው ለማድረግ የሚያደርገው ጥረት እንዳለ ይቀመጥለትና እኔ የሱን ታሪክ የማውቀው ሎኮ ተወልዶ ቡታጅራ ማደጉን ነው፡፡
መስሎ አዳሪው አዲሱ አሳማ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ጸሐፊ እንደመሆኑ መጠን ከደመወዙ በተጨማሪ ምናልባት ለሁላችንም የሚገርመን ሐራ ዘተዋሕዶ ለአደባባይ ሊውሉ የማይገባቸውን ጭምር ዝርዝር የቅዱስ ሲኖዶስ መረጃዎች የጠዋትና የከሰዓት ውሎ እያለች እንድታቀርብ ያስቻላት አዲሱ አሳማ እየተከፈለው በዘመናዊ መሳሪያ ታግዞ በሚያቀብላቸው መረጃ እንደሆነ ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡ ከሁሉ በላይ ግን በጣም ያሳዘነኝና ያሳሰበኝ ትልቁ ጉዳይ የወደፊት ትዳሩ ጉዳይ ነው፡፡ ለምን በዚህ ዕድሜው አላገባም? ምን ቸግሮት ይሆን? እያልኩ ያሳስበኝ ነበር፡፡ለካ ነገሩ ወዲህ ነው ዝርዝር መረጃውን ወደ ፊት አስፈላጊ ሆኖ ከታመነበት የማስነብባችሁ ቢሆንም አብርሽ ለካ በወይዘሮነት ይታማ ኖሯል፡፡

ምን ዓይነት መጠጋጋት ነው??
ታዲያ አዲሱ አሳማ ለምን በደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያን ላይ ትኩረት አደረገ?
አዲሱ አሳማ ደቡብ አፍሪካ እንደደረሰ ከሊቀ ጳጳስ አቡነ ያዕቆብ የቀረበለት ጥያቄ ምነው በሕማማቱ መጣችሁ? የሚል ነበር በቦታው ላይ የነበረ የመረጃ ምንጬ እንደነገረኝ መልሱ‹‹ ብጹዕ አባታችን ሰው ስለሌሎት ነው! ሰው ቢኖሮት እኮ ይሄ ጉዳይ እንኳን ወደዚህ ሊያስመጣ ጭራሽ አጀንዳም መሆን አይችልም›› የሚል ነበር መልሱ፡፡ ያው ከዚህ መልስ የምንረዳው የማጣራቱ ሂደት ግብ ተኮርና ሳይጣራ ያለቀ ሪፖርት እንደተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ተጨማሪ ማረጋጋጫ የሚሆነው ደግሞ ሙጬ ጆሐንስበርጎችን ሲያወያይ ንግግሩን የጀመረው በኮራትና በጀብደኝነት ስሜት ውስጥ ሆኖ ‹‹ሐራ ላይ የወጣውን አላነበባችሁም እንዴ?›› በሚል መሆኑ ከላይ ያነሳሁትን ሀሳብ ያጠናክርልናል፡፡ አዲሱ አሳማ በጣም ጉደኛ ከመሆኑ የተነሳ በአሁኑ ወቅት በሴረኞች እየታመሰ ያለው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ከዚህ በፊት የቀን መደበኛ ደቀ መዛሙርት ባሳተሙት ‹‹ባለቤት ያልነበረው መንፈሳዊ አልባው ኮሌጅ›› በሚለው መጽሔት ላይ እንደተገለጠው ቋሚ ሲኖዶስ ታኅሳስ 24 ቀን 2011 ዓ.ም ያየውን ጉዳይ ጥር 08 ቀን 2011 ዓ.ም በድጋሚ እንዲያይ ምክንያት የሆነው አዲሱ አሳማ ብር ተቀብሎ ቃለ ጉባኤው ቀሽቦ በወቅቱ የቋሚ ሲኖዶስ አባላት የሆኑት ብጹአን አባቶች ያልወሰኑትን ያልተነጋገሩበትን ጉዳይ ቃለ ጉባኤው ላይ ያሰፍርና ያስፈርማቸዋል፡፡ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ በአዲሱ አሣማ የተፈጸመውን ነውረኛ የቃለ ጉባኤው ቅሸባ ስለደረሰቡት በ08/05/11 ዓ.ም ቀሻቢውን አሣማ ልክ ልኩን በመንገር እንደገና አስወስነዋል፡፡፡ በዚህ ዓይነት አዲሱ አሳማ ገንዘብ እየተቀበለ የስንት ሀገረ ስብከቶችና አብያተክርስቲያናት ቃለ ጉባኤ ቀሽቦ ይሆን?


ከላይ ወዳነሳሁት ጥየቄ ለመመለስ አዲሱ አሳማ ወደ ደቡብ አፍሪካ ይሄዳልተብሎ ወደ ደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ ስም ዝርዝራቸውና ፋይላቸው ከተላከላቸው ስድስት አገልጋዮች መካከል አንዱ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ በቅርበት ላነጋገሩት ሰዎች ሁሉ መልሱ ‹‹ሊቀ ጳጳስ አቡነ ያዕቆብ ሕይወቴን አበላሹብኝ እሠራላቸዋለሁ ነበር›› ይህ ቁጭቱንና እልሁን የሚያውቁት እነ አቡነ ሳዊሮስ ለእኩይ ሴራቸው ሁለተኛው ምቹ የዲያብሎስ ፈረስ እንደሚሆንላቸው በማመናቸው አጣሪ ቡድን ውስጥ አካተቱት፡፡

እሱም በእስትፋሰ ዲያብሎሱ ታደሰ ወርቁ የተጻፈውንና በእነ አቡነ ቴዎፍሎስ የተቀነበበውንና አዲስ አበባ በተመለሱ በሶስተኛው ቀን ገቢ ያደረጉትን ባለ 58 ገጽ ሪፖርት እውነት ነው! አይኔን ግምባር ያድርገው! ብሎ ፈረመ፡፡ ከእነ አባ እእምሮና ከእነ መቶ አለቃ ንብረት የሰበሰበውን ዳጎስ ያለ እጅ መንሻ ምናልባትም በወይዘሮነቱ የሰበሰባትን ብር አንድ ላይ አድርጎ መሰለኝ ከደቡብ አፍሪካ መልስ ጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ አኬልዳማ ቪትዙን ገዝቶ ሲለማመድ እንደነበረ በኋላም በሁኔታው አበደ እንዴ አዲሱ አሳማ? በማለት ተገርመው እረ ባክህ ቢያንስ ልምምዱን እንኳ ከዚህ ውጪ አድርግ ብለው ስለመከሩት መኪና ልምምዱን አጧጥፎታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለፈጸመው አኩሪ እኩይ ተግባር የተሸለመው ግዙፍ ቴሌቪዥንና አንዳንድ ኤሌክትሮኒክሶችን ለመሸጥ ከዚህ በፊት ደቡብ አፍሪካ ደርሰው የመጡ ሰባክያንን እንዲያሻሽጡት ላይ ታች ሲል መከረሙን አውቃለሁ፡፡
አብርሽን በተለይ የኋላ ማንነቱን ስለማውቅ በግሌ ስለሚያሳዝነኝ ከእነዚህ የተራቡ ጅቦች መንጋጋ ወጥቶ ከእሪያነቱ በንስሐ እንዲመለስ እመኝለታለሁ፡፡ የቅርብ ጓደኞች ነን የምትሉ ደግሞ ቢያንስ እኛንም ራሱንም ከሐሜት ማዳን እንዲችል ወደ ሕግ(ትዳር) እንዲገባ እንድታበረታቱት ልመናዬን አቀርባለሁ፡፡
5. ሐራ ዘተዋሕዶ በደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያንና በሊቀ ጳጳሱ ላይ ያደረገችው ዘመቻ
ከዚህ በፊት ባሉት ክፍሎች ስለ ሐራ ዘተዋሕዶ ጸሐፊዎችና ማንነት በመጠኑ ያስነበብኳችሁ ይመስለኛል፡፡ ካለነበባችሁት ግን ከዚህ ጽሑፍ በፊት የቀደሙትን ክፍሎች ማንበቡ ለግንዛቤ ይረዳል ባይ ነኝ፡፡ ሐራውያንን በደንብ ለመረዳት እንዲቻላችሁ በሐራውያን እጅግ የተብጠለጠሉትን ብጹዕ አቡነ ያዕቆብንና በእጅጉ የተሞካሹትን ብጹዕ አቡነ ዲዮስቆርዮስን በንጽጽር ማየት ምን ያህል በይሁዳዊ፣ በሲሞናዊና በተቀናጀና በተሰናሰለ መልኩ አስተዳደሯን ከማዳከም ጀምሮ መሠረተ እምነቷን እሰከ መበከል እንዴት እንደተሠማሩ ለመረዳት ይረዳልና እነሆ፡-
ብጹዕ አቡነ ዲዮስቆርዮስ በሐራውያን እይታ
ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር ስላላቸው ግንኙነት ሐራውያን ምን እያሉ ዘገቡ?
· ሰበር ዜና – ፓትርያርኩ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቡነ ዲዮስቆሮስን አገዱ March 20, 2019
አቡኑ ከሐራውያን ጋር እጅና ጓንት ሆነው የሚሠሩ በመሆናቸው እሳቸውን የሚመለከቱ ጉዳይ ኮሽ ባለቁጥር ዴጄውን ጠርተው ቅዱስነታቸውን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ አሰድበዋል ሰዎች የጥላቻ መንፈስ እንዲኖረው ጠንክረው በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ቅዱስነታቸው ደግሞ አሁን የእኔ ተራ ነው በሚል ይመስላል መያዣ መተንፈሻ እስኪያጡ ድረስ ብጹዕነታቸውን በማሳደድ ላይ ናቸው፡፡ በርግጥ የቤተክህነቱን የሦስት ዓመት የአደባባይ ሙገሳ፤የማጀት እና የጓዳ ሙስና የሚያውቁ የቤተክህነቱ ሠራተኞች ገና ይተፏታል በማለት ላይ ይገኛሉ፡፡ አሁን የሠሩትን ጉድ ሁሉም እየተረዳ ነው ባዮች ናቸው፡፡ ከሀገር ለመውጣት በዝግጅት ላይ እንዳለች የምትታማው የሂሳብና በጀት መመሪያ ኃላፊዋ ወ/ሮ ጽጌረዳ ዓለሙን ወደ ቤቶች አስተዳደር ያዛወሩት አልተሳካም እንጂ ጉዳቸውን ለመሸፈን እንደነበር የሚናገሩ በርካቶች ናቸው፡፡ በነገራችን ላይ ቅዱስ ፓትርያርኩ ፈሊጥ ያለውና ከቂመኝነት የጸዳ አካሄድ ተጠቅመው ለቤተክርስቲያን ወገንተኛ ሆነው የቂም ፈጻሚ ጀሌዎች ሳይሆን ባለሙያዎችን አጣሪ ውስጥ አካተው የማጣራቱን ሂደት ቢያከናውኑ ለጆሮ የሚዘገንኑ ብዙ ጉዶች ሊገኝበት እንደሚችል እሙን ነው፡፡ ከላይ ላነሳሁትን ርእሰ ጉዳይ ማሳያ የሚሆነው ከኃላፊነታቸው ከወረዱ በኋላ እንኳ
- ‹‹በሕገ ወጥ መንገድ በእኔ ላይ የተሰጠውን የማጣራት ትእዛዝ ስለመቃወም ይመለከታል››
በማለት የጻፉት ደብዳቤ ለዚሁ ማሳያ ነው፡፡


በእኔ እምነት ምንም ችግር የሌለበት የሥራ መሪ ሥራህ ይገምገም ቢባል ደስተኛ ሆኖ መቀበል ነበረበት፡፡ ለመልካም አፈጻጸማቸው ሽልማት መሸላማቸው በሳቸው መጀመሩን አዳንቀው እንደጻፉ የስራ ኃላፊ ከሠራ በኋላ መገምገሙን መቀበል የእውነተኝነታቸውና የሥራ ሰው መሆናቸውን ማሳያ በሆነላቸው ነበር፡፡ ዳሩ ምን ያለበት ምን አይችልም ይባል የለ! አንዳንዶች ምናልባት እዚህ ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ አጨብጭቦ ሸልሞ የሸኛቸውን ለምን ይጠየቃሉ? ይሄ ግን አያስኬድም ምክንያቱም ቅዱስ ሲኖዶስ የተነበበለትን ሰማ እንጂ ገለልተኛ አካል ያጣራውን ሪፖርት አልሰማ! በዚያ ላይ የውስጥ አዋቂ ምንጮቼ እንዳስርዱኝ የቅዱስነታቸው ይጣራ ማለት ያስኬዳል ለማለት የሚከተሉትን ነጥቦች ያቀርባሉ፡፡ ፍርዱን ለአንባብያን ትቼአለሁ፡፡
- አቡነ ማርቆስ ብጹዕ ሥራ አስኪያጁ ሪፖርት ሲያቀርቡ እንዲህ ሠርተናል ይሄን አስመልሰናል ሲሉ ‹‹የበላ ያስመልሰዋል›› ብለው ማፌዛቸው የሚያውቁት ነገር ስላለና የእሳቸውን ጨምሮ፣አዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና ሌሎች ሀገረ ስብከቶች ለተፈጠሩ ሁከትና ብጥብጥ ከአቡነ ሳዊሮስ ጋር ሆነው እጃቸው ስላለበት ስለተናደዱና የሚያውቁት ነገር ስላለ ነው የሚሉ አባቶች አጋጥመውኛል፡፡
- ከዚህም በተጨማሪ እነ ታዴና ዲጄው አሉላ የአቡኑ የብሎግ ክንፍ በመሆናቸው ከሀገር አቀፍ የሰላምና ስብከተ ወንጌል ስምሪት ብቻ አንኳ አስከ 170 ሺሕ ብር እንደተቋደሱ በወቅቱ የኤፍሬም ውስኪ ቤት የቅርብ ጊዜ ትኩስ ዜና እንደነበር አውቃለሁ፡፡
- ከላይ አቡነ ማርቆስ እንዳሉት ሁለቱ መንትያ ሕንጻዎች በእሳቸው ዘመን ማብቂያ በሌሎች አባቶች ጥረት ቢመለሱም በአንጻሩ ደግሞ በርካታ የሚሆኑ የኪራይ ቤቶች ወደ ግለሰቦች ይዞታ ማለት ለስሙ ለቤቱ ትንንሽ ብሮችን በኪራይ መልክ ይክፈሉ እንጂ እስካሁን ወደ ቤተክርስቲያኒቱ ካዝና ያልገባ ቁጥሩን መጥቀስ ያልወደድኩት በርካታ ሚሊዮን በሚደርስ ብር እንደተቸበቸቡ ከቤተክህነቶቹ የቤት ተጠቃሚዎች ሳይቀር ሰምቻለሁ፡፡ በቅርቡ የቀሲስ ሽመልስ ቢሮ መታሸጉም ለዚሁ ይመስለኛል፡፡
- የሒሳብና በጀት ኃላፊዋ ወ/ሮ ጽጌረዳ ዓለሙ በደብረዘይት እያስገነቡ ያሉት ባለ G+4 ሕንጻ እና ራሱን የአቡኑ የእንትን ደላላ መሆኑን በቀረጸው የአቡነ ድምጽ እዚያው ጉደኛ ኤፍሬም ውስኪ ቤት ሲያስረዳ የነበረው ዳዊት ታደሰ የፎቅ ባለቤት መሆኑ ስመለከት እውነትም የበላ ያስመልሰዋል የሚለውን የአቡነ ማርቆስ ሀሳብ እንድጋራ አድርጎኛል፡፡


- ከዚህም በተጨማሪ በማንም ይጻፍ በማን የእኔ ጉዳይ ባይሆንም በሊቀ ጳጳስ አቡነ ዲዮስቆሪዮስ ተጻፈ የተባለው ‹‹ፍኖተ ጽድቅ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ›› በኮታ የመሸጥ ግዴታ ላለባቸው የአዲስ አበባ አድባራትና የሳሚ ሮቶ ትንሣኤ ማተሚያ እንጂ ለመጽሐፍ ሻጮች ሳይሰራጭ የመቅረቱ ጉዳይ አስራ ምናምን ገጽ አከባቢ ከመናፍቃን መጽሐፍ የተገለበጠ መሆኑንና ‹‹መጽሐፉ የእኔ ነው›› ባይ በመምጣቱ መሆኑን ስሰማ አባቶቻችን ምን ነካቸው? ማለቴ አልቀረም፡፡በዚሁ ግን በሁለተኛ ዕትሙ ላይ ታርሞ እንደሚወጣ አምናለሁ፡፡ለመናዬንም ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የማጣራት ሂደቱን አጠናክረው ቢቀጥሉ ሌቦችና ወንበዴዎችን ከቤተክርስቲያናችን ለማጽዳት ይረዳል ባይ ነኝ፡፡
ብጹዕ አቡነ ያዕቆብ በሐራውያን እይታ
ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር ያላቸው ግንኙነት ሐራውያን ምን እያሉ ዘገቡ?
ሁሉንም አክባሪ በመሆናቸው አንድ ቀን እንኳ ከፓትርያርኩ ጋር እንኳን የደብዳቤ ምልልስ፣ እንኳን በአደባባይ መስደብ ማሰደብ ቀርቶ ክፉ ደግ እንኳ ተነጋግረው ስለማያውቁ ምንም የጻፉት ነገር የለም፡፡
ብጹዕ አቡነ ዲዮስቆሪዮስ
በሚያስተዳድሩት ሀገረ ስብከት ምን ክስ ቀረበባቸው? ለምንስ ተዳፍኖ ቀረ? አቡነ ዲዮስቆርዮስ ከሀገረ ስበከታቸው አስተዳደር ጉባኤ ጭምር ክስ እያለባቸው በመሠረቱት ቲም ዲዮስቆርዮስ ምክንያት ጉዳዩ ተዳፍኖ እንዲቀርና በብልጠት ‹‹ለነፍሴ አስጋለሁ፣ ወደ ሀገረ ስብከቴ መሄድ አልችልም›› ብለው በስርዋጽ አጀንዳ በማስገባት የቅርሳ ቅርስና የቤተ መዘክር መምሪያ የበላይ ጠባቂ ለመሆን ጥረት ቢያደርጉም ስለ እውነት የሚተጋውና የሚለፋው ወዳጄ ዘመድኩን በቀለ ግን እውነታውን እንደሚከተለው አፍረጥርጦታል፡፡






ብጹዕ አቡነ ያዕቆብ
በሚያስተዳድሩት ሀገረ ስብከት ምን ክስ ቀረበባቸው? ለምንስ ተጋነነ?
በአንጻሩ አቡነ ያዕቆብ ሰው(ቲም) ስለሌላቸው ብቻ ከሚያስተዳድሩት አብያተክርስቲያናትና ሰበካ ጉባኤ አንድም ክስ ሳይቀርብባቸው ከማያስተዳድሯቸው ከእነ አባ አእምሮ ለእነ ዲጄው አሉላና ለተራቡና ለማይጠግቡ ጅቦች ለእነ ሙጬ የሀገረ ስብከቱን የገንዘብ ፍሰት በባንክ ሲስተም እንዲተሳሰር ስላደረጉት ለመብላት አመቺ ስላልሆነ ብቻ በሐራዊው እስትንፋሰ ዲያብሎሱ ታደሰ ወርቁ በተዘጋጀ የስድብ ሪፖርት እሳቸውን አስነስቶ በልተው የሚያስበሉ የቲም ዲዮስቆርዮስ ምክትል ኃላፊ የሆኑትን አቡነ ሳዊሮስን ለማስመደብ ሲባል ለሊቀጳጳሱ የሌለ ስም መስጠት እንደ ቤ/ክን ያለንበትን የዝቅጠት ደረጃ የሚያሳይ ነው፡፡ የደቡብ አፍሪካ ካህናትና ወንድሜ ዘመድኩን ስለ አቡነ ያዕቆብ ክስ ያሉትን እስቲ እናንብበው፡፡














ከዚሁ ጋር በተያያዘ
ቋሚ ሲኖዶስ: በተሐድሶ ኑፋቄ የተጠረጠሩትን አቡነ ያዕቆብን ከአትላንታ አብያተ ክርስቲያን አገደ! “ከሲኖዶሳዊ አንድነት ወደ ሲኖዶሳዊ ማጥራት?!” ተብሎ ቢወጣም
‹‹የአትላንታ ሰዓሊተ ምሕረት እና የፊላደልፊያ ቅ/ዐማኑኤል ውዝግብ በዕርቅ እንዲፈታ ቅ/ሲኖዶስ ወሰነ›› ተብሎ ውሳኔ መሰጠቱ ስንመለከት የአትላንታው አቡነ ያዕቆብ ተከራካሪ እነ አቡነ ቴዎፍሎስ ስላሉላቸው እንደሆነ ለመረዳት ብዙም አያዳግትም፡፡
አቡነ ያዕቆብ የደቡብ አፍሪካውስ ምን ተወሰነባቸው?ቅዱስ ሲኖዶስ: ብፁዕ አባ ያዕቆብን ከደቡብ አፍሪቃ ሀገረ ስብከት አገደ! “ገንዘቡንም እንዳያንቀሳቅሱ ካልታገዱ አደጋ ላይ ነን”/ምእመናን/ June 1, 2019 ተብሎ ውሳኔ መሰጠቱን ስንመለከት እውነትም ሰው የላቸውም ያስብላል፡፡
እዚህ ላይ ውድ የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች ለመሆኑ የአስተዳደር ጉዳይ ይበልጣል ወይስ የሃይማኖት ጉዳይ? መልሱን ለአንባቢያን ትቼአለሁ!
በዚህ በእኛ ዘመን የቤተክርስቲያናችንን ፈርጀ ብዙ ችግር መዘርዘር ከባድ ቢሆን የጥፋት ኃይሎች ሐራውያን እስካሁን የጻፉትን እናንተው ወደ ኋላ እየሄዳችሁ ሐራ ስለ እነማን ምንጻፈች? በስንት ብር ጻፈች? ብላችሁ ፈትሹ፡፡ እዚህ ላይ ግንዛቤ እንዲወሰድ የምፈልገው ጉዳይ በዚህ በእኛ ዘመን አንድ አባት የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና መንፈሳዊ አባት ለመባል እንደ ቲም ዲዮስቆርዮስ ባሉ የጳጳሳት ቡድን መሳተፍ ወይም ድጋፍ ማግኘት ወይም ተገዢ መሆንና ለሐራውያን መገበር ሲችል ብቻ መሆኑን ነው፡፡ ላነሳሁት ርእሰ ጉዳይ ግን ይህ ሁሉ ጥፋት እያለ
ለቤተ ክርስቲያን እመርታ የተመዘገበበት የብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የ3 ዓመታት ሪፖርት ለቅ/ሲኖዶስ ቀረበ፤ “በፈተናና ተግዳሮት መካከል የተሠሩ ናቸው!” May 23, 2019 ተብሎ መዘገቡም ለዚሁ ይመስለኛል፡፡
ሊቀ ጳጳስ አቡነ ያዕቆብ ቲም ዲዮስቆሪዎስ ውስጥ እንዲገቡ በተደጋጋሚ የተወተወቱና ካልገቡ ግን ቅሸባ እንደሚደርስባቸው በቁም ነገርም በጨዋታ መልክም ሲነገራቸው መኖሩን መገመት ይቻላል፡፡ ሐራ ዘተዋሕዶ ትሰድብሃለች ታዋርድሃለች ከዚያ በቀጥታ በቀኝ ትገዛሃለች፡፡ ቲም ዲዮስቆሪዎሶች ጋር ጠጋ ብለህ ካዳመጥክ በድፍረት የሚያወሩት ማቆችን እኛን ይጠብቁናል እና ደግሞ ማቅን እንጠብቃለን በማለት ነው፡፡ ማቆች ተብለው የተጠቀሱት ግን ከዚህ በፊት እንደገለጥኩት በተግባር ማቅ ጠሎች ናቸው፡፡
ሐራውያን በብጹዕ አቡነ ያዕቆብ ላይ እ.ኤ.አ በAugust 31, 2013፣August 27, 2013፣ August 25, 2013፣ April 22, 2019፣June 1, 2019 የተለያዩ ጽሑፎችን ያወጡ ሲሆን ሌሎችን ብጹኡን አባቶችንና የቤተክርስቲያየን አገልጋዮችን በመስደብና ከክብር በማሳነስ ተገዢ እንዳደረጉ ሁሉ ብጹዕነታቸውን መያዝ(መጨበጥ) ስላዳገታቸው ይመስለኛል፡፡ እንደ ሐራውያን አገላለጥ በእሳቸው ሀገረ ስብከት ስለተሠራው ምንም መልካም ነገር መናገር አለመቻላቸውን ነው የሚጠቅሱት፡፡ ከላይ በተጠቀሱት ሐራ ዘተዋሕዶ በተለጠፉ አምስት ጽሑፎች ትርኪሚርኪዎቹንና በሬ ወለደዎችን ትቼ የተወሰኑት ያነሷቸው ዋና ዋና ሀሳቦች፡-
- 6 አስተዳዳሪዎችንና ሓላፊዎችን፣ “አልፈልጋቸውም” በሚል የኤምባሲ ኔትወርካቸውን ተጠቅመው ተልእኳቸውን አስተጓጉለዋል
- ከዐሥር ዓመት በፊት 40ሺሕ ደርሶ የነበረው የተወላጅ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን ቁጥር ወደ 4ሺሕ ተመናምኗል፤ ጥቁር ደቡብ አፍሪቃውያኑ፣ ወደ ቤተ ክርስቲያን ከመምጣት ይልቅ ቤታቸው መቀምጥን መርጠዋል፤ ትተዋት ወደመጡት አንግሊካን የኮበለሉም አሉ
- ሊቀ ጳጳሱ በጎሠኝነትም ምእመናንን ይከፋፍላሉ፤ እርስ በርስ እንዲደባደቡና ከቤተ ክርስቲያን አንድነት እንዲለዩ አድርገዋል፤ ዕርቀ ሰላም እንዲወርድም ፈቃደኛ አይደሉም፤
- ገባሬ ሠናይ ተቋም ኾና በደቡብ አፍሪቃ መንግሥት የተመዘገበችው ቤተ ክርስቲያናችን፣ ላለፉት 8 ዓመታት ለፈቃድ ሰጪው አካል/ለደቡብ አፍሪቃ ሶሻል ዴቨሎፕመንት ጽ/ቤት/ የሒሳብ ሪፖርት አላቀረበችም
- “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ለደቡብ አፍሪቃውያን፥ የነፃነት አርኣያ፣ የማንነት መለዮ እና የድኅነት ተስፋ ነበረች፤ በነጋዴው ብፁዕ አባ ያዕቆብ የጋንጎችና አፋኞች አመራር ግን የማያባራ ትርምስና የምእመናን ልቅሶ ማዕከል ኾና ትገኛለች፤”ብለዋል – ጥቁር ደቡብ አፍሪቃውያኑ
- በመላው አፍሪካ የአብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ የምክትል ፕሬዝዳንትነታቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዳልተወጡ ቢጠቅሱም
እኔ ግን ለዚህ ጽሑፍ መረጃ መሆን እንዲችሉኝ ያሰባሰብኳቸው መረጃዎች የሚመሰክሩት ሌላ ሀቅ ነው፡-
- በግንቦት 2011 ዓ.ም የውጪ አብያተ ክርስቲያናትን አስመልክቶ በቅዱስ ፓትርያርኩ መግለጫ ቁጥር 7 ላይ ‹‹በውጭ አገር የሚገኙ ሀገረ ስብከቶች…ከቃለ ዓዋዲው ጋርና ከየአገሮቹ መንግሥታት ሕግ ጋር የተጣጣመ ሕገ ደንብ እንዲዘጋጅና ለጥቅምት 2012 ዓ.ም እንዲቀርብ…›› ይላል፡፡ የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ግን 1999 ዓ.ም ጀምሮ ይህን አጸድቆ እየሠራበት ስለሚገኝ እንደተሞክሮ ሊወሰድ ይገባል ባይ ነኝ፡፡ከዚሁ ጋር በማያያዝ ማንሳት የምፈልገው ጉዳይ በሁለቱ ሲኖዶሶች መካከል ትክለኛ ዕርቅ ተፈጸመ ሊባል የሚችለው የአገልግሎት ብቻ ሳይሆን የንብረትም አንድነት ሲኖር በመሆኑ ዕርቁ ፍጹም ሊሆን የሚችለው በግል ይዞታ ያሉ በየትኛውም አህጉረ ስብከት ያሉ አብያተ ክርስቲያናት አንድ ሲሆኑ ነውና ቅዱስ ሲኖዶስ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ባይ ነኝ፡፡
- በብፁዕ አቡነ ያዕቆብ ሥር ከሚገኙት አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንድም ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስም እንጂ ልክ እንደ አሜሪካው በአቡነ፣በአባ፣በቄስ እገሌ ስም ግብር ከፋይ ሆኖ የተመዘገበ አለመኖሩና ሁሉም በግበረ ሠናይ ተቋምነት የተመዘገቡ መሆናቸው እጅግ የሚያኮራ ነው፡፡በዚያ ላይ የደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያን ፈቃድ ታክስ ባለመክፈላቸው ሊሰረዝ ነው የሚለው ውዥንብር ለማጣራት የቅርብ መረጃ ከሊቀጳጳሱ ወይም ከቅርብ ወዳጆቻቸው ማግኘት ባልችልም የደቡብ አፍሪካው ሁነኛ ምንጬ እጁ ላይ ያገኘውንና የላከልኝን እ.ኤ.አ በ2017 የተሰጣቸውን ማረጋገጫ ማየቱ በቂ ይመስለኛል፡፡


3. በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ብዙ የተለፋበትና ዋጋ የተከፈለበት የሂሳብ አሠራር መክኖ ሲቀር በደቡብ አፍሪካ ግን ውጤታማ የሂሳብ ቁጥጥር መኖሩ እጅግ አስደሳች ነው፡፡ ይኸውም ገንዘብ ሲወጣና ሲገባ ቼክ ፈራሚዎችና ሊቀ ጳጳሱ ጋር በሚደርሱ የጽሑፍና የማረጋገጫ ስልኮች እንዲሰራ መደረጉ ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡
4. በጆበርግ ቅድስት ሥላሴ ጸረ ማርያሞች እንደ ፈለጋቸው ሲዘሉ በሀገር ቤት እንኳ ያልተቻለውን በእሳቸው ሥር ባሉ አብያተ ክርስቲያናት እንዲህ አይነት ነገር አለመታየቱ እጅግ የሚያስደንቅ ነው፡፡
5. 6ቱ አስተዳደሪዎች ጉዳይ ላይ ብዙ ልፋት እንደተለፋባቸው ይሄን 15 ገጽ ጨምሮ ሌሎች ደብዳቤዎች ማየቱ ብዙ ነገር አስረጂ ነው፡፡




6. ድብድብ፣ መለያየትና ክፉ ነገር አቡነ ያዕቆብ ደቡብ አፍሪካ በነበሩበት ጊዜ እንዳልነበረ እነዚህን የሐራ ተዋሕዶና የአዲስ አድማስ መረጃዎች መመልከቱ በቂ ነው፡፡


7. በአፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ የተጻፈላቸው የአድናቆት ደብዳቤ ከላይ በሐራውያን የተነሳውን ፍሬ አልባ ክስ ውድቅ የሚያደርግ ነው፡፡



8. ከገንዘብ እና ከጥቅመኝነት ጋር በተያያዘ ማንም ደፍሮ ስማቸውን የሚያነሳ በተለይ የሀገረ ስብከታቸው ሰው አላገኘሁም፡፡ ደግሞ ሰበሰቡት የተባለው ገንዘብ ኢትዮጵያ ወይም ደቡብ አፍሪካ ባንኮች ውስጥ መገኘት ነበረበት ወይም ደግሞ የገነቡት G+ ምናምን ፎቅ ወይም ዘመናዊ መኪናቸው መታየት ነበረበት የሚለውን ሀሳብ የሚጋሩ በርካቶች ናቸው፡፡ እሳቸው ከሕዝቡ ጋር ተቆራፍደው ያላቸውን እያካፈሉ እንደሚኖሩ ሩቅ ሳንሄድ የቤተክህነቱን ጥበቆች ጠይቅ ያሉኝም ነበሩ፡፡ የደቡብ አፍሪካው የመረጃ ምንጬ እንደሌሎቹ አባቶች የንስሐ ልጆቼ ሰጡኝ ብለው እንደነ አባ ሰብስቤ ብዙ መሰብሰብ የሚችሉ ቢሆኑም የሁል ጊዜ ንግግራቸው ‹‹እኔ ላይ ስባሪ ሳንቲም ሂሳብ ያለው ካለ ባደባባይ ይናገር!…›› ብለው በልበ ምሉነት እንዲሚናገሩ አጫውቶኛል፡፡ይህን ጽሑፍ በምጽፍበት ወቅት እንኳ በተለያዩ ሰዎች በኩል አሁን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ያዕቆብ ያሉበትን ሁኔታ ለማጣራት ብሞክርም በራቸውን ዘግተው ጸሎት ከማድረግ ቅዱሳት መጻሕፍትን ከማንበብና ባላቸው ትልቅ የስዕል ተሰጥኦ ቅዱሳት ስዕላትን በመሳል ጊዜአቸውን ከመሳለፍ ውጪ እሳቸውን ለማግኘት አዳጋች መሆኑን ነግረውኛል፡፡ አንድ ወዳጄ ከሳሏቸው በርካታ ስዕላት መካከል በስንት ልመና የሰጠኝ ስዕል እነሆ ብያለሁ፡፡

ይህን ስዕል ያጋራኝ ወዳጄ ርግቦቹ በኢሳ 9፡6 ላይ እንደሰፈረው ‹‹የሰላም አለቃ›› መሆኑን እናቱ ድንግል ማርያም ደግሞ አማናዊት ርግብ የሰላም እናት መሆኗን ለመግለጥ መሆኑን አስረድቶኛል፡፡ይበል! ብያለሁ
ስለ ሐራውያን ካነሳሁ እስትንፋሰ ዲያብሎሱ ታደሰ ወርቁ 58 ገጽ የጥፋት ሪፖርት በደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያን ላይ ለመጻፍ ምን አነሳሳው?
ሐራዊው ታዴ የነገር አባቱ ቤተመንግሥት ባልታወቀ ማዕረግና ሹመት ስለገባበት እንደ በፊቱ ገቢው ሊሆን አልቻለም፡፡ በዚህ ምክንያት በኢትዮጵያ ተቀዛቀዘውን ጸረ-ተሐድሶ የስላይድ ንግድ ወደ ውጪ መውሰድ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ሆነበትና በ‹‹ዲ/ን›› ንዋይ ይጋበዝና ደቡብ አፍሪካ ይሄዳል፡፡ ታዲያ ታዴ እንደለመደው ስላይዱን ሊቸበችብ ሲል ሊቀ ጳጳስ አቡነ ያዕቆብ ጋር ይደወልና ታደሰ ወርቁ የሚባል ሰው ያውቁታል ስለ ተሐድሶ ገለጻ ሊሰጥ ይፈልጋል ብለው ያማክራሉ፡፡ ሊቀ ጳጳሱም ታደሰንም አላውቅም እንዲህ ዓይነት መርሐ ግብርም በዕቅድና በፕሮግራም እንጂ ዘው ተብሎ የሚገባበት አይደለም፤ ወደፊት ተነጋግረን መርሐ ግብር ተይዞለት ሊመጣ ይችላል ብለው መልስ ይሰጣሉ፡፡ ታዴ ታዲያ ጨሰ፣ ተናደደ በቃ በእልህ ሊቀ ጳጳሱ ታደሰ የሚያክል ሰው በመከልከላቸው እጅግ ተበሳጨ፡፡ ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ይመሰስለኛል ሊቀ ጳጳሱን ለማጥቃት ውጥን የያዘው፡፡ ታዴ ትልቁ ሕልሙ የነበረው ደቡብ አፍሪካ ነጻ የትምህርት ዕድል ፍለጋ ነበር፡፡በኋላ ላይ ከዚህ በፊት ሲሰድበው ሲያንቋሽሸው ከነበረው ከእነ አባ አእምሮ ጋር የጠላቴ ጠላት ወዳጄ በመሚስል ፈሊጥ አንድም ዶላር 58 ገጽ አይደለም መጻሐፍም ያጽፋልና አንድ ላይ ገጥሞ የትግል መስመሩን ተቀላቀለ፡፡ብሮች ተስብሰበው ለዲጄው ለአሉላ ይስጡ እንጂ ዋናው ተጠቃሚና አከፋፋይ እስትንፋሰ ዲያብሎሱ ታዴ ነው ብለውኛል ደቡብ አፍሪካውያን ምንጮቼ፡፡
6. ማጠቃለያ
ጽሑፌን ከማጠቃለሌ በፊት የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ላመላክት
ለምዕመናን
- መቼም በእኛ ቤተክርስቲያን ምዕመኑና ካህናቱ(አገልጋዮቹ) ያልተገናኙባት ስለሆነች ያለ ሊቀጳጳስ ከዚህ በፊት ለሁለት ዓመታት አሁን ደግሞ ከ4 ወር በላይ እድትኖሩ ሴራ የሰሩትን አባቶችና ወንድሞች እውነትን ብቻ በመያዝ ከቂመነኝነት በጸዳ ሁኔታ እንድትፋለሙ ያስፈልጋል፡፡
- በድጋሚ የተመደቡት አጣሪዎቹ ሲደርሱ ከዚህ በፊት የተላኩት አጣሪዎች ምን ዓይነት ደባ እንደፈጸሙባችሁ በግልጽ መግለጥ ይገባችኋል፡፡
- አጣሪ ልዑካን ከዚህ በፊት እንደመጡት የአንድ ወገን ሪፖርት አድማጭና ፍረደ ገምድል እንዳይሆኑ እያንዳንዱ እንቅስቃሴያቸውን በመከታተል ምዕመኑን ከእረኛቸው የሚለዩ የዲያብሎስ መሣሪያዎች እነ ንዋይንና አንዳንድ ነጋዴ ቄሶችን እንቅስቃሴ በመከታተል ስለ እውነት መመስከር ካልቻሉ ከቤተክርስቲያኒቱ ገለል ብለው ወደ ንግዳቸው እንዲገቡ ማድረግ ይገባል፡፡
- ከሳሾቹ እነማን እንደሆኑና ምን ፈልገው እንደ ከሰሱ በግልጽ ሁሉም በተሰበሰበበት እንዲነገር(እንዲነበብ) ማድረግ ይገባል፡፡
ማስታወሻ!
በነገራችን ላይ ብጹዕ አቡነ ያዕቆብ በግፍ ለምን ይነሳሉ የሚለው ጉዳይ እንጂ የሚያነጋግረን ከዚህ በፊት በተለይ የደቡብ አፍሪካና የኬንያ ምዕመናን እንደምታስታውሱት በግፍ አቡነ ያዕቆብን ከደቡብ አፍሪካ የማሳደድ ሥራ ሲሰራ እሳቸውን የጎዱ መስሏቸው ወደ ኬንያ ቢልኳቸውም ብጹዕነታቸው ግን ለ30 ዓመታት የረባ መንበረ ጵጵስና ያልነበረውንና ብጹአን አባቶች ከዲያቆናት ጋር ተራ ጠብቀው የሚጠቀሙበትን የመጻዳጃ ቤት በማስቀረት ደረጃውን የጠበቀ ሁሉን ያሟላ እጅግ ውብ መንበረ ጵጵስና ካሰሩ በኋላ ባበረከቱት የልማት አስተዋጽኦ ከአንድ ምዕመን መኪና ተሸልመዋል፡፡ በኋላም ይህንኑ መኪና ለኬንያ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በስጦታ እንዳበረከቱ ነው የሰማሁት፡፡ እዚህ ላይ ከሁሉ የደነቀኝ የተከሰሱበት ክስ የሐሰት መሆኑ በቅዱስ ሲኖዶስ ተረጋግጦ ከኬንያ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲመለሱ በስማቸው የነበረውን ይሄንኑ መኪናውን ሸጠው አዲስ አበባ ላይ በርካታ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ ያለ ሥራ የቆሙ መኪናዎች ባሉበት በኮንትራት ላዳ ከመጠቀም ለራሳቸው መኪና ለመግዛት አለመምረጣቸው ነው፡፡ዛሬ ቤቱንም ይሁን መኪናውን አሳዳጃቸው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሳዊሮስ እየተንፈላሰሱበት ነው፡፡



ከዚህም በተጨማሪ በወቅቱ የሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ያዕቆብን ኬንያ መድረስ ተከትሎ በርካታ ስደተኞች የኤምባሲ ጉዳያቸው ተሳስሮባቸው የነበሩ እንደተፈታላቸው፣ ከደዌ ሥጋ ከደዌ ነፍስ የተያዙ መፍትሔ እንዳገኙ መስክሮች ናቸው፡፡በመላው አፍሪካ አብያተክርስቲያናት ኅብረት በምክትል ፕሬዝዳንትነት ተመርጠው ያበረከቱትን አስተዋጽኦ ስንጨምርበት ደግሞ በተግባር የልማትና የአስተዳደር አባት መሆናቸውን ማረጋገጫ ነው፡፡
በተመሳሳይ ወቅት በደቡብ አፍሪካ ደግሞ በመጤ ጠሎች (Xenophobia) ምክንያት በርካታ ኢትዮጵያውያን በግፍ ሞቱ ሌሎች በቁማቸው ተቃጠሉ፣ቤ/ክን ውስጥ የተደረገው ድብድብ ለዓለም በደቡብ አፍሪካ ቴሌቭዥን ተላለፈ፡፡ ግጥምጥሞሽ ይሁን በበደል ምክንያት አሁንም በጁሐንስበርግ እና ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በሌሎች የደቡብ አፍሪካ ከተሞች በኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ላይ ከ08/08/2019 እየደረሰ ጀምሮ ቅጥ አምባሩ የጠፋ መከራ በርካቶች ታስረዋል፣የቤት ኪራይ መከፈል እስከሚያቅትና ነገ ምን እንሆን ይሆን? በሚል ስጋት ላይ መሆናቸውን ስሰማ….እኔም በአእምሮዬ ምናልባት እውነተኛና ስለ ሕዝቡና ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን ለመጸለይ የማይታክቱ የቤተክርስቲያን አባት ገፍተው፣ አሳደው ፣የሐሰት ምስክር ሆነው… ይሆን እንዴ? እያለ በጥያቄ መሞገቱ አልቀረም፡፡ ይህንንም ሀሳቤን የበለጠ ያጠናከረልኝ ቴዲ ዘጎላ የተባለ ኦርቶዶክሳዊ ወጣት በዩቲዩብ ቻናሉ ላይ የለቀቀው መረጃ ነው፡፡

ሆድ አደሮች፣ሴረኞችና ተረፈ ይሁዳውያን የፈጸሙትን ግፍ የሚያሳይ ስለሆነ በደንብ ያድምጡት!!!
ዙሮ ዙሮ ነገሮችን በአስተውሎት በማየት ውሳኔዎቻችሁን በጥንቃቄ መመርመር ይህ ለምን ሆነብን ብሎ ራስን መፈተሽ አስፈላጊ ነው፡፡….ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ!
ለአጣሪዎቹ
እንግዲህ የአጣሪዎቹ ጉዳይ በተመለከተ አሁን አሁን ከፓትርያርኩ አከባቢ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ወደ ጎን በመተው ጊዜው ሲደርስ የምናየው ቢሆንም ቅዱስነታቸው ሌሎች አባቶችን ለመመደብ እንቅስቃሴ ላይ እንዳሉ ሰምቻለሁ፡፡ በርግጥ እውነቱና የተሰራውን ደባ ለተረዱት የደቡብ አፍሪካ ምዕመናን ማንም ይመደብ ማን ችግር አለው ብዬ አላስብም፡፡የሆነ ሆነ ከፍ ብዬ ብጹአን አባቶችን መምከር ባልችልም እንደቤተክርስቲያን ልጅነቴ ግን በሁለተኛው ዙር አጣሪ ሆነው ለሚሄዱት አጣሪዎች ጥቂት ልል እወዳለሁ፡-
- ክስን ፈረሙ የተባሉ ሰዎች በሕይወት ስለመኖራቸው፣ክርስቲያን ስለመሆናቸውና ትክክለኛነታቸውን ማረጋገጥ ቢቻል፤
- የሥላሴን ቤ/ክን ጨምሮ የደቡብ አፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት በማን ስም እንደተመዘገቡ፤ሀብትና ንብረት በእነማን ስም እንዳለ ማጣራት ቢቻል ፤
- እነ ጅቦ በአቡነ ያዕቆብ ግብዣ ተልኮአቸውን፣ ውሎ አዳራቸውን ከሳሾች ጋር እንዳደረጉት ተመሳሳይ ችግር እንዳይፈጠር ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ
የማያዳግም ሥራ ቢሰሩ ምኞቴ ነው፡፡ አጣሪዎቹ ካልተቀየሩ ሁሉንም በሚገባ አዳምጠው አንጀት አርስ መልስ ለሚገባው እንደሚገባው አድርገው መመለስ በአግባቡ የሚያውቁበት የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ እና ከሐምሌ 14 ጀምሮ ስለቀጣይ የአሠራር ሂደት ከልብ ወዳጃቸው ከአቡነ ቴዎፍሎስ መመሪያ ለመቀበል ወደ አሜሪካ ተጉዘው የነበሩት የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ፣ከዚህ በፊት አጣሪ ሆነው ሄደው ተልካሽ ሪፖርት ያቀረቡት የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ባልደረባው፣ ቀሲስ በላይ ጸጋዬን ስለ እውነት እንዲተጉ ሳልማጸን ባልፍ የቤተክርስቲያን አምላክ ይፈርደብኛል ብዬ አምናለሁ፡፡
አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር 2012 ዓ.ም ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ከዘረኞች፣ከሴረኞችና ከሰው ጅቦች የጸዳች ያድርግልን!!!
በሌላ ርእሰ ጉዳይ እስከምንገናኝ ቸር ሰንብቱልኝ!
ሳምኬት ነኝ!
ተጻፈ ነሐሴ 25 ቀን 2011 ዓ.ም
















































