በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በየቀኑ እየተፈለፈሉ ያሉ ሉተራዊና ምዕራባዊ አካሄድን የሚከተሉ ማኅበራት የት ያደርሱን ይሆን?

አስቀድመን በፌስ ቡክ ገጻችን ላይ አንድ ጥያቄ ጠይቀን ነበር፡፡ ይኸውም የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ወደ ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ለምን ተቀየረ? የሚል ጥያቄ ጠይቀን በጣም የሚገርማችሁ ማን መልስ ቢሰጥ ጥሩ ነው? ሞዐ ተዋሕዶ ነበር!!!ለቡ!!!

ለማንኛውም ከላይ ወደ አነሳሁት ርዕስ ልመለስ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚፈጠሩ ችግሮችን እንደ መልካምና ምቹ አጋጣሚ የሚጠቀሙ አሊያም ከችግሩ ፈጣሪዎች ጋር ቀድመው የተወያዩ በሚመስል መልኩ ችግር በተፈጠረ ማግስት የሚፈጠሩ ማኅበራትና ግበረ ኃይሎች ወይም ኅብረቶች(በነገራን ላይ #ኅብረት ዓይነተኛዋ የማጭበርበሪያ የዳቦ ስም ናት) በአብዛኛው ኢ-መዋቅራዊ ከመሆናቸው ባሻገር ከአብዛኛዎቹ ጀርባ ያሉት ግለሰቦች ተመሳሳይ መሆናቸው ከላይ ያነሳሁን ጥያቄ እንደጠይቅ አስገድዶኛል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ “ሕጋዊ በሆነ መንገድ የቤተ ክርስቲያንን መብት ለማስከበር ይሠራል፡፡” ብሎ ቃል እየገባ

እንዴት ልደግፍ? የእኔ ድርሻ ምንድነው? ምንተ ንግበር? ብሎ ከመጠየቅ ይልቅ ኃያላችንን ለማዳከም፣ የትኩረት አቅጣጫችን የተበታተነና ልክ እንደ ሉተራውያን በተለያየ ስም (መካነ ኢየሱስ፣ሙሉ ወንጌል፣ ቃለ ሕይወት፣ ጌጃ…) አንድ ሆነው ሲያበቁ ራሳቸውን በተለያየ ስያሜ እየሰየሙ የዋሕኑና ደጉን ምዕመን ማሰናከል ምን ይሉታል? እስካሁን ከዚህ በታች ከዘረዘርናቸው ማኅበራት፣ ኅብረት፣ ግብረ ኃይል ሂደት ሁላችንም መረዳት እንደምንችለው የስበት ማዕከላቸውና መዳረሻቸው  ገንዘብ መሰብሰብና የግል ተከታይ(ቲፎዞ) ማፍራት ነው፡፡ ያለ ቅዱስ ሲኖስ ዕውቅናና ፈቃድ ማኅበራት፣ ኅብረት፣ ግብረ ኃይል እያሉ ማቋቋም ለቤተ ክርስቲያነቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳያል፡፡ እንዲሁም እኔ አውቅላችኋለሁ በሚል የትዕቢት ስሜት አንዱን አባት ተቆርቋሪ፤ ሌላው ለዘብተኛ፤ የተቀረውን ደግሞ ደንታ ቢስ ለማስመሰል የሚሠራውን እያንዳንዱን ሸፍጥ ታሪክ የመዘገበው ስለሆነ ዋጋ ሳያስከፍለን አይቀርም፡፡ በብፁዓን አባቶችም መካከል መለያያት ለመፍጠር የሚጠቀሙበት እንዲህ ዓይነቱ ስልት ያረጀ ያፈጀ ከመሆኑም ባሻገር የእግዚአብሔር ቃል ግን በመ. ምሳሌ 6፡ 16-19 “እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው ፤ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፤…በወንድማማች መካከል ጠብን የሚዘራ፤” እንዲል በዚህ መንገድ የሚጓዙ በአባታችን በእግዚአብሔር ዘንድ ጽዩፍ ስለሆኑ የ10፣ የ20፣ የ100 ዓመት ደረጃውን የጠበቀ ስልታዊ ዕቅድ ቢያቅዱ፤ ቀን ከሌሊት በትጋት ቢሠሩ እንኳ ወጤቱ ፍሬ አልባ መሆን ወይም መራራ ፍሬ ማፍራት ነው፡፡

ለምሳሌ የሕዝቡን ትኩሳት ተጠቅሞ ለምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ተብሎ የተቋቋመውን ሚዲያ ግለሰቦች እንደፈለጋቸው እንዲሆኑበት በላይክ፣ በሰብስክራይብ እና በሼር እንዲጠቀሙበት ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ብለው ሲሰይሙ ዝም ስላል ዛሬ ደግሞ ራሱን ልክ የቤተ ክርስቲያኒቱ ዋንኛ ተጠሪ አካል አድርጎ የምክክርና የጥናታዊ ጽሑፍ መድረክ ለመላው ኦርቶዶክሳውያን ማለት ምን ማለት ነው? ማነው መላ ኦርቶዶክሳዊያንን ጠሪ ያደረጋችሁ ? ማነው በእኛ ላይ የሾማችሁ? መድረኩ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችን የመመለስ ሓላፊነት አላችሁ? ለእናንተ ሲሆን ቀኖና ቤተ ክርስቲያን አይሠራም እንዴ? ጉባኤው በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት፣በጠቅላይ ቤተ ክህነት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፤በጠቅላይ ቤተ ክህነት እውቅና አለው? ፈቃድ ያለውን የቤተ ክርስቲያኒቱን ሚዲያ መጠቀም ለምን አልቻላችሁም? ዙሮ ዙሮ ከዩቲዩብ ለሚገኝ ድቃቂ ሳንቲም ብሎ ኢ-መዋቅራዊና ሁሉን አቀፍ ያልሆነው #ሞዐ ተዋሕዶ ላይ ከፊት የተሰለፉ ሰዎችን ለመስበርና ለማሰበር የሚደረገው ሩጫና ጥድፊያ ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝን ማስተዋል ይጠቅማል፡፡

በአጠቃላይ ባለፉት ሁለት እና ሦስት ዓመታት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ የተፈጠሩ መጠነ ሰፊ  ችግሩችን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ለግለሰቦች የዕለት ጉርስ የዓመት ልብስ  ከመጥቀም ባሻገር ይሄ ነው የሚባል ሁለንተናዊ ጥቅምና ለውጥ ያላመጡ ማኅበራት፤ኅብረት እና ግበረ ኃይሎች መካከል፡-

  1. ፈለገ ባኮስ የሰባክያን እና ዘማርያን ኅብረት
  2. የአዕላፋት ድምፅ የካህናትና ምዕመናን ተናሥዖት ኅብረት
  3. ሠለስቱ ምዕት የመንፈሳዊያን ማኅበራት ኅብረት
  4. የአስተዳዳሪዎች ኅብረት
  5. የወጣቶችና ጎልማሶች ማኅበራት ኅብረት
  6. የነገረ መለኮት ምሩቃን ማኅበር
  7. የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
  8. ጴጥሮሳውያን የቤተ ክርስቲያን መብትና ክብር አስጠባቂ ማኅበራት ኅብረት
  9. ማኅበረ ካህናት ዘሰሜን አሜሪካ
  10. ማኅበረ ካህናት ዘዩኬና አየር ላንድ ሲሆኑ
  11. አሁን ደግሞ #ሞዐ ተዋሕዶ
  12. …ነገ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ችግር ሲፈጠር የሚፈጠሩ ይቀጥላሉ…

ከላይ የተዘረዘሩት እጅግ ጥቂቶቹ ሲሆኑ እነዚህ 99% እርስ በእርሳቸው በስውር መረብ የተሳሰሩ ናቸው፡፡ በእነዚህ ውስጥ ዋና ዋኛዎቹ ተዋንያን የራሳቸው ቋሚ ገቢ የሌላቸው፤ አለን የሚሉት ደግሞ በቃኝ የማያውቁ ሆድ አምላኩዎች ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የሁሉም መርሕ “የቤተ ክርስቲያንን መብት እናስከብራለን” ነው፡፡ የሚገርመው ነገር ደግሞ ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ማኅበር(ኅብረት) አንዲት ነገር ከለጠፈ ሳይጣራ፣ ሊሰጥ የሚችለው ጥቅም ፣ሊያስከትል የሚችለው ጉዳት ሳይጤን የእግር ኳስ ደጋፊ ይመስል እየተቀባበለ ይለጥፋል፡፡ ይሄ ከንቱነት ነው!!!

ሌላኛው ስጋቴ ማኅበረ ቅዱሳን እየቆየ ሲሄድ ዳንኤልና ግብረ አበሮቹ በሠሩት ሴራ ደመወዝዝ ከሚከፈላቸው መደበኛ የአድባራትና የገዳማት አገልጋዮች፣ ከሰባክያና ከሰ/ት/ቤት ጋር የመለያያት፣ያለመናበብ ብሎም የጥላቻ ስሜት እንደገጠመውና እንደተጋረጠበት ሁሉ የሞዐ ተዋሕዶ አጀማመርና አካሄድም ይሄንን ልዩነት የበለጠ የሚያሰፋው ካልሆነ በስተቀር የሚያጠብ ስላልሆነ ከተሳፈርንበት ጋላቢ ፈረስ ወረድ፤ ቆም ብለን ማሰብ አለብን!

በመጨረሻም በርካታ ተከታይ ያላቸው ሁለቱ ታላላቅ መምህራኖቻችን መ/ር ሰሎሞን ተስፋዬ እና ፍሬው አራት ዐይና የለጠፉትን በአጽንኦት ማየት የበርካታ ሰዎችን ስሜት ለመረዳት ይጠቅማልና ከታች ለጥፌዋለሁ፡፡

ስለ “ሞዐ ተዋሕዶ”ቆም! በደንብ ቆም! በትክክል ቆም! ተብሎ ይታሰብ!!!

ተጻፈ የካቲት 2014 ዓ.ም

“ሞዐ ተዋሕዶ ግብረ ኃይል” ከድጡ ወደ ማጡ…

ሰላም ተወዳጆች!

ይህን ጦማር እሰከምጽፍበት ቀን ድረስ የ”ሞዐ ተዋሕዶ” የምሥረታ ዜና ድንጋጤን፣ ግርምትንና ግራ መጋባትን ፈጥሮብኝ ከመሥራች ጉባኤ ተሳታፊ እስከ ጽንፍ ተቃዋሚ ሰዎችን ሀሳብ ለመረዳት ሞከርኩ ነገር ግን አሁን ድንጋጤዬ፤ ግርምቴና ግራ መጋባቴ ቀጥሏል፡፡

ድንጋጤዬ፡- በማስተዋልና በብስለታቸው የማከብራቸውና ተስፋ የምጥልባቸው መ/ር ፋንታሁን ዋቄ፣ ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ፣ ዶ/ር ዘርዓየሁ ስሜን የመሳሰሉ ሰዎች አልፎ አልፎ በፈቃደኝነት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን አሰስተወዋጽኦ ሲያደርጉ አእነንደነበረሩ በቢተታወቀቅመም በሚጠሉትና በሚኮንኑት በሆቴል መስብሰብን ተግባራዊ አድርገው ኢ-መዋቅራዊ፣ አደገኛ፣ ከፋፋይ፣ ሌላውን ያገለለ የተነናጥል የቡድንና የሸፍጥ አሠራር አሁን ግን አእነሰሱ ራሳቸው ተዘፍቀው መገኘታቸው ይገርማል! ከድጡ ወደ ማጡ ይልሃል ይሄ ነው!ሎቱ ስብሐት!

ግርምቴ፡- መድረኩን ሲመሩ የነበሩ አባቶች ጴንጤያዊ የማስፎከርና ዘመንኛና አስጨብጫቢ ቲፎዞ ፈላጊ ሰባክያን የሚጠቀሙበትን መንገድ እጅግ የተከበሩ ሰዎች በተሰበሰቡበት ጉባኤ በባዶ ፉከራ ሲያስጨበጭቡ መዋላቸው ይገርማል!፤ ለምሳሌ ይሄንን ለመረዳት ይቺን ያዳምጧት https://youtu.be/vLMPonfS5fk

ግራ መጋባቴ፡- ፍሬ አልባ ሆነው እንደመከኑ በርካታ ጥቅመኛ ማኅበራትና ግብረ ኃይሎች ስብስብ መሥራቾች  እና የቤተ ክርስቲያን መጠቃትና ተቆርቋሪነት መነሻ አድርጎ፣ ብዙ ተወርቶለት፣ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ሸክም የሚጋራ ተቋም ተመሠረተልን ብለን ተስፋ አድርገን ሳለ ለመሪዎቹ(ኮሚቴዎች) ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤትና የጥቅማ ጥቅም ስጦታ እነሆ ተብሎ እንዲመክንና የቴሌቪዥን መስኮት አዳማቂ ብቻ ሆኖ እንዲቀር የሆነውን የ”ጴጥሮሳውያን የቤተ ክርስቲያን ክብርና መብት አስጠባቂ ኅብረት” መስራቾች ዛሬ ደግሞ “ተዋሕዶ ታሸንፋለች!” ብለው በሌላ ገጽ፤ በሌላ መሠረት መምጣት ለምን ፈለጉ? መልስ የለም! ግራ መጋባቴ ቀጥሏል…

“የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት፣ በፍቅርና በመተሳሰብ ያሸንፋል! ከማለት ይልቅ “ኢትዮጵያ ታሸንፋለች” ሲሉ ምን እያሉ እንደሆኑ የሚያውቁት አይመስለኝም፡፡ በየጊዜው የሚነሱ ተዋንያን እንድናተርፍ ያደረጉን ረሀብ፣ማኅበራዊ ኢኮኖሚያዊ የሥነ መንግሥት የአመራር ችግር ነው፡፡ ነጻ ማውጣት የሚቻለው በልዑል እግዚአብሔር መሪነት በቃልም በሥራም እንጂየጭድ እሳት ይመስል በፍከራና በመንቦግቦግ አይደለም፡፡ ማሸነፍ የሚገኘው በጥበብ በማስተዋልና ሁሉን ተረድቶና አሳትፎ በመጓዝ ነው፡፡ታዲያ ኢትዮጵያ አሸንፋለች?

አሁንም ሁሉን አቀፍ ያልሆነ፣ኢ-መዋቅራዊና ከአባቶች ጋር መግባባትና ይሁኝታ ያላገኘ አካሄድ ይዞ ተዋሕዶ ታሸንፋለች ማለት ከድጡ ወደ ማጡ ይከተን ካልሆነ በቀር መፍትሔ ያመጣል የሚል ግምት የለኝም፡፡

ይሄንን ለማሳየት አንድ ምሳሌ ላንሳ በትግራይ ክልል የነበረውን ችግር ለመፍታት ከቱርክ ተሞክሮ ተወስዶ በዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም ተቋም ተጠንቶ በወቅቱ የነበረውን የእስላሞች እንቅስቃሴ ለማስተንፈስ ተብሎ የተቋቋመው “የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ” እና የሰላም ሚኒስቴር ማንንም ሳያማክሩ አንድ ውሳኔ ይወስናሉ፡፡ ይኸውም 95% የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኝ ባለበት ክልል የቅዱስ ሲኖዶስን አባላትን ሳያማክሩና የመፍትሔው አካል እንዲሆኑ ሳያደርጉ ቢያንስ እንኳን ዛሬ ራሳችንን ችለናል ብለው መግለጫ እስከ ማውጣት የደረሱ የትግራዋይ 4/5 ጳጳሳትን ሳያካትቱ ለሥልጣን የሚሻኮቱ የፓለቲካ ኃይሎችን ኩርፊያ ለማስማማት የተደረገው እንቅስቃሴ ተቃባይነትን ካለማግኘቱ ባሻገር አድርገናል ለማለት ያህል ለፖለቲካ ፍጆታ ዋለ እንጂ መፍትሔ እንደማያመጣ እየታወቀ የተዋቀረ ግብረ ኃይልና ስብስብ ነበር፡፡

ሞዐ ተዋሕዶ ግብረ ኃይል ከድጡ ወደ ማጡ ወሳጅ ጎዳና የሚሆነው ለምንድነው

ሀ. ማኅበሩ በርካታ የሠራቸው ፍሬያማ ሥራዎች፣ እንዲጫጩና ልክ ማደበሪያ እንደለመደ መሬት እንዲመክኑ ትልቁን ሚና ሲጫወት የቆየው በውጪ የስለላ ድርጅት ተላላኪነቱን በመጠቀም አቅም ያላቸውንና እውነተኛ የተዋሕዶ ልጆችን በማሳደድና ብፁዓን አባቶችን እንዲከፋፈሉና አንድነት እንዳይኖራቸው እንደ አይጥ በፁዓን አባቶች ቤት እየተሹለኮለካና ድብቅ ካሜራ ጭምር በማስቀመጥ ሲያተራምሰንየኖረው፤ ቀድሞ ከቁልፍ የሕወሐት ሰዎች ጋር ጥብቅ ቁርኝነት የነበረው፤ በኋላ ግን ጥቡዓን በሆኑ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ሁላችንም በተገኘንበት ደባውና ሴራው በማጋለጥ አንተ ሰላይ እጅህን ከቤተ ክርስቲያን ላይ አንሳ ስለተባለና ስለተነቃበት እናቱ እንሞተችበት  በአንድ ጉባኤ ስቅስቅ ብሎ ያለቀሰው እና ዛሬ ደግሞ የተጋለጠውንና ያልተሳካውን ካባውን ቀይሮ የአዲሱ ፓርቲ አባል ሁኖ በልጽጎ ፓርላማ ገብቶ ያለው ባያብል ሙላቴን የመሳሰሉ መሰሪዎችና ዲቃላዎችነቀርሳዎች ከጀርባ መኖራቸው ነው፡፡

  • ለ. በስልክና በትስስር መስመር ላይ ብቻ ያሉትን ብቻ ያካተተ መሆኑ ነው፡፡ ይህም ማለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ጉዳት፣ ስደት፣ መከራ እየደረሰባት ያለው ከየትኛውም ጊዜ ይልቅ በዚህ ዘመን መሆኑ እሙን ነው፡፡ ተዋሕዶ ማሸነፍ የምትችለው በቅዱስ ሲኖዶስ ምክርና ውሳኔ፤ በሊቃውንትና በገዳማውያን ጸሎትና ግሳጼ፣ በእውነተኛ ሰባክያን መሰጠትና ትምህርት፤ በሰ/ት/ቤት ተማሪዎች አገልግሎትና ትጋት እንጂ 90% የማኅበሩ ደጋፊ በሆኑበት ግብረ ኃይል ሊሆን አይችልም፡፡

ሐ. ማሸነፍ የምንችለው ችግር በተከሰተ ቁጥር ገንዘብና እርዳታ ሰብሳቢና አሰባሳቢ በመሆንና እዚህም እዚያም ግብረ ኃያልና ማኅበር በማቋቋም ሳይሆን ሕጻናት እየተጫወቱበት ያለውን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየደረጃው ያሉ መዋቅር ውስጥ ገብቶ በማገልገልና በማጠናከር እንጂ ምንም እንኳ ጠቃሚ ሀሳብ ብንይዝም የቤተ ክርስቲያኒቱ የበላይና ወሳኝ አካላት ምንም አያመጡም ወይም አቅም የላቸውም በሚመስል እሳቤ ወደ ጎን በማለትና እንደ አሜባ በማባዛት አይደለም፡፡ ስማቸው ሊወድቅ ወይም ገቢያቸው ሊቀንስ ሲጀምር በድርድ ያስቀመጧትን መረጃ ብቅ እያደረጉ ወሳኝ አካላት ናቸው ብለን እንድናስብ በይሉኝታ ላም እሳት ወልዳ ዓይነት የሆኑ ያሉን ማኅበራትና ግብረ ኃይሎች ይበቁናል፡፡

መ. የሞ ተዋሕዶ ባለ ሰባት ነጥቡ የአቋም መግለጫ ሲጠቃለል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ራሷን የቻለች፣ ተደማጭነት ያላት፣ ማንም እንደፈለገ የማያሽከረክራት ተቋም ሁና ማየት ነው ብዬ ወስጄዋለሁ፡፡ ይህ ከሆነ ቤተ ክርስቲያን ማሸነፍ የምትችለው ሁለንተናዊ በሆነ መንገድ ራሷን ስትችል እንደሆነ አምናለሁ፡፡

ነገር ግን በታሪካችን ውስጥ ይህ ጉዳይ ያልተሳካበትን መንገድ ማየቱ ለዛሬ ከጠቀመን እነሆ፡-

1ኛ. ደጃዝማች ወልደ ሰማዕት ገብረ ወልድ “ሕይወቴ” በሚለው መጽሐፋቸው ከገጽ 522-24 ላይ እንዳሠፈሩት በንጉሡ ጊዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ራሷን ችላ እንድትተዳደር ለማድረግ ማለትም ሀብቷ ባንድ ላይ ተጠቃሎ ቤተ ክርስቲያኗ በምታዘጋጀው በጀት መሠረት አብያተ ክርስቲያናት እንዲተዳደሩበት በሚል በአቶ ከበደ አበበ ሰብሳቢነት የተቋቋመው ሰባት ታላላቅ ሰዎች ያሉበት ግብረ ኃይል ዕቅድ እንዳይሳካ ያደረገው በረከታቸው ትድረሰንና መቼም ከሰው ስህተት ከብረት ዝገት አይጠፋምና በግፍ በሰማዕትነት ያለፉት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ በሚያስተምሯቸውና በሚረዷቸው ሰዎች ምክንያት የቤተ ክርስቲያኒቱ ተቋማት ሆነው ነገር ግን ጠቀም ያለ የሆነ የኪራይ ገንዘብ የሚያስገኙ ለግላቸው የሚውሉ ተቋማት ገቢ ወደ አንድ ቋት እንዲገባና ከዚያ እንዲጠቀሙ ሲነገራቸው ፈቃደኛ ባለመሆናቸው መሆኑን ጽፈዋል፡፡

2ኛ. ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ “አንድ አፍታ ላውጋችሁ” በሚለው መጽሐፋቸው ገጽ  246-47 በደርግ ዘመን ከንጉሡ ዘመን ግብረ ኃይል አባላት መካከል ሁለቱን በማካተት በኮሎኔል አጥናፉ አደራጅነት ቤተ ክርስቲያን ከመንግሥት ድጋፍ ወጥታ ራሷን የምትችልበት መንገድ እንዲፈጠር በዶ/ር ክነፈ ርግብ ዘለቀ ሰብሳቢነት የሚመራ ሰባት አባላት ያሉት ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ነበር፡፡ ነገር ግን በእነ ሊቀ ማእምራን አበባው ይግዛው ጠንሳሽነት ያልተሰጣቸውን አጀንዳ ፓትርያርኩ ለመንግሥት ሳያሳውቁ አቡነ ጳውሎስን ጨምሮ ሦስት ጳጳሳትን ሾመዋልና ከፕትርክና ይነሱ ብለው ሰበር የሆነ ሰባሪ አጀንዳና መለያየት ምክንያት ይሄኛውም ግብረ ኃይል ውጤታማ ሳይሆን እንደቀረ ጽፈዋል፡፡

3ኛ. በዚሁ በቅርብ ጊዜ ደግሞ በብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ መሪነት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ወቅት ቤተ ክርስቲያን ዘመኑን በዋጀ የአሠራር መንገድ እንድትጓዝና ራሷን እንድትችል ታቅዶ ጥልቅ የጥናት ሰነዶች ተዘጋጅተው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አድባራት ፭ቱ ከለባት ማኅበረ ቅዱሳን ቦታህን ሊቀማህ መጣብህ በሚል ውክቢያ እንዲዳፈን የተደረገው እንዲሁም የመከነውና በሞዐ ተዋሕዶ ሊዋጥ ሊሰለቀጥ በመንገድ ላይ ያለው ጴጥሮሳውያን የቤተ ክርስቲያን ክብርና መብት አስጠባቂ ኅብረት ለምን የተመሠረቱት አላማ ሊያሳኩ አቃታቸው? ብሎ ገምግሞ ያለውን ፈትሾ አጥርቶ የተነሳ ባለመሆኑ ነው፡፡(በፎቶ የቀረበውን የሁለቱን  መመሳሰልና አንዱ ሌላውን ይውጠው ዘንድ እንዲገባ ለቡ!)

በርግጥ ኢ-መዋቅራዊ አደረጃጀት እሳት ለማጥፋት፣ የሕዝብን ሥልጣን ይዞ ሕዝብ ላይ የሚያላግጥን ባለሥልጣን ለማስደንገጥና አደብ ለማስያዝ ጠቃሚ ቢሆንም ይህ ዓይነቱ አካሄድ አስተዳደሯ ክህነታዊ ለሆነው ለታላቋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካለመመጠኑም በላይ በማኅበሩ ውስጥ የተሰገሰጉ በጣት የሚቆጠሩ ለቅዱስ ሲኖዶስና ብፁዓን አባቶች ክብር የሌላቸውና ንቀትን የተለማመዱ አካላት አነሳሽነትና ገፋፊነት እየተደረገ ያለ  አካሄድ በመሆኑ አደጋው ከባድ ነው፡፡ አንዱ ማሳያ ገና ሲጀምር የፌስ ቡክ ገጹን ከቨር ፎቶ እንኳ የብፁዓን አባቶች ማድረግ ሲገባው የአንድ ሊቀ ጳጳስ ማድረጉ ትዝብት ውስጥ የሚከትና ለጥርጣሬ የሚጋብዝ ነው፡፡

ስለዚህ  “ሞዐ ተዋሕዶ ግብረ ኃይል” ከድጡ ወደ ማጡ የሚከተን እንዳይሆን ከሆቴል ወጥቶ ወደ ቤተ ክርስቲያን፤ ለቤተ ክርስቲያን የማውቅላት እኔ ብቻ ነኝ ከሚለው ግንጥል አካሄድ ወጥቶ ሁሉን አቀፍ እና በቤተ ክርሰቲያን መዋቅር ሥር ሆኖ ተጠያቂነትና ኃላፊነት በሚሰማው መንገድ ለመጓዝ ራሱን ቢያርም መልካም ነው እላለሁ፡፡

ይቆየን!

የካቲት 2014 ዓ.ም

በአቋም መግለጫ ጋጋታ ሀገርንም ሆነ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መታደግ አይቻልም!!!

ተወዳጆች እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የእረፍቷ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን!!!

በአቋም መግለጫ አወጣጥ ቅደም ትከተል ካልሆነ በስተቀር በቃል የቤተ ክርስቲያኒቱ ተቆርቋሪ መሳዮች በተግባር ግን ጥቅማቸው እስካልተነካ ጆሮ ዳባ ብለው ከኖሩ፥ አብዛኞቹ ለሠሩትና ወደፊት ለሚሠሩት የኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችን ወኔና ሥነ ልቡና የመስለብና የማምከን ሥራ ቤትና ዳጎስ ያለ ገንዘብ ከከተማ አስተዳደሩ በሽልማት መልክ የተቸራቸው፥ ሌሎቹ ድግሞ በማኅበራት ስም ተሰባስበው የቀድሞውን ሥርዓት ነቃፊ መስለው በስውር ግን አሽከርና ተላላኪ ሁነው በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ ደባ ሲፍጽሙ የኖሩ ለአቋም መግለጫ ሲራወጡ ስመለከት ግራ በተጋባ ስሜት ውስጥ ሆኜ ይህችን መጣጥፍ ጣፍኩኝ።

ከፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ጋር የማልስማማባቸው አንዳንድ ነገሮች ቢኖሩኝም ለዛሬ “አንዳፍታ ላውጋችሁ” ከሚለው መጽሐፋቸው ገጽ 368-9 ላይ የሰፈረ ሀሳባቸውን ተዋስኩኝ።  ምንም እንኳን የእምነቱ ተከታይ ባይሆኑም የፕሮቴስታንት ሚሲዮናውያን በሀገርና በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚፍጽሙትን ደባ “አድናቃፊና ደንቃራዎች” በሚል ንዑስ ርእስ ሥር እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል፦

“ወንጌላውያን ነን የሚሉ ሚሽኔሪዎች—የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን፥ በጠቅላላው የኦርቶዶክስን ሃይማኖት የሚጠሉ ወገኖች ኢትዮጵያ የመጡት ችግረኞችን ለመርዳት ወይም ያላመነውን ለማሳመን፥ ወይም የስዊዲን ሚሽኔሪዎች እንደሚሉት  የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ለመርዳት ሳይሆን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን አፍርሶ አዲስ ቤተ ክርስቲያን ለመሥራት መሆኑን ከነሱው ውስጥ አንዱ በሕልሙ ያየላትን አፍርሶ አዲስ ቤተ ክርስቲያን መሥራት በግላጭ ተናግሯል። ዝርዝሩን እኔና ሌሎች “The Missionary Factor in Ethiopia” በሚል ርዕስ ባሳተምነው መጽሐፍ ውስጥ ማየት ይቻላል። “

እነሱ በግላጭ እንዲህ እያሉ የኛዎቹ ግርግርን እየጠበቁ ውርውር የሚሉ ጥቅመኞችና ቲፎዞ አሰባሳቢዎች ራሳቸው አቋም አልባ ሆነው የሚወጡትም “የአቋም መግልጫ/ማሳወቂያ” ከቤተ ክህነት ቅርጫት ላያልፍ እንዲህ ማዳነቅ መቀባበል ምን የሚሉት ነው??? ምናልባት ይሄ አቋም አልባ መግልጫቸው የዘመናዊ ሙዳየ ምጽዋት ለቃቃሚዎች(youtubers) ፍጆታ ማሟያና ማስተዋወቂያ፥ ሰብስክራይብ ፥ ሼር አድርጉ እያሉ ቁም ስቅላችንን ለሚያበሉን አስተዋጾ እንዲያብረክት ካልሆነ በስተቀር ሀገርንም ሆነ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን  አስቦና አቅዶ ሊያጠፋ የተነሳ አካልን በብጣሽ ወረቀት ጋጋታ ማሸነፍ አይቻልም።

እዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባው ዛሬ ላይ በመናፍቃን እየተፈጸመ ያለው ግፍ እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ የመጣ አይደለም። ኦነግም በለው ሸኔ የግብር አባታቸውን ጸር ክርስቶሰ አቋም ያለውን ሉተርን መስለውና አህለው እንዲብቅሉ ትልቁን ሚና እየተጫወተች ያለችው ብዙም ያልተወራላትና አድፍጣ የጥፋት ሠራዊቶችን ያሰማራችብን የሉተር እናት ጀርመን ናት። እስቲ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ እንፈልግ!!!

  1. ለምን አውሮጳዊቷ ሀገር ወለጋ ላይ ከዛሬ 100 ዓመት በፊት ሆስፒታል ገነባች?
  2. ኦነጎችና ጀርመኖች ምን አዛመዳቸው?
  3. ዛሬ በየደረጃው ያሉ ኢትዮጵያን የሚያስተዳድሯት አብዛኛው መሪዎች በኢትዮጵያ የሉተራን ቤተ ክርስቲያን ክንፍ የሆንችው መካነ ኢየሱስ አባላት የሆኑት በአጋጣሚ ይሆን?
  4. ኤርትራ ከኢትዮጵያ ስትገነጠል የሚሽኔሪዎች ድርሻ ምን ነበር?
  5. የአናሲሞስ ነሲቡን በግእዝ ፊደላት የተጻፈውን የመጀመሪያውን መጽሐፍ ቅዱስ ማን በላቲን ብቻ ወደ ሚል መርሕ ወሰደው?
  6. ??? እያላቸሁ ቀጥሉበት

ደጃዝማች ወልደ ሰማዕት ገብረ ወልድ “ሕይወቴ” በሚል ድንቅ መጽሐፋቸው ገጽ 474-5 በ1966 ዓ/ም የነበረውን ሁኔታ እንዲህ ይገልጹታል፥-

“ የጊምቢ አውራጃ ቀደም ብለው ሚሲዮኖቸ የገቡበት ስለሆነ ከቀሩት አውራጃዎች ሁሉ ይብልጥ የሚሲዮን ትምህርት ቤቶችና የጤና አገልግሎት ያገኛል።———–በአይራ ጉሊሶ ወረዳ በአይራ መንደር በጀርመናውያን ሚሲዮናውያን የሚካሄደው ሆስፒታል ይገኛል። ጀርመናውያኑ የጤና አገልግሎት ብቻ ሳይሆን ሕዝቡ በእናት አገሩ ላይ እንዲያምጽ፣ ኢትዮጵያዊነቱን በሚያስክድ ፖለቲካ ይመርዙታል። ኦነግ ተጠንስሶ ወደ ቀሪዎቹ የአውራጃው ክፍሎች እንዲዛመት በማድረግ ላይ እንዳተኮሩ ደረስኩብት።—-“ ይላሉ።

ጉሊሶ ማለት የዛሬዋ የሰማዕታት መንደር ናት! ለቡ!!!

ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ በ”መድሎተ ጽድቅ ቁጥር ፫” ገጽ 275-6 ይህንኑ እንዲህ በማለት ገልጦታል፦

“ወደ እኛ ሀገር የመጡ የጀርመን ፕሮቴስታንት ሚሲዮናውያን በዋናነት የሰበኩትም ስለ “ኢየሱስ” ሳይሆን ኦርቶዶክስ ጠል እና ሴማዊ ሕዝብ ጠል የሆነ አስተሳሰብን ማሥረጽ ነበር። ከ100 ዓመታት ኦርቶዶክሳዊነትን  እና ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰብን የማስጠላት ዘመቻ በኃላም ውጤቱን አሁን በሀገራችን እየተመለከትን ነው።—-ሉተራውያን  የጀርመን ፕሮቴስታንቶች በኢትዮጵያ ላይ ያስቡትን የረጂም ዘመን ዕቅድ ይዘው ወደ ኢትዮጵያ ይዘመቱበት ሃኖቨር የተባለውን ቦታ የዚህ መጽሐፍ ጸሐፊ በዓይኑ ለማየት ችሏል። እንደዚሁም እነዚያው የጀርመን ሚሲዮናውያን ከእኛው ቤተ ክርስቲያን ካህናትና አገልጋዮች መካከል በስውር እየመለመሉ   ኦርቶዶክሳዊነትንና ኢትዮጵያዊ ማንነትን የሚጸየፍና እንደ ጭቋኝ እንዲመለከት እያደረጉ የሚቀርጹብትን የፕሮቴስታንት ስብከት የጀመሩበትን ቦታም እንዲሁ በምዕራብ ወለጋ ላይ  በዓይኑ  አይቷል።“

እንግዲህ ኦነግ በዳቦ ስሙ በሸኔ የሚፈጽመው እጅግ ዘግናኝ ጭፍጨፋ በማን ትምህርት እና ሥልጠና እንደሆነና ጀርመኖቹ ከአንድ ምዕተ ዓምት በላይ የመካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያንን እንዴት እንደተጠቀሙባት ሳሰብ ለእነዚህ ሰዎች የአቋም መግልጫ ምናቸው ነው??? ምንተ ንግበር??? እላለሁ።

አሁን በሥልጣን ላይ በየደረጃው ያሉት ዋንኞቹ መሪዎች ለማስመሰልና ለማደናገር ያህል ዛሬ ላይ የሆነ የጴንጤ ድርጅት ላይ አምልኮአቸውን ይፈጽሙ እኝጂ ዓላማ አንግበው የተነሱት የሉተራን ክንፍ ከሆነችው ከመካነ ኢየሱስ ነው። ያ ማለት የመሥራቾቻው ዓላማና ግብ የሆነው ሕዝቡ በእናት አገሩ ላይ እንዲያምጽና ኢትዮጵያዊነቱን በሚያስክድ ፖለቲካ እንዲመራና እንዲመራ መፈጸም ትይዩ ዓላማቸው ነው ማለት ነው።

ለሁላችንም የሚበጀን ግን ይህንን የክፋት አሠራር አስወግደን ለሁላችንም ማዕከላችን የሰላምና ፍቅር ባለቤት የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አርአያ ተከትለንና ተመልክተን መከባበር፣ መደማመጥና መከባበር እንጂ ሃይማኖተኛ መስሎ ሊያጠፉን የተነሱት የምዕራባውያንን እኩይ ተልዕኮ ተሸክሞ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ለመምራት መሞከር ሩቅ የማያደርስ ጎዳና ከመሆኑ ባሻገር ኦርቶዶክሳዊነትና ኢትዮጵያዊ ማንነትን እየተሠራ ያለውን ግፍ ታሪክና የታሪክ ጸሐፍት በአግባቡ እየመዘገቡት በመሆኑ በደም የጨቀየ የግፍ ታሪክ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ባንትጋ መልካም ነው።

ሌላው ጉዳይ ታላላቅ የኦሮሞ፣ የአማራ፥ የደቡብ እና ከሌሎችም ብሄር የተውጣጡ አርበኞች የገነቧትን ኢትዮጵያ በጽንፈኞች አንድነታችን፣ የህዝብ አብሮነት እንዲፈርስ መንቀሳቀስና ደጉን የኦሮሞ ሕዝብ ከለላ አድርጎ በከፋፍለህ ግዛው መርሕ አማራንና ትግራዋይን እንደ ሕዝብ ደም እንዲቃቡ እንደተደረገ ሁሉ፤ የጀርመኖቹ ምልምል በሆኑ ባለሥልጣናትና የኦነግ( ሸኔ) ሠራዊት የኦሮሞና የአማራ ሕዝብን እንደ ሕዝብ ደም ለማቃባት የሚደረገው ደባና ሩጫ እንዲቆም በጸሎት እየተጉ ቆም ብሎ ማሰብ፣ ማቀድ እንጂ የአቋም መግለጫ ጋጋታ ምን ያህል እንደ አሜባ እንደተበጣጠስን እንጂ ቆራጥንታችንና የዓላማ ሰዎች መሆናችንን የማያሳይ በመሆኑ በአስተውሎት ብንጓዝ እላላሁ።

ይቀጥላል+++

ተጻፈ ጥር 2014

እንኳን በሰላምና በጤና ለብርሃነ መስቀሉ አደረሰን! አደረሳችሁ!

ባይ ባይ ኢ-አማኒው  አሥር አለቃ ፋንታሁን ሙጬ!!!

የዘንድሮው የደመራ በዓል አከባበር ሀገራችንና ወገኖቻችን በጣም በከባድና በአሳዛኝ ሁኔታ ላይ ሁነው ብናከብርም ዳሩ #በመስቀል አደባባይ እጅግ ደስ የሚል የበረከት በዓል አክብረናል፡፡ ብዙዎቻችን ከረካንበት ነገር አንዱ በዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል ላይ ከ the…the…the…is… is…was…ነጻ የሆነ ተገቢው የሆነ የመድረክ መሪ አግኝተን እነ ሙጬን ከመሳሰሉ ደፋሮች ተላቀን በተገቢው ቦታ ተገቢውን ሰው በማየታችን ነው፡፡

ከመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ጋር በተያያዘ በአማኙም ይሁን በኢ-አማንያን ዘንድ ተደጋግሞ ከሚሰነዘሩ ትችቶች አንዱ ምነው ቤተክርስቲያኒቱ ሰው የላትም እንዴ? ምነው ሌላው ቢቀር present, past and future tense ለይቶ በማይናገር ሰው መድረኩን የምትጫወቱበት ይባል ነበር፡፡

ዘንድሮ እግዚአብሔር ይመስገን መድረኩ ለሚገባ ሰው በመሰጠቱ መምህራችን ቀሲስ ዳንኤል ይደልዎ! ብለናል፡፡ ለዚህ ትልቁን ድርሻ የተወጡት አድርባይነት የሌለባቸው ባሕታዊና የልማት አባት የሆኑት ብጹዕ አቡነ ያሬድ የጠቅላይ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ እንደሚሆኑ ጥርጥር የለንም፡፡ ምክንያቱም ልክ ወደ ኃላፊነት እንደመጡ የመጀመሪያ ሥራ ያደረጉት ለረጅም አመታት አንደ መዥገር ተጣብቆ ሲጫወትበት ከኖረበት የሰበካ ኩባኤ ማደራጃ መመሪያ ኃላፊነት በማስወገድ ነው፡፡ በዚህም ከአድርባይነት የጸዱ እውነተኛ የቤተክርስቲያኒቱ አባት መሆናቸውን በተግባር አስመስክረዋል፡፡

በምትኩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጪ ግንኙነት የበላይ ኃላፊ፣ የነገረ መለኮት ሊቅ፣ መምህር፣ ተመራማሪ፣የሃይማኖት፣ የታሪክ፣ የባህልና የሥነ ጥበብ ባለሙያና ፀሐፊ የሆኑት የቤተክርስቲያናችን ዕንቁ ልጅ ለሆኑት ለመምህር ቀሲስ ዳንኤል ሰይፈሚካኤል መስጠቱ ይበል ያሰኛል፡፡ ቅድስት ቤተክርስቲያን ብዙ ጊዜ የምትሰደበው እነ ሙጬ የመሳሰሉ መንገደኛና የምንግዜም ደም መጣጭ ሰዎች ሳይገባቸው ቦታ ይዘው ነው፡፡ ይህ የማስተካከያ እርምጃ በሌሎችም ዘርፎች እንደሚቀጥሉ ተስፋ አለን!!!

ባይ ባይ ኢ-አማኒው  አሥር አለቃ ፋንታሁን ሙጬ!!!

መልካም በዓል!

ይቆየን  

ጳጉሜን ለሁሉም፣ የሁሉም፣በሁሉም

ሰላም!ሰላም!ወዳጆች

ዛሬ ላካፍላችሁ የወደድኩት ርእሰ ጉዳይ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሀገር አቀፍ የአምስት ቀናት ጸሎት፣ ጾምና ምህላ ማወጁን ተከትሎ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ

  • ምን አገባውና ለምን ያውጃል?
  • ስለ ምህላውና ጾሙ አፈጻጸምና ጥቅም ከማውራት ይልቅ ፓትርያርኩ ለምን መግለጫው ላይ አልተገኙም?
  • ጳጉሜን 1፣2…የእንትን ቀን የእንትን ቀን እያልን ከማክበር በጾም በጸሎት ማሳለፍ ይሻላል ከሚሉ አስተሳሰቦችና አስተያየቶችን ጀምሮ  የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የወሰነው ውሳኔ ጊዜውን የዋጀ መልካም ተግባር ነው እስከሚሉት ዋልታ ረገጥ ሀሳቦች ሲንሰራሸሩ በማየቴ ጥቂት ለማለት ነው፡፡

በእኔ እምነት የሃይማኖት ተቋማትም ይሁኑ ሀገር ከገቡበት ቅርቃር መውጫ ብቸኛ መንገድ የቤተክርስቲያን ጸሎትና ጥበብ በመታመን ነው፡፡ ምክንያቱም ኢትዮጵያ የመዳኛና ከችግር የመውጫ ተስፋና መንገዷ እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ቅዱስ ዳዊት ‹‹ኢትዮጵያ ታበጽእ እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር ›› መዝ 67፡31 ፤‹‹ይገንዩ ቅድሜሁ ኢትዮጵያ ወጸላእቱሂ ሐመደ ይቀምሑ፤በፊቱም ኢትዮጵያ ይሰግዳሉ፣ ጠላቶቹም አፈር ይልሳሉ›› መዝ 71፡9  እንዲል ጠላት ከወረወረው ጦር ከክፉዎች ሴራና ከአባር፣ቸነፈር፣ከወረርሽኝ…መዳን የምንችለው በአግዚአብሔር ታምነን በምናደርገው ጸሎት ነው፡፡ በኮቪድ 19 ምክንያት ከ28 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ያልቃሉ ተብሎ ቢሟረትብንም ኢትዮጵያውያን ወደ ተስፋችን ወደ እግዚአብሔር ተግተን በመማጸናችን ሕዝበ ነነዌን ያሰበ አስቦ አድኖናል፡፡

ምንም እንኳን ቢዘገይም ዛሬም በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አነሳሽነት ለሀገር ሰላምና አንድነት ጾም፣ ጸሎትና ምህላ  መታወጁ መልካም ነው፡፡ ለዚህም የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን በመወከል በብዙ ድካም የሚወጡ የሚወርዱ የጉባኤው ዋና ጸሐፊ ሊ/ትጉሃን ቀሲስ ተጋይ ታደለ የመሳሰሉ ትጉኃን ምስጋና ይገባዋቸል፡፡

የዘንድሮውን የጳጉሜን የጾም፣ ጸሎትና ምህላ መርሐግብር አስመልክቶ ቢስተካከሉ የምንሻቸውን ሀሳቦች  ላጋራችሁ ፡፡

እንዲህ ዓይነት መርሐግብሮች ሲዘጋጁ ብዙ ጊዜ ለኢትዮጵያውያን በሙሉ እንደተዘጋጁ ቢነገርም እውነታው ግን መርሐ ግብሮቹ በደበዘዘ መልኩም ቢሆን ተፈጻሚ የሚሆኑት በከተሞችና ቴሌቪዥን ባላቸው ሰዎች ቤት በከፊል ነው፡፡ ስለዚህ ተፈጻሚ ሆነው ውጤት ማስገኘት እንዲችሉ መርሐ ግብሮቹ ለሁሉም፣ የሁሉም፣በሁሉም መሆን አለባቸው፡፡

  • ለሁሉም፡- ይህ ማለት አብዛኛው የሀገሪቱ ሕዝብ ማለት 80 በመቶው በገጠር ከመኖሩ አንጻር ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን ታስቦ ሊሆን ይገባዋል፡፡ በጦርነት ወቅት የመጀመሪያው ተጠቂና አገር ጠባቂ ይሄው ከግምት ውስጥ የማናስገባው 80 በመቶው በገጠር የሚኖረው ማኅበረሰብ በመሆኑ ወደ አዋጅ ከመገባቱ በፊት ዛሬም ነገም ቢሆን የምናዘጋጃቸው መርሐ ግብሮቻችን ሁሉ እነዚህን ወገኖች ታሳቢ ማድረጉን በቅድሚያ ማረጋገጥ ይገባል ማለት ነው፡፡
    • የሁሉም፡- ብዙ ጊዜ በቤተክርስቲያናችንም ይሁን በሀገራችን የሚታዩ ችግሮች ምንጭ እኔ ላስብልህ፣ላውራልህ፣ልስራልህ፣ልኑርልህ፣ላስተዳድርህ እና የመሳሰሉ ጽንፍ የወጡ የራስ ወዳድነት መገለጫ ጠባያት ናቸው፡፡ ስለዚህ የምናከናውናቸው የትኛውም ሀገራዊ ጉዳዮችና መርሐ ግብሮች ኅብረተሰቡ የእኔ ብሎ ተቀብሎ ያለነቀፋ በደስታ እንዲተገብራቸውና የሁሉ እንዲሆኑ ቀደሞ አቅዶ መሥራት ይገባል እንጂ ዋዜማ ላይ ደርሶ እኔ ባወጣሁሉህ መርሐ ግብር ተመራ ማለት ወደ ውጤት ከማደረስ ይልቅ የእነሱ እንጂ የእኛ ብሎ ተቀብሎ እንዳይተገብረው ያደርጋልና ለቡ፡፡
    • በሁሉም፡- ካልተሳሳትኩኝ የአሁኑም መርሐ ግብርም ሊከናወን የታሰበው ቴሌቪዥን ላላቸውና የከተማ ሰዎች ሥራ ጨርሰው ሲመለሱ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ነው፡፡ ይሄም እቅዱ ወጤታማ እንዳይሆን ያደርገዋል፡፡ ቴሌቪዥን ያለው ምን ያህሉ የኅብረተሰብ ክፍል ነው? 3ት ሰዓት ላይ ምን ያህሉ የኅብረተሰብ ክፍል ይመቸዋል? ለሚሉ መሰል በርካታ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የጾም፣ ጸሎትና ምህላ መርሐግብሮቻችን በሁሉም የሀገሪቱ ጫፎች ተደራሽ ሆነው መልስ ማምጣት የሚችሉ መሆን እንዲችሉ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ትሁን የሀገሪቱ የተለያዩ ተቋማት በሬድዮና በቀላሉ ተደራሽ የሆኑ የመገናኛ ብዙኃን እንደየቦታውና ሁኔታው አመቺ የሆነ ሰዓት በመጠቀም ይህ ታላቅ ሕዝብ በጋራ ወደ ጌታ፣ አምላኩና የፍጥረት ሁሉ ፈጣሪ ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔር እንዲጸልይ ሁኔታዎች ማመቻቸት ቀዳሚ ተግባር ቢሆን መልካም ነው፡፡

በአጠቃላይ ይህ ሕዝብ በት. አሞጽ 9፡7 ላይ ‹‹ የእስራኤል ልጆች ሆይ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ›› ቅዱስ ዳዊት በመዝ 86፡4 ‹‹… የኢትዮጵያም ሕዝብ እነዚያ በዚያ ተወለዱ›› ተብሎ የተመሰከረለት ታላቅ ሕዝብ በመሆኑ የምናዘጋጃቸው መርሐ ግብሮች ከ20 በመቶ የማይበልጠውን የከተማውን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ከ80 በመቶ በላይ የሆነውን የገጠሪቱ ሕዝባችንን ብዙኃኑን ያማከለ እንዲሆን በትኩረት መሥራት ይፈልጋል፡፡ በኢትዮጵያዊነቱ ከማይደራደረው የአፋር፣የሶማሌና የጋምቤላ ሕዝብ ጀምሮ የቤተክርስቲያናችንም ይሁን የሀገራችን ገጽታና ጸጋ ለማጠልሸት ከሚሠሩ ጥቂት ምግባረ ብልሹ ሰዎች በቀር አብዛኛው የሀገራችን ሕዝብ በእግዚአብሔር የሚያምን ሰለራሱ ሳይሆን ስለጎረቤቱና ስለወገኑ የሚያለቅስ ደግ ሕዝብ በመሆኑ አስፈሪውን ዘመነ ኮቪድ ጠብቆ እያሻገረን ያለው ጌታ አምላክ የሁሉ ፈጣሪ እግዚአብሔር አምላክ ሰላሙን፣ ፍቅሩን፣ አንድነቱን ያድለን ዘንድ፤

ተንሥኡ ለሰላም!

ተንሥኡ ለፍቅር!

ተንሥኡ ለጸሎት!

ነሐሴ 30 ቀን 2013 ዓ.ም

ዘመዴ አራስ ነብር ሆኖ ለቤተክርስቲያን ምስጦች ያሰተላለፈው ማስጠንቀቂያ

ዘመዴ መስከረም 5 ቀን 2013 ዓ.ም በለቀቀው 55ኛው የYouTube ‹‹የበረኸኞቹ መልእክት›› ላይ የቤተክርስቲያን አራሙቻዎችና ነቀርሳዎች የሆኑ አይነኬዎችን ነጭ ነጩን ነግሮ እኛም የማጽዳት ዘመቻውን እንድንቀላቀል ጠንከር ያለ ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያ አስተላልፏል፡፡  እግዚአብሔር በክብር ላይ ክብርን ያድልህ!! ድሮም በየገዳማቱ ለበረከትና አባቶች ለመርዳት ሲንከራተት የኖረ፤ እውነተኛ አባቶችን ከልቡ የሚወድ፤ በታላላቅ የጸሎት አባቶችም የተቀባ የቤተክርስቲያን የቁርጥ ቀን ልጅን ከእነዚህ ከግብዞች፣ከሌቦች፣ከመዓተኞች፣ከቤቱ ሸክሞች፣ከሃይማኖት አሰዳቢዎች ተርታ አሰልፎ ለማየት መሞከር የማይታሰብ ነበር፡፡ በእውነት ዘመዴ እነዚህ አይነኬ ነን ባዮች፣ የቤተክርስቲያን ምስጦች በመገሰጽህ ሁሌም እንደምኮራብህ ዛሬም እጅግ ኮራሁብህ!!!

መቼም የፌስቡኩን መንደር የተቆጣጠሩት፤ አየሩን የሞሉት የእነዚህ አስመሳዮችና ጭፍን ደጋፊዎች ተራ ተራውን፤ ገበሬ አስደንግጡን፣ ገንዘብ የሚሰበሰብበትን ብቻ እየፈለጉ የሚለጥፉ እንጂ እንዲህ ጠፈፍ ያለውን ነጭ ነጩን እውነት መግለጥ ስለሚያንገሸግሻቸውና ስለሚያቅለሸልሻቸው በፌስቡክና በድህረ ገጻችን ላይ ይህን ጮማ እና አንጀት ቅቤ የሚያርስ ፤ሰው ሁሉ የYouTube ‹‹የበረኸኞቹ መልእክት›› እንዲያደምጠው የሚመራ  ጽሑፍ ጽፈናል፡፡

አንዳንዶች hameretewahido.com ድረ ገጽ ላይ በማኅበሩ ካባ ተደብቀው ስለሚያጭበረብሩ ሰዎች የተጻፈውን ተመልክታችሁ የተንጫጫችሁ ነበራችሁ፡፡ እኛ ድሮም የምንለው፣የምንፈልገውና የምንደግፈው ማኅበረ ቅዱሳን የጥንቶቹንና መንፈሳውያኑን ፤ያለመታከትና ያለ ሥጋዊ ጥቅም የሚወጡ፣የሚወርዱ፣ የሚደክሙት፣  ደፋ ቀና የሚሉትን እንጂ ለቤተክርስቲያኒቱ የብጥብጥ፣የዝርፊያና የውንብድና መዋቅር የሚዘረጉትን አይደለም፡፡ ዘመዴ እንዳለው እነዚህ አራሙቻዎች ራሳቸውን ካላረሙ ነቅሎ መጣል ያስፈልጋል፡፡

ዘመዴ 1፡55፡52 በሚወስደው ሁሉም ሰው ተረጋግቶ ሊያደምጠው በሚገባውና እንኳን ለተናጋሪው ለሰሚው ቁና ቁና የሚያስተነፍሰውን ጭንቅላት ሊያፈነዳ የሚደረሰውን ‹‹የበረኸኞቹ መልእክት››  ማዳመጥ እጅግ ወሳኝ ነው፡፡ አስቲ ዘመዴ በቪዲዮው ማገባደጃ ላይ ስለ እነዚህ አራሙቻዎች፣ ምስጦች፣ ግብዞች፣ሌቦች፣ መዓተኞች፣ የቤቱ ሸክሞች፣ ሃይማኖት አሰዳቢዎች…ምን እንዳለ በወፍ በረር ከንግግሩ የወሰድኩትን ላስነብባችሁ፡፡  

ውድ አንባብያን 55ኛውን የዘመዴ የYouTube ‹‹የበረኸኞቹ መልእክት›› ከታላቅ ተማጽኖ ጋር እንዲያደምጡ ላልሰማ እንዲያሰሙ አደራ ለማለት እንወዳለን!!!! አደራ!!!አደራ!!!አደራ!!!ዘመዴ እንዲህ ይላል፡-

40 ሚሊዮኑ ለተጎዱ ሰዎች ይከፋፈል ተብሎ ነበረ፡፡ ነገር ግን በሻሸመኔም፣ በባሌም፣ በሐረርጌም፣ በአሩሲም ያሉት ስደተኞች የተጠየቅነው የባንክ አካውንት የለም የደረሰን ብር የለም ከየትና እንዴት ተብሎ ወጣ እንደተባለ አናውቅም ብለዋል፡፡ ኮሚቴው ቀርቦ ለሕዝብ ያስረዳ ሰውዬው ሳይፈርም ሰውዬው ሳያውቅ ሳይጠየቅ ስደተኞቹ ሳይነገራቸው የባንክ ቡክ ተዘጋጅቷል 40 ሚሊዮን ብር ሊከፋፈሉ ነው ማለት ይሄ ነውር ነው!!! ይሄ ግፍ ነው!! ይሄ ሌብነት ነው!!!ይሄ ወራዳነት ነው!!! ታላላቅ የተባላችሁ ሰዎች ቀርባችሁ አስረዱ ሻሸመኔ አሁንም ለቅሶ ላይ ናቸው፡፡ ግማሹ ወደ ጠበል ግማሹ ወደ ሰው ቤት እየሄደ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን ያሉት የሚያውቁት ነገር የለም፡፡ዘመድኩን በቀለ ለምኗል በቴሌቪዥን ሲነገር ሰምተናል ያየነው ነገር የለም ብለዋል፡፡ እግዚአብሔር ይፍረድ!!! ዝም ብትሉ እኔ ዝም አልልም!!! ሦስት አካላትን በስም ጠርቼ እናገራለሁ፡-

  1. የጴጥሮሳውያን ኅብረት የምትባል በቀሲስ ሙሉቀን የምትመራ ኃይል፤ የመስከረም 4ቱን ሰልፍ የጠመዳችሁ፣ ሙሴ የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ባል እዚህ ውስጥ ለምን እንደገባህ አናውቅም አናውቅህም ውጣ !!! ቀሲስ ሙሉቀን የምትባል ከዚህ ሴራ ውጣ! እናንት የመስከረም አራቱን ሰልፍ ያጨናገፋችሁ…ከአቡነ ዮሴፍ ጋር ከሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ጋር ቢሮ ተሰጥቷችሁ የምትሸርቡትን ሴራ እግዚአብሔር ያፈርሰዋል!!! ጴጥሮሳውያን የሚባል አስመላሽ ኮሚቴ የመብት አስከባሪ ኮሚቴ የሚባል ነውረኛ!!! ቤተክርስቲያንን አሳልፎ የሚሰጥ፤ ሻጭ፣ አውደልዳይ  ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ዳንኤል ክብረት እንድትጽፍልኝ እንድትደውልልኝ አልፈልግም ተሸክመሃቸው ዙር!!! አሉላ ሰሎሞን እንድትጽፍልኝ እንድትደውልልኝ አልፈልግም ተሸክመሃቸው ዙር!!! ታደሰ ወርቁ እንድትጽፍልኝ እንድትደውልልኝ አልፈልግም ተሸክመሃቸው ዙር!!! ጴጥሮሳውያን ኅብረት የምትባል ግን እጅህን ከቤተክርስቲያን ላይ አንሳ!!!…ምድረ ሌባ ሁላ ዘራፊ ሁላ እንደቋመጣችሁ ይቀራል ማለት ነው፡፡
  1. አቶ አንተነህ አቢሲኒያ ባንክ የነበርከው…እዚህ ዐቢይ ኮሚቴ ውስጥ በየት በኩል መጥተህ እንደገባህ አናውቅም ውጣ! አቢሲኒያ ባንክ እዚያው የሠራህውን ግፍ እዚያው ጨርስ፡፡ ውጣ! አናውቅህም ውጣ!!!
  2. አቶ ፋንታሁን ሙጬ ዕድሜ ልክህን ቤተ ክርስቲያንን እንዳደማህ አትኑር ውጣ!!!…ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ ከሕዝብ የተሰበሰበውን ልብስ፤ንብረት ሸጥሽው? የት አደረሽው? ለጥቅምሽ አዋልሽው የት አገባሽው? ቤተ ክህነት ገብቶ ተቀምጧል የተቸገሩት ባሌ ነው ያሉት፤ የተቸገሩት አሩሲ ነው ያሉት ሞዴስ የላቸውም፡፡ ዳይፐር የላቸውም፡፡ በሽተኞች ናቸው፡፡ ህጻናቱ ብርድ ላይ ናቸው፡፡ አምባሳደር ፍጹም  የኢትዮጵያ አምባሰደር በአሜሪካ የኢትዮጵያ አየር መንገድን አስፈቅደው ከቀረጥ ነጻ የገባውን ከፋንታሁን ሙጬ ጋር ተደራድረሽ ምንድነው ያደረግሽው? ወጥተሽ ለሕዝቡ አስረጂ! …ለሕዝቡ ይድረስ! ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ ችግር ካለ ችግሩን ተናገሪ!… ንብረቱ ኢትዮጵያ ከደረሰ ወር አለፈው፡፡ ችግረኞቹ አልደረሳቸውም፡፡ ምክንያቱ ምንድነው? ተናገሪ!…

የጴጥሮሳውያን ኅበረት የሚባል ተሞዳሟጅ የታከለ ኡማ አቃጣሪ የነበረ፤ በጥቅም ታስረው ቤተክርስቲያንን አሳልፎ የሰጠ፤ ፌክ ካህናት ሦስቱም ፤ቤተክርቲያንን አንገቷን እንድታቀረቅር ያደረጉ በዚህ ምክንያት ከመንግሥት ሹመኞች ጥቅማ ጥቅም የተሰጣቸው፤ የዘመኑ የቤተክህነት ሮናልዶዎች፤ ቅዱሳን ፓትርያርኮቹን ሊያለያዩ የተሾሙ የተቀመጡ፤ መርዞች፤ አንዴ እዚህ አንዴ እዚያ የሚያጫውቱ ተጠንቀቁ!!!…

40 ሚሊዮኑ ለባለጉዳተኞቹ ይድረስ…እኔ ኃላፊነት አለብኝ! አልቅሼ፣ አንቅልፍ አጥቼ፣ በጫካ፣ በመቃብር፣ በወንዝ በጀርመን ተንከራትቼ የለመንኩት ገንዘብ ነው፡፡ ይሄ ገንዘብ መንገድ ላይ እምዿ ቀሊጦ ብሎ እንዲቀር አልፈልግም!!!…ምሥራቅ ሐረርጌ አንድ ብር አልደረሳቸውም፡፡ ምዕራብ ሐረርጌ አንድ ብር አልደረሳቸውም፡፡ በቤተክርስቲያን ተጠልለው ያሉት የባንክ ቡክ ወጥቶላቸዋል፤ 37 ሚሊዮን ብር ወጥቷል የተባለው የት? ከየት? እንዴት? የእነማን? የለም!!! አልዋሽም !ምን አገባኝና ለየትኛው ዕድሜዬ ብዬ አልዋሽም፡፡ ታላላቅ ሰዎች እነ አቶ ትእዛዙ፣ እነ አቶ ብርሃን፣ እነ ወ/ሮ ኤልሳ የምትባሉ ተጠንቀቁ! ለራሳችሁ ስም ስትሉ ተጠንቀቁ!!! እውነት እንዲሠራ ግፉ!!! በዚህ ዓይነት አይደለም መዓት፤ አይደለም መቅሰፍት ሌላም ይገባን ነበር!…

ጴጥሮሳውያን የሚባል ማንም አይደለም…ጴጥሮሳውያን ውስጥ ያሉ በሙሉ የማኅበረ ቅዱሳን ልጆች ናቸው…ድጋሜ እናገራለሁ አሉላ ጥላሁን ወዳጄ ነህ፤ ወንድሜነህ እንዳትደውልልኝ!!! በሕዝብ ሁሉ ፊት ነው የምነግርህ እንዳትደውልልኝ! ስትደውልልኝ ደግሞ ያበጠ ነገር ይፈነዳል! ታደሰ ወርቁ ተሳስተህ እንዳትደውል! ስልክህን የማላነሳው ስለመላናግርህ ነው፡፡ሰለማልፈልግህ ነው፡፡ ጴጥሮሳውያን ኅብረቶች ነን የምትሉ በሙሉ ማለት ነው እንዳትደውሉ፡፡ አልፈልግም የማንንም መስማት አልፈልግም!!!… አንድ ሰው ስለ ጴጥሮሳውያን ኅብረት ቢያወራኝ አይመለከተኝም፡፡ ብሎክ ነው የማደርገው!!! ባለፈው ሽማግሌዎች ደውላችሁ ነው ያስቆማችሁኝ፡፡ ዳንኤል ክብረት እሪ ብለህ ነው ያስቆምከኝ፡፡ እነዚህ ነውረኞች!!! ባክህ ተዋቸው ዘመዴ ብለህ፡፡ የምተውበት ምክንያት ለካስ ለሌላ ጉዳይ ነው!!!…አንኗኗራትም ወይ ቤተክርስቲያኒቷ፤ ወይ እናንተ፤ ወይ እኛ አብረን እንጠፋታለን!!! እንዲሁ ተከድኖ ይብሰል የሚባል ነገር የለም፡፡ ፋንታሁን ሙጬ በፈጠረህ አምላክ ቤተክርስቲያኒቷን ዘላለም ስታደማት አትኑር! ከወ/ሮ እጅጋየሁ ጋር ሆነህ ስታደማት ኖርክ፤ ከነ በጋሻው ጋር ሆነህ ስታደማት ኖርክ፤ አሁን ደግሞ አታድማት ፋንታሁን ሙጬ በፈጠረህ አምላክ ተዋት! ተፋታት በቃ ቤተክርስቲያንን!!!

ፋንቱ ወልዴ.. የአሜሪካን ሕዝብ እኔ ነኝ የለመንኩት ፤ ክቡር አምባሰደሩን እኔ ነኝ የጠየኩት ቤተ ያሬድ ላይ ፤ መርካቶ ወስደሽ ሽጠሸውም ከሆነ ንገሪን፤ በየቀኑ እደውላለሁ አልደረሰንም ነው እያሉ ነው፡፡ ቤተ ክህነት ስደውል አለ ተቀምጧል እያሉኝ ነው፤ አረሳስታችሁ ልትሸጡት ነው፤ አዳዲስ ልብስ ነው፤ የሕጻናት ልብስ ነው፤ዳይፐር ነው፤ ሞዴስ ነው፤ ቤታቸው ንብረታቸው ተቃጥሎ ሜዳ ላይ ለወደቁት የአሜሪካ ሕዝብ የሰጠው ነው፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በነጻ ያስገባው ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ያለቀረጥ ያስገባው ነው፡፡ ክቡር አምባሳደሩን አቶ ፍጹምን እግዚአብሔር ይስጠው ረጅም ዕድሜ ይስጠው!!! የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኩራታችንን እግዚአብሔር ይስጠው!!! በጉምሩክ ላይ የሚሰሩትን እግዚአብሔር ይስጣቸው!!! ነገር ግን የእኛዎቹ ጉዶች ጉደኞች እናንተ መዓት ጠሪዎች የቤቱ ሸክሞች ሃይማኖት አሰዳቢዎች…መናጢ ሁላ፣ መናኛ ሁላ፣ተጠግተህ አንተ በደም ገንዘብ ልትከብር ትፈልጋለህ አፈር ብላ አትከብራትም…ሌቦች መዓተኞች የእናንተ መዓት ነው ይሄንን ሁላ የሚያመጣው…ለክሬ ነው የምሰራው ለማዕተቤ ነው የምሠራው ለየትኛው ዕድሜዬ ብዬ..

የቀረውን ከቪዲዮው ይከታተሉ

መስከረም 8 ቀን 2013 ዓ.ም

አማሳኞችና ቡድንተኞች በማኅበራትና በጎጥ ካባ፤ የሚፈጸሙት ደባ

ውድ አንባብያን እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ፍልሰተ ሥጋሃ ለማርያም፣ ለበዓለ ትንሣኤዋና ለበዓለ እርገቷ በሰላም አደረሳችሁ!!!

ቅድስት ቤተክርስቲያን የ40 ዘመን የዮዲት ጉዲትን ጭፍጨፋ፣ከ15 ዓመት በላይ የዘለቀ የግራኝ መሐመድ ጭካኔና ዘር የማጥፋት ዘመቻ፣በዚህ በእኛ ዘመን ደግሞ በአክራሪ ወሀቢስቶችና በየመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በተሰገሰጉ ፕሮቴስታንታዊ ጅሀዲስቶች ከሚደርስባት መከራ፣ስደት፣ ግፍና ጭካኔ ባልተናነሰ መልኩ ዛሬ ዛሬ ጥቅምንና ዘውግን መሠረት አድርገው በቤተክርስቲያን መዋቅር ውስጥ በተሰገሰጉ፤ መሠረተ እምነቷን፣ትውፊቷንና ቀኖናዋን ከአንገት አንጂ ከአንጀት በማይበቀሉ ሹመኞች እየደረሰባት ያለው ደባ፤ ተንኮልና የእናት ጡት ነካሽነት ተግባርበየጊዜው እንገታችንን እያስደፋን ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በርግጥ ቤተክርስቲያኒቱ በግለሰቦች ስብዕናና አመለካከት ላይ ያልተመሠረቱ ምዕመናንና ያለ ዕረፍት ስለቤተክርስያኒቱ የሚጸልዩ አባቶች ባለቤት በመሆኗ ዛሬ ድረስ በሕልውና ለመቆየት ችላለች፡፡

አሁን አሁን ግን ይህንን ሕልውናዋን የሚፈታተኑ ስሟን ተሸክመው ቤተክርስያንን በችግሯ እንኳ ስባሪ ፍራንካ የማይሉ፣ ምዕመኑን ግንባሩንና ደሩቱን ለሃይማኖቱ እንዲሰጥ ሲሰብኩ የሚውሉ፤ እነሱ ግን በችግር ጊዜ እንደ ዓይጥ በየስርቻው የሚወሸቁ፤ የግል ጥቅማቸውን ብቻ የሚሳድዱና ልክ እንደ መናፍቃኑ ድርጅቶች በቤተክርስቲያኒቱ ስም የግል አካውንት ከፍተው የሚንቀሳቀሱ ነገር ግን ስባሪ ሳንቲም ፈሰስ የማያደርጉ፤ የሚጎድልባቸው ጥቅም ብቻ የሚያስጨንቃቸው፤ በመዋቅሯ የማይፈተሹ፣ የማይመረመሩና ለሕጓም የማይታዘዙ፤ይባስ ብለው ደግሞ በቤተክርስቲያንና በምዕመኖቿ ላይ የሚደርሱ ሰቆቃዎችንና የጭቃኔ ተግባራት በምስል ወድምጽ በመቅረጽየተቸገሩ ምዕመናንና ገዳማትን እንረዳለን በሚል ሰበብበአካፋ ሰብስበው በሻይ ማንኪያ የሚያቃምሱ እንደ አሸን የፈሉ በርካታ አማሳኞችን ያቀፉ ማኅበራትና ቡድኖች መበራከታቸው  ብዙዎቻችንን እያስጨነቀ ያለ ጉዳይ ሆኖ ቀጥሏል፡፡

በእኔ እምነት ለዚህ ሁሉ ነገሮች ከዳረጉን አንዱ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የምትከተለው መዋቅራዊ አደረጃጀት ነው፡፡ ቅድስት ቤተክርስቲያን ሊኖራት የሚገባው መዋቅራዊ አደረጃጀት ሐዋርያዊ መሆን ሲገባው ሰባኪ መር፣አለቃ መር(ፓስተራዊ) መዋቅር መሆኑ በቤተክርስቲያኒቱከፍተኛ ችግር እያስከተለ መሆኑን በጉዳዩ ላይ የጠለቀ ዕውቀት ያላቸው ሙህራን ይገልጻሉ፡፡ በሐዋ 4፡32 ላይ ‹‹ያመኑትም ሕዝብ አንድ ልብ፤አንዲትም ነፍስ ነበሩአቸው፤ገንዘባቸውምሁሉ በአንድነት ነበረ…››  እንዲል ቅድስት ቤተክርስቲያንን አንዲት፣ ሐዋርያዊት  ሊያስብላት ከሚችሉ ነገሮች መካከል አንዱየገንዘብ አስተዳደሯ በአንድ ቋትና የሰው ኃይል አሰተዳደሯም የተማከለመሆኑ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ የሆነ አስተዳደራዊ መዋቅር ግን ሉተራዊ መዋቅር ነው፡፡ አንድ የእምነት ተቋም በሉተር ግላዊ አመለካከትና አስተሳሰብ ላይ የተመሰረተ ከሆነ የራሱን የግል ተቋም ከመሠረተ በኋላ የሰውም ይሁን የገንዘብ አስተዳደሩ በራሱ በሰባኪው(በፓስተሩ) እምነትና ፍላጎት የሚቀጥል ይሆናል፡፡ ዛሬም የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በዚህ ዓይነት አስተዳደራዊ መዋቅር ውስጥ የተዘፈቀች በመሆኗበውስጧ ያሉ የራሳቸው የግል አካውንት ፣ማኅተም፣ አስተዳደራዊ መዋቅር ያላቸው፤ምዕመኖቿንም በሚመቻቸው መልኩ የሚጠቀሙባቸውና የሚግጧቸው የግል ማኅበራትና የግል አብያተ ክርስቲያናት ቤቱ ይቁጠራቸው፡፡ ምናልባት ለአንዳንዶቻችን በማኅበር እየተደራጁ ስም ማጥፋትና ማሸማቀቅ (Character Assassination) አዲስ ነገር ሊመስለን ይችላል፡፡ ነገር ግን ይህ ድርጊት በንጉሡ ዘመን ነበረ፡፡ ይኸውም 50 በሚሆኑ ሆን ተብለው በተደራጁ ማኅበር ጠጪዎች አማካይነት በየመንደሩ እየዞሩ ስም የማጥፋት ዘመቻ በተለይ ደግሞ በቤተክርስቲያን ውስጥ ያልተመቿቸውና የማይገብሩላቸውን ጣፋጩን መራራ፤ መራራውን ጣፋጭ በሚያደርጉ የፊውዳል ባላባቶች ቤተክርስቲያን እረፍት እንዳታገኝ ይሠራ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች እውነተኞቹን የቤተክርስቲያን አባቶች እነ አቡነ ቴዎፍሎስን ሳይቀር የዛሬዎቹ ፌስቡከሮችና ብሎገሮች እንደሚያደርጉት የዛርና የዓይነ ጥላ መንፈስ ነግሶባቸው በየመንደሩ እየዞሩ ስም ሲያጠፉ የሚኖሩ ነበሩ፡፡ የዛሬዎቹም ስም አጥፊ ቡድንተኞችና ማኅበርተኞች ከእነዚህ ከግብር አባቶቻቸው በማኅጸን በተዋረሳቸው የዛርና የዓይነ ጥላ መንፈስ እንደሚንቀሳቀሱ እሙን ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በኤፌ 6፡12‹‹ ሰልፋችሁ ከሰማይ በታች ካሉት ከክፉዎች አጋንንትና ከጨለማ አበጋዞች ጋር ነው እንጂ ከሥጋዊ ከደማዊ ጋር አይደለምና›› እንዲል በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን 320 የሚደርሱ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ኪዳን የተቀበሉ ቅዱሳንን ጸሎትና ምልጃ ይዘን እነዚህ በጨለማ አበጋዞች ፤በዛርና በዓይነጥላ መንፈስ የሚዋጉንና ሁልጊዜ የጭቅጭቅ አጀንዳ በመፈበረክ ቅደስት ቤተክረስቲያንን የሚያውኩ የቤተክርስቲያን ነቀርሳዎች የሆኑ ቡድንተኞችንና ማኅበርተኞችን መዋጋት አለብን፡፡ ውድ ክርስቲያኖች ክርስቶስ ነጻ አውጥቶን ሳለ እስከ መቼ በጨለማ አበጋዞች እየተመራንና እየተበጠበጥን እንኖራለን?

በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን ወደ በርካታ የሆኑ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበራት ስብስብ እየተንደረደረች(accelerate) መሆኗን ብናውቅም ብዙዎቻችን ይሄንን ለማረም ከመነሳት ይልቅ የቤተክርስቲያን ቀዳዳ(ክፍተት) ተጠቅመን አዋጭ የሆነ፣ ታክስ የማይከፈልበት የግላችንን ማኅበር ለመመሥረት ያሰፈሰፍን መሆኑን ለመረዳት አሁን እንኳ በዚህ ‹‹የለውጥ አመራሩ›› ሀገሪቱን ከተረከበባት ጊዜያት በኋላ ለቤተክርስቲያንና ለምዕመናኑ ችግር አለሁ ቆሜአለሁ በማለት የተመሠረቱትን በርካታ ‹‹ኅብረቶች›› መለስ ብሎ ማየቱ በቂ ነው፡፡

ከሁሉ የሚገርመው ደግሞ በየጊዜው ለቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ ሆነው ከሚነሱ እያንዳንዱ ማኅበራት ጀርባ የማይቀሩ ግለሰቦችና ማኅበራት መኖራቸው ነው፡፡ እስቲ ሩቅ ሳንሄድ ቋሚ የአደጋ ጊዜ መፍትሔ አፈላላጊ ማኅበራትን ትተን ወደ ኋላ መለስ ብለን በሱማሌና በሐረሪ ክልል በቤተክርስቲያን ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ግፍ ተከትሎ እስካሁን የተመሠቱ ማኅበራትንና ቡድኖች በህሊናችሁ አስባችሁ በእነ ማን ተመሠረቱ? ከተመሠረቱ በኋላ ለቤተክርስቲያኒቱና ለምዕመናኑ ምን ፋይዳ አመጡ? አንዱን ማኅበር ከማጠናከርና ከማጎልበት ይልቅ ችግር በተፈጠረ ቁጥር አዲስ ማኅበር ለመመሥረት ጥድፊያና ግርግር ለምን አስፈለገን? የሚሉትን ጥያቄዎች ማንሳቱ ለአንቅሆ ያግዘን ይሆናል፡፡

ከላይ ለመጠቆም እንደሞከርኩት የቤተክርስቲያኒቱ በንጉሡ አጼ ኃ/ሥላሴ ዘመን ከሲሶ መንግሥት ባለድርሻነት መነቀልን ተከትሎ ለተፈጠረው መደናገጥ መፍትሔ ይሆን ዘንድ በአቡነ ቴዎፍሎስ አነሳሽነት የተተገበረው ቃለ ዐዋዲ ጊዜያዊ መፍትሔና እፎይታ ቢሰጥም ዘለቄታዊ ችግርን ግን የሚፈታ ሊሆን አልቻለም፡፡ በወቅቱ እነ አቡነ ቴዎፍሎስ ቃለ ዐዋዲው ጸድቆ እንዲተገበር በማድረግ በፍጥነት የወሰዱት የመፍትሔ እርምጃ ቤተክርስቲያኒቱን ከመውደቅ ለማዳን ችለዋል በዚህም እጅግ ሊመሰገኑ ይገባል፡፡ ምንም እንኳ አንዳንዶች ቃለ ዐዋዲውን ለቤተክርስቲያኒቱ ችግር ዘላለማዊ መፍትሔ አድርገው ቢያስቡም በወቅቱ ከነበሩ ሰዎችና የታሪክ ድርሳናት መረዳት የሚቻለው ግን ቃለ ዐዋዲው መሠረት ያደረገውና በከፊል የተቀዳው ከፕሬስባይተርያን (presbyterian)ና ከአንግሊካን (Anglican) ቤተ እምነቶች መዋቅር  በመሆኑ ፓስተራዊና ተዋረዳዊ አደረጃጀትን የተከተለ እንዲሆን ሆኗል፡፡በዚህ ላይ ደግሞ ንቡረ እድ  ኤርምያስ ከበደ ‹‹ኢትዮጵያ የዓለሙ መፋረጃ!›› በሚለው መጽሐፋቸው ከገጽ 423-425 ‹‹…ከጽንሰ ሓሳቡ አንስቶ፣ ደንቡንና ማብራሪያውን በጽሑፍ አርቅቆ እስከመቅረጽ ፤ከዚያም አስፈቅዶ በአዋጅ እስከማውጣትና በሥራ ላይ ያደረሰው እኔን ትሑት አገልጋዩን መሣሪያ አድርጎ መሆኑን…›› በማለት የገለጹትና ሙሉ ለሙሉ ልፋቴን ለአቡነ ቴዎፍሎስ ተሰጠብኝ የሚለውን ቅሬታቸውን ደምሮ ማየቱ ለብዙ ነገር ይጠቅማል፡፡ በአጠቃላይ ቤተክርስቲያን በዚህ ሕግ ምክንያት ሐዋርያዊ መዋቅር ከመከተል ይልቅ ሕዝባዊ ወይም ተዋረዳዊ ሆነች፡፡ በመሆኑም ቤተክርስቲያኒቱ ሁለት ዓይነት የማይሰናሰሉ አደረጃጀቶች እንዲታይባት ሆኗል ከላይ ቅዱስ ሲኖዶሱ ሐዋርያዊ ትውፊት የሚከተል ሲሆን እታች ያለው ሕዝባዊና እንደ ፓስተሮች በግለሰቦች ላይ የተደገፈ አደረጃጀት ነው፡፡ በዚህም ዛሬ ያሉን ማኅበራትም ከአስተዳደር አንጻር ዘመናዊ ፓስተራዊ አካሄድን የሚከተሉ የኦርቶዶክስ ተሐድሶዎች ናቸው ብሎ በድፍረት መናገር ይቻላል፡፡ ይህን እንድል ያስቻለኝ ገፊ ምክንያት ደግሞ ማኅበራት ከቤተክርስቲያኒቱ ጋር በምንም መልኩ ያልተሳሰረና ያልተሰናሰለ መዋቅራዊ አደረጃጀት ያላቸውና ቤተክርስቲያኒቱም የማትቆጣጠራቸውና የማታዛቸው አባላትን ያቀፉ፤ በገንዘብ አስተዳደርም ቤተክርስቲያኒቱ የማታዝበት፣የማትቆጣጠረውና የማትመረምሩ የራሳቸው የግል የባንክ ሒሳብ ባለቤቶች በመሆናቸው ናቸው፡፡ ከዘህም በተጨማሪ ማኅበራት በአደጋ ጊዜ የሚለቁት ለእርዳታ የሚሆን ገንዘብ ወደ ሂሳባችን አስገቡልን ማስታወቂያ ከቤተክርስቲያኒቱ ጋር የፉክክር መንገድ ላይ ያሉ እንጂ ቤተክርስቲያኒቱን ለመደገፍ የተቋቋሙ አይመስሉም፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆነው ከዚህ በታች ያለው የእርዳታ ማሰባሰቢያ ማስታወቂያ ነው፡፡

ቃለ ዐዋዲው በተመለከተ በርግጥ በርካታ መልካም ነገሮች ቢኖሩትም የቤተክርስቲያን አይጦችን በተመለከተ ግን መያዣ መጨበጫ ላሳጣን ውንብድና ዝርፊያ እንዲመቻቸው ያደረገና በሥሯ አለን የሚሉ ማኅበራትም ከአስተዳደር አንጻር ፓስተራዊ አካሄድን እንዲከተሉና ኦርቶዶክሳዊ ተሐድሶዎች እንዲሆኑ ያደረጋቸው ይሄው ቃለ ዐዋዲው እንደሆነ አፍን ሞልቶ መናገር ይቻላል፡፡

ለመሆኑ በቃለ ዐዋዲ የሚታዩ አስተዳደራዊ ክፍተቶች ምን ችግር እያመጡብን ነው?

በአንድ ወቅት በአውሮፓ እንደ አሸን ፈልተው የነበሩ የፕሮቴስታንት አብያተ እምነቶች የከሰሙትና ቤተ አምልኮዎቻቸውም ወደ ጭፈራ ቤትና ሙዚየም የተቀየሩት በሚከተሉት ፓስተራዊ(ሰባኪ መር) መዋቅር ምክንያት መሆኑ አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንም የሚታየው አስተዳደራዊ መዋቅር ከላይ ሐዋርያዊ፤ ከታች ደግሞ  ፓስተራዊ(ሰባኪ ወይም አለቃ መር) ቢሆንም ያለወደቀችውና በከበቧት ፈርጀ ብዙ ችግሮች እየተንገታገተች የቆየችው ከግለሰቦች ይልቅ በትክክል በእግዚአብሔር የሚያምኑና የሚታመኑ፤ በቅዱሳን ምልጃና ጸሎት የሚደገፉ መልካም፣ሩህሩህና ቸር የሆኑ፤ ሳይኖራቸው ለቤተክርስቲያን ችግር ነፍሳቸውን እንኳ ሳይሳሱ ያለንፍገት የሚቸሩ፤ ከአገልጋዮች ይልቅ በተሻለ መንፈሳዊ ልዕልና ላይ የሚገኙ ምዕመናን ባለቤት በመሆኗ ነው፡፡ይህ መዋቅራዊ ችግራችን በጊዜው ተፈትሾ ተገቢው እርምት ካልተደረገበት፤ ተገቢውን ትኩረት ያልሰጠነውና ሁሉን ተደራሽ ማድረግ ያልቻለው የወንጌል አገልግሎታችን፤ ስለ ምዕመናን ሁለንተናዊ ሕይወት መሻሻል አለማሰባችንና ደንታ ቢስነታችን እየተጓዝንበት ያለንበትን የቁልቁሊት ጉዞ ከማፋጠኑም በላይ ዋና ሥራችንና መደበኛ ጉዳያችን አድርገን ተተብትበን የተያዝንበት በቡድንተኛ ዘራፊዎችና አማሰኞች ጉዳይ መጨቃጨቅ፣ ዩኒፎርም ለብሶ ሰልፍ መውጣት፣ቢሮ ማሸግ፣ በየብሎጉና ማኅበራዊ ሚዲያው መጠዛጠዝ በዚሁ ከቀጠለ ያለምንም ጥርጥር በርካታ ምዕመናንን መጣታችንና እየጣሉን መውጣቸው አይቀርም፡፡

ከዚህ ቀጥሎ ይሄ ፓስተራዊ(ሰባኪ ወይም አለቃ መር) የሆነ መዋቅራዊ አስተዳደራችን ያስከተለውን ችግርና በማኅበራት ካባ በቤተክርስቲያን የሚፈጸመውን ደባ እንመልከት፡-

ማሳያ አንድ(scenario1) -በውጪ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ጉዳይ

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያ በዲያስጶራው ዓለም መስፋፋቷ እጅግ አስፈላጊና ጌታችን በማቴ 28፡19 ‹‹ሑሩ ወመሀሩ ኵሉ አሕዛበ…›› ብሎ ያዘዘውን ታላቁን የቤተክርስቲያን ተልኮ ለመፈጸም የሚያስችላት ነው፡፡ ለዚህም ታላቅ ተልዕኮ አጅግ ከባድ በሆነ የአኗኗር ሁኔታ ውስጥ አንኳ ሆነው የደከሙና የሚደክሙ ንጹሐንና እውነተኛ ብጹዓን አባቶች፣ካህናት፣የሰ/ት/ቤት ወጣቶችና ምዕመናን ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

በአንጻሩ ደግሞ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በውጭው ዓለም ያላት ባለቤትነት ለይስሙላ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ለምሳሌ በሰሜን አሜሪካ ከ10 የማያንሱ አህጉረ ስብከቶች ያሉ ሲሆን በእነዚህ አህጉረ ስብከቶች የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት በአብዛኛው በቻሪቲ ስም በግለሰብ ማለትም የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሆኑ ቅዱሳንና ብጹዓን አባቶች በግል ስማቸው ሳይቀር፣በቦርድ አሊያም በሆነ ጎጥ ስብስብ የተመዘገቡ፤አንዳንዶቹ ደግሞ በማን ስም እንደተመዘገቡ የማይታወቁና ሲብስ ደግሞ ብጹአን አባቶች ለይስሙላ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ይባሉ እንጂ የማያዙባቸውና የማያስተዳድሯቸው ናቸው፡፡ ቀሳውስቱም፣ዲያቆናቱም ሆኑ ምዕመናኑ የአገልግሎቱ ተሳታፊዎች እንጂ ባለቤቶች አይደሉም፡፡ በአንድ ወቅት በዚሁ በአማሪካን ሀገር የቅዱስ ዑራኤልን ታቦት ለመትከል ፈቃድ ሲጠየቅ በዚህ ስም ቀድሞ በአንድ ግለሰብ ስም የተመዘገበ ታቦት ስላለ አይቻልም መባሉን አስታውሳለሁ፡፡ ታዲያ ከዚህ በላይ ኪሳራና ዝቅት ምን አለ?

ከዚህ በላይ ደግሞ ሰሞኑን አንዳንድ መምህራነ ወንጌልና ፌስቡከሮች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን 2ኛ ዓመት የሰላምና የአንድነት ጉባኤ በሚል የዳቦ ስም ጥናታዊ ጽሑፍ ሲያቀርቡ በቴሊቭዥንና ማኅበራዊ ድረ ገጽ ዜና አድርገው ሲያሠራጩ በዚህ የዳቦ ስም  ሲደሰኩሩ ስመለከት አእምሮዬ በጥያቄ ይናጥ ገባ፤ እውነት እውነቱን እንነጋገር ከተባለ፤ የሰላምና አንድነት ጉባኤ ምንድነው? በየትኛው ጉዳይ ነው አንድነት ያለን? በአስተዳደራዊ መዋቅሩ ነው? በሀብትና ንብረቱ? በአብያተ ክርስቲያናቱ? ወይስ በአገልጋዮቹ? ምነው ባናሾፍ!!! እኔ የማምነው በዓሉ መከበር ካለበት ‹‹ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዮስ፣ብጹዓን አባቶችና ፖለቲከኞ ወደ ሀገር የተመለሱበት 2ኛ ዓመት›› ተብሎ መሆን እንዳለበት ነው፡፡ከበፊቱ የተለወጠው አዲሱ ነገር እኮ የብጹዓን አባቶች አንድ ላይ ለስብሰባ መቀመጥና ጥቂት አባቶች እነ አቡነ መቃርዮስን የመሳሰሉ ምነው እስካሁን አብረውን ቢኖሩ ብለን የምንቆጭባቸው የወንጌል ገበሬ፣ እውነተኛና ጀግና አባቶች አገር ውስጥ በሚገኙ ሀገረ ስብከቶች መመደባቸው ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ አንድነት አንድነት እያልን ብናቆለጳጵሰው ጥናታዊ ጽሑፍ አይደለም መጽሐፍ ብናሳትምለት እስካሁን ፍፁምና አማናዊ አንድነት ማለትም አስተዳደራዊ፣ መዋቅራዊ፣ በገንዘብና በሰው ኃይል አንድነት ስሌለን ራሳችንን ማታለል አቁመን መራራም ቢሆን ይህንን እውነት ልውጠው ይገባል!!!

ስለዚህ አማናዊ የሰላምና የአንድነት ጉባኤ ማክበር እንድንችል ሁለንተናዊ አንድነትን(በአስተዳደር፣በመዋቅር፣በሰውና በሀብት አስተዳደር) በጥናት ላይ ተመሥርተን ብናረጋግጥና በቻሪቲ ማዕቀፍ በግለሰቦች ስም የተመዘገቡትንና የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የማታዝባቸውን ንብረቴ ብላ ያልተመዘገበቻቸውን አብያተ ክርስቲያናት ከየሀገራቱ መንግሥታት ሕገ መንግሥት ጋር የሚናበቡ ሕገ ደንቦችን አዘጋጅቶ በማቅረብ አብያተክርስቲያኒቱን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስም የማስመዝገብ ሥራ ብንሠራ በወርቅ ቀለም የሚጻፍ፤ ታሪክ የማይዘነጋው ሥራ ከመሆኑ ባሻገር የሰላምና የአንድነት ጉባኤያቱ በዳቦ ስማቸው ሳይሆን አማናዊና ያማሩ ሆነው በሁላችንም ዘንድ እንዲከበሩ እድል እናገኛለን ማለት ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ሳይነሳ መታለፍ የሌለበት ጉዳይ ጎጥንና ቡድንተኝነትን መሠረት ያደረጉ በውጩው ዓለም ያሉ ‹‹ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን›› የሚለውን ከአንገት እንጂ ከአንጀት የማያምኑ ተከፋፍለው በጎሪጥና በጥንቃቄ እየተያዩ የሚኖሩ አብያተ ክርስቲያናት ጉዳይ ነው፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ የሚታወቁት ክፍፍሎች በሀገር ውስጥ ሲኖዶስ ሥር ያሉ ፣ በውጪው ሲኖዶስ ሥር ያሉ እና ከምን እንደደሆነ ገለልተኝነታቸው ባይታወቅም ‹‹ገለልተኛ›› ነን የሚሉ ሦስት ክፍፍሎች ናቸው፡፡  አራተኛው ግን ማህበራዊ ሚዲያውንና መገናኛ ብዙኃኑን በተቆጣጠሩ አባላቶቹና ደጋፊዎቹ ተሸፋፍኖና  የቆየውና ተደበስብሶ የኖረው በማኅበረ ቅዱሳን የዲቪ ፕሮግራም ተጠቃሚ በሆኑ ግለሰቦች የተመሠረቱ ‹‹የማኅበሩ አብያተ ክርስቲያናት›› ናቸው፡፡ የእነዚህ አብያተ ክርስቲያናት መሥራቾቹ ሀገር ውስጥ እያሉ በስብከታቸውና በሕይወታቸው የብዙዎቻችንን ቀልብ ገዘተው የኖሩ ስለነበሩ ወደ ውጪ ሀገር ሲሄዱ ለቤተክርስቲያን አንድነት ይሠራሉ ብለን ብዙዎቻችን ተስፋ አድርገን ነበር፡፡ ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆነና በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ እንዳለመታደል ሆኖ እነሱም እየተደራጁ አራተኛው ክፍፍል መሥርተው ቁጭ አሉ፡፡ እነዚህ አብያተ ክርስቲያናት መሥራቾቹን ከፓርኪግ፣ ከሱፐርማርኬትና ከታክሲ ሥራ ከመታደጋቸው በላይ ለዲቪ ተጠቃሚዎች የኑሮ መሠረትና የሀብት ምንጭ፣ ለሌሎች ደግሞ ማለት የማኅበሩ የዲቪ ወረፋ እስኪደርሳቸው ድረስ ወደ ሀገረ አማሪካ ለሚመላለሱ ሰባኪያን ለኑሮ መደገፊያና ማረፊያነትና በማገልገል ላይ ናቸው፡፡ እነሱን ለምን ይቅርባቸው? ደግ አደረጋችሁ!!

በነገራችን ላይ ከዚህ የጡመራ መድረክ አባላት መካከል እስካሁን ከማኅበሩ ጋር ብሆን የዚህ ዲቪ ተጠቃሚ እሆን ነበር ብለው የሚቆጩ አልጠፉም፡፡ ታዲያ ይሄንን ሁሉ ጉድ ይዘን ስለ አንድነት ማውራት አያሳፍርም?

ማሳያ ሁለት (scenario 2)፡-በሕጋዊ መንገድ የተመዘገቡና በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያ ስም የሚንቀሳቀሱ ማኅበራት ጉዳይ

እነዚህ ማኅበራት የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ያለባትን ቀደዳ ለመድፈንና አገልግሎቷን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሻገር ታስበው የተቋቋሙ ናቸው፡፡ ጊዜያት እያለፉ ሲመጡ ግማሹቹ በታሰበው ልክ አገልግሎት የማይሰጡ፤ ሎሎቹ ደግሞ ሸክም እየሆኑ፤ ቀሪዎቹ ደግሞ በቤተክርስቲያን ሀብትና ንብረት ጡንቻቸውን አፈርጥመው ብጹዓን አባቶችን ሳይቀር በቁጥጥራቸው ሥር በማዋል ራሳቸውም ይሁኑ ከእነሱ ተገንጥለው በወጡ አባሎቻቸው የቤተክርስቲያንን አገልጋዮችና ምዕመናን እያስፈራሩና እያሸበሩ የሚኖሩ፤ በሚፈጠሩ ግርግሮች ሁሉ የቤተክርስቲያንን ሀብትና ንብረት ለግል ጥቅማቸው የሚያጋብሱ ሆነዋል፡፡

አነዚህን ጉዳዮች የበለጠ አፍታቶ ለማሳየት በቤተክርስያን ስር ከተቋቋሙ ማኅበራት መካከል ማኅበረ ቅዱሳንን እንደ ማሳያ አሁን ካለበት የአገልግሎት ቁመና አንጻር በወፍ በረር እንቃኘው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ከቤተክርስቲያን የአገልግሎት ፈቃድ ያገኘው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ ሥር ሆኖ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ከቤተክርስቲያኒቱ አገልጋዮች ጋር በመሆን ለማስተማር ነበር፡፡

አሁን ግን ጡንቻውን በማፈርጠሙና አቅሙን በማጎልበቱ የሌለበትና የማይገባበት የአገልግሎት ዘርፍ የለም፡፡ ከዚያ ባለፈ ለረጅም ጊዜያት የማኅበሩ ሀብትና ንብረት  የቤተክርስቲያን ሀብትና ንብረት ነው እያለ ሲሰብከን የቆየ ቢሆንም በኋላ ግን በእነ አባ ሰቀ የሚደረገው ዘመቻ እየከበደ በመምጣቱና የገባበት ፍጹም የሆነ ንግድ ሥራ አዋጭና አጓጊ ስለነበር የሀብትና ንብረት ማሸሽ ድርጊት ውስጥ ተዘፈቀ፡፡ ለዚህ እንደ አንድ ማሳያ የሚሆነው የአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤትን ወደ ሽርክና ማኅበር(Privatize) ከዚያም ወደ ንግድ ድርጅት እንዲገባ ያደረገበት መንገድ ነው፡፡ የአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት ሲቋቋመ የነበረው ሰበካ አሁን ድረስ ይገርመኛል፡፡ የወላጅ ስስ ብልት ላይ ትኩረት ያደረገ ዲስኩር ‹‹ልጆቻችን ሙስሊምና ጴንጤ ት/ቤት ለማስተማር እየተገደድን ነውበዕውቀት የበለፀገ፤ በሥነ ምግባር የታነፀ፤ በኢትዮጵያዊ ማንነቱና መልካም ባህሉ የሚኮራ ትውልድ ማፍራት…ብቻ ያልተባለውን ጠይቁኝ፡፡ ዛሬስ? አባቴ ደህና ደሞዝ ተከፋይ ወይም ሙሰኛ አሊያም ባለጠጋ ካልሆንክ አቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት ልጆችህን ለማስተማር ማሰብ ዘበት ነው፡፡ እንዲያውም አንዲት ወዳጄ አሁን በቅርብ ደውላ እባክህ ማኅበሩ ላይ የምታውቃቸው ሰዎች ካሉ እባከህን በብር(እጅ መንሻ መሆኑ ነው) ይመዘግባሉ የሚባል  ስለሰማሁኝ ነው ብላኝ እርፍ፡፡ አቤት ውርደት! ብዬ እጅግ በጣም አዘንኩ፡፡ መራራ ፍሬ ይልሃል ይሄ ነው፡፡ በዚህ ሰዓት ት/ቤቱ ሙሉ በሙሉ በማኅበሩና በግለሰቦች ሼር ለተመሠረተው ለኤስድሮስ የኮንስትራክሽን፤ ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ተላልፏል፡፡ በዚህ መልክ በየማኅበራቱ የቤተክርስቲያን ናቸው ተብለው ሲሰበኩልን የነበሩ ሀብትና ንብረቶች ስንቶቹ ተላልፈው ይሆን?

የአባላቱን ጉዳይ ስንመለከት በዚህ ቡድን ግምገማ መሠረት ማኅበሩ እስካሁን ያፈራቸው አባላትን በሦስት ከፍለን ማየት እንችላለን፡፡ ይኸውም፡-

  1. ጳውሎሳውያን፡- ቅዱስ ጳውሎስ በ1ቆሮ 11፡28 ‹‹ የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው፡፡›› እንዲል ከ50 በመቶ በላይ የሚሆኑት ማኅበሩ ያፈራቸው አባላት ከሁሉ ነገር በፊት ቤተክርስቲያንን አስቀድመው በማኅበሩ በኩል ተገቢውን አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ናቸው፡፡ እነዚህ አባላት ከአሳዳጅነት፣ከሥልጣን ጥምና ከሴረኝነትም የጸዱ ብርቅዬ የቤተክርስቲያን ልጆች ናቸው፡፡ እነዚህ አባላት ምንም እንኳን የማኅበሩ ከሃሳብ መሪነት ማፈግፈግና መስሎ አደር ቤተ ክህነታዊ ጠባይና መልክ እየተላበሰ መምጣቱን ቢያውቁም ቤተ ክርስቲያንን ወደ ከፍታ ሊያመጡ የሚችሉ ሃሳቦችን በማመንጨት በማኅበረሰቡ ውስጥ አስርጾ ተገቢ ለውጥ እንዲመጣ በማድረግ ማኅበሩ ከተለመደው ዓይነት መሥሪያ ቤታዊ የአሠራር ሂደት እንዲወጣ የሚጥሩና የሚለፉ ናቸው፡፡ ምንም እንኳን ለጫናዎቹ መፈጠር ዋነኛው ምክንያት ራሱ ማኅበሩ ቢሆንም ማኅበሩ በአሁኑ ጊዜ ከውጭም ከውስጥም ከፍተኛ ጫናዎች እንዳሉበት ይታወቃል፡፡  እነዚህ አባላት ግን እነዚህን ጫናዎች ተቋቁመው፣ ብሎም ረትተው ለማለፍ የሚታገሉ አንዳንዴ ደግሞ የትላንቱን ውጤታማ የማኅበረ ቅዱሳን የአገልግሎት ጊዜያት በማሰላሰል ነገ የተሻለ ጊዜ ይመጣል ብለው የሚተጉና የሚያልሙ ናቸው፡፡
  2. ሳውላውያን፡- ቅዱስ ጳውሎስ በገላ 1፡3 ‹‹ በአይሁድ ሥርዓት በፊት እንዴት እንደኖርሁ ሰምታችኋልና፤ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ያለ ልክ አሳድድና አጠፋ ነበር፡፡›› እና ቅዱስ ሉቃስ በሐዋ 7፡60 ‹‹ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር፡፡›› ብለው እንደገለጹልን ምናልባት ከ30 እስከ 40 በመቶ የሚሆኑት ማኅበሩ አንከን አልባ፣ ጥፋት ቢኖርበት እንኳ ያለ ንስሐ መኖር እንዳለበት የሚያምኑ፣ ማኅበሩን በጥፋቱ የሚወቅሱና የሚገስጹ ሰዎች ቢገጥሟቸው በነፍሳቸው ተወራርደው ወደ ኋላ የማይሉ፤ ቀፎው እንደተነካ ንብ ግር የሚሉ፤ ስለ ማኅበሩ ሲሉ በድንጋይ ከመውገርና ከማስወገር ወደ ኋላ የማይሉ ለዘብተኞችና ጭፍን ደጋፊዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች መ/ር ዘመድኩን እንደሚለው አፈ ጻዲቆችና አውርቶ አደሮች፤ ከቅድስት ቤተክርስቲያን ይልቅ ለማኅበራቸው ሟቾች ከመሆናቸው በላይ ለእነሱ ቤተክርስቲያን ማለት ማኅበረ ቅዱሳን፤ ማኅበረ ቅዱሳን ማለት ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡እነዚህ አካላት ማኅበሩ ብቻ በቤተ ክህነቱና በቤተክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ አውራ ድርሻ ይዞ እንዲቀጥል የሚመኙና የሚሠሩ ናቸው፡፡ሳውላውያን በቤተክርስቲያን ጉዳይ ከአንድ ሊቀ ጳጳስ ይልቅ የማኅበሩ አመራር አባል በቤተክርስቲያን ጉዳይ ወሳኝ መሆኑን የሚያስቡ ናቸው፡፡ እነዚህ አካላት ግቢ ጉባኤንና የማኅበሩ ጽ/ቤት እንጂ በአካልም ይሁን በተግባር የቅድስት ቤተክርስቲያን መዋቅሮች የማይረዱና ተሳትፈውም የማያውቁ ምስኪኖች ናቸው፡፡ ውስጣቸው ሳውላዊ ቅናት ብቻ ነው ያለው፡፡እነዚህ አባላት ማኅበሩ ከቤተ ክርስቲያኒቱ የተቀበለውን ግቢ ጉባኤያትን የማብቃት ሚናውን በአግባቡ ባለመወጣቱ ምክንያት የተገኙ ናቸው፡፡እነዚህ አካላት የውስጡ ችግር ሲባባስ መከረኛውን ተሐድሶ እያነሡ የአባላቱን እና የምእመናኑን ቀልብ በማሳት መኖር የሚፈልጉ ናቸው፡፡  እነዚህ አካላትን ማለት ማኅበሩ ሳይኖር ቤተክርስቲያን እንደ ነበረች፣ ነገም ማኅበሩ ባይኖር ቤተክርስቲያን እንደምትኖር ማስተማርና መመለስ ካልተቻለ አካሄዳቸው ለማኅበሩም ይሁን ለቤተክርስቲያን አደገኛ ነው፡፡
  1. ድዮጥራጥሳውያን፡- እነዚህ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ በመልእክቱ  3ኛ ዮሐ 1፡9  ‹‹ወደ ቤተክርስቲያን ጻፍሁ፤ ዳሩ ግን ዋናቸው ሊሆን የሚወድ ዲዮጥራጥስ አይቀበለንም፡፡ ስለዚህ እኔ ብመጣ በእኛ ላይ በክፉ ቃል እየለፈለፈ የሚያደርገውን  ሥራውን አሳስባለሁ፤ ይህም ሳይበቃው እርሱ ራሱ ወንድሞችን አይቀበልምሊቀበሉአቸው የሚወዱትን ከልክሎ ከቤተክርስቲያን ያወጣቸዋል፡፡›› ይላል፡፡  

ዲዮጥራጥስ ቅዱስ ዮሐንስን በሚያህል ታላቅ ሐዋርያ የተነቀፈው ስለ ሦስትጉዳዮች ነው፡-

  • ሐዋርያትን ያለ ጥሪው ሹሙኝ ብሎአቸው አይሆንም ብለውታል፡፡ ሐዋርያትን የበቃውን ያልበቃውን አያውቁ ብሏቸው ነቅፏቸው ሔዷል፡፡(ለሥልጣን ጥም ሲል ነቃፊ ነበር)
  • በእነሱ ላይ የሚናገረው ክፉ ልፍለፋ ሳያንሰው ሌሎችን አትቀበሏቸው እያለ ያሳድም ነበር(አድመኛና አሉቧልተኛ ነበር)
  • ሐዋርያትን የሚቀበላቸውን ከቤተክርስቲያን ያስወጣ ነበር(አሳዳጅና የድኅነት እንቅፋት  ነበር)

ይሄኛው ምድብ ከ5 እስከ 10 በመቶ የማይበልጡት ማኅበሩ ያፈራቸው አባላት ለምሳሌ እልፍኝ አስከልካይ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት፣ እስትንፋሰ ዲያብሎስ ዲ/ን ታደሰ ወርቁ፣ የአማሪካው ክንፍ አደራጁ፣ የፖለቲካ ተንታኙና ቄሱ ኤፍሬም እሸቴ፣ ሐራዊውና ዲጄው አሉላ ጥላሁንና መሰሎቻቸውን የሚይዝ ክንፍ ነው፡፡ እነዚህ አካላት እነሱ ቀብተው ያሾሙት ካልሆነ በቀር ሌሎቹን የቤተክርስቲያን አባቶች የማይቀበሉ፣ሥልጣናቸውንና ጥቅማቸው የሚጋፋ ከመሰላቸው ታፔላ በመለጠፍ ንጹሐን የቤተክርስቲያኒቱን አገልጋዮችን በሐሰት የሚወነጅሉ፣የሚያሳድዱና ሌሎችም እንዳይቀበሏቸው በከፍተኛ ትጋት የሚሰሩ የዘመናችን ዲዮጥራጥሳውያን ናቸው፡፡እነዚህ አገልጋዮች ዛሬ ላይ ከምንደኝነት ወደ አደገኛ ማፍያነት ተሸጋግረዋል፡፡ ሌሎቹን ትቼ ለዚህ ማሳያ የሚሆኑ ሁለት የቅርብ ጊዜ ክስተቶችን ላቅርብ፡-

ክስተት 1

በሰኔ ወር ውስጥ ጮሌው ታዴ አንድ ቀን አንዱን የፈረደበት አባት ለማስፈራራት ይሁን ለማስረዳት በውል ባልረዳውም ብጹዓን አባቶች መኖሪያ አከባቢ ሲንከለከል አንድ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ሊቀ ጳጳስ ብቻውን ያገኙትና ‹‹ይሄኔ የእኛ ጉዳይ ቢሆን ያዙኝ ልቀቁኝ ብላችሁ ሀገር አይበቃችሁም ነበር፤ የእነሱ ሲሆን ግን ትንፍሽም አላላችሁም…›› ብለው በነገር ሸንቁጠውት ለመናገርም እድል ሳይሰጡት ወደ ቤታቸው ይገባሉ፡፡ ያ ወቅት ደግሞ ሦሰተኛው ፓትርያርክ ማለት የቅባቴዎቹ የተሾመበት ጊዜ ነው፡፡ እውነታቸውን እኮ ነው ወላ ምንደኞቹ ሐራዎች፣ዲዮጥራጥሳውያኑም ይሁኑ ፌስቡከሮች ስለዚህ ጉዳይ ትንፍሽ አላሉም፡፡ ምክንያቱም ጉዳዩ ወደ አደባባይ ተጋኖ እንዳይወጣ ስለተፈለገ፤ ቅባቴ በሆኑ ጳጳሳት ጠያቂነት ማለት እኛ በሽምግልና እንይዘዋለን ስላሉ ተከድኖ እየበሰለ ነው፡፡ እኛ እኮ ጉደኞች ነን የዶግማ ጥሰትን በሽምግልና??? ይገርማል እኮ እናንተዬ!!!  ወደ ፊት በዚህ ጉዳይ ከአዲስ አበባ እስከ ጎጃም የጀመርነውን ጥናት ስንጨርስ በዝርዝር ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡

እናላችሁ ታዴ ሆዴ በሊቀ ጳጳሱ ተገቢና ወቅቱን የጠበቀ ተግሳጽ አያበደ፣ እየተወራጨና እየተንጨረጨረ ደረጃ ሲወርድ ቀሲስ ሰሎሞን ቶልቻን ያገኝና ‹‹ እገሌ ጳጳስ ማን ስለሆነ ነው የሚናገረኝ? እሰራለታለሁ!...ምናምን እያለ ጳጳሱን ያገኛቸው ያክል ጨፈረበት፡፡ ይህን ጉዳይና እነዚህ ወንደሞቻችን የሚሠሩትንና ያሉበትን ሁኔታ ለአፍታ ሳስብ ወደያው ትዝ የሚሉኝ የየኋቸውና የነበብኳቸው የማፍያ ፊልሞችና መጻሕፍት ናቸው፡፡ በርካታ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች እነዚህ አካላት ታላቁ አባት አቡነ ጎርጎርዮስ የሚያስወቅሱ ሙት አስወቃሾች ናቸው በሚለው ይስማማሉ፡፡ ብጹዕነታቸው እነዚህ ሰዎች በሚሰሩት ነውርና በስማቸው መነገዳቸውን ሲያዩ ነፍሳቸው ምን ትል ይሆን ? ለቅጽበት ተነስተው ቢያገኟቸው ምን ይሏቸው ይሆን? ብለው የሚጠይቁ ብዙዎች ናቸው፡፡

እነዚህ አካላት ልክ እንደ ዲዮጥራጥስ ሹመት ተከልክለው ለራሳቸው የማይገባቸውንና ባልዋሉበት ሥልጣንና ሹመት ሲወስዱ እንደነ በጋሻው መጋቤ ሐዲስነቱን ከየት አምጥቶት ነው ብሎ መውቀስ ክልክልም ነውር ነው እንዴ? እሊህ የዘመናችን ዲዮጥራጥሳውያን በጊዜ ሂደት እንዴት ከቅን አገልጋይነት ወደ ማፍያነት  እንዳደጉ ትንሽ ጭልጭል እያለላችሁ ነው? ልቀጥል…

ክስተት 2

ይሄኛው ክስተት አሁን በቅርቡ መ/ር ዘመድኩን የሰኔ 23ቱን አመጽ ተከትሎ እነ ዳኒ ድምጻችሁ ጠፋ እያለ ሲወቅጣቸው እኛም ቢያንስ እናፋልገው ብለን አሰሳ ውስጥ በገባንበት ጊዜ ያገኘነው ክስተት ነው፡፡ ክስተቱ አንዲህ ነው፡-

ምንም እንኳ ታዴ የሞት ሞቱን እዚህ እዚያም የረገጠበትን ዲስኩር ቢያቀርም እነሱ ወዳጄ በአደባባይ ለመጻፍ ለመቃወም አቅም አያግኙ እንጂ የጦፈ ሥራ ላይ ናቸው፡፡ታዴና ዳኒ እየተጣደፉ እየተወራጩ ቦሌ መድኃኔዓለም ካቴደራል ይገባሉ፡፡ በተለይ የታዴ ብስጭቱን ማንም ሰው ከፊቱ ላይ ማንበብ ይችላል፡፡ በሁለቱ ሁኔታ ግራ የተጋባ አንድ ወዳጃችን ማንን ሊያስፈራሩ ነው? ወይም ምን ግዳይ አግይተው? ይሆን እያለ በቅርብ ርቀት ይከታተላቸው ጀመር፡፡ ጉዳዩ ወዲህ ነው፡፡ ‹‹ኀበ ሀሎ ገደላ ህየ ይትጋብኡ አንስርት›› እንዲል መጽሐፍ አንዲት የቢዝነስ አጋራቸው ለካ እበላለሁ ብላ ለሌላው ያጠመደችው መጥመድ ራሷን አንቆ ነፍስ ግቢ ነፍስ ውጪ ላይ ገብታባቸዋለች፡፡ ዲዮጥራጥሳውያን በሰጧት የማይጠቅም ሥልጠና እና በመሠረቱት የቀበሮ ጓደኝነት ተሳስታ በቤተክርስቲያን ጉያ ተደብቃ ካህናት፣ ምዕመናንና የሰንበት ተማሪዎች ላይ ግፍ መስራትና ማላገጥ የጀመረችው ወዳጃቸው ማታለሉና ማጭበርበሩ ሰውን እርስ በእርስ ማባላቱ ይብቃ ብለው በተነሱ የቦሌ መድኃኔዓለም ካቴደራል ቁርጠኛና እውነተኛ የሰ/ት/ቤት አባላትና የአጥቢያው ምዕመናን አጣብቂኝ ውስጥ ገብታ ኖሯል፡፡ እናላችሁ በዋናነት በታደሰ ወርቁ የሚመራው የማፍያ ቡድን በሌሎች አድባራት እንደለመደው ከአንዴም ሁለት ጊዜ የደብሩ አለቃ ወደ ሆኑት ሊቀ ሥልጣናት ቆሞስ አባ ጥዑመ ልሳን ጋር በቀጥታ በመግባት ይቺ ወደጃችን(ዘማሪት ማርታ መሆኗ ነው) ላይ ችግር እንዲፈጠር ያደረገውን የደብሩ ዋና ጸሐፊ መጋቤ ሥርዓት ዮሐንስን በአስቸኳይ እንዲያስነሱ ቀጭን ትእዛዝ ሰጥቶ ይወጣል፡፡ ይሄ ምዕመናንና የሰ/ት/ቤት አባላት ዘንድ ይደርሳል፡፡ እሳቸውም በደረሳቸው ተግሳጽና ማስፈራሪያ ተደናግጠው በጎን ሄደው ‹‹ሄሎ ካሽ›› የሚል ቅጽል ስም የወጣላቸውን የአሁኑን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ዋና ጸሐፊው ይነሳልኝ ብለው አልቅሰው ያመለክታሉ፡፡ በጎን ግን ለምዕመናን በሰበካ ጉባኤ ተነጋግረን ማርታ ላይ ማስጠንቀቂያ ልንጽፍ ተስማምተናል ይላሉ፡፡

ለወትሮው ላሜ ቦራዎች የነበሩትና በእነ ታደሰ እኩይ የሆነ የማፍያ ድርጊት የተበሳጩ ምዕመናንና የሰ/ት/ቤት አባላት ጥያቄ ማንሳት ጀመሩ ታደሰ ማነው? የየትኛው የቤተክርስቲያን የሥራ ክፍል ሹመኛ ነው? ከዘማሪት ማርታ ጋር ያለው ግንኙነት ምድነው? አለቃውስ ቢሆኑ በአንድ ራስ ሁለት ምላስ ሆነው እንዴት ይጫወቱብናል?  ብለው በጥልቀት ሲያጠኑ የስላይድ ነጋዴው ታዴ ጮሌው ፣ የዳንኤል ቡችላና አሽከር፣ በቤተክርስቲያን ውስጥ በየትኛው የሥልጣን እርከን ቦታ የሌለው እራሱን የሾመና ለዘማሪት ማርታም ‹‹ቤተኛ›› አንድም ‹‹ቤትተኛ›› እንደሆነ፤ በዚህም ምክንያት የቦሌ መድኃኔዓለምን ያክል የተሳለመው ቤተክርስቲያን እንደሌለ ይረዳሉ፡፡ ምዕመናኑና የሰ/ት/ቤት አባላቱ በሚራው የማፍያነት ተግባር የበለጠ ስለተበሳጩ መዝገብ ቤቷ ዘማሪ ማርታ ከደብሩ መነሣት እንዳለባት ቁርጥ ሀሳብ ላይ ይደርሳሉ፡፡ ዘማሪት ማርታ በደብሩ ላይ በምትፈጽመው እኩይ ተግባር(አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ወደ ፊት በዝርዝር ይቀርባል) ተንገሽግሸዋላ!!!

በነገራችን ላይ ይሄ አለቆችንና የአስተዳደር ሠራተኞችን እየገቡ ማስፈራራት አዲስ ነገር አይደለም፡፡ በቤተክርስቲያን መዋቅር ውስጥ ተቀጥረው ያሉ አካላት ባይደግፋቸውም እንኳ በግልጽ የማይቃወሟቸው ከሆኑ፤ አሊያም በከፊልም ይሁን በሙሉ ተባባሪ ከሆኑ ወይም እነሱን ደጅ ከጠኑና በራቸውን ካንኳኩ የትኛውም ደብር ቢሆን ገብተው አለቃውን በማስፈራራት አገሌን ወይም አገሊትን ብትነካ ይሄንን ጉድህን እንዘረግፈዋለን በማለት የማፊያ ተግባር በመፈጸም ለወዳጆቻቸው ተቻችሎ የመኖር ውለታ ይውሉላቸዋል፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ የቤተክርስቲያኒቱ አገልጋዮች ብጹዓን አባቶች እንዲሁም በእነሱ ዘንድ አይነኬ የሆኑ በተለይ የሸዋና የጎጃም ዘወጌ ያላቸው ሰዎች ጥፋትም ቢኖርባቸው እንኳ ወይም ችግር ሲገጥማቸው እስከሚላላጡ ድረስ ይረባረባሉ፡፡ከዚያ ውጪ ከሆንክ ትቦጫጨቃታለህ፡፡ የአፈ ቀላጤያቸው የሐራ ተዋህዶ አፍ ማላቀቂያና ማላገጫ ትሆናለህ፡፡ በቃ ይሄው ነው እጣ ፈንታህ!!!

ወደ ቀደመ ነገር እንመለስና እናላችሁ እነ ታዴ ጭሱም በደብሩ አለቃው ተቀባይነት አግኝቶ በምዕመኑ የከሸፈው ሴራ አለመሳካቱን ሲያውቁ ሌላ ሴራ ቀየሱ፡፡ ሰሞኑን ልክ እንደ አዲስ ክስተት ድቤ እየተደለቀለት ያለውን የግብረ ሰዶማውያን ጉዳይ በማንሳት አሳዳጊውንና የተንኮል አባቱ ዳንኤልን በመያዝ ለቤተክርስቲያኒቱ ተቆርቋሪ ናቸው ብለው የሚያምኗቸውን ባለጠጎችን በመሰብሰብ ‹‹እኛ የመጣነው ከአእላፋት ድምጽ የካህናትና ምዕመናን ተናሥዖት ኅበረት ነው (አቤት የኅብረት ብዛት የት ያደርሰን ይሆን?) እና እዚህ ቦሌ መድኃኔዓለም አጥቢያ ውስጥ የግብረ ሰዶማውያን ስብስብ አለ፣ ጸሐፊውንም እላይ ካሉ አባቶች ጋር ተነጋግረን እንዲነሳ ያደረግነው ጥርጣሬ ስላለን ነው፤ ይሄንን ጉዳይ የምትቃወሙ አካላት የእነዚህ ሰዎች ደጋፊዎች ናችሁ ማለት ነው›› እያሉ ሲፎክሩና ሲያስፈራሩ ዋሉ፡፡

እዚህ ላይ የዚህ ሁሉ ችግር መነሻ በጸሐፊውና በዘማሪት ማርታ መካከል የተከሰተው አለመግባባት መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ የቦሌ መድኃኔዓለም ሰ/ት/ቤትና ምዕመናን ‹‹ቁማሩን ቀድመው ስለበሉት›› የነብርን ጅራት አይዙ…እንዲሉ ምንም እንኳን እነ ዳኒ ለጊዜው በስብሰባው ላይ የተቃወሟቸውን ታላላቅና የተከበሩ ሰዎች ለጊዜው ለማሸማቀቅ ቢሞክሩም ቦሌዎች ግን የማፍያው ቡድን ያቀረበውን ሀሳብ ሳይቀበሉ አሳፍረው መለሷቸው፡፡ ዛሬ ላይ የቦሌ መድኃኔዓለም ምዕመናን ሄዳችሁ ብታነጋግሩ እዚህ ላይ ቢጻፍ ጸያፍ የሆኑ ብዙ ነገር ይዘረግፉላችኋል፡፡ ከስብሰባውም በኋላ ሁሉም በአንድ ድምጽ ለካ እነሲህ ሰዎቸ እንዲህ ቀላልና ወራዶች ናቸው እንዴ? ይሏችኋል፡፡ ይህ ሁሉ ድፍረት የሚፈጽሙት በማኅበረ ቅዱሳን ካባ ውስጥ ተደብቀው መሆኑን ስታስብ ደግሞ የማይጠቅም ብስጭት መበሳጨትህ አይቀርም፡፡ እኔ ግን የማይገባኝና የሚገርመኝ ነገር፤ ማኅበሩን ራሱ እንደሚጠሉት፤ ለውድቀቱም እንደሚሠሩ እያወቀ አንድ ችግር ሲፈጠር በቴሌቭዥኑ እያቀረበ የሚያደናብረንና ከአንገት በላይ በሆነ ልፍለፋቸው እንዲፎክሩ፣ እንዲሸልሉና እንዲያደናቁረን የሚያደርግበት ምክንያት ነው፡፡  ይሄ ደግሞ እነዚህ የእናት ጡት ነካሾች በማኅበሩ ካባ ተደብቀው ቤተክርስቲያኒቱን የማሸበርና የማፍያ ሥራ እንዲሠሩ እድል እንደሚሰጣቸው ጠፍቷቸው አይደለም፡፡ በእኔ እምነት ማኅበሩ በእነዚህ ሰዎችና በመሰሎቻቸው ላይ ያለው አገም ጠቀም የሆነ አቋሙን አስተካክሎ ምዕመናን ከውዥንብር መጠበቅ አለበት፡፡

አንዳንዶቻችሁ ምናልባት ማኅበሩን ራሱ እንደሚጠሉት፤ ለውድቀቱም እንደሚሠሩ ስል ከጭፍን ጥላቻ ወይም ከመረጃ እጥረት ሊመስላችሁ ይችላል፡፡ በፍጹም!!!  ልክ እንደከዚህ በፊቱ ማኅበረ ቅዱሳን የኅዳጣን(የዳኒና የጀሌዎቹ ብቻ) ሆኖ እንዲቀጥል፣ እነሱን ስላባረረ ብቻ የማኅበሩ አመራር ደካማ እንደሆነ፣ እኛ ያልጋገርነው…ዓይነት ጨዋታ መሆኗ ነው፡፡ ማኅበሩ የእነሱን ነውር ሸፍኖ የቀን ከሌሊት ህልማቸው እንዲሳካ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥራቸው ሥር ማስገባት ወይም ፈርሶ ማየት መሆኑን ለመረዳት ራሳቸው ማኅበሩንም አስመልክቶ ከሚጽፉት ጽሑፍና ከሚያራምዱት አጀንዳ ተነስቼ ለማስረዳት ልሞክር፡፡

 ታደሰ ወርቁ  በፋክት መጽሔት ቅፅ 2 ቁ.6 የሐምሌ 2005 ዓ.ም እትም  እና ቁጥር 7 ላይ ‹‹በቄሳራውያን መዳፍ ሥር ያለ አስኬማ›› እና ‹‹የተቋማዊ ለውጥ ጅምሮች›› በሚሉ ርዕሶች ሥር የእናት ጡት ነካሽ ኾኖ ‹‹ማኅበሩ ለሁለቱ ሲኖዶሶች ዕርቀ ሰላም ላይ አሉታዊ እይታ እንዳለው፣ የአዲስ አበባ ሰ/ት/ቤቶችን በተሐድሶ ሰበብ የቤተክርስቲያን ነውጥ አውጆ እንደነበረና አሳድሟቸው አንደነበረ፤ የጥምቀት ተመላሾችን ለራሱ ዓላማና ጥቅም ብሎ ማኅበሩ እንዳደራጃቸው…›› በአደባባይ በድፍረት ጽፏል፡፡ ይሄን ያለ አንደበት ዛሬ ደግሞ የማኅበሩን ቴሌቪዥን ለመደገፍ እየሠራን ነው ይልልሃላ!!! ቀጣፊ ማፍያ ሁላ!!!

ሌላው  ዳንኤል ከማኅበሩ የወጣበትን ትክክለኛ የመሠረታዊ ቅራኔ ምንጮች ቢያንስ ሰለ በማኅበሩ ሀብትና ንብረት ስለተሰበሰቡት ማይክሮ ፊልሞቹ፣ የልማት ተቋማት ማናጂንግ ዳይሬክተር በነበረበት ጊዜ ያጠፋቸው ጥፋቶችና ከማኅበር ወደ ግል ስለተሸጋገሩ መጻሕፍትና ንብረቶች ተሸፋፍኖ የቀረበበትና እና በወቅቱ የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ የነበረውና በአሁኑ ሰዓት አማሪካ የሚገኘው የማኅበሩ የዲቪ እድለኛ የሆነው ዲ/ን ሙሉጌታ ኃ/ማርያም በዕንቁ መጽሔት 4ኛ ዓመት ቁጥር 46 እትም ላይ ያደረገው ቃለ መጠይቅ ተከትሎ ዲ/ን ዳንኤል በደጀ ሰላም የጡመራ መድረክ በኩል በጽሑፍ ባቀረበው መልስ ‹‹…ማኅበሩ ስለ ቤተክርስቲያን በቂ መረጃ የሌለው፣ ዋና ሥራውን ትቶ አባላቱን እንደሚሰልል፤አባ ሠረቀንም ይሁን በጋሻውን የሚከሰው ማኅበሩን ስለነኩት እንጂ ለቤ/ክን አደጋ ነው ብሎ አለመሆኑን…›› በመግለጽ «ባልበላው ጭሬ ላፍሰው» የሚለው ተረት በተግባር በማኅበሩ ላይ ሊፈጽም የሚወድ መሆኑን አይተንበታል፡፡

ውድ አንባብያን ሙሉውን ጉግል አድርጎ ማንበብ ማኅበሩ በዳንኤል ልብ ውስጥ ያለውን ቦታና ለወደፊት ያቀደለትን ሴራ በደንብ ለመረዳት ያስችላልና አንብቡት፡፡

የሆነው ሆኖ እነዚህ አካላት በንስሐ ቢመለሱ ለቤተክርስቲያኒቱ ሊጠቅሙ የሚችሉ ሊሆኑ ስለሚችሉ፤ እነዚህን ከአገልጋይነት ወደ ማፍያነት የተቀየሩ የዘመናችን ዲዮጥራጥሳውያን መክረን ዘክረን ብንመለስ አይሻልም ጎበዝ? እኔ ግን በበኩሌ እስኪመለሱ ድረስ አልፋታቸውም፡፡

ማኅበሩም ለተመሠረት ዓላማ የሚገዛ ሆኖ እንዲቀጥል የማኅበሩን ካባ ለብሰው ምዕመናንና አገልጋዮችን የሚያሸብሩና የሚያሸማቅቁ አመሳኝና ማፍያ የሆኑ ዲዮጥራጥሳውያን ነቅተንባችኋልና ካባችንን አውልቁ ሊል ይገባል፡፡ ማኅበሩን ባለመረዳት የሚያሰደቡት ሳውላውያንን የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና በመስጠት፤ ማኅበሩ ሳይኖር ቤተክርስቲያን እንደነበረች፣ ነገም ማኅበሩ ባይኖርም ቤተክርስቲያን ለዘላለም እንደምትኖር በማስረዳት ከሳውላዊነት ወደ ጳውሎሳዊነት መመልስ አድካሚ ቢሆንም የግድ በፍጥነት ቅድሚያ ተሰጥቶት መከወን ያለበት ጉዳይ ነው፡፡

በዚያ ላይ ማኅበሩን ዋጥ ስለቅጥ አድረገው ሊበሉ ለተዘጋጁ ሰርጎ ገቦችና ለቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ ነን የሚለውን ታፔላ ለጥፈው እንደአሸን እየፈሉ ያሉ፤ ስምና ቁጥራቸው የበዙ ማኅበራት ጀርባ የዲዮጥርጣሳውያ ስውርና ግልጽ እጅ መኖሩ ስታይ የማንቂያ ደውል አትልልኝም!

ማሳያ ሦስት (scenario3)፡-በሕጋዊ መንገድ ያልተመዘገቡና በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያ ስም የሚንቀሳቀሱ ማኅበራት ጉዳይ

በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ትውፊት መሠረት በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚሰባሰቡ፤ እምነትን በተግባር ለመለማመድ የሚያግዙ፤ በክርስቲያኖች መካከል ማኅበራዊ መስተጋብርን የሚያጠናክሩ እንደ ጽዋ ማኅበራትና ሰንበቴዎች የመሳሰሉ ክርስቲያናዊ ስብስቦች አሉ፡፡ እነዚህ ስብስቦች በአንድም በሌላ መንገድ ለቤተክርስቲያን ድጋፍና አስተዋጽኦ ሲያደርጉ የኖሩ ናቸው፡፡

ከኢትዮጵያ እስራ ምእት በኋላ ፳፻፪ ዓ.ም የጥምቀት በዓልን ተከትሎ ወጣቱ ወደ ቤተክርስቲያን ለመመለስ ያሳየው ፍላጎት፣ ተነሳሽነትና የአገልግሎት ትጋት ትልቅ ተስፋን በውስጣችን ያጫረ ነበር፡፡ ኋላ ግን ወጣቶቹ ቤተክርስቲያን ያላት መዋቅር ማንም ተነስቶ የእገሌ ወእገሊት ማኅበር ብሎ ያለፈቃድ ለማቋቋም እና የግል ጥቅም ማጋበሻ ሊውል የሚችል ወተቷ የማይነጥፍ የፈረጅ ላም መሆኑን በተረዱ አማሳኝ መሪዎች መዳፍ ሥር ስለወደቁ ለቤተክርስቲያን አደጋና ችግር እየሆኑ መጡ፡፡ መጀመሪያ አከባቢ እነዚህ በድንገት እንደ ደራሽ ውሃ የመጡ ወጣቶችን በተለያዩ ሰ/ት/ቤቶች በኩል አስተምሮ ወደ መደበኛ አገልግሎት ለመቀላቀል ከፍተኛ ፍላጎትና ጥረት ቢደረግም እነ ፌቨን ዘሪሁንን በመሳሰሉ ጥቅማችን ይቀርብናል ብለው በሰጉ ሆድ አደር ተለጣፊዎች መክኖ ቀርቷል፡፡ አሁን አሁንማ አንዳንድ አለቆች ከሰንበት ተማሪዎች ጋር ሲጣሉ እንደማስፈራሪያ ይጠቀሙባቸዋል፣ በየአገልገሎቱም ላይ ዩኒፎርም የለበሱ ሰንበት ተማሪዎችንና ማኅበራቸውን የሚገልጡ ባጆችና አንጸባራቂ ሰደሪያዎች ያደረጉ በተቀራራቢ የዕድሜ ክልል ያሉ ወጣቶችን ከነ ጎፌሬያቸውና የሴቶች ታይት ከመሰለ ኢ-ክርስቲያናዊ አለባበሳቸው በአገልግሎት ላይ ጎን ለጎን ተሰልፈው ማየት ብርቅ አይደለም፡፡

እነዚህየጥምቀት ተመላሽ ወጣቶች የሌላቸውን የማኅበርና የአባላት ብዛት እየጠቀሱ ጡሩንባ መንፋታቸውን ረስተን በቤተክርስቲያን አገልግሎት ላይ እያደረሱ ያሉትን ሦስት አደገኛና ፈታኝ ሁኔታዎች እንመልከት፡፡

  • የመጀመሪያው ማንም ኦዲት የማያደርገውና የገጠር ቤተክርስቲያን ማሠሪያ፤ ለጥምቀትና ለተለያዩ በዓላት ማክበሪያ በሚል ሰበብ ከሀገር ውስጥ እስከ ውጪ ካሉ ምዕመናን ገንዘብ በገፍ ይሰበስባሉ፡፡ ይሄ ገንዘብ ከሦስት ተሰንጥቆ በዛ የሚለው አንዱ እጅ ለግል ኪስ ይውላል፡፡እዚህ ላይ ፌቨንና ጓደኞቿ የጀመሩትን የኢምፖርት ኤክስፖርት ንግድ ሥራ በርቱልን ብሎ አለማለፍ ምቀኝነት ስለሚሆን ግፉበት ብለናል፡፡ሌላው እጅ በጣም ትንሹ ለበዓል ማክበሪያ ሲውል፣ ሌላኛው ሲሶው ደግሞ በየአብያተ ክርስቲያናቱ ውስጥ እንደፈለጋቸው መንቀሳቀስ ይችሉ ዘንድ አንዳንድ ጥቅመኛ አለቆችንና አገልጋዮችን መግዣ አድርገው ይጠቀሙበታል፡፡
  • ሁለተኛው እነዚህ ወጣቶች በአብዛኛው የቅድስት ቤተክርስቲያንን ዶግማ፣ ቀኖናና ትውፊት በተገቢው መንገድ ያልተማሩ በመሆናቸው በቤተክርስቲያን አገልግሎት ላይ ሲሳተፉ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ለመጠበቅ የማይገደዱ በመሆናቸው ወደ ቤተክርስቲያን ለሚመጡ ታዳጊዎችና ወጣቶች አርአያነታቸው የወረደና ምናልባትም ውጪ ያሉ ወጣቶች ያሉበት የሥርዓተ ቤተክርስቲያን ጥሰት በቤተክርስቲያን የተፈቀደ እስኪመስል ድረስ ለሥርዓተ ቤተክርስቲያን የማይገዛ ፍሬ አልባ መራራ ትውልድ እናፈራበታለን ማለት ነው፡፡
  • ሦስተኛው አንዳንድ የሥነ ምግባር ጉድለት የታየባቸውን የሰ/ት/ቤት አባላት በሕጉ መሠረት ለማስተካከል ሲሞከር በማኩረፍ በማንኛው ነገር ቁጥጥርና ክትትል  ወደ ሌለበት የማኅበራት ኅብረት ዋሻ ሄዶ መሸሸግ የተለመደ ሆኗል፡፡ አሁን አሁንማ በአንዳንድ አጥቢያዎች ሰንበት ት/ቤትን ያገለለ የስብከተ ወንጌል ጉባኤ እስከ ማዘጋጀት ተደርሷል፡፡ ይሄ ደግሞ ሄዶ ሄዶ ከቃለ ዐዋዲው ውጪ በሆነ መንገድ ሁለት የተለያየ ሥርዓትን የሚያራምዱና የሚከተሉ ሁለት የተለያየ መዋቅር ያላቸው በጎሪጥ የሚተያዩ በተመሳሳይ ዕድሜ ያሉ ወጣቶች በአንድ አጥቢያ እንዲኖሩ አድርጓል፡፡ በዚሁ ምክንያት በተለያዩ አድባራት በሁለቱ የወጣቶች ስብስብ መካከል ግጭቶች የሚስተዋሉ ሲሆን ወደፊት ደግሞ ይሄ ግጭት ተባብሶ ወደ አላስፈላጊ ነገር ሊያመራ እንደሚችል በርካታ ጠቋሚ ነገሮች አሉ፡፡

ሌላው ደስ የማይለው ነገር እነዚህን ወጣቶች በማደራጀትና ሥልጠና በመስጠት የማኅበረ ቅዱሳን ስም በተደጋጋሚ የመነሳቱ ጉዳይ ነው፡፡ እንዲህ ተባለ እንዲያ እነዚህ ወጣቶች በአግባቡ መክረንና አስተምረን ወደ መስመር መስገባት ካልቻልን ነገ ለሚፈጠረው ቀውስ ከታሪክም ይሁን ከኅሊና ተወቃሽነት ሁላችንም ማምለጥ አንችልም፡፡ እነዚህ ወጣቶች የቤተክርስያኒቱ መሠረተ እምነት፣ ትውፊትና ቀኖና ሳይማሩ ወደ አገልግሎት የተሰማሩ በመሆናቸው ሥርዓተ ቤተክርስቲየንን ሳይጠብቁ ከነጎፈሬያቸው፣ ከነ ታይት ሱሪያቸው ቢያገለግሉ፣ በቅዳሴ ሰዓት ሰዎች ሲያስቀድሱ ቁጭ ብለው ብናያቸው አሊያም  የግል ወሬን እያወጉ ብንመለከታቸው ብዙም የሚደንቅ አይደለም፡፡

ዛሬ ላይ የማንቂያ ደውል ሆኖ ልብ ልንለው የሚገባው ነገር እነዚህ ወጣቶች ዛሬም ይሁን ነገ ላይ ተነስተን በቃለ ዐዋዲው ምዕ 3 አንቀጽ7፡1መ እና አንቀጽ12፡5 መሠረት ወደ ሰ/ት/ቤት መጠቃለል አለባችሁ ብንላቸው የሚሰሙን ይመስላችኋል? ለየትኛው የቤተክርስቲያን አካል ታዛዥ ይሆኑ ይሆን?  እኔጃ እኔ ግን እጅግ እፈራለሁ፡፡ ብቻ ጊዜ ይመልሰው!!!

የዚህ የጡመራ መድረክ አባላት ዓላማ የቅድስት ቤተክርሰቲያን ልጆች ከእኩይ ተግባራችን ተመልሰን ለኢትዮጵያና ለቤተክርስያን ትንሣኤ በጋራ እንድንሠራ የማንቃት ሥራ ለመሥራት እንጂ አንዱን አሞግሶ ሌላውን አንኳሶ ለማቅረብ፤ ማንንም ለማሳጣት ወይም ለማሸማቀቅ ባለመሆኑ እግዚአብሔር አምላክ ለሁላችንም ለቤተክርስቲያን ሕግና ሥርዓት የሚገዛ ቅንና እውነተኛ ልቡናና መንፈስ ያድለን!!! አሜን፡፡

ይቆየን

ሳምኬት ነኝ

ተጻፈ ነሐሴ 21 ቀን 2012 ዓ.ም

በኮሮና ተፈትሾ የተጋለጠው እና የተዝረጠረጠው የአዲስ አበባ አብያተ ክርስቲያናት አስተዳደራዊ ዝቅጠት

እንደምን ከረማችሁልን ውድ አንባብያን! እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ!!!

መቼም የቤተክርስቲያን ጉዳይ ልተወው ብትልም አይተውህም ምክንያቱም ቅድስት ቤተክርስቲያን ሕይወታችን፣ክብራችን፣ውበታችና ጌጣችን በአጠቃላይ ሁሉ ነገራችን ስለሆነች!!!  እናላችሁ ወረርሽኙ፣ የሀገሪቱ ሁኔታ፣ ቤተ ክርስቲያን ያለችበት ሁኔታ፣ በምዕመናን ላይ የሚደርሰው ግፍ…በማየት ይሄ ጊዜ ዝም ተብሎ በጸሎት የሚታለፍ ጊዜ ነው ብለን የዚህ መጦመሪያ መድረክ አባላት ለጊዜው ከመጻፍ ታቅበን ነበር፡፡ ነገር ግን ቅዱስ ጳውሎስ በሐዋ ሥራ 20፡29-30 ላይ ‹‹ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ…›› ብሎ እንደነገረን በዚህ ወረርሽኝ ጊዜ እንኳ ስለ ምዕመናንና ስለ ካህናት የሰቀቀን ኑሮ መጨነቅ ሲገባቸው ሰለቀረባቸው የሙዳየ ምጽዋት ግልበጣና በየዳንኪራውና መሸታ ቤቱ ስለቀረባቸው አስረሽ ምችው ብቻ በማሰብ በሚኖሩትየአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሹማምንትና ለወረርሽኙ ተብሎ የተቋቋመው ተስፋ ልዑክ መካከል የተከሰተው ውዝግብ ትኩረታችንን በመሳቡ ወደ መጻፍ መመለስ እንዳለብን ወሰንን፡፡ ውዝግቡ ወደ ውስጥ ሲፈተሽ በርካታ አስቀያሚና አሰፋሪ ነገሮች ቢኖሩትም የበለጠ ውዝግቡን ያጦዘው ግን በቤተክርስቲያን ችግር ላይ የክፋት፣ የተንኮልና የሴራ አጀንዳ እየፈበረከ ቤተክርስቲያን እረፍት እንዳታገኝ የሲኖዶስ ስብሰባ በመጣ ቁጥር እንደተከፈላቸው መጠንና ለአይነኬ ዘውጌዎች ብቻ ከፍተኛ ጥንቃቄ እያደረጉ አጀንዳ እየፈበረኩ ነገር በሚያራግበው የሐራ ዘተዋሕዶ ጸብ አጫሪ ጽሑፍ መነሻ ነው፡፡

ብዙ የተባለለት ነገም ብዙ የሚባልለት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እያደረሰብን ያለው ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሥነ ልቦናዊ ቀውስ ቀላል ባይሆንም በአንጻሩ ደግሞ ያመጣልን አዎንታዊ ጥቅሞች አሉ፡፡ ከእነዚህ መካከል ለዛሬ አንዱን ማየት አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡

እንደሚታወቀው በዚህ ቫይረስ ምክንያት ከሰፈር የጉልት ገብያ ጀምሮ እስከ ዓለም አቀፍ ታላላቅ ኩባንያዎች በወረርሽኙ ያልተነካ የለም፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ ተጽእኖ ከደረሰባቸው ተቋማት መካከል አንዷ እናት ቤተክርስቲያን  ናት፡፡ ምንም እንኳን እስካሁን የሰማሁት የቀነሰችው የሰው ኃይል ባይኖርም ካህናትና የካህናት ቤተሰቦች ግን እያሰሙት ያለው እሮሮና ነገስ? የሚለው ጥያቄ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ነው፡፡አንዳንድ የምንቀርባቸው ካህናት የንስሐ ልጆቻቸውና ብጹዓን አባቶችን ሳይቀር ደጅ መጥናትና አፍጦ ቸግሮኛል የምታደርጉትን አድርጉ ብሎ ለልመና መውጣት ሌላው የታየ አሳቃቂ ነገር ነው፡፡ በየደጃፎቻቸው የተለጠፉ የየአብያተክርስቲያናቱ ወደ አካውንት ብር አስገቡልን የተማጽኖ ደብዳቤና ከዚህ ባለፈ ደግሞ በሀገር ውስጥም ይሁን በውጪ ያሉ ካህናት ከተረጂ ሰዎች(የደሀ ደሀ ተብለው ከተመደቡ) ጋር ለእርዳታ ተሰልፎ መታየት ሌላው አንገት ያስደፋን ጉዳይ ነው፡፡ ይሄ ደግሞ በርካታ የኪራይ ሱቆችና ቤቶች ባላቸው አብያተክርስቲያናት ጭምር መሆኑን ማየት እጅግ ያስለቅሳል ያበሳጫልም!!!

ለምን ግን ይሄ ሁሉ ሆነብን? ባለ ራዕይ፣ ተስፈዮችና ተራማጅ የሆነ ሀሳብ ባለቤት የሆኑ ወንድሞችና እህቶች እናት ቤተክርስቲያን እኮ ለሀገር ሊተርፍ የሚችል አቅም አላት፤ የራሷ ባንክና የተለያዩ ትልልቅ ድርጅቶችን መመስረት ትችላለች ብለው አልነገሩኝም እንዴ? ለተጨማሪ አንድ ወር እንኳን የሚሆን የደሞዝ ክፍያ እንዴት አጣን? የወረርሽኚ ጊዜ ቢራዘምስ? እንደ ሌሎቹ ሀገራ ሙሉ ለሙሉ ከቤት መውጣት አይቻልም ቢባልስ? ለሚሉት ጥያቄዎች መልስ ማግኘት ስለከበደን የዚህ መጦመሪያ መድረክ አባላት መረጃ  ለመሰብሰብ ቢያንስ ትልልቅ ወደ ሆኑ አብያተ ክርስቲያናት ለቅኝት ተሰማራን፡፡ የሁላችንም የተሰበሰበ መረጃ የሚጠቁመው በአብዛኛው አብያተ ክርስቲያናት የሚሰማው ድምጽ አንድ ነው ይኸውም፡-

አምስቱን ከለባት  ኮረና ጉድ ሠራቸው! ተዋርደው አዋረዱን! የሚል ነው፡፡ ሆይ ጉድ! (በነገራችን ላይ አምስቱ ከለባት የሚባሉት ሙዳየ ምጽዋት ገልባጮች፣ ነውረኞች፣ራስ ወዳድ፣ መሸተኞች፣ሴሰኞች፣ሆድ አደር..የሆኑ በየደብሩ የሚገኙ አለቃ፣ጸሐፊ፣ሒሳብ ሹም፣ ቁጥጥር እና ገንዘብ ያዥ ናቸው፡፡ በግብራቸው ውሻ ተብለዋል፡፡ራዕ 22፡15)

በአዲስ አበባ ያለውን የሰው ሀብትና የፋይናንስ አስተዳደር ብልሽትና ዝቅጠት ለማስተካከል ከዚህ በፊት ብዙዎች የጮኹለት በሎም ተግባራዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ ሞክረው በዛር መናፍስት አንጋሽነትና በጋኔናዊ ትብትብ አሠራር በተካኑ ሆድ አደር የአዲስ አበባ አለቆች የከሸፈው የቤተክርሰቲያን አባቶችና ልጆች ድካም መና ባይቀር ኖሮ ከዚህ ሁሉ ውርደት በታደገን ነበር፡፡ ለነገሩ ልብ ከሰጠን ይሄም የማንቂያ ደውል ነው!

ለምን አንዲህ ዓይነት ችግሮች ተከሰቱብን? ለሚለው ጥያቄ ጥቂት መልሶችና መፍትሔዎች  እንመልከት፡-

  1. በአንድ ቋት ያለመተዳደር ችግር፡- ለብዙዎቻችን ይሄ ሀሳብ ዛሬ የተወለደ ሊመስለን ይችላል፡፡ በቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ዘመን ተነስቶ ሆድ አደር ጥቅመኛ መንፈሳዊ ሹማምንት ተረባርበው አክሽፈውታል፡፡ንጉሡ ‹‹ሃይማኖት የግል ነው ሀገር የጋራ ነው፡፡›› አዋጅ ለማወጅ የተገፋፉት በዚህና በተያያዥ ጉዳዮች ፖለቲከኛ ካህናት ያሳዩት አቋም ሳይሆን አይቀርም የሚሉ አሉ፡፡ቤተክርስቲያንን የማዳከም ሥራ የጀመረው ማነው?ለሚለው አንዳንዶች አጼ ኃ/ሥላሴን ያደርጋሉ፡፡ ለእኔ ግን ትላንትም ዛሬም ቤተክርስቲያንን ለዚህ ችግር የዳረጓት ቤተክርስቲያንን ኃ.የተ.የግ.ማኅበር አድርገው የሚኖሩና ለዚሁ የሚሠሩ ጥቂትና ሆድ አደር የሆኑ የየአብያክርስቲያናቱ አለቆች እና ጀሌዎቻቸው ናቸው፡፡ ለዚህ ደግሞ በእኔ እምነት ተጠያቂዎቹ የአዲስ አበባ ካህናት ጭምር ናቸው…ከጥቂት አመታት በፊት እንኳን የነበረውን የፋይናንስ አስተዳደርን የማስተካከል እንቅስቃሴ ማኅበረ ቅዱሳን ከሥራህ ሊያፈናቅልህ… ነው ሲባሉ እንዴት? በምን አቅም? ማለት ሲገባ ማለቴ ቢወስዱ እንኳ የአምስቱ ከለባትን ቦታ እንጂ የቀዳሹን የአወዳሹን ቦታ አልነበረም፡፡ ከለባቱ ግን መጡብን ሊመጡብን ነው ከማለት ይልቅ መጡብህ ሊመጡብህ ነው ብለው የሁል ጊዜ የችግር ገፈት ቀማሽ ምስኪን ካህናትን በማደናገር እኩይ ተግባራቸውን አጠናክረው ለመቀጠል አወናበዷቸው፡፡ ታሪካዊ ስህተት!!!

ስለዚህ ለቤተክርስቲያን በትክክልና በእውነት የምናስብ ከሆነ በአንድ ቋት የመተዳደር ጉዳይ እንደገና በጥናት ላይ ተመሥርተን አጥብቀንና ጠንክረን መጀመር አለብን! ስለዚህ ሳንሰለች መጮህ አለብን!!!

2.በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ያለው የላሸቀ የሰው ኃይል አስተዳደር፡-በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚሾሙ ሥራ አስኪያጆች ልባቸውና አእምሮአቸው ላይ ተነቅሰው ሥራ የሚጀምሩት ‹‹ሲሾም ያልበላ..›› የሚለውን ነቀርሳ የሆነ ተረትና ምሳሌ ይመስለኛል፡፡ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ታሪክ ከንብረ ዕድ ቆሞስ አባ ገ/ማርያም በስተቀር በቤተክርስቲያን ላይ ያላላገጠና ሀብቷን ያልዘረፈ ሥራ አስኪያጅ አላየሁም፡፡ እንደአለመታደል ሆኖ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከየአድባራቱ በታላቅ ጉጉት የሚጠበቀው ሪፖርት የበጀት፣የሥራ አፈጻጸም አሊያም የልማት ሪፖርት ሳይሆን ስንት ሰው ሞተ? ወይም ስንት ሰው ሥራ ለቀቀ? ነው፡፡ ምክንያቱም በአንድ አጥቢያ በአንድ ሞተ ከዳ በትንሹ እስከ ሦስት ሰው መላክ ይቻላል፡፡ በዚህ ደግሞ ብዙ መላ(ፍራንካ) ይሰበሰብበታል፡፡ በእኛ ቤት አንድ ሰው በደጅ ጠኚነት ቆይቶ ሰው ሲሞትለት ወይም ሲለቅነት ሁለት ጊዜ ቀረጥ ተቀርጦ(የድጋፍ ደብዳቤ ለተጻፉለትት ለ5ቱ ከለባት እና ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሹማምንት) ነው የሚቀጠረው፡፡ ይህ ደግሞ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን በዓለማችን ላይ በሰው መሞት ወይም ስንብት ተስፋ የሚኖር ብቸኛው ተቋም ያደርገዋል ማለት ነው፡፡

ለዘመነ መሳፍንት መነሳት ዓይነተኛ ምክንያት ተደርጎ የሚወሰደው ለጉዳዮች ከማዕከላዊ መንግሥት የተማከለ ምላሽ ማጣት መሆኑን ብዙ የታሪክ ሊቃውንትና ጸሐፍት ይስማማሉ፡፡ ዛሬም ቤተክርስቲያን በሰው ሀብትና በፋይናንስ አስተዳደር የተማከለ አሠራር ስሌላት…የምናያቸው ያፈጠጡ ችግሮች በአፍጢማችን እያዳፉን ስንወድቅ ስንነሳ አለነው፡፡

ስለዚህ በመንፈሳዊ ኮሌጆች የሚማሩ ደቀ መዛሙርትም ይሁኑ ስለ ቤተክርስቲያ ከግላዊ ጥቅምና ከዘውጌነት በጸዳ መልኩ በአንድ አጥቢያ ሊኖረው ስለሚገባ የሰው ኃይል እና የፋይናንስ አስተዳደር ላይ የጥናት ወረቀቶችን በማዘጋጀት  ለቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የሚሆን ግብአት  በማቅረብ ዘለቄታዊ መፍትሔ በጋራ ካልፈለግን በቀር እየተሸማቀቅንና እያለቀስን እንቀጥላለን ማለት ነው፡፡ለዘመናት የዘለቀው ለብልሹ አሠራር መሠረት የሆነው የሞተ ከዳ ዘመናዊ የቅሸባ ቢዝነስ በዚሁ ከቀጠለ የአስተዳደር ልሽቀቱ፣ የእኛም ልቅሶ ይቀጥላል ማለት ነው፡፡

3.ተጠያቂነት የጎደለው የሥራ ኃላፊዎች ዝውውር፡-በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚመደቡ አለቆች ሥልጣን የዛፍ ላይ እንቅልፍ ነው፡፡ በአብዛኛው አንድ አለቃ(አምስቱ ከለባት) መቼና በምን ምክንያት እንደሚቀየር ሀገረ ስብከቱና አለቆቹ ብቻ በውስጥ መስመር የሚያውቁት በመሆኑ አንድ አለቃ ከግብረ አበሮቹ ጋር የሚፈለገውን ያክል ከዘረፈ በኋላ ያለ ተጠያቂነት እንዳካበተው የዘረፋ ሥራ ልምድ ሁኔታ ወደ ሚቀጥለው ከፍ ያለ አሊያም አነስ ያለ ደብር እንደሚዘዋወር ሰለሚያውቅ እንደ ልቡ ሆኖ ይኖራል፡፡ እነዚህ የዘረፋ የሥራ ልምድ ያላቸው አለቆች ከሚያከናውኑት ሳሳ ያለ የቤተክርስቲያን አስተዳደር በተጨማሪ ዋና ሥራቸው አበጥ ያለ  ካዝናና ደከም ያለ የሰበካ ጉባኤ ያለበትን ደብር እየፈለጉየከተማው ሀብታሞች እንኳ ለሚቀኑባቸው የማይቋረጥ ውስኪ አውራጅና ጮማ ቆራጭ ለሆኑ የሀገረ ስብከቱ ቋሚ ደላሎች ሪፖርት ማድረግ ነው፡፡ ከዚያም እየናረ ሄዶ እስከ ብር 500 ሺ በደረሰው የዝውውር ገብያ መጫረት ነው፡፡በዚህ መንገድ ከፍለው ዝውውር የፈጽሙና ከደሀ መቀነት የተገኘና የዕንባ ሚሊዮን ብሮችን ለማፈስ የታደሉ፣ የግፍ ሕንጻዎችን የገነቡ፣ የነሱ ሳያንስ ለውሻማዎቻቸው ሳይቀር ቅንጡ መኪናዎችን የገዙ የቤክርስቲያን አይጦች በስም መዘርዘር ባያስፈልግም አንተ ግን ከፈለክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ደላሎችን አንድ ውስኪ አውርደህ ማናዘዝ ነው፡፡የእነዚህ አለቆችና የአምስቱ ከለባት ዝውውር ፍጹም ሓላፊነትና ተጠያቂነት የጎደለው  በመሆኑ ሁሉም ቃል ኪዳን የተገባቡ ይመስል ቋንቋቸው አንድ ነው፡፡ ትንሽ ጠንከር ያለ ሰበካ ጉባኤ ሲገጥማቸው… እኔ አባ እገሌ እንደሆንኩ አንዲት ሻንጣ ነች ያለችኝ እሷን አንጠልጥዬ መጓዝ ነው ይሉልሃላ! በዘረፋ የገዙትን መኪናውስ ቤቱንስ የት ረስተውት ይሆን? …ከዚያም አባታችን የዛሬ ዓመት ሂሳብ አልተዘጋም፣ ንብረት አልተቆጠረም፣ ሪፖርት አልተደረገም ሲባል…እኔ ከመጣሁ በኋላ እንጂ ከእኔ በፊት ያለውን አትጠይቁኝ በሚል የውሾን ነገር ያነሳ…አንድ ዓይነት ፈሊጥ የዝርፊያ አጋራቸውን ይከላከላሉ፡፡

ትላንት ትላንት ጴንጤው እንዴት ከኦርቶዶክስ ተቀየርክ? ሲባል ሰካራም በሆኑና ሥነ ምግባር በጎደላቸው አገልጋዮች ምክንያት ይሉ ነበር ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ ለመንጋው በማይራሩ ሌቦችና ቀጣፊ አገልጋዮች እንደሚሆን እርግጥ ነው፡፡

ስለዚህ ሰበካ ጉባኤ፣ ምዕመናን፣ሰ/ት/ቤቶች የቤተክርስቲያን የሥራ ኃላፊዎች ሲዘዋወሩ ኃላፊነትና ተጠያቂነት ባለው መልኩ እንዲሆን ድምጻችንን ማሰማት ያለብን ከመሆኑ ባሻገር፤ አለቆች ወይም አምስቱ ከለባት መልካም ሲሰሩ ደረጃቸው ከፍ የሚልብት፣ ሲማስኑ ደግሞ ከደረጃ ዝቅ ብለው የሚያገለግሉበት አሠራር መዘርጋት በጣም አስፈላጊና ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ ርእስ ለይቶ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን እንደማሳያ ማንሳት ያስፈለገው የአዲስ አበባው አስተዳደር መስተካከል ለየሀገረ ስብከቱ መስተካከልወሳኝ በመሆኑ ነው፡፡

በዚህ በእኛ ዘመን…በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ተዘግተዋል፣ተቃጥለዋል፣ፈራርሰዋል፤ በተዳከመ የቤተክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር ምክንያት ብዙዎች በሰማዕትነት ታርደዋል፣ ከእነ ሕይወታቸው ተቃጥለዋል፤ እርስ በእርሳችን በዘውግ፣ በጥቅም ተለያይተናል፣ በሦስት ፓትርያርኮች ለመመራት እየተውተረተርን ከመሆኑ በላይ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን ጥላሸት ለመቀባት የሚደረገውን ርብርብና ከፋፍሎ ለመግዛት በፖለቲከኞች በየጊዜው የሚሸረቡትን ሴራዎች ደምረንበት፤መረን የለቀቀውን ይሄንን አስተዳደራዊ ልሽቀት በጊዜ ማረም ካልቻልን ጸጸታችን መመለሻ የሌለው ይሆናል፡፡ ለቤተ ክርስቲያንና ለኢትዮጵያ ትንሣኤ ከባለ ሥልጣን እስከ ተራ የመንደር ዱርዬ በብዙ ማስፈራሪያና ዛቻ ተከበው ቀን ከሌሊት ሁሉ ነገራቸው ለሆነችው እናት ቤተክርስቲያናችን ለሚተጉ እነ መ/ር ዘመድኩን የመሰሉ ትጉህ የቤተክርስቲያን ልጆች እንቅስቃሴና ልፋት ከባድና አድካሚ የሚያደርገው ቤተክርስቲያን እየተመራች ያለችው ለመንጋው በማይራሩ፣ጨካኝ፣ ራስ ወዳድ፣ ሙዳየ ምጽዋት ገልባጮና መሸተኞች በሆኑ አምስቱ ከለባት መሆኑ ነው፡፡ የዚህ የጡመራ መድረክ አባላት ዓላማ የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች ከእኩይ ተግባራቸው ተመልሰው ለኢትዮጵያና ለቤተክርስቲያን ትንሣኤ በጋራ እንድንሠራ የማንቃት ሥራ ለመሥራት እንጂ ማንንም ለማሳጣት ወይም ለማሸማመቅ ባለመሆኑ እግዚአብሔር አመላክ ለእነዚህ የእናት ጡት ነካሾች ልብ ይስጥልን እንላለን!!!

በዚህ በጾመ ፍልሰታ እግዚአብሔር አምላካችን በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ከእነዚህ የእናት ጡት ነካሾች ቤተክርስቲያናችንን ነጻ እንዲያወጣልን በጸሎት እንጠይቅ፡፡

በሚቀጥለው ክፍል

ዘረኝነትና ማኅበራት(በውኑ ማኅበራት ከዘረኝነት የጸዱ ናቸው?) የሚለውን እንመለከታለን

ይቆየን!

በጩኸት፣በደባና በቡድንተኝነት ውሸት እውነት ሊሆን አይችልም!

መቼም ቤተ ክርስቲያን ያልወለደችው የለም! የዲጄው አሉላን ዓይነት አካይስትና ልቡሰ ሥጋ አጋንንት፣ እንደ ቅዱስ ዲዮስቆሪዮስ ከእውነትና ከእውነት ጋር ብቻ ወገንተኛ የሆኑ አቡነ ሩፋኤልን ዓይነት ቅን ልብ ያላቸው እውነተኛ አባቶች፣  እንደነ ‹‹ቀሲስ›› በላይ ጸጋዬን ዓይነት ዕውራነ ልብም ጉዳትን የሚጸንሱ፣ በደልንም የሚወልዱ ሆዳቸው ተንኮልን በማዘጋጀት የተካኑ በዚሁ ብቻ የሚኖሩትን አፍርታለች፡፡ቤተክርስቲያን የአደባባይ ብቻ ሁኖ የቀረው  ልቅሶአችንን ስትመለከት፣ በዚህ የቤተክርስቲያ የመከራ፣ የስደትና የሰማዕታት ዘመን እንኳ ሴረኞች ውስጥ ለውስጥ ሴራቸውን መቀጠላቸውን፤ ነጋዴዎችም ትርፍ በትርፍ መሆናቸውን፤ በአደባባይ ብቻ ለዓለም ሙተናል  ብለው የሚሰብኩን አባቶች የገዛ ወንድቸውን ለፍቅረ ሲመት ሲሉ ሸጠው በሹመት መንበሽበሻቸውን ስትመለከት ምን ትል ይሆን??? አሁን አሁን ኦርቶዶክሳውያን ለፍቶ አዳሪ እውነት ተናጋሪ መሆናችን ቀርቶ መስሎ አዳሪዎች ሁነን መኖሩ ሰምሮልናል፡፡ ይገርማችኋል ዛሬ አንድ ወዳጄን አግኝቼው ምን ባክህ የሲኖዶሳችን ስብሰባ እኮ አሁንም ልክ እንደ ድሮው ማንን እንሹም? ማንን እንሻር? ማንን ከሀገረ ስብከቱ እናፈናቅል?…ሁኖ እንደ ቀጠለ ነው አይደል? ብዬ በጨዋታ መካከል አነሳሁለት፡፡እንዴ የቅዱስ ሲኖዶስ ስበሰባ እኮ ተቋርጣል!ሐራ ላይ አላነበብክም እንዴ? እረ እነ እገሌም እነ እገሊትም… ፖስት አድርገውታል! አለኝ፡፡ እኔም በጣም የማከብረው ትልቅ ወዳጄ ስለሆነ ሰሞኑንም በሥራ ጫና ምክንያት ወደ ማኅበራዊ ሚዲያ ስላልጎበኘሁ እንዴ እውነት ተቋርጦ ይሆን እንዴ? ብዬ ጥርጣሬ ገባኝ፡፡ ከአሁን ከአሁን ተለያይተን ባረጋገጥኩ ብዬ ስመኝ ተለያየንና ምሳ ሰዓት ስለነበር አንድ የቅርብ ወዳጄ የሆኑ ብጹዕ አባት ጋር ስደውል…ወዲያው ነገሩ ገብቶአቸው ኖሮ አይ የእኔ ልጅ በቃ ሐራ ትጫወትባችኋለች አይደል? እረ እንደዚህ የሚባል ውሳኔ ከየት መጣ አሉኝ? በምጸት ንግግር፡፡

ከሁሉ የገረመኝ ዛሬ ይህን ጹሑፍ እስከጻፍኩበት ጥቅምት 20 ቀን 2012 ዓ.ም ሌላውን በሀሰትና መረጃና በተሳሳተ ዜና ሲኮንኑ የሚውሉት የሀሰት መረጃውን ያስተላለፉት አንዳቸውም ይቅርታ አሳስተናችኋል የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ እንደ ቀጠለ ነው አለማለታቸውን አስገርሞኛል፡፡በርግጥ ዲጄው አይፈረድበትም የጫጉላ ጊዜውን ስላልጨረሰ ይሆናል ብዬ ባስብም ወሬ አራጋቢዎቹ ግን ይቅርታ ባለመጠየቃችሁ እጅግ አፍሬባችኋለሁ፡፡

እኔም ደግሞ የተዘናጋሁት አንድ የዲጄው አሉላ ወዳጅ በቃ አሁን ላገባ ነው ሐራ ላይ አልጽፍም ብሎ መማል መገዘቱ አስረግጦ በነገረኝ ተዘናግቼ ነው!ለካ ድመት መንኩሳ….ነው ጉዳዩ! ስለ ዲጄው ካነሳሁ አይቀር ይገርማችኋል ቀኑ እሁድ ከቅዳሴ መልስ ነው መስከረም 25 ቀን 2012 ዓ.ም! አንዱ ወዳጄ ደወለልኛና ሽማግሌው፣ ወታደሩና ዲጄው እኮ ‹‹ለመንገደኛው ሁሉ ተክሊል በማደል ላይ ያለችው ቸርች›› ለእርሱም አሻረችው አለኝ፡፡ ለጥቂት ጊዜ ግር አለኝ፡፡ ቀጠለ እድሜ ለማኅበሩ ሽማግሌው(አንዳንዶች ዕድሜውን ከሃምሳ ሲያዘልሉት ሌሎች አይጠቅመውም ይላሉ) የታናሽ ታናሽ…ታናሹ ከምትሆን በሃያዎቹ መጀመሪያ ላይ ካለችው ወጣት ጋር መጋባቱን ፎቶ ላከለኝ፡፡ እኔም ጎሽ ቤተክርስቲያን ከአሉላ ዓይነት ብር አምላኩ እፎይ ልትል ነው ብዬ ደስ አለኝ፡፡ ትዳር ደጉ ስንቱን ገርቷልና ነው፡፡መቼም መንፈስ ቅዱስ ፊት ጸፍቶ አፍ ከፍቶ ያናግራል እንዲሉ የመርሐ ግብር መሪው መ/ር አስቻለው ከበደ እስከ ዛሬ አላምንም ብትሉም ቅዱሳን ፓትርያርኮችን፣ ብጹአን አባቶችን፣ አበው መነኮሳትን በአጠቃላይ ቤተክርስቲያኒቱን በአደንዛዥ ዕፅ እና በሲጋራ በተጨማለቁ ጣቶቹና አንደበቱ ያለ ማንም ከልካይ ሲሰድብ፣ሲያዋርድ ማሳቂያና መሳለቂያ ሲያደርገን የነበረውን ሰው ቤተክርስቲያን አክብራ(አንግሳ) የክብር ዙፋን ላይ እንዳስቀመጠችው አረጋገጠልን፡፡ልብ ያለው ልብ ይበል!!!

እዚህ ላይ ሌላው ትኩረቴን የሳበው ጉዳይ ደግሞ ሠርጉን ተከትሎ ያለስሙ ስም ሰጥተው በተሳዳቢነቱ ሊገስጹት ሲገባ ነገ የስድብ ውርጅብኝ ፍራቻ በሚመስል መልኩ በጥንቃቄ መመርመር የሚገባቸው ሙገሳ ሲያቀርቡ የዋሉትን ሰዎች ጉዳይ ነው፡፡ በመሠረቱ ጥቂት ጥገኛና አድርባይ ያልሆኑ ወንድሞችና እህቶች በስተቀር ሌሎች በአብዛኛው ፌስ ቡካቸው ላይ ሰውን ታጠቅ ታጋል ቤተክርስቲያንህን ጠብቅ የሚሉ በተግባር ግን ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት ከተሰለፉ የፌስ ቡክ አርበኞች ብፁዓን አባቶችን የሀገረ ስብከታቸውን ጭምር ስም በመጠቀም ጥል ከሚዘሩ በርካቶች በአደባባይ መምህር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ ነን! የሚሉ በተግባር ግን ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ የሚልከሰከሱ ውሾችን ከመከተል መቆጠብ አለብን፡፡

ከዚህ በኋላ ሐራውያንና በድብቅ ሦስት ወይም አራት አካውንት ከፍተው የሚንቀሳቀሱ ታዋቂ ነገር ግን የምዕመናን ሕይወት ቀጣፊ ሰባክያንን እንዴት እንደሚጫወቱብን በተከታታይ እንመልከታለን፡፡

ለአሁኑ ግን ቅድም እንደነገርኳችሁ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ረቡዕ ጥቅምት 12 ቀን 2012 የቀጠለ ሲሆን እስከ ዛሬ ድረስ ከዘጠኝ አጀንዳዎች በላይ ተመልክቷል፡፡ የዘንድሮውን ስብሰባ እንደድሮው ለመዘገብ የተቸገረው ዲጄው አሉላ ጥቅምት 13 ቀን ሰበር ዜና፡ቅ/ሲኖዶስ ስበሰባውን ሊያቋርጥ ነው ብሎ ከዘገበ በኋላ በ15 እና በ16 የአይነኬ አካላት አጀንዳ በመታየቱ ምክንያት ለመዘገብ ቢቸገርም እንደ ተለመደው ዛሬ ጥቅምት 20 ቀን 2012 ዓ.ም አቡነ ያዕቆብ ላይ አጣሪ ሆነው ከተመደቡት አንድ ‹‹ብፁዕ›› አባት በወንድማቸው ላይ በሠሩት አኩሪ ተግባር ያገኙትን ሹመትና ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ ከደቡብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ተነሱ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ተመደቡ! ብሎ አስነብቦናል፡፡

ሐራውያን እኩያንና የዲያብሎስ የግብር ልጅ ፍቅረ ነዋይ ወዳጅነታቸውን ለማረጋገጥ እስቲ ሰለ ሴራቸውና ለምን አቡኑን የማሳደድና ስማቸውን የማጠልሸት ተግባር ላይ ተጠመዱ የሚሉትን እናንሳ፡፡

ከጥቅምት 13 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ቅዱሳንና ብጹዓን አባቶች ያላሉትንና ያልወሰኑትን የአቡሃ ለሐሰት ልጆች ናቸውና ፈብርከው እውነተኞቹንና ብርቱ ተጋዮቹን እነ ዲ/ን ዓባይነህ ካሴን ጭምር ብዙዎች በየፌስ ቡኩ ሲቀባበለው ተሳስተን አሳሳትናችሁ እንኳን አላሉንም፡፡

ከዚህ በፊት እንደነገርኳችሁ ሐራውያንና መስሎ አዳሪ እስስት ሰባክያን ሁሉም ሰው ወርሃዊ ተቀላቢ ይመስል ዘወትር ቢሄድ በማያጣቸው በአምስት ኪሎው ውስኪ ቤት እና በአራ ኪሎዎቹ ካፌዎችና ሬስቶራንቶች ቃለ ጉባኤ ተይዞ ይጻፍበት አይጻፍበት ተብሎ ይወሰንብሃል ወይም ይወሰንልሃል፡፡በቃ የእነዚህ እፉኝቶት ተግባር ይሄው ነው፡፡ ይገርማችኋል ከቅ/ሲኖዶስ አጀንዳዎች አንዱ የኢየሩሳሌም ሀገረ ስብከት ነበር፡፡ እናላችሁ ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም ስብሰባው ላይ ባልተገኙበት ሁኔታ ከአንድ ቀን ተኩል በላይ  ቅ/ሲኖዶሱ በሸዋና በትግሬ ጳጳሳት መካከል የከረረ ጭቅጭቅ ውይይት አድርጎ መሸናነፍ ስላልቻለ(የጎጥ ጉዳይ መቼም ከባድ አይደል!) ከዚያ ሁሉ ውይይት በኋላ አስተዋይ በሆኑ ብፁዓን አባቶች አስታራቂነት እኔ ለማንሳት የማልፈልገው ያ ሁሉ ውንጀላና ክስ ብሎም አንዳንዱ ውግዘት የሚያስፈልገው ጉዳይ በሁለቱም በኩል በቃ በቃ ሊቀ ጳጳሱና አምስቱ መነኮሳት ይታረቁ ተብሎ እጅግ ወደ አስፈሪ ደረጃ ሊደርስ የነበረው ውይይት ተቋጨ፡፡ ሐራ ዘገበችው? እረ በጭራሽ!አፌን በዳቦ ብላ እልፍ! ለምን የኢየሩሳሌሙን አጀንዳ ደብቆ በማስቀረት ላለመዘገብ ተፈለገ? ብሎ አለመጠየቅ መንጋነት ነው፡፡ በእኔ እምነት ሊቀ ጳጳሱ በሌሉበት ሊቀ ጳጳሱን ሁነው የተሰይመው አንዱ ቡድን የሸዋ ስለነበር ሐራ ደግሞ ሸዋና እንትን መናፍቅ፣ ተሐድሶ፣ሙዳየ ምጽዋት ገልባጭ ቢሆን ምን ግዳቸው፡፡ አይነኬ ናቸው! እንደ ድመት እንትን ይሸፋፈንልሃል፡፡ ዛሬ ደግሞ እኚሁ ከጳጳሳት የማንም ቡድንተኛ ያልሆኑት የፈረደባቸው ሊቀ ጳጳስ ክቡር ዶክተር አቡነ ያዕቆብ አጀንዳ ይታይ ስለነበር ልብ ብላችሁ ካስተዋላችሁ ብፁዕነታቸው መልስ ሰጥተው የተወሰነው ከሰዓት 9፡00 ገደማ ነው፡፡ ሐራውያን የደቡብ አፍሪቃን ቤተክርስቲያን እንደ ቅርጫ ለመከፋፈል ላሰፈሰፉት የቤተክህነቱ አይጦች ጋር ቀሪ ያልተወራረደ ሂሳብ ስላላቸው አሁን ልገልጠው በማልፈልገው ሰው በኩል የአባቶችን እያንዳንዱን ንግግር በቀጥታ ስለሚከታተሉ ሳያስተውሉት አባቶች ገና ከስብሰባ ሳይወጡ 10፡00 አከባቢ ነው የለቀቁት፡፡

ይታይሃል ቤተክርስቲያን በእነማን እጅ እንደወደቀች? ሐራውያን ለምን በአቡነ ያዕቆብን ብቻ ለይተው ለማሳደድ ፈለጉ የሚለውንና በሁለተኛው ዙር አጣሪ ሆነው የሄዱት አካላት ምን ምን ተግባራትን ፈጽመው፤እነማንን አግኝተው ተመለሱ፣ የአጣሪዎቹን ግለ ታሪክ በማስረጃ አስደግፌ እስከማቀርብ ድረስ ብዙ በጥልቀት መግባት አልፈልግም፡፡ ነገር ግን ከአጣሪዎቹ መካከል የገዛ ወንድማቸውን ያው ከዚህ በፊት እንደሰማችሁት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ጠባቂ ለመሆን ካላቸው ከፍተኛ ጉጉት የተነሳ ውስጥ ለውስጥ 50 እና 100 ብር ከግንቦቱ ስብሰባ በፊት ለቀን ተማሪዎች በመስጠት መከራቸውን ሲያዩ መቆየታቸው ፀሐይ የሞቀው ሀገር ያወቀው ጉዳይ ነበር፡፡ ይህን ጥማታቸውን የተረዱት ሴረኞች ወጥመዳቸው ውስጥ ካስገቧው በኋላ በመጀመሪያ ሴራ ላይ የተሳተፉ የብዙ ሴረኞች ስም ከሚጠፋ እነ ሙጬን 58 ገጽ ሪፖርት ወደ 9 ገጽ አሳጥሮ ማቅረብና ሴረኞችን ሸፍኖ አብረው በአንድ ት/ቤት የተማሩ፣ በአንድ ገበታ የተመገቡ ተከራካሪ ቡድን የላቸውም የተባሉትን ወንድማቸውን አንዱን ስለ ብዙዎች አሳልፎ የመስጠት ፈሪሳዊና ቤተክህነታዊ ጠባይ ቅድሥት ሥላሴ ኮሌጅም እያሉ የሚታወቁበትና የኖሩበት በመሆኑ ምናልባት ነገ ብዙ መከራ የሚቀበሉበትን የኮሌጅ የበላይ ጠባቂነት ተሸለሙ ማለት ነው፡፡ ይሄ ካልተሳካ ደግሞ በትክክል ከደቡብ አፍሪቃውያኑ ቄሶች በነበረኝ የስልክ ምልልስ ማረጋገጥ እንደቻልኩት እኒህ ሊቀ ጳጳስ ይመደቡልን ዓይነት ሀሳብ ዙሪያ ሲሽከረከሩ መክረማቸውን ለመረዳት ችያለሁ፡፡

ለመሆኑ ሊቀ ጳጳስ ክቡር ዶክተር አቡነ ያዕቆብ ሐራውያን እንደሚስሏቸው ናቸውን? ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች የሰበሰብኩትን እነሆ

  • ብፁዕነታቸው በምንም መንገድ ክፉ  ያደረገባቸውን እንኳ አንድ ቀን በአደባባይ በክፉ የማያነሱ፣ የሌላውን በደል የራሳቸው አድርገው የሚሸከሙ፤
  • በጸሎታቸው በኢትዮጵያ በመላው አፍሪካ በርካቶች ከሰይጣን እስራት የፈቱ፣ልጅ ላልነበራቸው ለበርካቶች ልጅ እንዲወልዱ ምክንያት የሆኑ፣ በተግባር ዕውራን የነበሩትን ያበሩ፣ሽባ የተረተሩ በአጠቃላይ ጥቂት አሉን ከምንላቸው የጸሎትና የፈውስ አባቶች መካከል አንዱ መሆናቸውን ኢትዮጵያ፣ኬንያ፣ደቡብ አፍሪቃ…ያሉ ማንም ሰው ቢጠይቅ ለዚህ ሕያው ምስክር የሆኑ በርካታ ሺህዎችን በቀላሉ ማግኘት ይቻላል፤
  • በስም ሳይሆን በተግባር በተፈተነ መልኩ በተለይ በእንግሊዘኛ ቋንቋ በማስተማር፣ በመግባባትና በመሥራት ያሉና ከሚችሉ ከጥቂት አባቶች መካከል የሆኑ፤
  • በዘር፣በወንዝ፣በጎጥ ጨርሰው የማያምኑ በዚህ የማይታሙ ፍጹም በብትሕውና ሕይወታቸውን የሚገፉ፤
  • ለራሳቸው የተለየ የክብር ቦታና ከበሬታ እንዲሰጣቸው የማይፈልጉ፣ ሁሉንም እንደየ አቅሙ ተሸክመው ከሕጻናት ጋር እንደ ሕጻን፣ ከአዋቂዎችም ጋር እንደአዋቂ ሆነው ብቻ ሰው እውነተኛ የክርስቶስ ተከታይ ሆኖ ብቻ እንዲኖር እንጂ በአገልግሎት ዘመናቸው ሁሉ ለማንም ሸክም ያልሆኑ፣ ከምዕመናን ጥቅም ሰብሳቢና ፈላጊ ያልሆኑ ቤተ ክርስቲያኑቲ በምትሰጣቸው ደሞዝ ብቻ ለመኖር የሚሞክሩ፣ በልተው የማያስበሉ ምንም አይነት ከቤተክርስቲያን ገንዘብ የመንካት አባዜ የሌለባቸውና በዚህ ማንም ምንም ማስረጃ ማቅረብ የማይችል መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን

ከ Divinity College International መስከረም 24 ቀን 2012 ዓ.ም  በአመራር፣ በአስተዳደርና በስነ መለኮት የክብር ዶክትሬት( Honorary Doctrate) አበርክቶላቸዋል፡፡ከዩኒቨርስው ምንጮች ለመረዳት እንደቻልነው ከበርካታ ተወዳዳሪዎች መካከል ለክብር ዶክትሬቱ ያበቃቸው በሚመሯቸው አህጉረ ስብከቶች በማኅበረሰብ ልማት፣ ወጣት መሪዎችን በማፍራትና በማሳደግ ባበረከቱት አመርቂ የእግዚአብሔር ሥራ፤በማኅበረሰቡ ውስጥ ባበረከቱት አብሮና ተከባብሮ የመኖርና የሀገር ግንባታ ሥራ፣ አንጻባራቂ የሆነ የክርስትና እምነትን የማስፋፋት ተግባር፤ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን እምነት የማስተዋወቅና የማስፋፋት ሥራ እና በመላው አፍሪካ አብያተክርስቲያናት ሕብረት(AACC) በምክትል ፕሬዝዳትነት ባበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ምክንያት መሆኑን ነው፡፡

አሁን የሄዱት አጣሪዎች የእነ ሙጬን ሪፖርት ከ58 ገጽ ወደ 9 የመከመለስ ሥራ ከመስራታቸው በሻገር ከዚህ በፊት በእነ መጋቤ ሃይማኖት ቆሞስ አባ ጥዑመ ልሳን አዳነ ዘመን የተባረሩ የቀድሞ የሰበካ ጉባኤ አባላትን የእነ ገዛኸኝ አበበን በደቡብ አፍሪካ የእነ ማዘር ካባን ሪፖርት ብቻ በማቅረብ በደቡብ አፍሪቃ ያሉት ካህናት ነጋዴዎችና አገልግሎት በአግባቡ እንደማይሰጡ፣ቤተ ክህነቱ ለበርካታ ጊዜያት ለክስ ያመቸው ዘንድ መዋቅሩን የማፈራረስ ሥራ ማለት ሐራ እንዳለችው ለሦስት ጊዜያት ብቻ ሳይሆን ለበርካታ ጊዜያት የሚጠይቁትን ባለመፈጸም ያለ ሊቀ ጳጳስ ሁለት ወይም ሦስት ዓመት እንዲቆይ በማድረግ መዋቅሩን የማፈራረስ ሥራ ሠርተው ሲያበቁ የፈራረሰ መዋቅር ነው ያለው፤ አብያተ ክርስቲያናቱ አልተደራጁም፣ ሥራ አስኪያጁ ደካማ ነው፣ የደቡብ አፍሪካ ካህናትና ሰበካ ጉባኤ አባላት አንፈልጋቸውም ብለዋል ብሎ የምዕመናኑን የካህናቱን ትክክለኛ ምስክርነትና በተለይ አቡነ እንጦስ በአደባባይ ሰው በተሰበሰበበት ብፁዕነታቸው በደቡብ አፍሪካ ማንም ሊፍቀው የማይችል ትልቅ ታሪክ ነው የሰሩት! ብለው በአንደበታቸው የመሰከሩትን ገሸሽ አድርጎ ፍጹም ሐሰት የሞላበት ሪፖርት ማቅረብ ከጸሐፍት ፈሪሳውያን ክስ ተለይቶ የማይታይ ከመሆኑም በላይ እነዚህን ምዕመናን ከአባታቸው የመለየት ሥራ በመሥራታቸው ታሪክ ይፋረዳቸዋል! ተስፋሆሙ ለስዱዳን የሆነ መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ይዋጋቸዋል ብዬ አምናለሁ! በዚህ በውሸታቸውም ዋጋም ይከፍሉበታል ብዬ አምናለሁ፡፡

በመጨረሻም ብፁዕነታቸው ለቅዱስ ሲኖዶስ አበላት የተናገሯቸውን ንግግሮች አንስቼ ጽሑፌን ላጠናቅቅ፡፡

  • በመጀመሪያ ደረጃ ዕዳ በደሌንና ወንጀሌን ከ58 ገጽ ወደ 9 ገጽ ስላወረዳችሁልኝ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ፡፡(በርካታ አባቶች ቅዱስነታቸውን ጨምሮ ፈገግ ያስባለ ንግግር)
  • መቼስ እኔ በዚህ ጉዳይ ማድረግ የነበረብኝ ዝም ማለት ነበር፡፡ ምክንያቱም ክርስቶስ እንኳ ሲሰቀል አልተናገረምና፡፡ እኔ ግን የእናንተ የአባቶቼ አእምሮ እንዳይቆሽሽ ብዬ ብቻ ነው የምናገረው ደቡብ አፍሪቃውያንን በተመለከተ ይሄው እኔው ራሴ በዙሉ ወይም በቆ(ጦ)ሳ ቋንቋ እንዲተረጎም ያደረኩት የ14ቱ የቅዳሴያት መጽሐፍ፣ይኸው በ2008 ዓ.ም ወደ እንግሊዘኛ ተተረጎሞ እንዲታተም ያደረኩት ውዳሴ ማርያም፣ ቀሲስ በቀለ እነ ሙጬ ስሜን አጥተዋል ይጠየቁልን ብለው ለቅዱስነታቸው ያስገቡትና ለእኔ ግልባጭ ያደረጉት የእነ ሙጬን ተንኮልና ሴራ የሚያጋልጥ ደብዳቤ(ከፍ እያደረጉ መጻሕፍቶቹንና ደብዳቤውን እያሳዩ)፤ ደቡብ አፍሪቃውያን የሚጠቀሙበትን አብያተ ክርስቲያናትን በተመለከተ 33 ያደረስኩ ሲሆን በተለይ አምስቱ ታላላቅ ካቴዴራሎችን ለደቡብ አፍሪካውያን የገነባሁ እኔው ነኝ፡፡ሳውዝ አፍሪቃ ስደርስ ኢትዮጵያውያን የሚገለገሉበት የነበረ አንድ ቤተክርስቲያን ብቻ ሲሆን ወደ ዘጠኝ የሚደርሱትን አብያተ ክርስቲያናትንና ከ20 ሺህ ካሬ ሜትር በላይ በሚሆን ቦታ ላይ የካህናት ማሰልጠኛ ገዳም ገንብቼ ሁሉንም በግለሰብ ስም አሊያም በቦርድ ሳይሆን በኢ/ኦ/ተ/ቤ ስም እንዲመዘገቡ አድርጌአለሁ፡፡ ነገም እነዚህን አብያተ ክርስቲያናት በአግባቡ በጥንቃቄ የማስረክብ ሲሆን ለቅዱስ ሲኖዶስም ሪፖርት አቀርባለሁ፡፡ ከአራት ዓመት በፊት በሐሰት ክስ ከደቡብ አፍሪካ ተነስቼ ወደ ምስራቅ  አፍሪቃ ስላክ ከ30 ዓመት በላይ መንበረ ጵጵስና ያልነበረውን ኬንያ ግዙፍ መንበረ ጵጵስና ሠርቼ በግሌ ከተሸለምኩት ዘመናዊ መኪና ጋር አስረክቤአለሁ፡፡ በጅቡቲም በእነ አባ ዮናስ ዘመን የቅድስት ማርያምን ቤተክርስቲያን፤ በደቡብ ሱዳን ጁባም የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያንን አሠርቼ ያጠናቀቅኩ ሲሆን ከከፍተኛ ባለ ሥልጣናት መካከል አንዱ በጽኑ ደዌ ይሰቃይ የነበረ ወንድማችን ስለተፈወሰ በደስታ ወደ 4 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ሰጥቶን ተረክቤ ለምዕመናኑ አስረክቤአለሁ፡፡ በዛምቢያ፣በቦስትስዋና፣ በኢኳቶሪያል ጊኒ የተሰሩና በግንባታ ላይ ያሉትን ማየት ይቻላል፡፡አባቶች በተቻለ መጠን መለያየትን ከመዝራት፣ በሌላው ሀገረ ስብከት ጣልቃ ከመግባት ተቆጥበን እርስ በእርሳችን ተጋግዘንና ተደደጋግፈን ብንሰራ መልካም ይመስለኛል፡፡ከዚያ ውጪ ገና በጨለማው ዘመን ከዛሬ አራት ዓመት በሩዋንዳ ከኤርትራ የቅዱስ ገብርኤል ከኢትዮጵያ የመድኃኔዓለም ታቦት ይዘው ተለያይተው ይኖሩ የነበሩትን እግዚአብሔር ረድቶኝ በአንድነት እንዲያገለግሉ ማድረግ ችዬአለሁ፡፡
  • አባቶቼ አሁን የመደባችሁኝ ቦታ በርካታ የሌላ እምነት ተከታዮች ያሉበት ያልተደራጀ ቦታ ስለሆነ የምለምናችሁ በጸሎታችሁ እንድታግዙኝ ብቻ ነው፡፡አደራ አባቶቼ ቅድስት በሆነች ጸሎታችሁ አግዙኝ! ደቡብ አፍሪቃ ላይ ከአንድ ቤተ ክርስቲያን አሁን ወዳለበት እንዲደርስ የረዳኝ እግዚአብሔር ይረዳኛል ብዬ አምናለሁ፡፡
  • ቅዱስ አባታችን አቡነ ማትያስ ስላደረጉልኝ በጎ ነገር ሁሉ እጅግ አመሰግንዎታለሁ፡፡

በማለት ለእሳቸው ተብሎ የተፈጠረውን እስካሁን በስም የማናውቀውን ሀገረ ስብከት ማለቴ ነው ሩቅ ምሥራቅ ሀገረ ስብከት ፍጹም ትህትናና ታዛዥነት በተሞላበት መንገድ ምንም ሳያንገራግሩ ተቀብለው መውጣታቸውን አንድ ወዳጄ የሆኑ ሊቀ ጳጳስ ሌላው ቢሆን ስንት ግርግርና ጭቅጭቅ ነበረብን ብለው በአድናቆት አጫውተውኛል፡፡ለነገሩ በጩኸት በደባና በቡድንተኝነት ውሸት እውነት ሊሆን አይችልም! የበለጠ ደግሞ ነገ እውነታዎቹ ፍንትው እያሉ መውጣታቸው አይቀርም፡፡

የሆነ ሆኖ አሁንም ምንም እንኳን የተመደቡት አባት መልካም አባት ቢሆኑም በአሕዛብና በመናፍቃን ፈረጀ ብዙ ፈተናና ችግር ያለበትን የከንባታ ሀዲያ ሊቀ ጳጳስ ሀገረ ስብከታቸውን እንደያዙ በሪፖርት አቅራቢዎቹና በሐራ ተዋሕዶ መሠረት ፈረጀ ብዙ ችግር ወደ አለበት መመደባቸው ለደቡብ አፍሪቃ ምዕመናን ይጠቅም ይሆን? ውጤታማስ ያደርጋቸው ይሆን? ደምጹን ያለአግበባብ የቀሙት የደቡብ አፍሪካ ምዕመንንና ካህናት  ምን ይላሉ? የሚሉትንና ሌሎችንም የሰዎች አስተያየትና ከማጣራቱ ሂደት ጋር ያሉ የድምጽ፣የምስልና የወረቀት መረጃና ማስረጃዎችን ይዤ እመለሳለሁ!

እስከዚያው ግን ለሁለቱም ብፁዓን አባቶቼ መልካምና ስኬታማ የአገልግሎት ዘመን እመኝላችኋለሁ፡፡አሜን፡፡

ሳምኬት ነኝ

ጥቅምት 20 ቀን 2012 ዓ.ም

አልሰማችሁም እንዳይለን ምን እናድርግ?

እንዴት ከረማችሁልኝ ወዳጆቼ?

መቼም እንደምትረዱት እየገጠመን ያለው ችግር እንኳን ጽፈንና አውርተን አይደለም ጸጥ ብለን በተቀመጥንበትም የምናደምጠው ነገር ጆሮን ጭው የሚያደርግ ስለሆነ ሌላ ሸክምና ድካም ላለመጨመር ብለን ነበር እስካሁን ዝም ብለን የከረምነው፡፡ አሁን ግን በአንድ ጉዳይ ላይ ሀሳብን መግለጥ የሚያስፈልግ ስለመሰለን ይህችን ጽሑፍ ጻፍንላችሁ፡፡

ወዳጆቼ የጀመርነው ዘመቻ ጌዴዎን ገታ ያደረግነው በአንዳንድ ወዳጆቻችን ምክር መሠረት ለጊዜው ቢዘገይ መልካም መሆኑን ስለተመካከርን እንጂ ጅብ እንደነከሰው እንስሳ ከዚህ በፊት የነካካናቸው ጉዳዮችን ዘንግተን አይደለም:: እንዲያውም ይገርማችኋል ጽሑፎቹን ካነበቡ በኋላ የሚያውቁንም ይሁኑ የማያውቁን እውነተኛ የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች ያደረሱንልን ሸከማቸው የከበዱንና አእምሮን ወጥረውና አስጨንቀው የሚይዙ በደንብ የደለቡ ማስረጃዎችና መረጃዎች አውጡን… ልቀቁን… እያሉ አጨናንቀውናል፡፡ ዳሩ ቦ ጊዜ…ነው፡፡

ለዛሬ በየጊዜው ከሚታወጁ ምህላዎች ጋር በተያያዘ አንድ ሁለት ጉዳዮች ውስጤን እየኮረኮሩ አላስቀምጥ ስላሉኝ ነው ለመጻፍ የተገደድኩት፡፡ መቼም በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የታዘዘው የሦስት ቀን ምህላ ያልሰማ ክርስቲያን አይኖርም፣የወደፊቱን የማኅበረ ሥላሴዎቹ የሰባት ቀን የምህላ ጥሪ፣የጎንደር ፣የአክሱም …ችግራችን እስካልተፈታ ወደፊትም ይቀጥላል፡፡ እንዴት አሳለፍናቸው? ስለቀጣዮቹስ ምን እያሰብንነው?

በርግጥ አሁን ያለንበት ወቅት በማኅበርም ይሁን በግል ከልብ ሁነንና እርስ በእርስ ያሉን ልዩነቶችንና ጎራዎችን ወደ አንድነት በማምጣት ልንተጋበት የሚገባ ጊዜ ነው፡፡ ታዲያ ምህላዎቻችን ታላቁ ነቢይ ኢሳይያስ በምዕ 1፡ 15 ‹‹እጃችሁን ወደ እኔ ብትዘረጉ ዓይኔን ከእናንተ እሰውራለሁ፤ ልመናንም ብታበዙ አልሰማችሁም ፤ እጆቻችሁ ደም ተሞልተዋል፡፡››እንዳለ ፍሬ አልባና መልስ የማያስገኙ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ይፈልጋል፡፡ ብዙዎቻችን በተለይ ቤተክህነቱ አከባቢ ቅርበት ያለን አካላትእ ንደምናውቀው ክብር፣ ሀብትና ሥልጣን እሽቅድድም ላይ ያሉ ጥቂት በቡድን የተደራጁ ኃያላንና ራሳቸውን የቤተክርስቲያኒቱ አድራጊ ፈጣሪ አድርገው የሾሙ ብጹአን አባቶችን (ብዙዎቻቸው በሌላ ሰው ስም ወይም አካውንት የሚጠቀሙ ቢሆንም) እነሱን ጨምሮ ምህላ በታወጀባቸው ጊዜያት እንኳ የብዙዎቻችን የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን አለመዘጋታቸውን፣ ሃያ አራት ሰዓት ሊባል በሚችል ሁኔታ መስመር ላይ(online) መሆናችንና ከገንቢ ጽሑፍ ይልቅ አፍራሽ፤ ከማጽናናት ይልቅ በኀዘን ላይ ኃዘን የሚጨምር፣ ከሰላም ይልቅ ጥልና መለያየትን የሚሰብክ መሆኑን ስመለከት ለመሆኑ ቅዱስ ያሬድ ‹‹…እጅ ይጹም…›› ያለው የፌስቡክ እና የድኅረ ገጽ ተጠቃሚዎችን አይመለከትም እንዴ? ብዬ እንድጠይቅ አድርጎኛል፡፡

በእኔ እምነት እንደነዚህ ዓይነት ግብ ተኮር የሆኑ ምህላዎች ሲታዘዙ ኅሊናችንን በመግዛት አእምሮንና ጊዜን ከሚቆጣጠሩ የማኅበራዊ ሚዲያዎችና የመገናኛ ብዙኃን ማደንዘዣ ወሬዎች ካልተራቀ ብሎም ደግሞ ለእነዚህ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ይውል የነበረውን ገንዘብ መመጽወት እና ብዙውን ጊዜያችንን ከተንቀሳቃስ ስልኮቻችን ይልቅ የጸሎት መጽሐፍ የምንይዝበት ማድረግ ካልቻልን ምህላዎቻችን ፍሬ የሚያፈሩ ምላሽ የሚያስገኙ አይመስለኝም!!! ስለዚህ ከማኅበራዊ ሚዲያና መገናኛ ብዙኃን የድንዛዜ መንፈስ ወጥተን ለመለያየት በር የሚከፍቱ ወሬ አራጋቢነትን ተጸይፈን እውነተኛ የምህላ ሰዎች ልንሆን ይገባል እላለሁ፡፡

እዚህ ላይ ልብ ማለት የሚገባን ነገር መቶ ቀን የተማርነው የዓውደ ምህረት ትምህርት አሊያም በየወሩ በየአውደ ምህረቱ የሚዘጋጁት የሦስት ቀንና የአራት ቀን ልዩጉባኤያት ፍሬ አልባ ሁነው በአንድ መስመር የማህበራዊ ሚዲያ ጽሑፍ የምንረበሽ፣ መረጋጋት የሌለን፣ ፈሪና ወኔ አልባ እየሆንን መምጣታችንን ስመለከት ደግሞ ማህበራዊ ሚዲያ አንዱ የኦርቶዶክሳውያን ወኔ ሰላቢ ሆኖ አግኝቼዋለሁና ማኅበራዊ ሚዲያም ይሁን የመገኛ ብዙኃንን እንዴትና መቼ መጠቀም እንዳለብን መወሰኑ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው፡፡ከዚህ በተጨማሪ በዚህ ዙሪያ ጥናቶች ተሠርተው ኅብረተሰባችን ከተያዘበት ባርነት ነጻ የማውጣት ሥራ፣ ተደጋጋሚ ውይይቶችና ምክክሮች ማድረግ ይገባናል፡፡

ሁለተኛው ጉዳይ በራሳችን ዜጎች በኢትዮጵያውያን እየደረሰብን ያለው ወረራና ዓይን ያወጣ ቤተክርስቲያንንና ኦርቶዶክሳውያንን ጠል ዘመቻና ሰይጣናዊ ተግባር ስልታዊ እና ውጤት ተኮር በሆነ መልኩ ልንዋጋው የሚገባን መሆኑ እንዳለ ሆኖ ሌላ ዘመቻ የሚያስፈልገው ጉዳይ አለ፡፡ ይኸውም በመካከላችን ያሉ ልዩነቶችና ደካማ የቤተክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር መኖር ነው፡፡ መቼም ይህን ጉዳይ ሳነሳ ቅር የምትሰኙ ጥቅመኞች እንዳላችሁ ቢገባኝም እነዚህ ጉዳዮች ማንሳት ችግሮቻችንን ለመፍታት መነሻ ሰለሚሆን ማንሳቱ የግድ ነው፡፡

በመካከላችን ያሉ ልዩነቶችን መዘርዘሩ ለቀባሪ አረዱት ስለሚሆንብኝ ብዙም ለማለት አልፈልግም፡፡ ይሄ ደግሞ 365 ቀን ምህላ ብንይዝም እንዳንሰማ ያደርገናል ብዬ አምናለሁ፡፡እኔ ግን ተፈትቶ ባየው ደስ የሚለኝ በብጹአን አባቶቼ ውስጥ የማየው ዘርን፣ ወንዝንና ጥቅምን መሠረት ያደረገ ቡድንተኝነት ነው፡፡ በርግጥ ለዚሁ የተሰለፉ ማኅበራዊ ገጾች ልክ የጥቅምት 2012 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ተቋረጠ፣ አይቀጥልም…ምናምን እያሉ ሰው ግራ የሚያጋቡ፤ የበሬ ወለደ ወሬ በማመላለስ ብቻ በሚያገኙት ብር እቁብ የሚጥሉ፤ ሁልጊዜ የሲኖዶስ ስብሰባ በመጣ ቁጥር አጀንዳ የሚፈበርኩ የጨለማው ሲኖዶስ ቡድን አባላት በቃችሁ ማለታችን እንዳለ ሁኖ ማለት ነው፡፡

እውነቱን እንነጋገር ከተባለ በቅድስት ቤተክርስቲያን አባቶች፣ ሰባክያን፣ ዘማርያንና ማኅበራት መካከል ያሉ ልዩነቶች በሀገራችን ተዋሐዱ እየተባሉ እየተለመኑ ያሉ 107 የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አለ ብዬ አላስብም፡፡ ይህ ልዩነት የበለጠ እንዲሰፋ ደግሞ ቀን ከሌሊት ለእኩይ ተግባር የሚተጉ ራሳቸውን የቤተክርስቲያኒቱ የሕዝብ ግንኙነት ሓላፊዎች አድርገው የሾሙ ጥቂት ጥቅመኛ የቤተክርስቲያን መዥገሮች አሉ፡፡ በጣም የሚገርማችሁ ከጥቂት ጊዜ ወዲህ የቅዱስ ፓትርያርኩንና የብጹአን አባቶችን የዕንባ ጎርፍ በማየት አምላካችን በእነሱ ዕንባ ሊታረቀን ነው ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ወዲያው ደግሞ ሀገረ ስብከት ለመቀማማት፣ወደ ከተማ አሊያም ወደ ውጪ አህጉረ ስብከት ለመመደብ በብጹአን አባቶች መካከል የሚደረገውን ፍትጊያና መገፋፋት፣የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ጠባቂ፣ዲን …ማናምን ለመሆን የሚሸረበውን ሴራ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን የፍቅረ ነዋይ አምሮት መወጫ ለማድረግ የሚደረገውን ትርምስ፣ የሲኖዶስ ስብሰባ በመጣ ቁጥር ‹‹ታዋቂ›› ሰባክያንና ግለሰቦች በብጹአን አባቶች ማረፊያ ሲርመሰመሱ ስመለከት ቀደሞ በአባቶች ዕንባ መነሻነት የጨበጥኩት የመሰለኝ ተስፋ መልሶ እንደጉም ተኖ ይጠፋል፡፡ በሌላ በኩል ይህ አደረጃጀት፣ ቅንጅትና ስምሪት ምነው ለወንጌል አገልግሎት ቢጠቀሙበት ብዬ መቆጨቴ አልቀረም፡፡ በርግጥ በአባቶቻችን መካከል የምናያቸው ልዩነቶች ነቢዩ ሰሎሞን በምሳ16፡28‹‹ ጠማማ ሰው ጥልን ይዘራል፤ ጆሮ ጠቢ ሰው የተማመኑትን ወዳጆች ይለያያል፡፡››እንዲል የአባቶቻችን መለያየትና ቡድንተኝነት ምክንያት አንገተ ደንዳኖች፣ልቦናቸውና ጆሮአቸው ያልተገረዘ ጠማማና ጆሮ ጠቢሰ ዎች በአባቶች ዙሪያ መኮልኮላቸው ነው፡፡ ስለዚህ አባቶቻችንን የእነዚህ ጠማማና ጆሮ ጠቢ ኢ-ክርስቲያናዊ ማንነት የተላበሱ ሰዎችን ማንነት በማጋለጥ ልንረዳቸው ይገባል፡፡ በዚህም መንገድ አባቶቻችን አንድ ከሆኑ የቤተክርስቲያንና የሀገር አንድነትና ሰላም ይመለሳል፡፡ እኛም የማንም ጆቢራዎች ማላጋጫ አንሆንም ማለት ነው፡፡

የሰላምና የአንድነት አምላክ እግዚአብሔር ሰላሙንና ፍቅሩን ሰጥቶን ምህላችን በእርሱ ዘንድ የሚደመጥና መልስ የሚያመጣ እንዲሆን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን!

ሳምኬት ነኝ!

ተጻፈ ጥቅምት 17 ቀን 2012 ዓ.ም