ዘመቻ ጌዴዎን ክፍል 4 የቀጠለ…. የተራቡና የማይጠግቡ ጅቦች በደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያን

4. በደቡብ አፍሪካ አጣሪ ሆነው ተመደበው ስለነበሩ ግለሰቦች ማንነት

በመሠረቱ በመጀመሪያ አጣሪ ሁነው የተመደቡት ሦስት ልዑካን ሲሆኑ እሊህም አቡነ ማቴዎስ የመገናኛ ብዙሃን የበላይ ጠባቂ፣ ሊ/ማ ፋንታሁን ሙጬ እና መ/ሃ አብርሃም ገረመው ናቸው፡፡ ብጹዕ አቡነ ማቴዎስ ከልዑካኑ ጋር ከተጓዙ  ነገሩ ስለሚበላሽ አስቀድሞም ብጹዕነታቸው የተመረጡት በዓላማ ስለነበረ ማለት ቲም ዲዮስቆሪዮስ ስለሆኑ ከተመረጡ በኋላ ምክንያት ፈጥሮ ማስቀረት ስለሚቻል ማለቴ ነው፡፡ ከደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ ቪዛ ከተመታላቸው በኋላ ጥሩ ህልም አላየሁም፣ሊቀ ጳጳሱ ስልክ አላነሱልኝም እዚያ ሄጄ የማንም ዱርዬ መጫወቻ መሆን አልፈልግም ፣ቪዛ ቶሎ ስላልደረሰከአሜሪካ ጉዞዬ ጋር ስለተጋጨብኝ በሚል ተልካሻ ምክንያት ሆን ብለው ከአጣሪ ቡድኑ ጋር ሳይሄዱ ቀርተዋል፡፡ በመሠረቱ አቡነ ማቴዎስ ከተወለዱበት የምንጃር ሾንኮራዋ ምንታምር ቀበሌ ጀምሮ ከቤተሰባቸው ጋር የነበራቸው ያለመስማማት ጠባይ፣በመናገሻ አምባ ማርያም እያሉ የፈጸሙት ተግባር፣ ጳጳስ ከሆኑ በኋላ በመከራ ከታረቋቸው ለቤተሰቦቻቸው በገዙት የFSR አይሱዚ በንግድ ሥራ መሠማራታቸው፣አቧሬ አከባቢ በገነቡት ቤት የሚያስተዳድሩትን ‹‹የግል ቤተሰብ›› እንዲሁም ከሱማሌው የቤተክርስቲያንና የምዕመናን ቃጠሎና ስደት በኋላ አሞኛል በሚል ሰበብ ከሀገረ ስበከቱ ሸሽተው አዲስ አበባ የኢኦተቤ የመገናኛ ብዙኃን የበላይ ጠባቂ በብዙ ልመና ከሆኑ በኋላ የሚፈጽሟቸውን ተግባራት ስለማውቅ ብዙም አልገረመኝም፡፡ብጹዕነታቸው የሱማሌው ድንጋጤ አስካሁን ስላልለቀቃቸው እሳቸው ያላሳዩንን ጥብአት በቴሌቪዥን መስኮት እየቀረቡ ዘራፍ! ማለት ዋና ሥራቸው ሁኗል፡፡  ታዲያ የብጹዕነታቸውን መቅረት በፈጠረላቸው ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ደፋሮቹና ጅቦቹም ግብዣው የተላካላቸው አቡነ ያዕቆብ ከሚመሩበት ሀገረ ስብከት ቢሆንም ሁሉም እንደሚያውቀው የሄዱበትን የተንኮል(የሴራ) ድርጊት ለማከናወን  በመሆኑ ማለትም  ከኢትዮጵያው ሲኖዶስ ከእነ አቡነ ሳዊሮስ ከአሜሪካ ደግሞ ከእነ አቡነ ቴዎፍሎስ ጋር ነገር ለመተብተብ ስለማይመቻቸው ያረፉት እነ አባ አእምሮ ባዘጋጁላቸው ቦታ ነበር፡፡ እነዚህ ሁለቱ አጣሪዎች ምቹ የሰይጣን ፈረስነታቸውን ለመረዳት ማንነታቸውን ማወቁ አስፈላጊ በመሆኑ እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ፡-

ሀ. ሊቀ ማዕምራን ፋንታሁን ሙጬ

ከዚህ በፊት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በፈጸመ ታሪክ የማይረሳው እኩይ ተግባር ምክንያት በሐራውያን ‹‹መስኪድ አልባው እስላም›› ተብሎ የነበረው አሥር አለቃ ፋንታሁን ሙጬ በጥቅምት 2002 ዓ.ም በጊዜያዊነት የአዲስ አበባ ሥራ አስኪያጅ ሆኖ ተመርጦ ከገባ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ አብያተክርስቲያናት ሲሞናዊነት መደብ ይዞ እንዲሰራበት ሕጋዊ እውቅና የሰጠ የቤተክርስቲያን የምንጊዜም ጠላትና የተራቡና የማይጠግቡ የቤተክህነቱ ጅቦች ራስ ነው፡፡ እኔ ሰለ ፋንታሁን ብዙ ከማወራ የአሁኑ ሊቀጠበብት ዘሪሁን ሙላቱ(ዶ/ር) ፈታሒ በጽድቅ በሚል የብዕር ስም ባዘጋጃት ‹‹የሐውልቱ ሥር ቁማርተኞች›› ተብላ በተሰራጨችው እና እስከ እስር በዳረገችው አነስተኛ ባለ 50 ገጽ መጽሐፍ ከገጽ 9-23 ላይ አሥር አለቃ ፋንታሁን ሙጬን በአግባቡ ስለገለጠው ሙሉ ንባቡን ለእናንተ ትቼ በወፍ በረር ሙጬን(በነገራችን ላይ ቤተክህነት ውስጥ የእርሱን ስም መጥራት ያረክሰናል በሚል የሚጠሩት በአባቱ ስም ነው) ላስተዋውቃችሁ፡-

ዳሰሳ ዘአሥር አለቃ ፋንታሁን ሙጬ

 ‹‹ይህ ሥነ ምግባሩ የተበላሸ፣ ቀኖና ቤ/ክን ያፈረሰ፣ በወሲብ ቅሌትና በዝሙት ኃጢአት እግዚአብሔር ለማይድን በሽታ አሳልፎ የሰጠው ሲሆን …ይህ ግለሰብ ለዚህ የዋና ሥራ አስኪያጅነት ሥልጣን የሚያበቃው መንፈሳዊ ሕይወትም ይሁን ሥጋዊ ጤንነት እንዲሁም የስራ ልምድ የሌለው በመሆኑ ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን በሚሊንየሙ ድፍን አንደ ሺህ ዓመት ያላጋጠማትን ፈተና አሁን እየተጋፈጠች ትገኛለችና ብጹአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ካህናትና ምዕመናን በጸሎትና በጾም ሊያስወግዱት የሚገባ ልቡሰ ሥጋ ሰይጣን ነው፡፡…..››

  • የትምህርት ችሎታውም..‹‹..አቶ ፋንታሁን ሙጬ በቅድስት ሥላሴ በነበረው የትምህርት ቤት ቆይታው በጣም ሰነፍ ከመሆኑ የተነሳ 3ኤፍ የሚል ቅጽል ስም ወጥቶለት እንደነበር ..እስከ ዛሬ ድረስ በቅጽል ስምነት ይጠቀሙበታል፡፡…ሌሎች ነጻ የትምህርት ዕድል ማግኘት ሲገባቸው በኦስትርያ ቬና ያለች የሮም ካቶሊክ ቤ/ክን ት/ቱን ብትፈቅድለትም መማር ስላቃተው ይኸው ከ10 ዓመት ያላነሰ ት/ቱን መጨረስ አቅቶት እስከ ዛሬ ድረስ ሲዳክር ይገኛል….አቶ ፋንታሁን ሙጬም በኦስትርያ ቬና የካቶሊክ ቤ/ክን ዩኒቨርስቲ ሲቀላቀል የፈረመው ፎርም በካቶሊክ ቀኖና መሠረት ሚስት እንደሌለው ወደ ፊትም እንደማያገባ ውሉ ላይ በጣት አሻራው ፈርሞ ነበር ት/ቱን የጀመረው፡፡ ይሁንና እውነትና ንጋት እያደረ መጥራቱ አይቀርምና የኋላ ኋላ ሚስት እንዳለው የሚያውቁ ኢትዮጵያውያን መረጃውን ለካቶሊክ ቤ/ክን በፎቶ አስደግፈው አቀረቡ፡፡ እርሱም በግንባር ቀርቦ ሲጠየቅ ሚስቴ አይደለችም ወደ ፊት እኔም ማግባት አልፈልግም ይልቁንም የካቶሊክ ቄስ ነው መሆን የምፈልገው በማለት መሀላውን አጸናው፡፡….የእሱ ማምታታትና ማጭበርበር ያበሳጫቸው ምዕመናን ሚስቱ ኦስትርያ ቬና የምትመጣበትን መንገድ አመቻችተው እንድትመጣ አደረጉ…በነበራት የጉብኝት ጊዜ የህግ ባለቤቱ መሆኗን ገልጻለች የጉብኝት ጊዜዋን ጨርሳ ወደ ሀገሯ በመጣች ጊዜ እርሱም አብሯት መጥቷል፡፡ ከዚህ በኋላ ወዲያውኑ መርዝ በጥብጦ ስላጠጣት የሞቷ ቀን ተፋጥኗል፡፡…››
  • ‹‹…ሰብአዊነት የሌለው አቶ ፋንታሁን ሙጬ ሰብአዊ መብት የሚባል ነገር አላውቅም እስከ ማለት መድረሱ ድፍረት ቢሆንም እስከ አሁን ድረስ በዚህ ጨካኝና ደርግ ሰው ንጹሐን የቤተክርስቲያን አባቶች በረሀብ በእንግልት በመሰቃየታቸው…መቼም ሰውን በተግባሩ መሰየምና መግለጽ ስድብ ሳይሆን ባህርይውን ማብራራት እንደሆነ በተለይ በስነ ጽሑፍ የተሰማሩ ሁሉ የሚያውቁት የአገላለጽ ስታይል ነው፡፡አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ጴጥሮስን በአንድ ወቅት ሰይጣን ብሎ ገስጾታል፡፡የገሊላውን ሄሮድስን ደግሞ ቀበሮ ብሎታል፡፡ይህ ማለት በእንስሳቱ መመሰል ሳይሆን በእንስሳቱ ባሕርይ ሰዎቹን መግለጽ ነው፡፡…ስለሆነም መቼም ቅዱስ ሚካኤል የረገጠው ዲያብሎስ በአካል ገዝፎ በመልክ መስሎ በባህርይ ተስተካክሎ ሊመሰልልን ብቻ ሳይሆን ወክሎ ሰይጣንን ሊሰራ የሚችልም ተዋናይ ሰው ብንፈልግ ‹ሁሉም ሰው እረ ፋንታሁን ሙጬ አለልን› እንደሚል እርግጠኛ ነን፡፡…የላሜህ መንፈስ የተጸናወተው አቶ ፋንታሁን በነበረው ቆይታ ወለተ ገብርኤልና ወለተ ሚካኤል የተባሉ ሁለት እህትማማቾችን አገባችኋለሁ በማለት በሩካቤ እንደተገናኛቸው እርሱ ራሱ አንዳንዴ እየቃዠ የሚያወራ ሲሆን…››
  • ሥጋዊ ጤንነቱን በተመለከተ…አቶ ፋንታሁን ሙጬ ተስፋ የቆረጠ ስለተያዘበት በሽታ እንኳን ዛሬ ድረስ በቂ መረጃ የሌለው አጥፍቶ ጠፊ ነው፡፡ …አቶ ፋንሁን ሙጬ በትዳሩ ላይ ባደረሰው ከፍተኛ ደባ፣ ቅሌትና የወሲብ መዘዝ ብዙዎችን ወደ መቃብር አሳዷል፡፡ የዚሁ ክፉ ተግባሩ ዋንኛ ተጠቂ ደግሞ በባለቤትነት አግብቷት የነበረችው ባለቤቱ ወ/ሮ ሠናይት ነበረች ነፍሷን ይማረውና አሁንም በሕይወት የለችም፡፡ ሌሎች ከአራት ያላነሱ ጓደኞቹ ደግሞ ማለትም እንድን ሴት ለአራት ለአምስት እየሆኑ ይተኙ ስለነበረ…››
  • ይህም በእጅጉ የሚያሳየው ነገር ቢኖር አቶ ፋንታሁን ሙጬ ታዲያ እንኳን የቅድስት ቤተክርስቲያን ጉዳይ ሊያሳስበው ቀርቶ የራሱ  ጉዳይና ጤንነት የማያሳስበው ተስፋ የቆረጠ ሰው መሆኑን ብቻ እንረዳለን፡፡ 
  • የኢኮኖሚ አቅሙ …ይህ ሰው በላ አጥፍቶ ጠፊ ግለሰብ ከዚህ በፊት አይሰርቅም አይዋሽም እንድንል የሚያስችለን የኢኮኖሚ መሠረትም ሆነ አቅም አልነበረውም ዳሩ ግን አሁን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ጥሬ ገንዘብ ያለው ያለ አግባብ ብልጽግናን በአቋራጭ የተቆናጠጠ ወቅታዊ ባለጸጋ ሆኗል፡፡ ይህንንም የባለጸግነት መንገድ ያገኘው ባለው የስራ ልምድና የትምህርት ችሎታ ሳይሆን በዘረፋና በሙስና ነው፡፡
  • ፖለቲካዊ ሕይወቱ…አቶ ፋንታሁን ሙጬ የፖለቲካ ሕይወቱን የጀመረው እንዲህ በቀላሉ በቅርብ የሚገመት አይደለም በደርግ ዘመን ብላቴን ሄዶ የውትድርና ሳይንስ በመማር ከሰለጠነ በኋላ በሱሉልታ ከተማ መሳሪያ ታጣቂ ሆኖ ደርግን አገልግሏል፡፡ በኋላም የተጠቀሰውን ክላሽ መምሬ ጥበቡ ለተባሉ ቄስ ጎፋ ገብርኤል ቤ/ክን ወስዶ አስረክቧል፡፡ አቶ ፋንታሁን ሙጬ በደርግ ዘመን በነበረው ንቁ እግዚአብሔር የለሽ የፖለቲካ ምልከታው የሃምሳ አለቃነት ማዕረግን የተቀበለ ጨካኝ የደርግ ሰው ነው፡፡ ይህ ሰው በደርግ ዘመነ መንግሥት የእግዚአብሔርን ስም እንዳይጠራ ሰዎች ክርስትና እንዳያስነሱ በየቀበሌውና በየሰፈሩ ቤት ለቤት እየዞረ እግዚአብሔር የለም በሚል እወጃው ብዙዎችን አስክዷል፡፡ ለዚሁ ሥራው ከፍተኛ ተባባሪው ከነበረው በዚያን ጊዜው ጓድ ጌታቸው ጓዴ በአሁኑ ሊቀ ኅሩያን ጌታቸው ጓዴ ጋር የእግዚአብሔርን ስም ካህናት እንዳይጠሩ በስመ አብ …ቀርቶ በስመ ሌኒን ወማርክስ እክህደከ ኢምፔሪያሊዝም በማለት…ካህናት መስቀላቸውን እየጣሉ ሽጉጥ እንዲጨብጡ ቤ/ክንን እየዘጉ ቤተመንግሥት እንዲገቡ የወንጌል አገልግሎን እየናቁ የፖቲካው ባራኪና ተንታኝ እንዲሆኑ የበኩሉን ጥረት በማድረግ በተሰለፈበት የውትድርና መስኩ የ50 ዓለቅነትን ማዕረግ ከደርግ ተቀብሏል፡፡ በማለት ይገልጠዋል ሊቀ ጠበብት ዘሪሁን ሙላት(ዶ/ር)

ከጥቂት ጊዜ ወዲህ በተለይ ደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያን ላይ ከፈጸመው ደባ በኋላ

  1. በብጹዕ አቡነ ማቴዎስ የኢኦተቤ የመገናኛ ብዙሃን የበላይ ኃላፊ ቀድሞ ቃል የተገባለት ይሁን አይሁን ባላውቅም አዲስ ገንዘብ መብያ መስክ ይሆንልኛል ብሎ የቋመጠበትንና መልሼ አገኘዋለሁ በሚመስል ሁኔታ የኢኦተቤ የመገናኛ ብዙሃን ሥራ አስኪያጅነት ለማግኘት ከደቡብ አፍሪካ በሰበሰበው ዳጎስ ያለ ገንዘብ እየረጨ እንዳለ ለማረጋገጥ ችያለሁ፡፡
  2. እጅግ በጣም ያስደነቀኝ ሌላው ጉዳይ ደግሞ መጽሐፍ ‹‹ዮሴፍን የማያውቅ ንጉሥ ተነሣ›› እንዲል…እሱና ሎሎች የቤተክርስቲያን አይጦች በማኅበረ ቅዱሳን የሐመር መጽሔትና ቴሌቪዥን የተከበረ እንግዳ እየሆኑ የመቅረባቸው ጉዳይ ነው፡፡ ቤተክርስቲያንና አገልጋዮቿ ላይ ላይ ድብደባ፣ ቃጠሎና ሰይጣናዊ ፈተና ከሚያደርሱባት አክራሪ እስላሞች በላይ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትንና ጠቅላይ ቤተክህነትን በሙስና በዘረኝነት እነዲጨማለቅ በር ከፋች የሆነውን በልቶ የማይጠግበውን ጅብ አስር አለቃ ፋንታሁን ሙጬን ስለ ቤተክርስቲያን ተናጋሪ ማድረግ ምዕመናን ላይ ማሾፍ ይመስለኛል፡፡ በዚያ ላይ እርም ያለባቸውን እነ ፋንታሁን ሙጬ፣ የአዲስ ዘመኑ ሽጉጥ ታጣቂ፣ጫት ቃሚና አፋር ላይ የመኪና አድርሶ በገንዘብ ኃይል እስር ቤት ከመማቀቅ የተረፈውን ‹‹አፈ መምህር›› ተብዬውን  ስለ ቤተክርስቲያን ተናጋሪ አድርጎ ማቅረብ እርም ስለሆነ ለውጥ ያመጣል ብዬ አላስብም፡፡ ሙጬን የመጋበዙ ትልቁ ምክንያት የቆሸሸ ማንንቱን ለማጠብ የታቀደ እንጂ ስለ ቤተክርስያን ለመናገር ምንም ዓይነት ተነሳሽነት ብቃትና ቁመና ስላለው እንዳልሆነ ቀደምቱ የማቅ አባላት በደንብ ያውቃሉ፡፡ በዚህ ተከታታይ ክፍል እየቀረበ ባለው የማኅበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ መንግሥት ሊሰማን ይገባል! ሕዝቡ ሊነሳ ይገባል! እያሉ መንጫጫት ከንቱ ጩኸት ነው ባይ ነኝ፡፡ ምክንያቱም ከተናገሪዎቹ መካከል ጥቂቶቹ እጅግ የቆሸሸ ስብእና ያላቸው ተረፈ አካናውያን ናቸውና ነው፡፡ሰውን ልናታልል እንችላለን የቤተክርስቲያን ራስ ክርስቶስን ግን ማታለል አይቻልም፡፡ በኤር 40፡3‹‹…በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርታችኋልና ቃሉን አልሰማችሁምና ይህ ነገር ሆነባችሁ፡፡›› እንዲል በማስተዋል ሆነን ይሄ ሁሉ ፈተና በእኛ ኃጢአት፣ በደልና ክፋት እንዲሁም መለያየትና ዘረኝነት መጣብን! ብለን ንስሐ ከመግባት ጋር የተቀናጀ የመፍትሔ ሥራ መሥራት ይገባል እላለሁ፡፡

ማስታወሻ፡-ስለዚህ የመጽሔት፣የጋዜጣ፣የሬድዮና የቴሌቪዥን አዘጋጆች እባካችሁ! እባካችሁ! እባካችሁ!…የምትጋብዟቸው ሰዎች መለፍለፍ ስለሚችሉ ብቻ ነገር ግን ለቤተክርስቲን አንዳች የማይጨነቁ፤ ለመንጋውን ምንም ዓይነት ርኅራኄ የሌላቸውን የዘመናችን ፀሐፍት ፈሪሳውያን ከመጋበዛችን በፊት ከፍተኛ ጥንቃቄ ካላደረጋችሁ በርካታ እርም የሆነ ነገር አዝለው ስለሚዞሩ  ከመፍትሔና ከማሸነፍ ይልቅ የበለጠ ውድቀትን ለቤተክርስቲያን የሚያመጣ በመሆኑ ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን ጉዳይ በሙስና፣በዘረኝነትና በክፋት የሰለጠኑትን ሳይሆን እውነተኛ የቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ሰዎች መጋበዝ እንዲገባ መረዳት አለብን፡፡በመጽሐፈ ኢያሱ የተጠቀሰው በእኛም እንዳይደርስብን ማለቴ ነው፡፡

ኢያ 7፡11-12  ‹‹…ሕዝቡ በደሉ ከእነሱ ጋር የተማማልኩት መሓላዬን አፍርሰው እርም ካሉት ገንዘብ ወሰዱ ሰርቀውም ከገንዘባቸው ጋር ጨመሩ፡፡ እንግዲህ ወዲህ የእስራኤል ልጆች በጠላቶቻቸው ፊት ቆመው መዋጋት አይችሉም፤የተረገሙ ሆነዋልና ጀርባቸውን መልሰው ይሸሻሉ አሁንም የተረገመውን ሰው ከእናንተ ለይታችሁ ካላወጣችሁ እንግዲህ ወዲህ ከእናንተ ጋር በረድኤት አልኖርም፡››

በርግጥ በማኅበሩ ቴሌቪዥን የተነሳው ርእሰ ጉዳይ አጅግ አስፈላጊ፣ ጊዜውን የጠበቀና በደንብ የተጠናና የተደራጀ መፍትሔ የሚፈልግ እንደሆነ እሙን ነው፡፡ ዛሬ ዛሬ እንዲያውም ቅድስት ቤተክርስቲያንን ከውጪው ፈተና ይልቅ ከውስጥ በሰው አሳማዎችና ጅቦች እየገጠማት ያለው ፈተና እጅግ የበረታ ነው፡፡ የውጪውንስ አውግዘን፣ ጽፈን፣ ሲብስ ደግሞ ተዋግተንም ቢሆን ድል እናደርጋለን የውስጡን ግን ለመዋጋት እልህ አስጨራሽ ነው፡፡ አሁን ለምሳሌ ፋንታሁን ሙጬ ብንወስደው ብዙ ተስፋ የቆረጠበት ነገር ስላለ ሰለምንም ነገር ተናገር ብትሉት በጣም ደፋር ስለሆነ የሐሰት ካባውን ግጥም አድሮጎ ለብሶ ማውራት ይችላል፡፡ እንዲህ ዓይነት ሰዎች ደግሞ አጥፍቶ ጠፊዎች ስለሆኑ ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን የትኛውንም መስዋዕትነት ሊከፍሉ የሚችሉ ክርስቲያኖችን ጥበብ በጎደለው መልኩ እንዲጓዙና ያልተገባ መስዋዕትነት እንዲከፍሉ ሰለሚያደርጉ እንጠንቀቅ የታናሽነት ምክሬ ነው!!!

ዳሰሳ ዘሐዲስ ሃሳማ አብርሃም ገረመው

ከእድገቱ ከ‹‹ሎኮ›› የገጠር መንደር ጀምሮ የሚያውቁት አንዳንድ ወንድሞች እንዲሁም ከየኔቢጤነት የማይተናነስ የአምስት ኪሎ ቅድስት ማርያም ደጅ ጠኚነት ሕይወቱን የሚያውቁት አባቶች ሁሉም በአንድ ቃል የነገሩኝ አዲሱ አሳማ አንዳንዶች ደግሞ ሲራመድ ሲገላበጥ ሲያዩት ዶልፊኑ እያሉ የሚጠሩት አብርሃም እንዴት ከትህትና ወደ አሳማነትና ወደ ጅብነት እንደተሸጋገረ እንደሚያደንቁ ነው የሚነግሩኝ፡፡ እኔም ቅድስት ሥላሴ ከመግባቱ በፊት ስለማውቀው ምንም እንኳን ደቡብ አፍሪካ ለመሄድ ሲል ራሱን የሆሳዕና ሰው ለማድረግ የሚያደርገው ጥረት እንዳለ ይቀመጥለትና እኔ የሱን ታሪክ የማውቀው ሎኮ ተወልዶ ቡታጅራ ማደጉን ነው፡፡

መስሎ አዳሪው አዲሱ አሳማ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ጸሐፊ እንደመሆኑ መጠን ከደመወዙ በተጨማሪ ምናልባት ለሁላችንም የሚገርመን ሐራ ዘተዋሕዶ ለአደባባይ ሊውሉ የማይገባቸውን ጭምር ዝርዝር የቅዱስ ሲኖዶስ መረጃዎች የጠዋትና የከሰዓት ውሎ እያለች እንድታቀርብ ያስቻላት አዲሱ አሳማ እየተከፈለው በዘመናዊ መሳሪያ ታግዞ በሚያቀብላቸው መረጃ እንደሆነ ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡ ከሁሉ በላይ ግን በጣም ያሳዘነኝና ያሳሰበኝ ትልቁ ጉዳይ የወደፊት ትዳሩ ጉዳይ ነው፡፡ ለምን በዚህ ዕድሜው አላገባም? ምን ቸግሮት ይሆን? እያልኩ ያሳስበኝ ነበር፡፡ለካ ነገሩ ወዲህ ነው ዝርዝር መረጃውን ወደ ፊት አስፈላጊ ሆኖ ከታመነበት የማስነብባችሁ ቢሆንም አብርሽ ለካ በወይዘሮነት ይታማ ኖሯል፡፡ 


ምን ዓይነት መጠጋጋት ነው??

ታዲያ አዲሱ አሳማ ለምን በደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያን ላይ ትኩረት አደረገ?

አዲሱ አሳማ ደቡብ አፍሪካ እንደደረሰ ከሊቀ ጳጳስ አቡነ ያዕቆብ የቀረበለት ጥያቄ ምነው በሕማማቱ መጣችሁ? የሚል ነበር በቦታው ላይ የነበረ የመረጃ ምንጬ እንደነገረኝ መልሱ‹‹ ብጹዕ አባታችን ሰው ስለሌሎት ነው! ሰው ቢኖሮት እኮ ይሄ ጉዳይ እንኳን ወደዚህ ሊያስመጣ ጭራሽ አጀንዳም መሆን አይችልም›› የሚል ነበር መልሱ፡፡ ያው ከዚህ መልስ የምንረዳው የማጣራቱ ሂደት ግብ ተኮርና ሳይጣራ ያለቀ ሪፖርት እንደተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ተጨማሪ ማረጋጋጫ የሚሆነው ደግሞ ሙጬ ጆሐንስበርጎችን ሲያወያይ ንግግሩን የጀመረው በኮራትና በጀብደኝነት ስሜት ውስጥ ሆኖ ‹‹ሐራ ላይ የወጣውን አላነበባችሁም እንዴ?›› በሚል መሆኑ ከላይ ያነሳሁትን ሀሳብ ያጠናክርልናል፡፡ አዲሱ አሳማ በጣም ጉደኛ ከመሆኑ የተነሳ በአሁኑ ወቅት በሴረኞች እየታመሰ ያለው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ  ከዚህ በፊት የቀን መደበኛ ደቀ መዛሙርት ባሳተሙት ‹‹ባለቤት ያልነበረው መንፈሳዊ አልባው ኮሌጅ›› በሚለው መጽሔት ላይ እንደተገለጠው  ቋሚ ሲኖዶስ  ታኅሳስ 24 ቀን 2011 ዓ.ም ያየውን ጉዳይ ጥር 08 ቀን 2011 ዓ.ም በድጋሚ እንዲያይ ምክንያት የሆነው አዲሱ አሳማ ብር ተቀብሎ ቃለ ጉባኤው ቀሽቦ በወቅቱ የቋሚ ሲኖዶስ አባላት የሆኑት ብጹአን አባቶች ያልወሰኑትን ያልተነጋገሩበትን ጉዳይ ቃለ ጉባኤው ላይ ያሰፍርና ያስፈርማቸዋል፡፡ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ በአዲሱ አሣማ የተፈጸመውን ነውረኛ የቃለ ጉባኤው ቅሸባ ስለደረሰቡት በ08/05/11 ዓ.ም ቀሻቢውን አሣማ ልክ ልኩን በመንገር እንደገና አስወስነዋል፡፡፡ በዚህ ዓይነት አዲሱ አሳማ ገንዘብ እየተቀበለ የስንት ሀገረ ስብከቶችና አብያተክርስቲያናት ቃለ ጉባኤ ቀሽቦ ይሆን?

ከላይ ወዳነሳሁት ጥየቄ ለመመለስ አዲሱ አሳማ ወደ ደቡብ አፍሪካ ይሄዳልተብሎ ወደ ደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ ስም ዝርዝራቸውና ፋይላቸው ከተላከላቸው ስድስት አገልጋዮች መካከል አንዱ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ በቅርበት ላነጋገሩት ሰዎች ሁሉ መልሱ ‹‹ሊቀ ጳጳስ አቡነ ያዕቆብ ሕይወቴን አበላሹብኝ እሠራላቸዋለሁ ነበር›› ይህ ቁጭቱንና እልሁን የሚያውቁት እነ አቡነ ሳዊሮስ ለእኩይ ሴራቸው ሁለተኛው ምቹ የዲያብሎስ ፈረስ እንደሚሆንላቸው በማመናቸው አጣሪ ቡድን ውስጥ አካተቱት፡፡

ከዚህ በፊት አጣሪ ሆኖ ባጠፋው ከፍተኛ ስሕተት ዘመድኩን የሰጠው አስተያየት

እሱም በእስትፋሰ ዲያብሎሱ ታደሰ ወርቁ የተጻፈውንና በእነ አቡነ ቴዎፍሎስ የተቀነበበውንና አዲስ አበባ በተመለሱ በሶስተኛው ቀን ገቢ ያደረጉትን ባለ 58 ገጽ ሪፖርት እውነት ነው! አይኔን ግምባር ያድርገው! ብሎ ፈረመ፡፡ ከእነ አባ እእምሮና ከእነ መቶ አለቃ ንብረት የሰበሰበውን ዳጎስ ያለ እጅ መንሻ ምናልባትም በወይዘሮነቱ የሰበሰባትን ብር አንድ ላይ አድርጎ መሰለኝ ከደቡብ አፍሪካ መልስ ጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ አኬልዳማ ቪትዙን ገዝቶ ሲለማመድ እንደነበረ በኋላም በሁኔታው አበደ እንዴ አዲሱ አሳማ? በማለት ተገርመው እረ ባክህ ቢያንስ ልምምዱን እንኳ ከዚህ ውጪ አድርግ ብለው ስለመከሩት መኪና ልምምዱን አጧጥፎታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለፈጸመው አኩሪ እኩይ ተግባር የተሸለመው ግዙፍ ቴሌቪዥንና አንዳንድ ኤሌክትሮኒክሶችን ለመሸጥ ከዚህ በፊት ደቡብ አፍሪካ ደርሰው የመጡ ሰባክያንን እንዲያሻሽጡት ላይ ታች ሲል መከረሙን አውቃለሁ፡፡

አብርሽን በተለይ የኋላ ማንነቱን ስለማውቅ በግሌ ስለሚያሳዝነኝ ከእነዚህ የተራቡ ጅቦች መንጋጋ ወጥቶ ከእሪያነቱ በንስሐ እንዲመለስ እመኝለታለሁ፡፡ የቅርብ ጓደኞች ነን የምትሉ ደግሞ ቢያንስ እኛንም ራሱንም ከሐሜት ማዳን እንዲችል ወደ ሕግ(ትዳር) እንዲገባ እንድታበረታቱት ልመናዬን አቀርባለሁ፡፡

5. ሐራ ዘተዋሕዶ በደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያንና በሊቀ ጳጳሱ ላይ ያደረገችው ዘመቻ

ከዚህ በፊት ባሉት ክፍሎች ስለ ሐራ ዘተዋሕዶ ጸሐፊዎችና ማንነት በመጠኑ ያስነበብኳችሁ ይመስለኛል፡፡ ካለነበባችሁት ግን ከዚህ ጽሑፍ በፊት የቀደሙትን ክፍሎች ማንበቡ ለግንዛቤ ይረዳል ባይ ነኝ፡፡ ሐራውያንን በደንብ ለመረዳት እንዲቻላችሁ በሐራውያን እጅግ የተብጠለጠሉትን ብጹዕ አቡነ ያዕቆብንበእጅጉ የተሞካሹትን ብጹዕ አቡነ ዲዮስቆርዮስን በንጽጽር ማየት ምን ያህል በይሁዳዊ፣ በሲሞናዊና በተቀናጀና በተሰናሰለ መልኩ አስተዳደሯን ከማዳከም ጀምሮ መሠረተ እምነቷን እሰከ መበከል እንዴት እንደተሠማሩ ለመረዳት ይረዳልና እነሆ፡-

ብጹዕ አቡነ ዲዮስቆርዮስ በሐራውያን እይታ

ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር ስላላቸው ግንኙነት ሐራውያን ምን እያሉ ዘገቡ?

·         ሰበር ዜና – ፓትርያርኩ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቡነ ዲዮስቆሮስን አገዱ March 20, 2019

አቡኑ ከሐራውያን ጋር እጅና ጓንት ሆነው የሚሠሩ በመሆናቸው እሳቸውን የሚመለከቱ ጉዳይ ኮሽ ባለቁጥር ዴጄውን ጠርተው ቅዱስነታቸውን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ አሰድበዋል ሰዎች የጥላቻ መንፈስ እንዲኖረው ጠንክረው በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ቅዱስነታቸው ደግሞ አሁን የእኔ ተራ ነው በሚል ይመስላል መያዣ መተንፈሻ እስኪያጡ ድረስ ብጹዕነታቸውን በማሳደድ ላይ ናቸው፡፡ በርግጥ የቤተክህነቱን የሦስት ዓመት የአደባባይ ሙገሳ፤የማጀት እና የጓዳ ሙስና የሚያውቁ የቤተክህነቱ ሠራተኞች ገና ይተፏታል በማለት ላይ ይገኛሉ፡፡ አሁን የሠሩትን ጉድ ሁሉም እየተረዳ ነው ባዮች ናቸው፡፡ ከሀገር ለመውጣት በዝግጅት ላይ እንዳለች የምትታማው የሂሳብና በጀት መመሪያ ኃላፊዋ ወ/ሮ ጽጌረዳ ዓለሙን ወደ ቤቶች አስተዳደር ያዛወሩት አልተሳካም እንጂ ጉዳቸውን ለመሸፈን እንደነበር የሚናገሩ በርካቶች ናቸው፡፡ በነገራችን ላይ ቅዱስ ፓትርያርኩ ፈሊጥ ያለውና ከቂመኝነት የጸዳ አካሄድ ተጠቅመው ለቤተክርስቲያን ወገንተኛ ሆነው የቂም ፈጻሚ ጀሌዎች ሳይሆን ባለሙያዎችን አጣሪ ውስጥ አካተው የማጣራቱን ሂደት ቢያከናውኑ ለጆሮ የሚዘገንኑ ብዙ ጉዶች ሊገኝበት እንደሚችል እሙን ነው፡፡ ከላይ ላነሳሁትን ርእሰ ጉዳይ ማሳያ የሚሆነው ከኃላፊነታቸው ከወረዱ በኋላ እንኳ

  • ‹‹በሕገ ወጥ መንገድ በእኔ ላይ የተሰጠውን የማጣራት ትእዛዝ ስለመቃወም ይመለከታል››

በማለት የጻፉት ደብዳቤ ለዚሁ ማሳያ ነው፡፡

በእኔ እምነት ምንም ችግር የሌለበት የሥራ መሪ ሥራህ ይገምገም ቢባል ደስተኛ ሆኖ መቀበል ነበረበት፡፡ ለመልካም አፈጻጸማቸው ሽልማት መሸላማቸው በሳቸው መጀመሩን አዳንቀው እንደጻፉ የስራ ኃላፊ ከሠራ በኋላ መገምገሙን መቀበል የእውነተኝነታቸውና የሥራ ሰው መሆናቸውን ማሳያ በሆነላቸው ነበር፡፡ ዳሩ ምን ያለበት ምን አይችልም ይባል የለ! አንዳንዶች ምናልባት እዚህ ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ አጨብጭቦ ሸልሞ የሸኛቸውን ለምን ይጠየቃሉ? ይሄ ግን አያስኬድም ምክንያቱም ቅዱስ ሲኖዶስ የተነበበለትን ሰማ እንጂ ገለልተኛ አካል ያጣራውን ሪፖርት አልሰማ! በዚያ ላይ የውስጥ አዋቂ ምንጮቼ እንዳስርዱኝ የቅዱስነታቸው ይጣራ ማለት ያስኬዳል ለማለት የሚከተሉትን ነጥቦች ያቀርባሉ፡፡ ፍርዱን ለአንባብያን ትቼአለሁ፡፡

  • አቡነ ማርቆስ ብጹዕ ሥራ አስኪያጁ ሪፖርት ሲያቀርቡ እንዲህ ሠርተናል ይሄን አስመልሰናል ሲሉ ‹‹የበላ ያስመልሰዋል›› ብለው ማፌዛቸው የሚያውቁት ነገር ስላለና የእሳቸውን ጨምሮ፣አዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና ሌሎች ሀገረ ስብከቶች ለተፈጠሩ ሁከትና ብጥብጥ ከአቡነ ሳዊሮስ ጋር ሆነው እጃቸው ስላለበት ስለተናደዱና የሚያውቁት ነገር ስላለ ነው የሚሉ አባቶች አጋጥመውኛል፡፡
  • ከዚህም በተጨማሪ እነ ታዴና ዲጄው አሉላ የአቡኑ የብሎግ ክንፍ በመሆናቸው ከሀገር አቀፍ የሰላምና ስብከተ ወንጌል ስምሪት ብቻ አንኳ አስከ 170 ሺሕ ብር እንደተቋደሱ በወቅቱ የኤፍሬም ውስኪ ቤት የቅርብ ጊዜ ትኩስ ዜና እንደነበር አውቃለሁ፡፡
  • ከላይ አቡነ ማርቆስ እንዳሉት ሁለቱ መንትያ ሕንጻዎች በእሳቸው ዘመን ማብቂያ በሌሎች አባቶች ጥረት ቢመለሱም በአንጻሩ ደግሞ በርካታ የሚሆኑ የኪራይ ቤቶች ወደ ግለሰቦች ይዞታ ማለት ለስሙ ለቤቱ ትንንሽ ብሮችን በኪራይ መልክ ይክፈሉ እንጂ እስካሁን ወደ ቤተክርስቲያኒቱ ካዝና ያልገባ ቁጥሩን መጥቀስ ያልወደድኩት በርካታ ሚሊዮን በሚደርስ ብር እንደተቸበቸቡ ከቤተክህነቶቹ የቤት ተጠቃሚዎች ሳይቀር ሰምቻለሁ፡፡ በቅርቡ የቀሲስ ሽመልስ ቢሮ መታሸጉም ለዚሁ ይመስለኛል፡፡
  • የሒሳብና በጀት ኃላፊዋ ወ/ሮ ጽጌረዳ ዓለሙ በደብረዘይት እያስገነቡ ያሉት ባለ G+4 ሕንጻ እና ራሱን የአቡኑ የእንትን ደላላ መሆኑን በቀረጸው የአቡነ ድምጽ እዚያው ጉደኛ ኤፍሬም ውስኪ ቤት ሲያስረዳ የነበረው ዳዊት ታደሰ የፎቅ ባለቤት መሆኑ ስመለከት እውነትም የበላ ያስመልሰዋል የሚለውን የአቡነ ማርቆስ ሀሳብ እንድጋራ አድርጎኛል፡፡
  • ከዚህም በተጨማሪ በማንም ይጻፍ በማን የእኔ ጉዳይ ባይሆንም በሊቀ ጳጳስ አቡነ ዲዮስቆሪዮስ ተጻፈ የተባለው ‹‹ፍኖተ ጽድቅ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ›› በኮታ የመሸጥ ግዴታ ላለባቸው የአዲስ አበባ አድባራትና የሳሚ ሮቶ ትንሣኤ ማተሚያ  እንጂ ለመጽሐፍ ሻጮች ሳይሰራጭ የመቅረቱ ጉዳይ አስራ ምናምን ገጽ አከባቢ ከመናፍቃን መጽሐፍ የተገለበጠ መሆኑንና ‹‹መጽሐፉ የእኔ ነው›› ባይ በመምጣቱ መሆኑን ስሰማ አባቶቻችን ምን ነካቸው? ማለቴ አልቀረም፡፡በዚሁ ግን በሁለተኛ ዕትሙ ላይ ታርሞ እንደሚወጣ አምናለሁ፡፡ለመናዬንም ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የማጣራት ሂደቱን አጠናክረው ቢቀጥሉ ሌቦችና ወንበዴዎችን ከቤተክርስቲያናችን ለማጽዳት ይረዳል ባይ ነኝ፡፡

ብጹዕ አቡነ ያዕቆብ በሐራውያን እይታ

ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር ያላቸው ግንኙነት ሐራውያን ምን እያሉ ዘገቡ?

ሁሉንም አክባሪ በመሆናቸው አንድ ቀን እንኳ ከፓትርያርኩ ጋር እንኳን የደብዳቤ ምልልስ፣ እንኳን በአደባባይ መስደብ ማሰደብ ቀርቶ ክፉ ደግ እንኳ ተነጋግረው ስለማያውቁ ምንም የጻፉት ነገር የለም፡፡

ብጹዕ አቡነ ዲዮስቆሪዮስ

በሚያስተዳድሩት ሀገረ ስብከት ምን ክስ ቀረበባቸው? ለምንስ ተዳፍኖ ቀረ? አቡነ ዲዮስቆርዮስ ከሀገረ ስበከታቸው አስተዳደር ጉባኤ ጭምር ክስ እያለባቸው በመሠረቱት ቲም ዲዮስቆርዮስ ምክንያት ጉዳዩ ተዳፍኖ እንዲቀርና በብልጠት ‹‹ለነፍሴ አስጋለሁ፣ ወደ ሀገረ ስብከቴ መሄድ አልችልም›› ብለው በስርዋጽ አጀንዳ በማስገባት የቅርሳ ቅርስና የቤተ መዘክር መምሪያ የበላይ ጠባቂ ለመሆን ጥረት ቢያደርጉም ስለ እውነት የሚተጋውና የሚለፋው ወዳጄ ዘመድኩን በቀለ ግን እውነታውን እንደሚከተለው አፍረጥርጦታል፡፡

ብጹዕ አቡነ ያዕቆብ

በሚያስተዳድሩት ሀገረ ስብከት ምን ክስ ቀረበባቸው? ለምንስ ተጋነነ?

በአንጻሩ አቡነ ያዕቆብ ሰው(ቲም) ስለሌላቸው ብቻ ከሚያስተዳድሩት አብያተክርስቲያናትና ሰበካ ጉባኤ አንድም ክስ ሳይቀርብባቸው ከማያስተዳድሯቸው ከእነ አባ አእምሮ ለእነ ዲጄው አሉላና ለተራቡና ለማይጠግቡ ጅቦች ለእነ ሙጬ የሀገረ ስብከቱን የገንዘብ ፍሰት በባንክ ሲስተም እንዲተሳሰር ስላደረጉት ለመብላት አመቺ ስላልሆነ ብቻ በሐራዊው እስትንፋሰ ዲያብሎሱ ታደሰ ወርቁ በተዘጋጀ የስድብ ሪፖርት እሳቸውን አስነስቶ በልተው የሚያስበሉ የቲም ዲዮስቆርዮስ ምክትል ኃላፊ የሆኑትን አቡነ ሳዊሮስን ለማስመደብ ሲባል ለሊቀጳጳሱ የሌለ ስም መስጠት እንደ ቤ/ክን ያለንበትን የዝቅጠት ደረጃ የሚያሳይ ነው፡፡ የደቡብ አፍሪካ ካህናትና ወንድሜ ዘመድኩን ስለ አቡነ ያዕቆብ ክስ ያሉትን እስቲ እናንብበው፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ

ቋሚ ሲኖዶስ: በተሐድሶ ኑፋቄ የተጠረጠሩትን አቡነ ያዕቆብን ከአትላንታ አብያተ ክርስቲያን አገደ! “ከሲኖዶሳዊ አንድነት ወደ ሲኖዶሳዊ ማጥራት?!” ተብሎ ቢወጣም

‹‹የአትላንታ ሰዓሊተ ምሕረት እና የፊላደልፊያ ቅ/ዐማኑኤል ውዝግብ በዕርቅ እንዲፈታ ቅ/ሲኖዶስ ወሰነ›› ተብሎ ውሳኔ መሰጠቱ ስንመለከት የአትላንታው አቡነ ያዕቆብ ተከራካሪ እነ አቡነ ቴዎፍሎስ ስላሉላቸው እንደሆነ ለመረዳት ብዙም አያዳግትም፡፡

አቡነ ያዕቆብ የደቡብ አፍሪካውስ ምን ተወሰነባቸው?ቅዱስ ሲኖዶስ: ብፁዕ አባ ያዕቆብን ከደቡብ አፍሪቃ ሀገረ ስብከት አገደ! “ገንዘቡንም እንዳያንቀሳቅሱ ካልታገዱ አደጋ ላይ ነን”/ምእመናን/ June 1, 2019 ተብሎ ውሳኔ መሰጠቱን ስንመለከት እውነትም ሰው የላቸውም ያስብላል፡፡

እዚህ ላይ ውድ የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች ለመሆኑ የአስተዳደር ጉዳይ ይበልጣል ወይስ የሃይማኖት ጉዳይ? መልሱን ለአንባቢያን ትቼአለሁ!

በዚህ በእኛ ዘመን የቤተክርስቲያናችንን ፈርጀ ብዙ ችግር መዘርዘር ከባድ ቢሆን የጥፋት ኃይሎች ሐራውያን እስካሁን የጻፉትን  እናንተው ወደ ኋላ እየሄዳችሁ ሐራ ስለ እነማን ምንጻፈች? በስንት ብር ጻፈች?  ብላችሁ ፈትሹ፡፡ እዚህ ላይ ግንዛቤ እንዲወሰድ የምፈልገው ጉዳይ በዚህ በእኛ ዘመን አንድ አባት የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና መንፈሳዊ አባት ለመባል እንደ ቲም ዲዮስቆርዮስ ባሉ የጳጳሳት ቡድን መሳተፍ ወይም ድጋፍ ማግኘት ወይም ተገዢ መሆንና ለሐራውያን መገበር ሲችል ብቻ መሆኑን ነው፡፡ ላነሳሁት ርእሰ ጉዳይ ግን ይህ ሁሉ ጥፋት እያለ

ለቤተ ክርስቲያን እመርታ የተመዘገበበት የብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የ3 ዓመታት ሪፖርት ለቅ/ሲኖዶስ ቀረበ፤ “በፈተናና ተግዳሮት መካከል የተሠሩ ናቸው!” May 23, 2019 ተብሎ መዘገቡም ለዚሁ ይመስለኛል፡፡

ሊቀ ጳጳስ አቡነ ያዕቆብ ቲም ዲዮስቆሪዎስ ውስጥ እንዲገቡ በተደጋጋሚ የተወተወቱና ካልገቡ ግን ቅሸባ እንደሚደርስባቸው በቁም ነገርም በጨዋታ መልክም ሲነገራቸው መኖሩን መገመት ይቻላል፡፡ ሐራ ዘተዋሕዶ ትሰድብሃለች ታዋርድሃለች ከዚያ በቀጥታ በቀኝ ትገዛሃለች፡፡ ቲም ዲዮስቆሪዎሶች ጋር ጠጋ ብለህ ካዳመጥክ በድፍረት የሚያወሩት ማቆችን እኛን ይጠብቁናል እና ደግሞ ማቅን እንጠብቃለን በማለት ነው፡፡ ማቆች ተብለው የተጠቀሱት ግን ከዚህ በፊት እንደገለጥኩት በተግባር ማቅ ጠሎች ናቸው፡፡

ሐራውያን በብጹዕ አቡነ ያዕቆብ ላይ  እ.ኤ.አ በAugust 31, 2013August 27, 2013፣ August 25, 2013፣ April 22, 2019June 1, 2019 የተለያዩ ጽሑፎችን ያወጡ ሲሆን ሌሎችን ብጹኡን አባቶችንና የቤተክርስቲያየን አገልጋዮችን በመስደብና ከክብር በማሳነስ ተገዢ እንዳደረጉ ሁሉ ብጹዕነታቸውን መያዝ(መጨበጥ) ስላዳገታቸው ይመስለኛል፡፡ እንደ ሐራውያን አገላለጥ በእሳቸው ሀገረ ስብከት ስለተሠራው ምንም መልካም ነገር መናገር አለመቻላቸውን ነው የሚጠቅሱት፡፡ ከላይ በተጠቀሱት ሐራ ዘተዋሕዶ በተለጠፉ አምስት ጽሑፎች ትርኪሚርኪዎቹንና በሬ ወለደዎችን ትቼ የተወሰኑት ያነሷቸው ዋና ዋና ሀሳቦች፡-

  • 6 አስተዳዳሪዎችንና ሓላፊዎችን፣ አልፈልጋቸውም በሚል የኤምባሲ ኔትወርካቸውን ተጠቅመው ተልእኳቸውን አስተጓጉለዋል
  • ከዐሥር ዓመት በፊት 40ሺሕ ደርሶ የነበረው የተወላጅ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን ቁጥር ወደ 4ሺሕ ተመናምኗል፤ ጥቁር ደቡብ አፍሪቃውያኑ፣ ወደ ቤተ ክርስቲያን ከመምጣት ይልቅ ቤታቸው መቀምጥን መርጠዋል፤ ትተዋት ወደመጡት አንግሊካን የኮበለሉም አሉ
  • ሊቀ ጳጳሱ በጎሠኝነትም ምእመናንን ይከፋፍላሉ፤ እርስ በርስ እንዲደባደቡና ከቤተ ክርስቲያን አንድነት እንዲለዩ አድርገዋል፤ ዕርቀ ሰላም እንዲወርድም ፈቃደኛ አይደሉም፤
  • ገባሬ ሠናይ ተቋም ኾና በደቡብ አፍሪቃ መንግሥት የተመዘገበችው ቤተ ክርስቲያናችን፣ ላለፉት 8 ዓመታት ለፈቃድ ሰጪው አካል/ለደቡብ አፍሪቃ ሶሻል ዴቨሎፕመንት ጽ/ቤት/ የሒሳብ ሪፖርት አላቀረበችም
  • “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ለደቡብ አፍሪቃውያን፥ የነፃነት አርኣያ፣ የማንነት መለዮ እና የድኅነት ተስፋ ነበረች፤ በነጋዴው ብፁዕ አባ ያዕቆብ የጋንጎችና አፋኞች አመራር ግን የማያባራ ትርምስና የምእመናን ልቅሶ ማዕከል ኾና ትገኛለች፤”ብለዋል – ጥቁር ደቡብ አፍሪቃውያኑ
  • በመላው አፍሪካ የአብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ የምክትል ፕሬዝዳንትነታቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዳልተወጡ ቢጠቅሱም

እኔ ግን ለዚህ ጽሑፍ መረጃ መሆን እንዲችሉኝ ያሰባሰብኳቸው መረጃዎች የሚመሰክሩት ሌላ ሀቅ ነው፡-

  1. በግንቦት 2011 ዓ.ም የውጪ አብያተ ክርስቲያናትን አስመልክቶ በቅዱስ ፓትርያርኩ መግለጫ ቁጥር 7 ላይ ‹‹በውጭ አገር የሚገኙ ሀገረ ስብከቶች…ከቃለ ዓዋዲው ጋርና ከየአገሮቹ መንግሥታት ሕግ ጋር የተጣጣመ ሕገ ደንብ እንዲዘጋጅና  ለጥቅምት 2012 ዓ.ም እንዲቀርብ…›› ይላል፡፡ የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ግን 1999 ዓ.ም ጀምሮ ይህን አጸድቆ እየሠራበት ስለሚገኝ እንደተሞክሮ ሊወሰድ ይገባል ባይ ነኝ፡፡ከዚሁ ጋር በማያያዝ ማንሳት የምፈልገው ጉዳይ በሁለቱ ሲኖዶሶች መካከል ትክለኛ ዕርቅ ተፈጸመ ሊባል የሚችለው የአገልግሎት ብቻ ሳይሆን የንብረትም አንድነት ሲኖር በመሆኑ ዕርቁ ፍጹም ሊሆን የሚችለው በግል ይዞታ ያሉ በየትኛውም አህጉረ ስብከት ያሉ አብያተ ክርስቲያናት አንድ ሲሆኑ ነውና ቅዱስ ሲኖዶስ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ባይ ነኝ፡፡
  2. በብፁዕ አቡነ ያዕቆብ ሥር ከሚገኙት አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንድም ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስም እንጂ ልክ እንደ አሜሪካው በአቡነ፣በአባ፣በቄስ እገሌ ስም ግብር ከፋይ ሆኖ የተመዘገበ አለመኖሩና ሁሉም በግበረ ሠናይ ተቋምነት የተመዘገቡ መሆናቸው እጅግ የሚያኮራ ነው፡፡በዚያ ላይ የደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያን ፈቃድ ታክስ ባለመክፈላቸው ሊሰረዝ ነው የሚለው ውዥንብር ለማጣራት የቅርብ መረጃ ከሊቀጳጳሱ ወይም ከቅርብ ወዳጆቻቸው ማግኘት ባልችልም የደቡብ አፍሪካው ሁነኛ ምንጬ እጁ ላይ ያገኘውንና የላከልኝን እ.ኤ.አ በ2017 የተሰጣቸውን ማረጋገጫ ማየቱ በቂ ይመስለኛል፡፡

3. በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ብዙ የተለፋበትና ዋጋ የተከፈለበት የሂሳብ አሠራር መክኖ ሲቀር በደቡብ አፍሪካ ግን ውጤታማ የሂሳብ ቁጥጥር መኖሩ እጅግ አስደሳች ነው፡፡ ይኸውም ገንዘብ ሲወጣና ሲገባ ቼክ ፈራሚዎችና ሊቀ ጳጳሱ ጋር በሚደርሱ የጽሑፍና የማረጋገጫ ስልኮች እንዲሰራ መደረጉ ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡

4. በጆበርግ ቅድስት ሥላሴ ጸረ ማርያሞች እንደ ፈለጋቸው ሲዘሉ በሀገር ቤት እንኳ ያልተቻለውን በእሳቸው ሥር ባሉ አብያተ ክርስቲያናት እንዲህ አይነት ነገር አለመታየቱ እጅግ የሚያስደንቅ ነው፡፡

5. 6ቱ አስተዳደሪዎች ጉዳይ ላይ ብዙ ልፋት እንደተለፋባቸው ይሄን 15 ገጽ ጨምሮ ሌሎች ደብዳቤዎች ማየቱ ብዙ ነገር አስረጂ ነው፡፡

6. ድብድብ፣ መለያየትና ክፉ ነገር አቡነ ያዕቆብ ደቡብ አፍሪካ በነበሩበት ጊዜ እንዳልነበረ እነዚህን የሐራ ተዋሕዶና የአዲስ አድማስ መረጃዎች መመልከቱ በቂ ነው፡፡

7. በአፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ የተጻፈላቸው የአድናቆት ደብዳቤ ከላይ በሐራውያን የተነሳውን ፍሬ አልባ ክስ ውድቅ የሚያደርግ ነው፡፡

8. ከገንዘብ እና ከጥቅመኝነት ጋር በተያያዘ ማንም ደፍሮ ስማቸውን የሚያነሳ በተለይ የሀገረ ስብከታቸው ሰው አላገኘሁም፡፡ ደግሞ ሰበሰቡት የተባለው ገንዘብ ኢትዮጵያ ወይም ደቡብ አፍሪካ ባንኮች ውስጥ መገኘት ነበረበት ወይም ደግሞ የገነቡት G+ ምናምን ፎቅ ወይም ዘመናዊ መኪናቸው መታየት ነበረበት የሚለውን ሀሳብ የሚጋሩ በርካቶች ናቸው፡፡ እሳቸው ከሕዝቡ ጋር ተቆራፍደው ያላቸውን እያካፈሉ እንደሚኖሩ ሩቅ ሳንሄድ የቤተክህነቱን ጥበቆች ጠይቅ ያሉኝም ነበሩ፡፡ የደቡብ አፍሪካው የመረጃ ምንጬ እንደሌሎቹ አባቶች የንስሐ ልጆቼ ሰጡኝ ብለው እንደነ አባ ሰብስቤ ብዙ መሰብሰብ የሚችሉ ቢሆኑም የሁል ጊዜ ንግግራቸው ‹‹እኔ ላይ ስባሪ ሳንቲም ሂሳብ ያለው ካለ ባደባባይ ይናገር!…›› ብለው በልበ ምሉነት እንዲሚናገሩ አጫውቶኛል፡፡ይህን ጽሑፍ በምጽፍበት ወቅት እንኳ በተለያዩ ሰዎች በኩል አሁን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ያዕቆብ ያሉበትን ሁኔታ ለማጣራት ብሞክርም በራቸውን ዘግተው ጸሎት ከማድረግ ቅዱሳት መጻሕፍትን ከማንበብና ባላቸው ትልቅ የስዕል ተሰጥኦ ቅዱሳት ስዕላትን በመሳል ጊዜአቸውን ከመሳለፍ ውጪ እሳቸውን ለማግኘት አዳጋች መሆኑን ነግረውኛል፡፡  አንድ ወዳጄ ከሳሏቸው በርካታ ስዕላት መካከል በስንት ልመና የሰጠኝ ስዕል እነሆ ብያለሁ፡፡


ይህን ስዕል ያጋራኝ ወዳጄ ርግቦቹ በኢሳ 9፡6 ላይ እንደሰፈረው ‹‹የሰላም አለቃ›› መሆኑን እናቱ ድንግል ማርያም ደግሞ አማናዊት ርግብ የሰላም እናት መሆኗን ለመግለጥ መሆኑን አስረድቶኛል፡፡ይበል! ብያለሁ

ስለ ሐራውያን ካነሳሁ እስትንፋሰ ዲያብሎሱ ታደሰ ወርቁ 58 ገጽ የጥፋት ሪፖርት በደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያን ላይ ለመጻፍ ምን አነሳሳው?

ሐራዊው ታዴ የነገር አባቱ ቤተመንግሥት ባልታወቀ ማዕረግና ሹመት ስለገባበት እንደ በፊቱ ገቢው ሊሆን አልቻለም፡፡ በዚህ ምክንያት በኢትዮጵያ ተቀዛቀዘውን ጸረ-ተሐድሶ የስላይድ ንግድ ወደ ውጪ መውሰድ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ሆነበትና በ‹‹ዲ/ን›› ንዋይ ይጋበዝና ደቡብ አፍሪካ ይሄዳል፡፡ ታዲያ ታዴ እንደለመደው ስላይዱን ሊቸበችብ ሲል ሊቀ ጳጳስ አቡነ ያዕቆብ ጋር ይደወልና ታደሰ ወርቁ የሚባል ሰው ያውቁታል ስለ ተሐድሶ ገለጻ ሊሰጥ ይፈልጋል ብለው ያማክራሉ፡፡ ሊቀ ጳጳሱም ታደሰንም አላውቅም እንዲህ ዓይነት መርሐ ግብርም በዕቅድና በፕሮግራም እንጂ ዘው ተብሎ የሚገባበት አይደለም፤ ወደፊት ተነጋግረን መርሐ ግብር ተይዞለት ሊመጣ ይችላል ብለው መልስ ይሰጣሉ፡፡ ታዴ ታዲያ ጨሰ፣ ተናደደ በቃ በእልህ ሊቀ ጳጳሱ ታደሰ የሚያክል ሰው በመከልከላቸው እጅግ ተበሳጨ፡፡ ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ይመሰስለኛል ሊቀ ጳጳሱን ለማጥቃት ውጥን የያዘው፡፡ ታዴ ትልቁ ሕልሙ የነበረው ደቡብ አፍሪካ ነጻ የትምህርት ዕድል ፍለጋ ነበር፡፡በኋላ ላይ ከዚህ በፊት ሲሰድበው ሲያንቋሽሸው ከነበረው ከእነ አባ አእምሮ ጋር የጠላቴ ጠላት ወዳጄ በመሚስል ፈሊጥ አንድም ዶላር 58 ገጽ አይደለም መጻሐፍም ያጽፋልና አንድ ላይ ገጥሞ የትግል መስመሩን ተቀላቀለ፡፡ብሮች ተስብሰበው ለዲጄው ለአሉላ ይስጡ እንጂ ዋናው ተጠቃሚና አከፋፋይ እስትንፋሰ ዲያብሎሱ ታዴ ነው ብለውኛል ደቡብ አፍሪካውያን ምንጮቼ፡፡

6. ማጠቃለያ

ጽሑፌን ከማጠቃለሌ በፊት የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ላመላክት

ለምዕመናን

  1. መቼም በእኛ ቤተክርስቲያን ምዕመኑና ካህናቱ(አገልጋዮቹ) ያልተገናኙባት ስለሆነች ያለ ሊቀጳጳስ ከዚህ በፊት ለሁለት ዓመታት አሁን ደግሞ ከ4 ወር በላይ እድትኖሩ ሴራ የሰሩትን አባቶችና ወንድሞች እውነትን ብቻ በመያዝ ከቂመነኝነት በጸዳ ሁኔታ እንድትፋለሙ ያስፈልጋል፡፡
  2. በድጋሚ የተመደቡት አጣሪዎቹ ሲደርሱ ከዚህ በፊት የተላኩት አጣሪዎች ምን ዓይነት ደባ እንደፈጸሙባችሁ በግልጽ መግለጥ ይገባችኋል፡፡
  3. አጣሪ ልዑካን ከዚህ በፊት እንደመጡት የአንድ ወገን ሪፖርት አድማጭና ፍረደ ገምድል እንዳይሆኑ እያንዳንዱ እንቅስቃሴያቸውን በመከታተል ምዕመኑን ከእረኛቸው የሚለዩ የዲያብሎስ መሣሪያዎች እነ ንዋይንና አንዳንድ ነጋዴ ቄሶችን እንቅስቃሴ በመከታተል ስለ እውነት መመስከር ካልቻሉ ከቤተክርስቲያኒቱ ገለል ብለው ወደ ንግዳቸው እንዲገቡ ማድረግ ይገባል፡፡
  4. ከሳሾቹ እነማን እንደሆኑና ምን ፈልገው እንደ ከሰሱ በግልጽ ሁሉም በተሰበሰበበት እንዲነገር(እንዲነበብ) ማድረግ ይገባል፡፡

ማስታወሻ!

በነገራችን ላይ ብጹዕ አቡነ ያዕቆብ በግፍ ለምን ይነሳሉ የሚለው ጉዳይ እንጂ የሚያነጋግረን ከዚህ በፊት በተለይ የደቡብ አፍሪካና የኬንያ ምዕመናን እንደምታስታውሱት በግፍ አቡነ ያዕቆብን ከደቡብ አፍሪካ የማሳደድ ሥራ ሲሰራ እሳቸውን የጎዱ መስሏቸው ወደ ኬንያ ቢልኳቸውም ብጹዕነታቸው ግን ለ30 ዓመታት የረባ መንበረ ጵጵስና ያልነበረውንና ብጹአን አባቶች ከዲያቆናት ጋር ተራ ጠብቀው የሚጠቀሙበትን የመጻዳጃ ቤት በማስቀረት ደረጃውን የጠበቀ ሁሉን ያሟላ እጅግ ውብ መንበረ ጵጵስና ካሰሩ በኋላ ባበረከቱት የልማት አስተዋጽኦ ከአንድ ምዕመን መኪና ተሸልመዋል፡፡ በኋላም ይህንኑ መኪና ለኬንያ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን  በስጦታ  እንዳበረከቱ ነው የሰማሁት፡፡ እዚህ ላይ ከሁሉ  የደነቀኝ የተከሰሱበት ክስ የሐሰት መሆኑ በቅዱስ ሲኖዶስ ተረጋግጦ ከኬንያ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲመለሱ በስማቸው የነበረውን ይሄንኑ መኪናውን ሸጠው አዲስ አበባ ላይ በርካታ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ ያለ ሥራ የቆሙ መኪናዎች ባሉበት በኮንትራት ላዳ ከመጠቀም ለራሳቸው መኪና ለመግዛት አለመምረጣቸው ነው፡፡ዛሬ ቤቱንም ይሁን መኪናውን አሳዳጃቸው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሳዊሮስ እየተንፈላሰሱበት ነው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በወቅቱ የሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ያዕቆብን ኬንያ መድረስ ተከትሎ በርካታ ስደተኞች  የኤምባሲ ጉዳያቸው ተሳስሮባቸው የነበሩ እንደተፈታላቸው፣ ከደዌ ሥጋ ከደዌ ነፍስ የተያዙ መፍትሔ እንዳገኙ መስክሮች ናቸው፡፡በመላው አፍሪካ አብያተክርስቲያናት ኅብረት በምክትል ፕሬዝዳንትነት ተመርጠው ያበረከቱትን አስተዋጽኦ ስንጨምርበት ደግሞ በተግባር የልማትና የአስተዳደር አባት መሆናቸውን ማረጋገጫ ነው፡፡

በተመሳሳይ ወቅት በደቡብ አፍሪካ ደግሞ በመጤ ጠሎች (Xenophobia) ምክንያት በርካታ ኢትዮጵያውያን በግፍ ሞቱ ሌሎች በቁማቸው ተቃጠሉ፣ቤ/ክን ውስጥ የተደረገው ድብድብ ለዓለም በደቡብ አፍሪካ ቴሌቭዥን ተላለፈ፡፡ ግጥምጥሞሽ ይሁን በበደል ምክንያት አሁንም በጁሐንስበርግ እና ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በሌሎች የደቡብ አፍሪካ ከተሞች በኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ላይ ከ08/08/2019 እየደረሰ ጀምሮ ቅጥ አምባሩ የጠፋ መከራ በርካቶች ታስረዋል፣የቤት ኪራይ መከፈል እስከሚያቅትና ነገ ምን እንሆን ይሆን? በሚል ስጋት ላይ መሆናቸውን ስሰማ….እኔም በአእምሮዬ ምናልባት እውነተኛና ስለ ሕዝቡና ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን ለመጸለይ የማይታክቱ የቤተክርስቲያን አባት ገፍተው፣ አሳደው ፣የሐሰት ምስክር ሆነው… ይሆን እንዴ? እያለ በጥያቄ መሞገቱ አልቀረም፡፡ ይህንንም ሀሳቤን የበለጠ ያጠናከረልኝ ቴዲ ዘጎላ የተባለ ኦርቶዶክሳዊ ወጣት በዩቲዩብ ቻናሉ ላይ የለቀቀው መረጃ ነው፡፡


ሆድ አደሮች፣ሴረኞችና ተረፈ ይሁዳውያን የፈጸሙትን ግፍ የሚያሳይ ስለሆነ በደንብ ያድምጡት!!!

ዙሮ ዙሮ ነገሮችን በአስተውሎት በማየት ውሳኔዎቻችሁን በጥንቃቄ መመርመር ይህ ለምን ሆነብን ብሎ ራስን መፈተሽ አስፈላጊ ነው፡፡….ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ!

ለአጣሪዎቹ

እንግዲህ የአጣሪዎቹ ጉዳይ በተመለከተ አሁን አሁን ከፓትርያርኩ አከባቢ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ወደ ጎን በመተው ጊዜው ሲደርስ የምናየው ቢሆንም ቅዱስነታቸው ሌሎች አባቶችን ለመመደብ እንቅስቃሴ ላይ እንዳሉ ሰምቻለሁ፡፡ በርግጥ እውነቱና የተሰራውን ደባ ለተረዱት የደቡብ አፍሪካ ምዕመናን ማንም ይመደብ ማን ችግር አለው ብዬ አላስብም፡፡የሆነ ሆነ ከፍ ብዬ ብጹአን አባቶችን መምከር ባልችልም እንደቤተክርስቲያን ልጅነቴ ግን በሁለተኛው ዙር አጣሪ ሆነው ለሚሄዱት አጣሪዎች ጥቂት ልል እወዳለሁ፡-

  1. ክስን ፈረሙ የተባሉ ሰዎች በሕይወት ስለመኖራቸው፣ክርስቲያን ስለመሆናቸውና ትክክለኛነታቸውን ማረጋገጥ ቢቻል፤
  2. የሥላሴን ቤ/ክን ጨምሮ የደቡብ አፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት በማን ስም እንደተመዘገቡ፤ሀብትና ንብረት በእነማን ስም እንዳለ ማጣራት ቢቻል ፤
  3. እነ ጅቦ በአቡነ ያዕቆብ ግብዣ ተልኮአቸውን፣ ውሎ አዳራቸውን ከሳሾች ጋር እንዳደረጉት ተመሳሳይ ችግር እንዳይፈጠር ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ

የማያዳግም ሥራ ቢሰሩ ምኞቴ ነው፡፡ አጣሪዎቹ ካልተቀየሩ ሁሉንም በሚገባ አዳምጠው አንጀት አርስ መልስ ለሚገባው እንደሚገባው አድርገው መመለስ በአግባቡ የሚያውቁበት የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ እና ከሐምሌ 14 ጀምሮ ስለቀጣይ የአሠራር ሂደት ከልብ ወዳጃቸው ከአቡነ ቴዎፍሎስ መመሪያ ለመቀበል ወደ አሜሪካ ተጉዘው የነበሩት የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ፣ከዚህ በፊት አጣሪ ሆነው ሄደው ተልካሽ ሪፖርት ያቀረቡት የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ባልደረባው፣ ቀሲስ በላይ ጸጋዬን ስለ እውነት እንዲተጉ ሳልማጸን ባልፍ የቤተክርስቲያን አምላክ ይፈርደብኛል ብዬ አምናለሁ፡፡  

አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር 2012 ዓ.ም ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ከዘረኞች፣ከሴረኞችና ከሰው ጅቦች የጸዳች ያድርግልን!!!

በሌላ ርእሰ ጉዳይ እስከምንገናኝ ቸር ሰንብቱልኝ!

 ሳምኬት ነኝ!     

ተጻፈ ነሐሴ 25 ቀን 2011 ዓ.ም                

ዘመቻ ጌዲዎን 4

የተራቡና የማይጠግቡ ጅቦች በደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያን


በዛሬው ዘመቻ ጌድዎን ክፍል ላቅርብላችሁ የወደድኩት ጉዳይ በት.ኤር 19፡3 ላይ ‹‹…የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡-የሰማውን ሰው ጆሮ ጭው የሚያደርግ ክፉ ነገር እነሆ በዚህ ስፍራ አመጣለሁ፡፡›› እንዲል በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ላይ በደፋሮቹና እምነት አልባዎቹ የተራቡ ጅቦች መሪነት የደረሰው ግፍና የተቀነባበረው ሴራ ጆሮዬን ጭው ስላደረገውና ስላስደነገጠኝ እንዲሁም በአሁኑ ሰዓት ቅድስት ቤተክርስቲያን እየተጓዘች ያለችበትን የኋሊት ጉዞና የደረስንበትን የሃይማኖት፣የቀኖና የሕገ ቤተክርስቲያን ጥሰት እንዲሁም የሥነ ምግባርና የሞራል ዝቅጠትና ውድቀት ደረጃ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ በመሆኑ ማነህ ወዳጄ! የተኛህ ንቃ ለማለት ጽፌዋለሁ፡፡

ይህ ጽሑፍ ስድስት ንኡስ ርእሶች ማለትም

  • ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የነበራቸው ድርሻ
  • በሊቀ ጳጳስ አቡነ ሳዊሮስ የሚመራው ክንፍና በአቡነ ቴዎፍሎስ የሚመራው ቡድን
  • በደቡብ አፍሪካ የጆሐንስበርግ ቅድስት ሥላሴ ከሳሾች
  • በደቡብ አፍሪካ አጣሪ ሆነው ተመደበው ስለነበሩ ግለሰቦች ማንነት
  • ሐራ ዘተዋሕዶ በደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያንና በሊቀ ጳጳሱ ላይ ያደረገችው ዘመቻ
  • ማጠቃለያ

ያሉት ሲሆን በእርጋታ እንድታነቡ እጋብዛለሁ

መልካም ንባብ!!!

በየትኛውም የመገናኛ ብዙኃን፣የምስል ወድምጽ እንዲሁም የህትመት ሚዲያ ስለቤተክርስቲያን የተጻፉ ጽሑፎችን ከመከታተልና ከመመረጅ በላይ የሚያስደስተኝ ነገር የለም፡፡ ታዲያ ያሄ የያዘኝ አባዜ አንድ ቅዳሜ ላይ በብስለቱና በአስተዋይነቱ በሀገር ደረጃ አጅግ ከምናከብራቸው ታላላቅ ኢትዮጵያውያን ጋር በትጋትና በታማኝነት በመስራት የሚታወቀው ጋዜጠኛና ጸሐፊው ተረፈ ወርቁ(ዲ/ን) ግዮን መጽሔት ቅፅ 2 ቁጥር 64 ሐምሌ 2011 ዓ.ም  እና ቁጥር 61 ሰኔ 2011 ዓ.ም ‹‹የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በደቡብ አፍሪካ ከትናንትና እስከ ዛሬ›› በሚል ርእስ በሁለት እትሞች የዳበረ፣ ጥልቅና ብስል ጽሑፍ በደቡብ አፍሪካ ስላለችው የኢትዮጵያ ቤ/ክን በአግባቡ አስቃኝቶናል፡፡ የእኔ አእምሮ ደግሞ ጥያቄ ከመጠየቅ አይቦዝንምና ዲ/ን ተረፈ ወርቁ በዚህ ጊዜ ለምን ስለዚህ ርእሰ ጉዳይ ማንሳት ፈለገ? ሀገረ ስብከቱና ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ያዕቆብ አሁን በምን ሁኔታ ላይ ናቸው? …የሚሉና በርካታ ጥያቄዎች አእምሮዬን ያናውጡት ጀመር፡፡ አሳ ጎርጓሪ …እንደሚባለው ለካ ጉዳዩ ሌላ ነው….

  • ሊቀ ጳጳሱ በዘረኞችና በጥቅመኞች መረብ ተጠልፈው በተረፈ ይሁዳውያን ተሽጠው፣ ከአዲስ አበባ እንዳይወጡ ተደርጎ፤ የደቡብ አፍሪካን ቤተክርስቲያን በአሜሪካ እንደለመዱት የግል ንብረት (PRIVATE LIMITED COMPANY) ለማድረግ ባሰፈሰፉ አካላት፤ በእስትንፋሰ ዲያብሎሱ ታደሰ ወርቁ አርቃቂነትና ፀሐፊነት በተዘጋጀው ባለ 58 ገጽ ኢሰብአዊ ሪፖርት ፣ በተራቡ ጅቦች በአሥር አለቃ ፋንታሁን ሙጬ አቅራቢነት በአዲሱ አሳማ አብርሃም ገረመው ቃለ አቀባይነት፤በዲጄው አሉላ ብሎግ ለጣፊነት፣ በእነ አቡነ ሳዊሮስ ሴራ ጠንሳሽነት፣ እንዲሁም በቅርብ አባ ቶማስ በሚባሉ መነኩሴ ድብደባ የደረሰባቸው የረቀቀ ሴራ (Conspiracy Expert)  አቡነ ቴዎፍሎስ(በቀድሞው አባ ጽጌ ደገፋው) የግል ቤተክርስቲያን በየአህጉሩ የመያዝ ፍላጎት እንዲሁም በጥቃቅን ነፍሳት ተባባሪነት ሊቀ ጳጳሱ ሰው ስለሌላቸው ብቻበይፋ ከሚታወቁት የጳጳሳት ቡድን መካከል የአንዱም አባል በላመሆናቸው ምክንያት በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት እስከ ጥቅምት ሲኖዶስ ከኢትዮጵያ እንዳይወጡ መደረጉን ስሰማ ደግሞ ጉዳዩን በጥልቀት እንዳየውና ነገር አለ!…እንድል አደረገኝ ፡፡

ወደ ዋናው ጽሑፍ ከመግባቴ በፊት ለንጽጽር እንዲመች በ”ዜን” መጽሔት፣ ቅጽ 1 ቁጥር 3 ሰኔ 2002 ዓ/ም ‹‹ጅብ ( ዥብ)›› ተብሎ የወጣውን ጽሑፍ ማየት እኔ ሰለማስነብባችሁ የተራቡ የሰው ጅቦች ለመረዳት ይጠቅማልና እነሆ፡-

‹‹ጅብ የሚለው ቃል ዐዲስ አማርኛ መዝገበ ቃላት ሲፈታው ” የአውሬ ሥም የውሻ ፣ የድብ ፣ የተኩላ ፣ የቀበሮ ፣ ዓይነት … በማሽተት አውቆ ወገኖቹን የሚጠራ ፣ በደን የሚኖር የአህያ ጠላት ….” ይለዋል።…እንደሚታወቀው ጅብ ስጋ በል እንስሳ ነው። የሚበላው ሲያጣ ግን አትክልትና ፍራፍሬ ቢሆን ይቀማምሳል። በአደን ወቅት በብድንም በተናጠልም ያጠቃሉ ፤ በብዙ ተረቶቻችን ላይ ጅቦች ፈሪ ተደርገው ይሳላሉ ይህ የተሳሳተ ግምት ነው ጅብ የሚመገበው ምግብ እጥረት ካጋጠመው ከአንበሳም መንጋ ቢሆን አስጥለው ይመገባሉ።…ጅቦች ስሪያ ሚፈፅሙት በብድን ነው። አንዷን ሴት ጅብ እየተፈራረቁ ይሰርሯታል። ይህንን ለማድረግ ግን ጉልበተኛ ፣ ታጋይ ና ጠንካራ ካልሆነ አንድ ወንድ ጅብ እንዳማረው ይቀራል። ሴቷ ጅብ ለተገናኛት ሁሉ እርካታን የምትቸር ናት።…በድምፃቸው መልዕክት መለዋወጥ ሲችሉ ከዱር እንስሳት ከልብ ከት ከት ብሎ በመሳቅ ብቸኞቹ ናቸው። ጅብ 16 ሰዓት በትጋት ሲያድን ቆይቶ የተቀረውን ሰዓት ከሰው እይታ ከለል ብሎ ያርፋል።…››

እዚህ ላይ ሁለት ጉዳዮችን ልብ ብላችሁ እንድታነቡ ተማጽኖዬ ላቅርብ፡-

ጉዳይ 1፡- ጅብ የሚለው ቃል አነሱን አምባ መጠጊያ አድርገው ቤተክርስቲያንና ልጆቿን ለሚቦጠብጡ ለግል ጥቅማቸውና ብልጽግናቸው የሚሯሯጡ ሆዳሞች እንጂ ቅዱሳንና ብጹአን አባቶችን አይመለከትም፡፡

ጉዳይ 2፡- የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ያዕቆብ ብጹዕነታቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ የተፈጸመባቸውን ኢሰብአዊ፣የዘረኞችና የመንጋ ሴረኞች ርብርብ ካዳመጡ በኋላ ‹‹ በኀጢአት ከማንም አልበልጥም፤ በጽድቅም ከማንም አልበልጥም እኔ ሰው ነኝ! መድኃኔዓለም አይደለሁም፤ እኔ አሁን የምናገረው ስለ ደቡብ አፍሪካ ምደባ አይደለም፤ እኔ የቅዱስ ፓትያርኩን  እግር እያጠብኩ መኖር እችላለሁ፡፡ የተፈፀመብኝ ድርጊትም ይሁን ሪፖርቱ ኢ-ሰብአዊ ነው፡፡  ››  እንዳሉት ብፁዕነታቸው እንደ ማንኛውም ሰው አስተዳደራዊ ድክመት ሊታይባቸው ይችላል፡፡ ነገር ግን እንኳን በነፍስ ግድያ ሊጠረጠሩ ወደ ኋላ ሄጄ ግለ ታሪካቸውን ለማጥናት እንደሞከርኩት ‹‹ዜና ቤተክርስቲያን›› ሐምሌና ነሐሴ 1998 ዓ.ም ባሳተመው ጋዜጣ ላይ ብጹእነታቸው ገና በአዲስ አበባ እንደ ዛሬው በአጀብ የሚጓዙ ሰባክያን ባልነበሩበት ዘመን ከ25-45 ኪ.ሜ በእግራቸው እየተጓዙ በአዳሜ ቱሉ፣በጨፌ ጂላ፣ቡልቡላ፣ቡታ ጅራ እና የዝዋይ አጎራባች በታዎች ምዕመናን በተዋሕዶ እምነት እንዲጸኑ አደርገዋል ከዚህ በተጨማሪ በኢአማንያን በተከበቡ ሁለት ከተሞች የሰ/ትቤት የማደራጃ ኮርስ ሰጥተዋል፣ በርካታ ሰ/ት/ቤቶች አንዲቋቋሙ የአንበሳውን ድርሻ ተወጥተዋል፡፡ ባዶ እግራቸውንና በብስክሌት እየተጓዙ ስብከተ ወንጌል ያስፋፉ፤የዓውደ ምሕረት የወንጌል ት/ት ባልተስፋፋበት ጊዜ እንኳን ነፍሰ ገዳይና አስገዳይ ለሆነው ዲያብሎስ ጭንቅ የሆኑ፣ ልጅ አልባ፣ ጤናና ሰላም አልባ ለነበሩ ሰዎች መፍትሔ ከመሆን ውጪ እንደሌሎቹ የግል ሀብት፣ ንብረት(መኪና፣ፎቅ…) ምቾትና ድሎት ሳይፈልጉ ለሕዝብ የኖሩና የሚኖሩ ከአዋቂው ጋር እንደ አዋቂ፣ ከወጣቱ ጋር እንደ ወጣት፣ ከሕጻናት ጋር ዝቅ ብለው ለሰው እንጂ ለራሳቸው የማይኖሩ አባት መሆናቸውን ለረጅም አመታት የሚያውቋቸው የደቡብ አፍሪካ ምዕመናን ጭምር ለዚህ ምስክር መሆናቸውን ተረድቻለሁ፡፡ የእኔ ጽሑፍ ዓላማ ግን የእሳቸውን በጎ ሥራ እያነሱ ማሞጋገስ ሳይሆን ድክመቶቹን ሁሉ እሳቸው ላይ በመደፍደፍ በደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያን ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ምዕመኑ ያለ አባትና አጽናኝ እንዲኖር በምንም መልክ ከእርሳቸው ጋር የማይገናኙ ጉዳዮችን በማቀናጀት በእነ ሆድ አምላኩ የደረሰውን ግፍ በማሳየትና መፍትሔ ለማምጣት ነው፡፡

የኢትዮጵያውያን ኑሮ በደቡብ አፍሪካ

ደቡብ አፍሪካ በጣም መልካም፣በሥነ ምግባር የታነጹ ዜጎች ባለቤትና ለሚሠራና ለሚተጋ ሰው በልፋቱ መጠን ዋጋ የምትከፍል ሀገር ናት፡፡ ደቡብ አፍሪካ የሁሉም አፍሪካውያን እናት በመሆን ከዚህም በተጨማሪ ለያዥ ለገናዥ እጅግ ፈታኝ የሆኑ ወንበዴዎችንና ዘራፊዎችን ተሸክማ ሁሉንም በህግና በሥርዓት ለመመለስና ለማስተናገድ የምትጥር ሀገር ናት፡፡

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያውን በደቡብ አፍሪካ ምን ዓይነት የስጋት የጭንቀትና የፍርሃት ሕይወት ተጋፍጠው እየኖሩ እንዳለ ለመረዳት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ቴሌቭዝን(ኢቢሲ) የካቲት 11 ቀን 2011 ዓ.ም ‹‹ስደት፣ ተስፋ፣ ሞት…›› በማለት ያቀረበውን ዘጋቢ ፊልም ማየቱ በቂ ነው፡፡ በተለይ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ቀደሞም ቢሆን ከኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ጋር ተያይዞ ለቤት ኪራይና ለልጆች የትምህርት ቤት ክፍያ እንኳ ለመክፈል የሚቸገሩ በበዙበት፤ ሰሞኑን የተከሰተው አስደንጋጭና ልብን በኃዘን የሚሰብር ዜና በዚያ ላሉ ወገኖቻችን የበለጠ ሕይወትን ውስብስብ እንደሚያደርገው እሙን ነው፡፡ በደቡብ አፍሪካ ያሉ ምዕመናን ዕለት ዕለት ከሚገጥማቸውና ከሚደርስባቸው የውንብድና ተግባር ጋር በተያያዘ …እኔ ደግሞ መቼ ይሆን ተራዬ ደርሶ የምዘረፈው? የምደበደበው? ወደ ሀገሬስ የሚመለሰው አካሌ ወይስ በድኔ? እያሉ በጭንቀትና በሰቀቀን የሚኖሩ ቢሆኑም ብቸኛ አምባቸው፣ መጠጊያቸውና መጽናኛቸው ቅድሰት ቤተክርስቲያን ብቻ በመሆኗ እነሱ ይቸገራሉ እንጂ ቤተክርስቲያን ተቸግራ ማየት የማይፈልጉ ናቸው፡፡የአንዳንድ አድርባይ ቄሶችና በየመጠጥ ቤቱ የመንድር ሴት ይመስል ወሬና ተንኮል እየፈበረኩ ከሚያመሹ መሸተኞች በቀር በደቡብ አፍሪካ ሴቶቹ በጣም ምስጉን ትጉህ የሥራ ሰዎች ሲሆኑ በተለይ በtown ያሉ ወንዶች ግን በአብዛኛው መንደርተኛና ሀሜተኞች ናቸው ተብለው ይታማሉ ::የደቡብ አፍሪካ ምዕመናን ቅድስት ቤተክርስቲያን የሕልውናቸው መሠረት መሆኗን በአግባቡ የተገነዘቡ በመሆናቸው የቤተክርስቲያን አገልግሎት ከሚጓደል የቤተሰባቸውን ኑሮ መጓደል የሚመርጡ፤ በሸፍጥና በተንኮል ቤተክርስቲያንን ለሚበድሉ ደግሞ ልክ የሚያስገቡ ቆራጦች መሆናቸውን የኢትዮጵያ ቤ/ክን በተሐድሶ በተናወጠችበት ጊዜያት እንኳ የስላይድ ነጋዴው የእነ እስትንፋሰ ዲያብሎሱ ታደሰ ወርቁ ቧልትና ቀልድ ሳያስፈልጋቸው ጸረ-ማርያሞችንና ፖለቲከኞችን ተጋፍጠውና አሸንፈው ከዘመን ቀድመው በጽናት የቆሙ የተዋሕዶ የቁርጥ ቀን ልጆች ናቸው፡፡

ታዲያ ዘርፈ ብዙ ማኅበራዊና ኢከኖሚያዊ ችግር ያለበትን ምዕመን ቤተክርስቲያን እንኳ መጥቶ እንዳይጽናና ለግል ጥቅም ሲባል በሬ ወለደ ዓይነት ወሬ እየፈጠሩ የግል ጥቅምና ፍላጎትን የምዕመናንን ጉዳይ አድርጎ ማቅረብና በውጪ ያለችዋን ቤተክርስቲያን ሰላማዊ አገልግሎት መበጥበጥ መናፍቃንና አሕዛብ በቤተክርስቲያን እያደረሱ ካሉት ተጽእኖ ቢበልጥ እንጂ ያንሳል እንዴ? ከዚህ በላይስ ምን ግፍ አለ?

ለመሆኑ በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንና ምዕመናን ላይ እየደረሰ ላለው በደል እነማን ምን አስተዋጽኦ አላቸው?

  1. ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

በመሠረቱ ቅዱስነታቸው የደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያንን በወሬና በክስ ካልሆነ በስተቀር በተግባር አያውቋትም፡፡ጳጳሱን ለመከታተል እንዲያመቻቸው ናዝሬት ማርያም ከሰባት ዓመት በላይ አንዳች የልማት ሥራ ሳያከናውኑ ቀጥታ ወደ ደቡብ አፍሪካ የሄዱት ሰርጎ ገቡ፣ ተመሳስሎ ነዋሪና የንስሐ ልጆች ብር ስልቻ የሆኑት  የመንደራቸውን ሰው ያለ አቅማቸው በሥራ አስኪያጅነት ቢያስቀምጡም፤ የእነ አቡነ ሳዊሮስ ሴራና ውትወታ እንዳለ ሆኖ የቅዱስነታው ትልቁ ጉዳይ ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ያዕቆብ እንጂ የደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያን ወይም ምዕመናን እንዳይደሉ ከብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ በርካታ ምዕመናን የተረዱት ጉዳይ ነው፡፡ በርካታ ሰዎች ከሚፈጽሙት ተግባር በመነሳት እንዳለመታደል ሆኖ ቅዱስነታቸውን ቂመኛ ናቸው ይሏቸዋል፡፡ ለዚህም  በግልም ይሁን እንደ ተቋም(ደብር፣ገዳም…) ከደረሰባቸው ችግር ስለ ቂመኝነታቸው ብዙ ቢወራም እኔ ግን ሁለት የቅርብ ጊዜ ምሳሌዎችን ላሳይ፡-

ማሳያ 1፡-የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ባደረጉት ሰላማዊና ኮሌጁ የትምህርትና የምርምር ማዕከል ይሁን እንቅስቃሴና ሂደት ክብሬንና ሥልጣኔ ተጋፍተዋል በሚል ሰበብ ቂም ስለያዙባቸው የትኛውም ፓትርያርክ አድርጎት የማያውቀውንና መንፈሳዊ ኮሌጁ ከ900 በላይ ተማሪዎች ባስመረቀበት የ2011 ዓ.ም የምርቃት መርሐ ግብር ላይ ቂም ስለያዙ ብቻ አለመገኘታቸው እጅግ አሳፋሪ ተግባርና ከዚሁ ከቂመኛ ጠባያቸው የመነጨ እንደሆነ በርካቶች ከምርቃት በፊትና በኋላ ሲያወሩ ሰምቻለሁ! በዚህም የተበሳጩ በርካታ ተማሪዎች ከምርቃቱ በኋላ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ መኖሪያ ቤት ሄደው ይመርቁን ማለታቸው ሰምቻለሁ እነዚህንም ፎቶዎች አይቻለሁ፡፡

አንዳንዶች መደበኛ አገልጋዮች በመሆናቸው የቅዱስነታቸው በትር እንዳይወርድባቸው ፊታቸውን መሸፈን አስፈልጓል

ማሳያ 2፡- የቀድሞው ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ዲዮስቆርዮስ ጋር በተለያዩ ጊዜያት ተፈጥረው በነበሩት አለመግባበት ቂም ስለያዙ ልክ መውረዳቸውን ተከትለው እየጠዘጠዟቸው መሆኑን ራሳቸው አቡነ ዲዮስቆርዮስ በየጳጳሳቱ ቤት፣ በቤተክህነቱ የተለያ መምሪያዎች ከበተኑት ደብዳቤ በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡

ታዲያ ቅዱስነታቸው ገና የካቲት ላይ ተሹመው ግንቦት ላይ ባልዋሉበትና ባላደሩበት የተሳሳተ መረጃ ይዘው አቡነ ያዕቆብ በማኅበረ ቅዱሳን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ስለ ማኅበሩ ምስረታና የእሳቸውን አስተዋጽኦ መናገራቸውን ተከትሎ እሳቸው ማኅበረ ቅዱሳን ናቸው፣ እኔ ፓትርያርክ እንዳልሆን ጥረት አደርገዋል፣ ይንቀኛል፣ የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ደጋፊ…እና የመሳሰሉትን ተልካሻ ምክንያቶች አጠገባቸው ሁነው ገድለ ዲያብሎስ በሚጽፉና በረከሰ ማንነታቸውን አባቶችን በማጋጨት እራሳቸው የግጭቱ አጣሪ በመሆን በሚኖሩ ሆድ አደር ጅቦት ተሳስተው ባገኙት አጋጣሚ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ያዕቆብን መበቀል ይፈልጋሉ እየተባሉ መታማታቸው አልቀረም፡፡ በግንቦት የ2011 ቅዱስ ሲኖዶስ ላይም የደቡብ አፍሪካ ጉዳይ ሲነሳ የሐሰት ክስ መሆኑን እያወቁ በተመሳሳይ ወቅት ክስ ያለባችው ስድስት ሊቃነ ጳጳሳት ጉዳይ ምንም ትኩረት ሳይሰጡ ለይተው የብፁዕነታቸውን የሥራ ሞራል ለመንካት አስበው ‹‹እስከ ጥቅምት ሲኖዶስ ድረስ እዚሁ ኢትዮጵያ ይቆዩ››እንደገና ይጣራ..››. የሚለውን ሀሳብ ይዘው በጽኑ ሲሞግቱ የነበረ ሲሆን በዚህም ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት ከላይ ያነሳሁትን ሀሳብ በሚያጠናክር መልኩ በትዝብት ከመመልከት በላይ አንዳንዶች በይፋ ከብጹነታቸው ጋር የግል ችግር አልዎት እንዴ? ብለው እስከ መጠየቅ ደርሰዋል፡፡

በእኔ እምነት ግን ቅዱስነታቸው አቡነ ያዕቆብ ላይ የመረረ የጥላቻ አቋም አንዲኖራቸው ያደረጋቸውና በየጊዜው ከሚነሱ ከሳሾች ጋር ተባባሪ የሚሆኑበት ምክንያት አቡነ ጳውሎስ ላይ የነበራቸውን ቂም ለመወጣት ብቸኛና ቻይ ሆነው ያገኙት ሰው አቡነ ያዕቆብ ስለሆኑ ይመስለኛል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አንዳንድ ብጹአን አባቶች በጋራም በተናጥል ቅዱስነታቸውን ለምን አይተዋቸውም? ብለው በጠየቋቸው ሰዓት እሳቸው ማኅበረ ቅዱሳን ናቸው  ነበር መልሳቸው፡፡

ዙሮ ዙሮ ይህ አካሄድ ቤተክርስቲያንን የሚጎዳ በመሆኑ ሁለቱ አባቶች ገድለ ዲያብሎስ ጸሐፊዎችና ተርጓሚዎችን፣ነጭ ውሸት አውሪዎችንና ክፉ አማካሪዎችን ከአጠገባቸው አርቀው ከራሳቸው ክብርና ሥልጣን ይልቅ በዚህ ውዝግብ መካከል ነቢዩ በትን.ኤር23፡1‹‹የማሰማርያዬን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮውላቸው!›› እንዳለው ለምዕመናኑ ሲባል ተቀራርበው ቢወያዩ በቀላሉ መፍትሔ ይመጣል ባይ ነኝ፡፡

2. በሊቀ ጳጳስ አቡነ ሳዊሮስ የሚመራው ክንፍ

ከአቶሚክ ቦንብ በላይ አጥፊ ተግባራትን በሌሎች ሀገረ ስብከቶች ጣልቃ በመግባት በሥልጣን ዘመናቸው ያከናወኑትና ቅዱስ ሲኖዶስን በጸሐፊነት ሲያገለግሉ የቆዩት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሳዊሮስ ደቡብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ላይ ልባቸው ተተክሎ ከቀረ አራት ዓመታት በላይ አለፉ፡፡ ብጹዕነታቸው የዛሬ አራት አመት በፊት ችግር ተፈጠረ ተብሎ ቅዱስ ሲኖዶስ እሳቸውን፣ ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤልንና አባ ቃለ ጽድቅን ለአጣሪነት በመደበበት ወቅት የጆበርግና የፕሪቶሪያ ጮሌዎች አጣሪ ቡድኑ አንድ ከሆነ ተንኮላቸው ሊነቃባቸውና ሊጋለጥ መሆኑን ስለተረዱ የአቡነ ሳዊሮስን የንዋይ ፍቅር ካጠኑ በኋላ አበል በሚል ሰበብ ከአቡነ ሕዝቅኤል ደብቀው 17 ሺህ ራንድ እና መጠኑ ያልታወቀ ዶላር በፖስታ አድርገው በእጅ መንሻ መልክ ያበረክታሉ፡፡ ሌላው የሴራ ቡድን ደግሞ ወሬውን ከእነ መረጃው አቡነ ሕዝቅኤል ጆሮና እጅ ይደርሳል ብጹዕነታቸው ድርጊታቸው አሳፋሪ ከብጹዕነታቸው የማይጠበቅ በመሆኑ ሊወቅሷቸው ቢሞክሩም ለምን ነቁብኝ ብለው ተጣልተዋቸው ማጣራቱን ሳይፈጽሙ እጅ መንሻ የተቀበሉበትን የሀሰት ክሶች ሰብስበው ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ፡፡ አቡነ ሕዝቅኤልና አባ ቃለ ጽድቅ ማጣራቱን ፈጽመው ዘግይተው ተመለሱ፡፡ በዚህም የተነሳ እስከ ዛሬ ድረስ ሁለቱ ሊቃነ ጳጳሳት አይነጋገሩም፡፡ አቡነ ሳዊሮስም ከዚያች ጊዜ ጀምሮ በጸሐፊነታቸውና በቲም ዲዮስቆርዮስ የተሸፈነላቸውን የተመደቡበትን ሀገረ ስብከታቸውን ፈርጀ ብዙ ድክመትና ጉድለትና የካህናት በደል ወደ ጎን በመተው በደቡብ አፍሪካ ተመድቦ ለመስራት ብዙ ደክመዋል፡፡ለቤተክህነቱ የማይጠግቡ የተራቡ ጅቦች በርካታ መዋዕለ ንዋይ አፍሰዋል፡፡የመረጃ ምንጬቼ የሚያደርጉትን የስልክ ልውውጥ መነሻ በማድረግ ልክ እንደ አባ ጥዑመልሳን አዳነ ዋና እስኪሆኑ ድረስ ራሳቸውን ም/ሊቀጳጳስ አድርገዋል፡፡ቢሳካላቸውስ ኖሮ? ልክ እንደ ኢትዮጵያ ምዕመናን ደቡብ አፍሪካውያንን በሴራ መምራት ይቻል ይሆን? ደግሞ ሁሉንም ጉዳይ ትተነው አሁን እዚያስ ቢመደቡ እንዴት አድርገው ተግባብተው ሊሠሩ አስበው ይሆን? እንጃ! ግን አይታወቅም አስተርጓሚ ቀጥረው ይሰሩ ይሆናል!

ሊቀ ጳጳሱ አሁን ይረዱ አይረዱ አላውቅም እንጂ እስከ ቅርብ ጊዜ ለሀገረ ስብከትዎ እንዲህ መታወክ ተጠያቂው አቡነ ሳዊሮስ ናቸው ሲባሉ አረ በፍጹም ሊሆን አይችልም እሳቸው ለእኔ ተከራካሪ ናቸው ይሉ እንደነበር አንድ ወደጃቸው አጫውቶኛል፡፡ ዳሩ ብጹዕነታቸው ሁሉን አክባሪ እንጂ በማንም ግለሰብና ሀገረ ስበከት ጉዳይ ጣልቃ ገብተው እንደማያውቁ፣ በሲኖዶስ ስብሰባ ላይ እንኳ ወሳኝ ጉዳይ ካልሆነ በቀር ከመናገር መስማትን የሚመርጡ መሆናቸውን ከበርካታ ሊቃነ ጳጳሳት መረዳት ችያለሁ፡፡ በአሁኑ የግንቦት ስብሰባ ላይ አልተሳካም እንጂ ተሳክቶ አቡነ ያዕቆብ ከሀገረ ስብከታቸው ቢነሱ ኖሮ፤ አነስተኛ ደመወዝና መተዳደሪያ አጥተው በየአህጉረ ስብከቱ የሚንከራተቱ ሊቃውንት ባሉባት ቤተክርስቲያን ሌሎች በደብዳቤ ያልተሾመባቸውን የብር ማግበስበሻ ስልቶቹን ትቼ የትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት ሥራ አስኪያጅና የወለቴ  ማዕዶተ ዮርዳኖስ ቅዱስ ዮሐንስ እና አባ ኪሮስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪነትን ደርቦ ሁለት ደመወዝ ጠቅልሎ የሚበላውን መልአከ መዊዕ ሳሙኤል እሸቱ(ሳሚ ሮቶ) ቤተክህነቱ አከባቢ በደቡብ አፍሪካ ጉዳይ የሽብርና የፕሮፖጋንዳ ወሬን በመንዛት ውጤታማ የነበረውን  ሰሳመሚ ሮቶን ቢሳካ ኖሮ የደቡብ አፍሪካ ሥራ እስኪያጅ ለማድረግ በወሬና በተግባር በመንቀሳቀስ ብዙ ዋጋ ከፍለዋል፡፡

መልአከ መዊዕ ሳሙኤል እሸቱ(ሳሚ ሮቶ)

እነዚህ አካላት ከዚህ ሁሉ ጥልፍልፍ ሴራ አለመሳካት በኋላ ሳይመደቡና በማይመለከታቸው ጉዳይ ጅብ በቀደደው እንዲሉ… ወደ ፊት በዝርዝር የማቀርብላችሁ ሲሆን ሩዋንዳ ቤተክርስቲያን በጋራ ሄደው የፈጸሙት ነገር ለዚሁ የሴራ አብሮነት አንዱ ማሳያ ነው፡፡

የሴራ ቡድኑ አባላት በዩጋንዳ

ከአዲስ አበባው የአቡነ ሳዊሮስ ክንፍ ጋር ትስስር ያላቸው የደቡብ አፍሪካ ጁሐንስበርግና ፕሪቶሪያ ከሳሾች

ሀ. አቶ ገዛኸኝ አበበ

ይህ ግለሰብ የኮ/ል መንግሥቱ ኃ/ማርያም የእህት ልጅ ሲሆን ከአጎቱ ያልተናነሳ ግፍና በደል በመሥራት ላይ እያለ በድንገት የተከሰተውን የመንግሥት ለውጥ ተከትሎ መጀመሪያ ወደ ኬንያ የገባ ሲሆን ኬንያ በነበረበት ወቅት በስኳድነቱ በበርካታ ወንጀሎች እጁ የተጨማለቀና በኋላም የአንድ ወዳጁን የዙምባቡዌ ቪዛ ከፓስፖርቱ ላይ ገንጥሎ የራሱ ፓስፖርት ላይ በመለጠፍ በማጭበርበር ወደ ቤ/ክን በመጠለያነት ገብቶ ነፍሱን ካዳነ በኋላ የራሱን ስራ ወደ ሌላ ማላከክ እይዘዋለሁ ብሎ እስቦ የነበረውን የመንግሥት ከፍተኛ ሥልጣን በለውጡ ምክንያት በማጣቱ ጅብ በማያውቁት ሀገር….እንዲሉ ራሱን ንስሐ የገባ በማስመሰል ኢትዮጵያ ላይ ያለውን የሥልጣን ጥማት ለማሳካት ምቹ አውድ ሆና የታየችው ቤ/ክን ስለሆነች በውስጡ የተቀበረውን ወያኔን ያለማሸነፍ ንዴት ቤተክርስቲያን ላይ ማፍሰስ አለበት እንዴ? ይሄ መታረም ያለበት ነው፡፡ ደግሞም ያስጠለለችውን ቤ/ክን ውለታ ረስቶ በአባቶችና በአገልጋዮች ላይ ሁከትና ያለመረጋጋት በመፍጠር መኖር ነውር ከመሆኑም በላይ እጅግ አሳፋሪ ድርጊት ነው፡፡ ደግሞስ ጀግና ከሆነ ወያኔ ሲያበረው የት ነበር? ስኳዱ ገዛኸኝ ብዙም ያልዳበረችውንና በቂ ገቢ ያላመጣችለትን የሒሳብ መዝገብ አያያዝ(አካውንቲንግ) ትምህርት መነሻ በማድረግ የሀገረ ስብከቱ እና የፕሪቶሪያ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ሒሳብ ሹም እስከ መሆን የደረሰ ይሁዳዊ ሥልጣን አግኝቶ ነበር፡፡ በኋላ ላይ የሀገረ ስብከቱ ሥራአስኪያጅ የነበሩት ፕ/ር ዘሪሁን የፕሪቶሪያ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረትን ሒሳብ ለሳርስ(SARS) መቅረብ ስላለበት ይመርመር ሲባል ከዚያ ግዜ ጀምሮ ረብሻና ብጥብጥ እንደጀመረ አንድ እውነተኛ የማቅ አባል የሆነ ወዳጄ አጫውቶኛል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ  በወቅቱ የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳዳሪ የነበሩትን ቆሞስ አባ ገ/ሥላሴ መርሻ የነበራቸው ጽኑ ቤተክርስቲያናዊ አቋም ስላልተመቸው ያለውን ወታደራዊ ልምድ በመጠቀም የአንድ ቄስ ሚስት የሆነችውን ሴት በማግባባት ዘመናዊ ካሜራ አዘጋጅቶ ገብታ እሳቸው ቤት ሊደፍሩኝ ነው ብላ እንድትጮኸ፤ በቤተክርስቲያኑ ዙሪያ ደግሞ ፖሊስ አዘጋጅቶ ዲፖርት ለማድረግ ዝግጅት በማድረግ የግፍ ድራማውን ሊሰራ ሲሉ ለቤተክርስቲያን ቢሰራ፣ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ ቢያወራ የማየይሰለቸውና የማይደክመው ደቡብ አፍሪካዊ ቄስ ቶምሰን(ተ/ሚካኤል) ጉዳዩን በቅርበት ይከታተል ስለነበረ በወቅቱ ለዓለም ሃይማኖቶች ምክር ቤት ጉባኤ ለንደን ከነበሩት ከብጹዕ አቡነ ያዕቆብ ጋር በስልክ በመነጋገር መነኩሴውን ዲፖርት ከመደረግ ያተርፏቸዋል፡፡ በኋላ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ዳኛው ለመሆኑ ድርጊቱ የተፈጸመው የት ቦታ? ብሎ ጠየቅ ለከሳሾችና ለኦፐሬሽኑ መሪ አቶ ገዛኸኝ አስደንጭ ጥያቄ ነበር፡፡ ዳኛው መልሱን መነሻ በማድረግ ወደ እሳቸው ቤት የሄደችው እሳ ከሆነች መነኩሴውን መጠየቅ አንችልም በማለት እኩይ ዕቅዳቸውን ሁሉ አከሸፈባቸው፡፡ በነገራችን ላይ ይሄ ተልእኮ  ተሳክቶ ቢሆን ሁለት ግብ ነበረው አንደኛ አባን ገ/ሥላሴን አባሮ ያለምንም ተቀናቃኝ ቦታውን መቆጣጠር ሁለተኛው ደግሞ እንድትጮኸ የታዘዘችው መሪ ተዋናይ የሚያስቸግራቸው ቄስ ሚስት ስለነበረች ሥልጣንህ ፈርሷል ብሎ ማሳደድ ነበር፡፡

አቶ ገዘኸኝ እነ ሙጬ(ጅቦ) ‹‹ለማጣራት›› ደ/አፍሪካ በነበሩበት ወቅት ማታ ማታ በተከታታይ አንዳንዴ ከአቡነ ሳዊሮስ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከአቡነ ቴዎፍሎስ ጋር ያደርጉት በነበረው የስልክ ኮንፈረንስ ላይ ለመገኘት ዘወትር ማታ ማታ በድብቅ ወደ ጆበርግ ሥላሴ ይጓዝ እንደነበረ ከቦታው የደረሰኝ መረጃ ያረጋግጣል፡፡

እንግዲህ ምዕመናን የአዲስ አበባ አብያተክርስቲያናት በሰንበት ተማሪዎችና በምዕመናን ጥረት ከጡረተኛና በተለይ አምባገነን ከሆኑ ማርክሲስት የወታደር ቤት የሰበካ ጉባኤ አባላት ነጻ በመውጣት ላይ እንዳለች የደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያንም ንስሐ በገቡ በቅዱስ ቁርባን በተወሰኑ ከአድሎአዊነት በጸዱ የሰበካ ጉባኤ አባላት የመመራት እድል እንዲገጥማት ምኞቴ ነው፡፡

 ለ. ‹‹ዲ/ን›› ንዋይ ገሠሠ

ንዋይ ወደ ደቡብ አፍሪካ ከመምጣቱ በፊት የUN የሱዳን ቡድን ውስጥ የነበረ የጤና መኮንንና በማቅ ስም ከሚነግዱ ጥቂት መሥራች አባላት መካከል አንዱ ነው፡፡ በተለይ እሱ ያለበት የፕሪቶሪያ ሐመረ ኖኅ ኪዳነምሕረት እሱ ከመምጣቱ በፊት ምንም ዓይነት ኮሽታ የማይሰማባትና የተረጋጋ አገልግሎት የሚፈጸምባት ቦታ ሁና ቆይታለች፡፡ ንዋይን የሚያውቁት ሰዎች የውሃ ውስጥ አረንጓዴ እባብ ነው ይሉታል፡፡ ንዋይ ሰበካ ጉባኤ በነበረበት ዘመን ከ9 ወር የሙዳየ ምጽዋት ቆጠራ የተገኘው አጠቃላይ ገንዘብ 35 ሺህ ራንድ ብቻ ነበር፡፡ የዚህ ትልቁ ምክንያት ደግሞ አሜሪካ የሚገኙት የግብር አጋሮቹ እንደሚያደርጉት ለገጠሪቱ አብያተክርስቲያን፣ አድባራትና ገዳማት መርጃ የሚሆን አሥራት እየተቀበሉ ዋጥ ስልቅጥ ማድረግ ነው፡፡ በዚህ ምክንያትም የፕሪቶሪያ ቤተክርስቲያን ራሷን መቻል አቅቷት ከሀገረ ስበከቱ ድጎማ እስከ መደረግ ደረሳለች፡፡

ሐራውያን በሊቀ ጳጳሱና በደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያን ላይ እንዲጽፉና እንዲሳደቡ ከ3ሺህ ዶላር ያላነሰ አሰባስቦ ለዲጄው ለአሉላ የከፈለ ይሄው ግልሰብ ነው፡፡ ይሄ ብር እንግዲህ የእነ አባ አእምሮን ክፍያ ሳይጨምር ነው፡፡ ንዋይ ከሚስቱ በኩል በየጊዜው የሚደርስበትን ቁጣና ድብደባ የሚመወጣው ቤተክርስቲያን ላይ ነው(ፕሮጄክሽን መሆኑ ነው)፡፡ በነገራችን ላይ ሚስቱ አባ ጥዑመልሳን አዳነን በጣም ስላናደዳት በአደባበይ በጥፊ የላሰች ወለተ ሄሮዳድያ ናት፡፡

ንዋይ የደቡብ አፍሪካው ነውጥ አልበቃው ብሎ የአምባሳደር አለምፀሐይ መሠረትን የዩጋንዳ ሹመት ተከትሎ ቢሄድም እዚያ ያለው ምዕመንና ካህን አንድ በመሆኑ ያቀደው እኩይ ዓላማ ሳይሳካለት አፍሮ ተመልሷል(ፕሪቶሪያዎች አንድ ሰሞን ጠፍቶባችሁ የነበረው ለዚህ ነው) ፡፡ አዲስ አበባ የሚኖር አንድ የሁለታችን ወደጅ እንዳረጋገጠልኝ ጊዜ እየጠበቀ የሚነሳ መጠነኛ የአእምሮ ቀውስ እንዳለበት ነግሮኛል፡፡ ምህረቱን እንዲልክለት ምኞቴ ነው፡፡

3. በደቡብ አፍሪካ የጆሐንስበርግ ቅድስት ሥላሴ ከሳሾች

የሊቀ ጳጳስ አቡነ ያዕቆብ ዋና ከሳሾች የሆኑት አስተዳድረዋቸው የማያውቁትና የማያውቋቸው በስደተኛው ሲኖዶስ ‹‹ሥር›› በስም እንጂ በተግባር ያልነበሩ አካላት ናቸው፡፡ በእኔ እምነት ይህ ክስ ኢፍትሐዊ(አድሎአዊ) የሚሆንበት ትልቁ ምክንያት ብጹእነታቸውን መክሰስ የሚችሉት ካወቁዋቸውና ከእነሱ ጋር ከሰሩ በኋላ ነበር፡፡ ባልዋሉበት ባላደሩበት ባላስተዳደሩት እንዴት ተጠያቂ ሊሆኑ ቻሉ? ይሄ እኮ ማለት በሱዳን አስተዳደራዊ ጉዳይ የኢትዮጵያን መንግሥት እንደመጠየቅ ያለ ነው፡፡

በነገራችን ላይ የሁለቱ ሲኖዶሶች አንድነት አብዛኛው የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች ቢያስደስትም የጆሐንስበርግ ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክንን የግል ንብረት አድርገው ለሚተዳደሩት ለእነ አባ አእምሮ ታከለ፣ ለእነ መቶ አለቃ ንብረትና ግብረ አበሮቻቸው አስደንጋጭ መርዶና ባልተዘጋጁበት ወቅት የመጣ ትልቅ ዱብዕዳ  ነው ምክንያቱስ? ቢባል ቤተክርስቲያኑ ወደ ህጋዊ አካሄድ ገባ ማለት ጉሮሮአቸው ተዘጋ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ መከፈል ያለበት ዋጋ ሁሉ ተከፍሎ ቤ/ክኑ የግል ንብረት እንደሆነ መቆየት አለበት፡፡

 የጆሐንስበርግ ቅድስት ሥላሴ ካቴደራል የማን ነው?መሪዎቹስ እነማን ናቸው?

ይህ ካቴደራል በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሥር ያለ ተብሎ ለስሙ ይጠራ እንጂ በቅዱስነታቸው ጨርሶ የማይታወቅ በአብዛኛው የአንድ ዘር ስብስብ የተያዘ የግል ይዞታ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ይህ ቤ/ክን አስራት በኩራት፣ፈሰስ፣ሰበካ ጉባኤ ጨርሶ የሚሉት ቃላት ላለፉት በርካታ አመታት ተሰምተው አይታወቁበትም፡፡ ቤ/ክኑን  በግል ንብረትነት የያዙትና በግል እያስፈራሩ የሚኖረው በኢትዮጵያ ምድር የተወለዱ ደራጎኖች እነ መቶ አለቃ ንብረት ጌታነህ እና ከ6 ዓመታት በላይ ሊቀመንበር የሆነው አቶ ገበየሁ ባሕሩ ናቸው፡፡ አባ አእምሮ ደግሞ ኢትዮጵያ ሳለ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስቀጥራችኋለሁ እያለ የስንቱን ምስኪን ካህንና አገልጋይ ቤት፣ ከብትና ንብረት አሽጦ በድንበር በኩል ወደ ደቡብ አፍሪካ ከገባ በኋላ ለእነ ንብረት ምቹ የዲያብሎስ ፈረስ ሆኖ ስላገኙት በአግባቡ እየተጠቀሙበት ይገኛል፡፡ የጆሐንስበርግ ቅድስት ሥላሴ ካቴደራል የሚመሩ ሰዎች የቆሸሸ ስብእና እንመልከት፡-

ሀ. አባ አእምሮ ታከለ

በተለይ የዩቲዩቡን ቃለ ምልልስ ጊዜ ኖሮአችሁ ብታደምጡ ሰለ ሰውዬው የበለጠ ትረዳላችሁ

እኚህን ‹‹መነኩሴ›› የማውቃቸው ገና መርካቶ ራጉኤል ስብከተ ወንጌል ውስጥ እያሉ ነበር፡፡ ከዚያም በፋንታሁን ሙጬ የሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ዘመን የላፍቶ ሚካኤል አስተዳዳሪ ሆነው ይሾማሉ፡፡ ያው አዲስ አበባ ላይ ለመሾም የመጀመሪያ መስፍረት ብር(አሁን ካልጨመረ ለአስተዳደሪነት 100ሺህ-200ሺህ) ሁለተኛው ደግሞ  አፈ ቀላጤ መሆን ብቻ ነው፡፡ እዚህ ላይ ልብ እንድትሉልኝ የምፈልገው አንዳንዶች ሙጬና አባ አእምሮ ዝምድና አላቸው ይላሉ እነ የማውቀው ግን አባ እእምሮን ያሾማቸው ዘራቸው ወይም የቤ/ክን ዕውቀታቸው ሳይሆን ብራቸው፣ የመክፈል አቅማቸው ብቻ ነው፡፡ አንዳንዶች አባ አእምሮን በሰራው እኩይ ተግባር ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ መመለስ እንደማይችል ይገልጻሉ፡፡ ምንም እንኳን ዛሬ ከባለቤት አልባው ቤ/ክን በገፍ በተዘረፈው ገንዘብ ቢወዳጁም እጅና ጓንት ቢሆኑም የትላንቶቹ ደጀ ሰላማውያን የዛሬዎቹ ሐራዎች ከዚህ በፊት በደጀ ሰላም ብሎጋቸው ጁን 23፣ 2012 በሙስና የሚታሙት የላፍቶ ደ/ትጉሃን ቅ/ሚካኤል አስተዳዳሪ አባ አእምሮ ታከለ የአ/አ ሀ/ስብከት ም/ሥ አስኪያጅ ኾና ተሾሙ›› በሚለው ርእሰ አንቀጽ ሥር

‹‹ላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተዘዋውረው በአስተዳዳሪነት ከተሾሙ ሁለት ዓመታትን ብቻ ነው ያስቆጠሩት – አባ አእምሮ ታከለ ፡፡ በሁለት ዓመት የደብሩ ቆይታቸው ግን ካራታቸው በመዝገብ ላይ ያልሰፈረ የወርቅ እና የውጭ ምንዛሬ ስርቆትን ጨምሮ ለተፈጸሙ ሕገ ወጥ የነዋየ ቅድሳት ሽያጭ እና የሙዳይ ምጽዋት ቆጠራ እንዲሁም ያለ ደረሰኝ ገቢ የመሰብሰብ ድርጊቶች ዋነኛ ተጠያቂ መኾናቸው በሰፊው ይነገራል። በደብሩ የአንድ ወገን የጎጠኝነት አስተሳሰብ እንዲስፋፋና ሌሎች በርካታ አስተዳደራዊ ችግሮችም እንዲከሠቱ ምክንያት የመኾናቸው ጉዳይ አደባባይ የወጣ ምስጢር መኾኑን ብዙዎች ይመሰክራሉ። በድንገት ተነሥተው ከሄዱበት ገዳም በጣም በአጭር ጊዜ ውስጥ ምንኩስና ከተቀበሉ በኋላ ብዙም ሳይቆዩ የላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ የኾኑት አባ አእምሮ÷ ይህን ሹመት ለማግኘት ለቀድሞዎቹ የሀ/ስብከቱ አስተዳደር ሓላፊዎች እስከ 2ዐ ሺሕ ብር ገደማ መማለጃ መስጠታቸው ተጠቁሟል፡፡ አባ አእምሮን በቅርበት የሚያውቋቸው ሰዎች ሰውዬው ገንዘብ አምላኩቤት ለመሥራትና መኪና ለመግዛት የሚቋምጡ፣ የመጠጥ ሱስ እና ከምንኩስና ሕይወት ይኹን ከጥሩ ምእመን ጋራ የማይጣጣሙ እኵይ ጠባዕያትን የተላበሱ ስለመኾናቸው ይመሰክሩባቸዋል፡፡…››

እንግዲህ አባ አእምሮ በላፍቶ ሚካኤል በደብሩ በታሪክ ተሠርቶ ታይቶ የማይታወቅ ትልቅ ውንብድና ከሰሩ በኋላ ባልታወቀ ሁኔታ(በእኔ እምነት ምናልባት በዘረፋና በተንኮል ሊቅነታቸው ሊሆን ይችላል)  ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ም/ሥራ አስኪያጅ ሁነው ይሾማሉ፡፡

ይህ ሰዓት ደግሞ አስር አለቃ ፋንታሁን ሙጬ በቅዱስ ሲኖዶስ ወሳኔ መሠረት ይከሰስ የተባለበት ጊዜ ነበር፡፡ የትላንቶቹ ደጀ ሰላማውያን የዛሬዎቹ ሐራዎች ከዚህ በፊት በደጀ ሰላም ብሎጋቸው በNov 2010 << የሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ ሹመት እያነጋገረ ነው >> በሚል ርእስ ሥር

‹‹የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን በተመለከተ በቅዱስ ሲኖዶስ የተሠየመው አጣሪ ኮሚቴ ለጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ባቀረበው ሪፖርት እንዲሁም በ29ው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ስብሰባ ላይ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሪፖርት ውስጥ ተካትቶ በቀረበው የቁጥጥር አገልግሎት ሪፖርት ቃለ ዓዋዲውን ተከትሎ ከመሥራት እና መልካም አስተዳደርን ከማስፈን አኳያ በተገኘባቸው ከፍተኛ ግድፈት የተነሣ ከሥራ አስኪያጅነት ሐላፊነታቸው እንዲወገዱ፣ የፈጸሟቸው በደሎች ሁሉ ተጣርቶ በሕግ እንዲጠየቁ የተወሰነባቸው ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ማዕርግ የልማት ጉዳዮች ዘርፍ ሥራ አስኪያጅ ሆነው መሾማቸው ጥያቄዎችን እያስነሣ ይገኛል፤ በቤተ ክርስቲያኒቱ ወቅታዊ ችግሮች ዙሪያ በምእመኑ ዘንድ አንድ አቋም እና ግንዛቤ እየተፈጠረ የመጣበትን አትኩሮት ለማስቀየስ የሚደረግ ጥረት አካል ተደርጎም ተወስዷል፡፡›› ሙሉውን ከብሎጉ ያንብቡ!

እዚህም ላይ ታዲያ ጮሌው አባ አእምሮ ትልቅ ውለታ ሠራለት፡፡ ሙጬን ከሳሽ መሆን የሚችለው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ነበር፡፡ የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ አጀንዳውን ይዞ በሚነጋገርበት ጊዜ አባ አእምሮ ይሄ ክስ እኮ ሙጬን ብቻ አይመለከትም ሁሉንም የአስተዳደር አካላት የሚመለከት ነው ብንተወው ይሻላል ብሎ በማስፈራሪያ ጭምር ይናገራል፡፡ በዘረፋው ላይ የተነካኩት አብዛኛው የአስተዳደር ጉባኤ አባላት ያላዩትን ነገር ስላሳያቸው በማመስገን የውሾን ነገር ያነሳ…ብለው ተማምለው የአጀንዳውን ግብአተ መሬት አከናወኑ፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አባ አእምሮና ሙጬ በፍቅርና በጥቅም ትስስር ከነፉ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ፋንታሁን ሙጬ አባ አእምሮን በማንኛውም ጉዳይ መተባበር ግዴታው ነው፡፡ ለዚህም ይመስላል በእነ አቡነ ሳዊሮስ የደቡብ አፍሪካ ጉዳይ ከግብ እንዲያደርስ ሙጬ የተመረጠው፡፡ የቤተክርስቲያን ራስ ክርስቶስ ግን ተንኮላቸውንና ሴራቸውን በሙሉ አከሸፈባቸው፡፡ በነገራችን ላይ አባ አእምሮ ከሊቀ ጳጳስ አባ ያዕቆብ ጋር ምንም ዓይነት ጠብም ይሁን ንግግር የላቸውም አያዉቃቸውም፡፡ በቃ ወደ ካናዳ እና አሜሪካ ለመሸጋገር ከፍተኛ ምኞትና ህልም እንዲሳካ ከፈለጉ ለአቡነ ቴዎፍሎስ ይህን ሴራ በስኬት መውጣት እንዳለባቸው መመሪያ ስለተሰጣቸው ነው፡፡

ለ. አቶ ገበየሁ ባሕሩ

ይህ ግለሰብ ‹‹የሰበካ ጉባኤው›› ሊቀመንበር ከሆነ ወደ አስር አመታት ሊጠጋው የደረሰ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ከቤተክርስቲያኒቱ በዘረፈው ገንዘብ የሁለት ግሮሰሪ ባለቤት ሁናል፡፡ኢትዮጵያ ላይ ደግሞ ፎቅ በማስገንባት ላይ ነው፡፡በጭራሽ ሕጋዊ አሠራር በቤተክርስቲኒቱ እንዳይኖር የሚፈለገው ይህ ግለሰብ ያለ ማኅበረ ምዕመናኑ ጥቆማና ፈቃድ ለእኩይ ተግባሩ የሚመቹትን ሰዎች (ሄኖክና የሺን) በደብዳቤ ጥሪ የሰበካ ጉባኤ አካል እንዳሉ ለማስመሰል ምዕመናኑን እያታለለ ይገኛል፡፡

ሐ. መቶ አለቃ ንብረት ጌታነህ

ይህ ግለሰብ የሥላሴ ቤተክርስቲያን ካዝና(ባንክ ቤት) ሲሆን የትኛው ገቢ ይሁን ወጪ በእርሱ በኩል ካላለፈ ሊበላህ ይደርሳል፡፡ በሽጉጥ ያስፈራራሃል ያሳድድሃል ብቻ ምን አለፋችሁ ገንዘብ ከፈለክ ለእሱ መገዛት ብቻ ነው ምርጫህ፡፡ 45 ሺሕ ራንድ ይከራይ የነበረውን ሕንጻ በተቆጣጣሪነት በንጽሕና ያገለግል የነበረውን አቶ ሕሊና ለገሰ አላስበላ ብሎ ስላስቸገረው ብቻ ካባረረ በኋላ የዚህን ኪራይ ብር እየተቀበለ አከፋፋይ የነበረው ይኸው ሰው ነው፡፡ በነገራችን ላይ ብሩን በልተው በልተው ግራ ሲገባቸው አጣሪዎች ወደ ደቡብ አፍሪካ በመጡ ወቅት ከነ ሙጬ ጋር ይመካከሩና አባ አእምሮ አንድ ነገር በዓውደ ምሕረት ላይ እንዲናገሩ ያደርጋሉ ‹‹… የዚህ ሕንጻ ተከራዮች ገቢ የለንም እያሉ ነው፤ ለአንድ ኢትዮጵያዊ ተከራይ ሰጥተነው 20 ሺህም ያግኝ 10ሺህ ለቤ/ክኑ እኩል ያካፍላል…›› እያሉ ሲናገሩ ሕንጻውን በእጅ አዙር ሸጠው ወደ አሜሪካ ለመጓዝ አስበው መሆኑን የነቁት በተለይ ማኅበረ ተክለ ሃይማኖቶች ‹‹…እርስዎ ሰውዬ በጣም ተንኮለኛና ክፉ ሰው ነዎት፣እኛ ከእርሶ ጋር አንኖርም…››ብለው ስላስደነገጧቸው ቆሌያቸው ተገፈው ነው ያሉት፡፡ በእነ መቶ አለቃ ንብረት እየሰለጠኑ ያሉት ታዳጊ በዝባዦች እነ ነጻነት፣ ዳኜ የመሳሰሉት ወጣቶች ከቤተክርስቲያኒቱ ብር እየተሰጣቸው የፈለጉትን ይመልሳሉ ያልፈለጉትን ያስቀራሉ፡፡ ምን አለፋችሁ የቤተክርስቲያኒቱን ብር መነገጃ አድርገውታል፡፡ አሁን በቅርብ ጊዜ ከታምሩ አበበ ጋር ለክሱ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ እንኳ ወጪያቸው ሙሉ ለሙሉ የተሸፈነው ከቤተክርስቲያን ወጪ ተደርጎ ነው፡፡ ይህንን እዚያ ካሉ አገልጋዮች ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

መ. አቶ ታምሩ አበበ

አቶ ታምሩ ተቃዋሚ መስሎ የኖረና እሱ ባለበት አካባቢ ባለ የፖለቲካ ቡድን ሰብሳቢ ቢሆንም ራሱን የደቡብ አፍሪካ የኮሚኒዩቲ ሰብሳቢ አድርጎ የሾመ፣ምንም አይነት መተዳደሪያ የሌለው ከእነ ንብረት ወርሃዊ ክፍያ እየተከፈለው የሚኖር እግዚአብሔር የሰጠውን የንስሐ ዕድሜ በአግባቡ መጠቀም ያልቻለ ከንቱ ሰው ነው፡፡ ይህ ግለሰብ ትክክለኛው የደቡብ አፍሪካ የኮሚኒቲ ሰብሳቢ ፕ/ር ሙላቱ ፍቃዱ መሆኑን ቢያውቅም የቤተክርስቲን ጠላቶችን ሐራውያን እነ አሉላን ተጠቅሞ በተረቀቀለት ማታለያ የኮሚኒዩቲ ደብዳቤ ላይ የፈረመ ነው፡፡

በመሠረቱ ማንም ሰው የትኛውንም የፖለቲካ አቋም መያዝ መከተል መብቱ ነው፡፡ ቤ/ክንንና ምዕመናን ግን ለፖለቲካ እኩይ ዓላማ መጠቀሚያ ለማድረግ መሞከር ያረጀ ያፈጀ አካሄድ ነው፡፡ አቶ ታምሩ የደቡብ አፍሪካ ምዕመናን እንደሚያውቁት ምንም እንኳን እነ ንብረት  እንደ መደበኛ አገልጋይ ደመወዝ ቢከፍሉትም በተደጋጋሚ ቤተሰቡን ማስተዳደር ልጆቹን ማስተማር ባለመቻሉ እየተለመነለት እንደሚኖር አገር ያወቀው ፀሐይ የሚቀው ጉዳይ ነው፡፡ አቶ ታምሩ የተሾመበት ሴራ በመክሸፉ ወደ ደቡብ አፍሪካ መመለስ ጨንቆት ይህንን ጽሑፍ እስከ ጻፍኩበት ጊዜ ድረስ አዲስ አበባ ውስጥ ከእነ አባ አእምሮ በሚደረግለት ድጎማ እንደሚኖር ለማወቅ ችያለሁ፡፡

በነገራችን ላይ አቶ ታምሩ ቅዱስ ፓትርያርኩን እንዲያገኝ ያመቻቸለት ‹‹ወንዱ እጅጋየሁ እየተባለ የሚጠራው›› አቶ ቴዎድሮስ ሞላ(ቴዲ ሞላ) የመርካቶው አራጣ አበዳሪና ተበዳሪ የቅድስት ቤተክርስቲያን መዋቅር ውስጥ ለመግባትና ታዋቂነትን ለማግኘት ሲል በአሁኑ ሰዓት ሁለት መኪናዎቹን ሸጦ ያሉትን ስልኮች ዘግቶ ከደረሰበት ኪሳራ ለማገገም ሲል ራሱን የአቡነ ማትያስ ዋና የግል አማካሪ እንደሆነ አድርጎ የሚያስወራ ነው፡፡ ይህ ግለሰብ በስመ መርካቶ ነጋዴነት ቤተክህነት ገብቶ (በአብዛኛው አባቶች ብር ሲያዩ መቼም ብር እንደሚሉ ስላጠና) አሳክማለሁ፣ የቤት እቃ አሟላለሁ፣ ቅዱስነታቸው በየቦታው ሲዘዋወሩ የሚሰጧቸውን የስጦታ ዕቃዎች እኔ እገዛለሁ እያለ ቤተሰቡን ችግር ላይ ጥሎ ከክስረቱ ለማገገም መርካቶ ራጉኤልና የተለያዩ አብያተክርስቲያናት ላይ የሱቅ ባለቤት የሆነ በቤተክርስቲያን ላይ የተሰማራ ደላላ ነው፡፡ ቴዲ ሞላ በአሁኑ ሰዓት ከደህና የንግድ ሥራውና ውጤታማ የመርካቶ ራጉኤል አገልግሎቱ ተለይቶ በአራጣ የተበደረውን ብድርና በየቦታው ያሉትን ዕቁቦች መክፈል ባለመቻሉ እኔ የማውቃቸውን ሁለት ዘመናዊ መኪናዎች ሽጦ፣ በጤንነቱም ላይ ከባድ የሆነ የዲስክ መንሸራተት ደርሶበት ራሱን የቤተክህነቱ ፈላጭ ቆራጭ፣አድራጊ ፈጣሪና ያደገበትን የበለጸገበትን መርካቶና አከባቢውን ለቆ የወንበዴዎች ዋሻ ቤተክህነቱን ተጠግቶ የሚኖር የከሠረ ነጋዴ ነው፡፡ አቶ ቴዲ ቤተክህነት ውስጥ እያጭበረበረ ካለበት ህቡዕ ደሞዝተኛነትና የድለላ ሥራዎቹን ከቤተክህነቱ መዋቅር ውስጥ ገለል ካላለ ስለ እርሱ ጉዳይ በቀጣይ በዝርዝር በመረጃ አስደግፌ የምመለስበት ይሆናል፡፡

ሠ. ‹‹ቀሲስ›› በቀለ

እኚህ ቄስ ለባለ 58 ገጹ ሪፖርት መስረጃነት እንደ ዋና ተደርገው የቀረቡና ከ9 ዓመታት በላይ ያለትዳር አጋር የቆዩና በዚህ ጽሑፍ ለማካተት ልቡናዬ ያልፈቀደውን እኩይ ተግባራት የፈጸሙ ናቸው፡፡ ከአባ አእምሮ ጋር የልብ ወዳጅ ያህል ቅርበት ያለው አንድ ደቡብ አፍሪካ ያለ ወዳጄ እንደ ነገረኝ ከሆነ በፈጸመውም የማጭበርበር ሥራ ምዕመናን አንቀው ይዘው ሲጠይቁት መቼ ነው አቡነ ያዕቆብ ያስደበደቡህ? ብለው ሲያፋጥጡት አውነቱን አባ አእምሮ የሐሰት ምስክር መሆን ይችል ዘንድ 40 ሺህ ራንድ እንደከፈሉት እውነቱን አስወጥተውታል፡፡ ይህ ድርጊቱ ከተሰማ በኋላ በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ምዕመናን በመሰባሰበብ ክስ የመሰረቱበት ሲሆን በፈጸመው የሐሰት ምስክርነት ምክንያት በካህናትና በምዕመናን አንድነት አይንህን ለአፈር እንደተባለ ለማረጋገጥ ችዬአለሁ፡፡ ሊቀ ጳጳሱም ቢሆኑ እስከ ዛሬ ድረስ ያለ ሚስት እየኖረ ከሆነ ሥልጣነ ክህነቱን መያዝ ይገባቸው ነበር ብዬ አምናለሁ፡፡ የአቶ በቀለን መከሰስ ሳነሳ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ያዕቆብ በእነ ሙጬ ላይ በስም አጥፊነት ለምን ክስ አይመሰርቱም? ብዬ አንድ ወዳጃቸውን ብጥይቀው የሰጠኝ መልስ የሚከተለው ነው‹‹የተፈጸመባቸውን ድርጊት ኢሰብአዊ አስመልክቶ በርካታ ወዳጆችና የሕግ ባለሙያዎች በዚህ ጉዳይ ውክልና ይስጡንና እንክሰሳቸው ብለው ቢጠይቋቸውም የብፁእነታቸው መልስ ግን…ይሄንን ጉዳይ ለመድኃኔዓለም አሳልፌ ስለሰጠሁ በዓለማዊ ፍርድ ቤት ክስ በመካሰስ ቤተክርስቲያኔን አላዋርድም›› ነበር መልሳቸው ብሎኛል፡፡ በእኔ እምነት ግን እንዲህ ማን ይነካናል ብለው በትዕቢት ለተወጠሩ አሳማዎች ክሱ ከአስፈላጊ በላይ ነው ባይ ነኝ፡፡

በተዘዋዋሪ መንገድ የደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያን እንዳትረጋጋ ያደረጉ ብፁአን አባቶች

ሀ. የካሊፎርንያ ኔቫዳና አሪዞና ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ቴዎፍሎስ

በምንኩስና ስማቸው አባ ጽጌ ድንግል ደገፋው የደቡብ ጎንደር መነኮሳትን ብቻ በመሾም ይታወቅ ከነበረውን የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ  ሲኖዶስ መካከል ሾልከው ከገቡ ጎጃሜ መካከል አንዱ ናቸው፡፡ ብጹዕነታቸው በአሜሪካ ወደ ሎስ አንጀለስ ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላለፉት 22 ዓመታት አገልግለዋል ። ለዚህም የረዳቸው የአደባባይ ንግግር ያይደል የጠረጴዛ ላይ የጥልቅ ሴራዎች(Conspiracy) ሊቅ በመሆናቸው እንደሆነ በቅርብ የሚያውቋቸው አባቶችና ወንድሞች ገልጸውልኛል፡፡ እኚህ አባት በቅርብ አባ ቶማስ የሚባል መነኩሴ እጅግ ተበሳጭቶ ከደበደባቸው ውጪ በአደባባይ ሲናገሩ ድምጻቸው አይሰማም፡፡ ይህን የበለጠ ለመረዳት በውጪው ሲኖዶስ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ በነበሩበት ወቅት ማኅበረ ቅዱሳን ጠልነታቸውን የገለጹበትን የጻፉትን ደብዳቤ ማንበብ በቂ ሊሆን ይችላል፡፡

ታዲያ ብጹዕ አቡነ ቴዎፍሎስ ያለ ግል ቤተክርስቲያን የአሜሪካ ኑሮ ስለሰለቻቸው ደቡብ አፍሪካ በመጀመሪያ የአሁኑ የሲኖዶስ ጸሐፊ አቡነ ዮሴፍን በመቀጠልም ራሳቸው የደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያንን መውረስ ነበር እቅዳቸው፡፡ ለዚህ ምስክር የሚሆነው አጣሪዎቹ እነ ሙጬ ደቡብ አፍሪካ የነበረው የማያቋርጥ የስልክ ምልልስ፣ የእስትንፋሰ ዲያብሎሱን የታደሰ ወርቁን ጽሑፍ በማረም እንዲሁም በቅዱስ ሲኖዶ ስብሰባ ላይ የደቡብ አፍሪካ ጉዳይ በአግባቡ ታዮቶ መወሰን አለበት ብለው በርካታ ብጹአን አባቶች ቢያቀርቡም አቡነ ቴዎፍሎስ ግን እንዴት የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መልሱ ይታያል? በመንፈስቅዱስ የሚመራ ጉባኤ እንዴት ውሳኔውን ይቀለብሳል? ብለው ሀሳብ በመስጠት ነገሩን የበለጠ ውስብስብ በማደረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አደርገዋል፡፡ በቅዱስ ሲኖዶስ ታሪክ እንኳን ገና በቃለ ጉባኤ ሰፍሮ ያለተፈረመ ቀርቶ የተፈረሙ በርካታ ቃለ ጉባኤያት ተግባራዊ የማይሆንበት ቤት መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አቡነ ኤልያስና በጵጵስና አሿሿማቸው ላይ ጥያቄ እየተነሳባቸው ካሉ የስውዲኑ ብጹዕ አቡነ ሕርያቆስ ሌላኛው የደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያን ሰላምና መረጋገት እንዳይኖራት ጥረት ከሚያደርጉ ያለ ሀገረ ስብከታቸው ጣልቃ ከሚገቡ አባቶች መካከል ይገኙበታል፡፡ በአቡነ ሕርያቆስ አሿሿማቸውላይ እየተነሳ ያለው ጥያቄ በእኔ እምነት የስርዓተ ቤተክርስቲያንን ጠንቅቆ ያለማወቅ ነው ባይ ነኝ፡፡ ከዚህ ይልቅ ለእኔ ትልቁ ጉዳይና ጥያቄ አንድ መነኮስ ትልቁና የመጨረሻው የሥልጣነ ክህነት ማዕረግ ጵጵስና ከደረሰ በኋላ እንዴት አንድ ተራ ምዕመን የማይሰራውን ሴራ ለመስራት ይተጋል? የሚለው ነው

ለ. ብጹዕ አቡነ ሉቃስ

የሴቲት ሁመራና የሰሜን አፍሪካ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሉቃስ የደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያንን አጥብቀው እንዲከታተሉ ምክንያት የሆነው ም/ሊቀጳጳስ ነኝ ባዩ እና ከደቡብ አፍሪካ በበርካታ ክሶችና ቅሌት የተባረረው አባ ጥዕመልሳን የሚያቀርብላቸውን እኩይ ወሬና በራሱም ይሁን በንስሐ ልጆቹ በኩል የሚያቀርብላቸው ገጸ በረከት ስላታለላቸው ነው፡፡ አባ ጥዑም ደቡብ አፍሪካ ከተመደቡ ጀምሮ ከአዋሳ ጀምሮ ባላቸው መተሳሰር ምክንያት የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊነታቸውን በመጠቀም ከአባ ጥዑመ ልሳን ጋር በመሆን አቡነ ያዕቆብን ለማስነሳት ከፍተኛ ትግል አድርገዋል፡፡ በወቅቱም አቡነ ያዕቆብ ጳጳሳትን ወደ ብጹዕነታቸው በመላክ ከሀገረ ስበከታቸው ላይ እጃቸውን እንዲያነሱ እንዳሰሰቧቸውና በእምቢተኝነት እስከአሁን እንደቀጠሉ ለማወቅ ችያለሁ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አቡነ ሉቃስ በቻሉት ሁሉ ከአቡነ ያዕቆብ ተቃራኒ መቆም ሥራቸው  ሆነ፡፡ በ2011 ዓ.ም የግንቦቱ ሲኖዶስ እነ ታምሩ አበበ ክሱን ከዳር ለማድረስ ይሰበሰቡ የነበሩት በአቡነ ሉቃስ ቤት ሲሆን ተከታታይ ስብሰባቸው ግን በአንድ አስደንጋጭ ክስተት ምክንያት መቀጠል አልቻሉም፡፡ ይኸውም የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ሳይጠናቀቅ  አቡነ ሉቃስ ድንገት ይታመሙና ወደ ላንድማርክ ሆስፒታል ይገባሉ፡፡ ሒኪሞቹ የብጹዕነታቸው ሕመም ጋግሪን መሆኑን ይነግሯቸዋል፡፡ በኋላም አንድ እግራቸውን መቁረጥ ግድ ሆነና ተቆረጠ፡፡ ይህን አጋጣሚ ስሰማ እጅግ ከመደንገጤም በላይ በቃ ለዚሁ ነው የምንፋጀው? የምንገፋፋው? ማለቴ አልቀረም፡፡ያው ሁሉም ቀሪ ኃላፊ ነው፡፡ መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ከላይ እስከ ታች ላለነው ልብ ይስጠን፡፡

እዚህ ላይ ልብ ያለው ልብ ይበል! አነዚህ ሰዎች ይህን ሁሉ ርብርብ ያደረጉበት ትልቁ ምክንያት የደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያ በአቡነ ያዕቆብ ወደ ሕጋዊ መስመር ከገባ በቃ ቤተክርስቲያንን የግል መተዳደሪያ፣መነገጃ ማድረግ ሊቀር ስለሆነ ነው፡፡ ጎበዝ ይሄ እኮ የሕልውናቸው ጉዳይ ነው፡፡ ስለዚህ የእነዚህ እኩያን ትልቁ ስሜታቸውና ፍላጎታቸው የራሳቸውን ሰው ማስመደብና በልተው የማያስበሉትን በእነሱ አስተሳሰብ ሞኝ የሆኑትን አባት  ማስነሳትና በሀገረ አሜሪካ እንዳሉት ግብር ከፋይ የግል ይዞታ አብያተክርስቲያናት ማድረግ  ነው፡፡ ይህ ካልተሳካ ደግሞ በኢትዮጵያ በኩል ባለው ቡድን ቤተክርስቲያኑቱን ያለ ርኅራኄ መዝረፍ ማዘረፍ ነበር፡፡

4. በደቡብ አፍሪካ አጣሪ ሆነው ተመደበው ስለነበሩ ግለሰቦች ማንነት

ይቀጥላል…

ውድ አንባብያን! በቀረው የሱባኤ ጊዜ በደቡብ አፍሪካ ያሉ የኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ ምዕመናንን የገጠማቸውን ፈተና ሁሉ ያርቅላቸው ዘንድ በጸሎት እንድናስባቸው አደራ እላለሁ!

ተጻፈ ነሐሴ 08 ቀን 2011 ዓ.ም

እስትንፋሰ ዲያብሎስ ሐራዊ ታደሰ ወርቁ

ዘመቻ ጌዴዎን ክፍል ሦስት

እጅግ ጨዋ ስለሆነው ስለ ታደሰ መጻፍ ከመጀመሬ በፊት በጣም ሲያስጨንቀኝ የነበረው ነገር በምን ቃል፣ በምን መንገድ ልገልጸው እችላለሁ የሚለው ነበር፡፡ የቤተክርስቲያንን ትምህርት ባለማወቅ ፍጹም ጨዋ (ያለተማረ)ና የዳንኤል ቶፋ(የሌላን ሰው ሥራ ወክሎ የሚሰራ)  የሆነውን ይህን ሐራዊ ለመግለጥ ግሩም ግብርከ የሚያስብል አንድ አስገራሚ ፍጥረት አገኘሁኝ፡፡ ይኸውም በአለማችን እጅግ አስፈሪውና በብዛት በደቡብ አሜሪካ (በተለይ በኮሎምቢያ) የሚገኘው ስኮፖላሚን (Scopolamine) ወይም በተለምዶ እስትንፋሰ ዲያ ሎስ (Devil’s Breath) በመባል የሚታወቀው ተክል(ዕፅ) ነው፡፡

ከላይ የመምትመለከቱት ሦስተኛው እፀ ፋሪስ(አስተናግር) ነው፡፡ አበባው እንዳያምታታችሁ ነው እዚህ ጋር የገባው፡፡ ሁለቱ ግን እስትንፋሰ ዲያብሎስ በአበባ እና በፍሬ ጊዜ ነው

ይህን ዕፅ የወሰደ ሰው ሲንቀሳቀስ ስናየው ፍጹም ጤነኛ፣ የተረጋጋ፣ እና በሙሉ አዕምሮው የሚያስብ ይመስላል።ምንም ዓይነት የመጦዝ ወይም ራስን የመሳት ስሜት አይታይበትም፡፡ ነገር ግን እውነታው ከዚህ የራቀ ነው።የዚህን ዕፅ ፍሬ ዱቄት በአፍንጫቸው በኩል ውልብ ያለባት ሰዎች ፈረንጆቹ እንደሚሉት በደመ ነፍስ የሚንቀሳቀስ፣ ፍጹም ታዛዥ (Zombie) ሁነው ይታያሉ። ዕጹን ላቀመሰው ሰው ፍጹም ታዛዥ ሆኖ መከተል ብቻ ነው። እቤት እንሂድ እሺ፣ ወደ ባንክ እንሂድ እሺ፣ አልጋ ላይ እንተኛ እሺ፣ መኪናህን ስጠኝ እሺ፣ ያለህን ንብረት በሙሉ ስጠኝ እሺ፣ ሚስትህን ልተኛት እሺ፣ ባልሽን ልተኛው እሺ፣ ገደል ልክተትህ እሺ…እሺ…እሺ…ብቻ። ብቻ ምን አለፋችሁ የሚታዘዘውን ትዕዛዝ ሁሉ በሙሉ ፈቃደኝነትና ትብብር መፈጸም ብቻ ነው። ይህን ሁሉ ሲያደርጉ ራስን መሳት ብሎ ነገር የለም። ፍጹም ጤነኛ። ብቻ አድርግ የተባለውን ሁሉ ማድረግ ነው። በሌላ አገላለጽ ሰውየው ጤነኛ ያልሆነ ወይም አዕምሮው የተወሰደበት ወይም እንዳይሰራ የተደረገበት ነገር ግን ጤነኛ የሚመስልና የሚጠየቀውን በፍጹም አዛኝነትና ታዛዥነት የሚፈጽም ማለት ነው። ፈረንጆቹ ሲገልጹት “scary hallucinations which even induce a dangerous, zombie-like state” ይሉታል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ በሀገሪቱ መዲና በአዲስ አበባ ተመሳሳይ ነገሮች እየተፈጠሩ እንዳሉ ሰምተናል።በቅርብ የምናውቀው ሰውም ለፍቶ ያጠራቀመውን 80 ሺህ ብር እራሱ ወደ ባንክ በባጃጅ ወስዶ፣ ከባንክ አውጥቶ እንደሰጠ እናውቃለን። የሚያስታውሰው የሆነ ሰው አፍንጫውን እንዳሸተተው ብቻ ነው። ከዚያ ውጪ ዘግይቶ የተገነዘበው የባንክ አካውንቱ ባዶ መሆኑን ብቻ ነው። ተመሳሳይ ሌላ ታሪክ እንጨምር። አዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በአንዱ የሚሰራ የሆነ ሰውም የሆኑ ሰዎች ሰላምታ ሰጥተውት እንደተሳሳሙ ያስታውሳል፤ ነገር ግን ሞባይሉን፣ ላፕቶፑን፣ ዋሌቱን፣ ብቻ በወቅቱ ይዞት የነበረውን ሁሉ እራሱ አውጥቶ እንደሰጠም ሰምተናል። ታሪኩ ብዙ ነው። የሰማችሁ ወይም የደረሰባችሁ ታውቁታላችሁ። 

በዚህ እጅግ አስፈሪ በሆነ ዕጽ የተጠቁት እንደሚያስረዱት ከሆነ አንዳንዶቹ ከምግባቸው ውስጥ፣ ሌሎቹ ከሚጠጡት ነገር ውስጥ ብን ተደርጎባቸው፣ አሊያም በመልከ መልካም ሴቶች እሽት በስሱ ሳይታወቃቸው አፍንጫቸውን በመሳም ወይም በማሻሸት እንዲስቡ ተደርገዋል። ሌሎቹ ደግሞ ሳያስቡት ዕጹ ባለበት ጥጥ ድንገት አላፊ ሰው አፋቸውን ወይም አፍንጫቸውን ጠረግ አድርጎ እንዳለፈ ብቻ ነው የሚያውቁት። ከዚያ በኋላ ስለሆነው ነገር የሚያውቁት ነገር አይኖርም። ከዕጹ ተገዢነት ሲነቁ ታዲያ በራሳቸው ፈቃድ ተደፍረው፣ ገንዛባቸውን እራሳቸው ከባንክ አውጥተው ሰጥተው፣ የቤታቸውን ዕቃ ራሳቸው መኪና ተከራይተውና ራሳቸው ጭነው ለማያውቋቸው ሰዎች አስረክበው እንደነበረ ያውቃሉ። ታዲያ ምን ዋጋ አለው፤ ስለተፈጠረው ሁኔታ ምንም የሚያስታውሱት ነገር የለም። ሰዎቹን እንኳን አያስታውሱም። ብቻ ንብረታቸው የለም አለያም አካላዊ ጥቃት ደርሶባቸዋል።

ታዲያ ሐራዊ የዳንኤል ክስረት ቡችላ ታደሰ እና እስትንፋሰ ዲያብሎስ ምን አገናኛቸው ነው ጥያቄው?

ወሬ በማነፍነፍ ላይ ….ምን እየሠሩ ነው?

ከላይ ከተገለጠው ከዕፁ ጠባይ በመነሳት እናንተ እንዴት እንደምትረዱት ባላውቅም እኔ ግን በደንብ የማውቀው ወዳጄ ታዴና እስትንፋሰ ዲያብሎስ በሁለት መልክ ይመሳሰሉብኛል፡፡

መመሳሰል ፩. በቁሙ

የእስትንፋሰ ዲያብሎስ ተክልን ማንኛውም ሰው አበባውን ሲመለከተው፤ ወደ አፍንጫው አስጠግቶ ሲያሸተው እንዲሁም የአበባው ውበት ለሰውም ይሁን ለንቦች ተስማሚ መዓዛ ያለውን ይህን ተክል በምንም ዓይነት እንዲህ የአደንዛዥና ሀቅልን ሰላቢ ፍሬ ባለቤት ይሆናል ብሎ ለማሰብ ይከብዳል፡፡ ልክ እንደ ዕፁ ሁሉ ሐራዊው ታዴ አንገቱን እያቅለሰለሰ፣ ነጭ ነጠላ ለብሶ በተቀደሰው አደባባይ ቆሞ ለእኩይ ዓላማና ለንግዱ ሥራ ያመቸው ዘንድ ‹‹ተሐድሶ››፣ ‹‹አጽራረ ቤተክርስቲያን››፣ ‹‹ሐራ ጥቃ››…እያለ እና ከመዝገበ ቃላት በተውሶ ያገኛቸውን ቃላት በተንሸራታች ጽሑፎች(Business Slide) ሲገልጥላችሁ እንዴት ዓይነት በቤተክርስቲያን ፍቅር የተቃጠለ የመናፍቃን ጠላት ነው ማለታችሁ አይቀርም፡፡ ጉዳዩ ግን ሌላ ነው ጨዋው ታዴ በማቅ ላይ በፈጸማቸው እኩይ ተግባራት ምክንያት ከተባረረ በኋላ ለእንጀራ ሲል ውሎው ከሲሞናውያን፤ አዳሩ ደግሞ እሱን አስመስሎና አሳህሎ ከወለደው ከግብር አባቱ ጋር ሆነ፡፡ ስለዚህ በቁሙ እስትንፋሰ ዲያብሎስ ያልኩበት ምክንያት ይህ ሐራዊ በተቀነባበሩና በሐሰት በተሞሉ የሐሰት ሰነዶች ያለ ማጣራት አባቶችን እገሌ ይወገዝ፣ እገሌ ይባረር፣ እገሌ ከሹመት ይሻር እና የመሳሰሉትን ምክረ ሀሳብ አቅርቦ የችኮላና አስተውሎት የጎደለው ውሳኔ እንዲወስኑ ያፈዘዛቸውና ያደነገዛቸው ጊዜ በርካታ ነው፡፡ በነገራችን ላይ አብዛኛውን ጊዜ አባቶቻችን የሚነቁትና የሚደነገጡት አንድን ሰው ካወገዙና ከለዩ በኋላ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በእንተ ስማ ለማርያም ብለው ዋጋ ከፍለው በትጋት ከተሠማሩባትና ካደጉባት ከእናት ቤተ ክርስቲያን አስወጥቶ ባዶ እጃቸውን አስቀርቶ ጎዳና ተዳዳሪ ያደረጋቸው ፣ ትውልደ አራዊት በሆኑ በመናፍቃን ያስበላቸው፣ ልክ እንደ ዮዲት ጉዲት ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመበቀል እንዲነሳሱ ያቆሰላቸው በርካቶች ናቸው፡፡ ስለዚህ ይህ ሐራዊ በቁሙ እስትንፋሰ ዲያብሎስ ነው ብንል ያንስበታል እንጂ አይበዛበትም!!!

መመሳሰል 2. በተጠቃሚነት

ከዚህ ማስፈንጠሪያ ላይ እንደምትመለከቱት (https://www.youtube.com/watch?v=ToQ8PWYnu04) አንዴ በዚህ ሱስ(ሰውን አፍዝዞ በመዝረፍ) ከተለከፋችሁ ለነፍስ ግድያ እንኳ ወደ ኋላ አትሉም፡፡ ይህን ሐራዊ የዚህ ዕፅ ሱሰኛ እንደሆነ እንድጠረጥር ያደረገኝ ነገር ምን መሰላችሁ ከሐራዊው ታደሰ ጋር ለማውራት እድል የገጠማቸው ሁሉ በተደጋጋሚ የሚነግራቸው አቡነ እገሌ፣አባ እገሌ፣ቄስ እገሌ…በቃ ሁሉንም  በቁጥጥር ስር ማዋል እንደሚችል ሲናገር መስማት የተለመደ ነው፡፡ እኔም በተለያዩ አጋጣሚዎች አዲስ አበባም ይሁን ክፍለ ሀገር በአገልግሎት(እሱ ለገለጣ) በተገናኘንበት ጊዜያት የተረዳሁት ጉዳይ በቃ ታዴ እንኳን ለመሳተፍ ለማውራት እንኳ በሩቅ ከሚፈራቸው ከቅዳሴና ከማኅሌት አገልግሎቶች ውጪ ሁሉን አዋቂ እንደሆነ ፋታ በሌለው ወሬው ሲነግራችሁ አጃኢብ! ማለታችሁ አይቀርም፡፡ ከሁሉ በላይ ያስደነገጠኝና እኔም በተግባር ማረጋገጥ የቻልኩት ነገር በተለይ አቡነ ዲዮስቆርዮስና አቡነ ሳዊሮስ በሐራውያን ቁጥጥሩ ሥር ስለ መሆናቸው ‹‹እኛ ያለ እነሱ ፤ እነሱ ያለ እኛ ሕልውና የለንም›› እያለ ሲያወራ የሰማሁበት ቀን ነው፡፡ ምናልባት ይህንኑ ዕፅ እየተጠቀመ አደንዝዟቸው ይሆን እንዴ? እንጃለቱ! እንዲህስ አያድርግብን!!! ከዚህም በተጨማሪ በስህተት እንኳ በቤተክርስቲያን ጉባኤ ቤቶች አልፎ የማያውቀው ሐራዊው ታደሰ የቤተክርስቲያን አለቆች ሰባኪያነ ወንጌል አበክረው የሚያውቋቸውን፤ ምንም ሕጸጽ የማይገኝባቸውን አገልጋዮች በፊት ለፊታቸው ተሐድሶ መናፍቅ ሲል ደንዝዘው ያለተቃውሞ የሚሰሙት በእስትንፋሰ ዲያብሎስ አደንዝዟቸው ሊሆን እንደሚችል መጠርጠር የጀመርኩት ግን መቼም በ‹‹ቅድሰት ሀገር›› አራት ኪሎ የማይታይና የማይሰማ ነገር ምን አለ? ዕፁን አራት ኪሎ አለሌና ጨዋ ሰባክያን ዘማርያንና አዝማሪያን በሚሰባሰቡባቸው ቦታዎች በማየቴ ደግሞ ጠላታችሁ ድንግጥ ይበልና እስካሁን ድንጋጤዬ አልለቀቀኝም፡፡

ሮሚና ካፌና ቱሪስት ሆቴል ጎን ይህ ዕፅ መገኘቱ ምን እንድምታ ይኖረው ይሆን? እኔጃ! እኔ ግን አእምሮዬ በበርካታ ጥያቄዎችና ጥርጣሬዎች ተወጥሯል!!!

በዚሁ አጋጣሚ ሐራውያንን ጨምሮ የማታውቁት ሰው ሻይ ቡና ቢጋብዛችሁ ባትቀበሉ ይመረጣል፤ ከተቀበላችሁም በምንም ተዐምር ምግባችሁን ወይም መጠጣችሁን ትታችሁ ሽንት ቤት ወይም ስልክ ብላችሁ አትውጡ። ሽንት ቤት መሄድ ካለባችሁ ብርጭቋችሁን ባዶ አድርጋችሁ መሆኑን አረጋግጡ። ከተረሳም ስትመለሱ አትጠጡት። ቢቻል ከማናውቃቸው፣ እንደነ ታዴ ካሉ ጮሌዎችና ከማናምናቸው ጋር ባንዝናና ይመረጣል። ለማንኛውም ንቁና ጠንቃቃ መሆን ሁሌም አይጎዳም!!!

እናላችሁ እኔና ታዴ ከረጅም ጊዜ በፊት በመተዋወቃችን እንዲሁም አብረን በማገልገላችን ምክንያት እጅጉን አጃጅሎኝ እንደኖረ የገባኝ ዘግይቶ ነው(ይቅርታ ነገር ቶሎ ስለማይገባኝ ነው)፡፡ ባለፈው ጊዜ አንኳ ትዝ ይላችሁ የለ? መቼ ነበር? ጊዜው ተዘነጋኝ…ታዴ መቼም የራሱን ሊበራል ተሐድሶነት ይረሳና ብዙ ጊዜ ወጥ ረገጥ ይሆናል፡፡ ታዲያ  በዚህ ድርጊቱ የተበሳጩ እስካሁን ማንነታቸውን በውል ያላወቅናቸው ደብዳቢዎች ሲፈነካክቱት የእጁን አገኘ! ገና ይቀረዋል! ሲሉ በእርሱ ምክንያት ከብዙ ሰው ተጣላቼ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ ታዴ ከዚያ የዋህ ማንነት ወጥቶ ወደ ፋሽሽታዊነት ተቀይሮ በሐራ ዘተዋሕዶ ላይ ዲጄው አሉላን በፒያሳው ኢንተርኔት ቤት ለጣፊ(blog poster) አድርጎ በቅብዐተ ተንኮል ከሾመው በኋላ ከጥቅምት 2002 ዓ.ም ጀምሮ በተለይ፡-

  ከመስከረም 2006 ዓ.ም እስከ መጋቢት 2011 ዓ.ም ቅዱስ ፓትርያርኩን ብቻ የሚመለከቱ 50 ጉዳዮችን የለጠፉ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 46ቱ ምዕመናን በቤተክርስቲያኒቱ የበላይ አካላት ላይ ፍጹም ጥላቻ እንዲኖራቸውና አባቶችን በንቀት እንዲመለከቱ የሚያደርጉ ናቸው፡፡ በውስጥ ያሉትን ጸያፍ እና ከአንድ ተራ አሳዳጊ የበደለው ከሚባል ሰው እንኳ የማንሰማቸውን የእርኩሳን መናፈስት ልጆች መሆናቸውን የሚገልጡ ቃላት ትቼ ጥቂቶቹ እንዲህ ይላሉ ተጽዕኖ አልባ መሪየመነጋገርና የመደራደር አቅም የሌላቸውፓትርያርኩ ከመንግሥት ጥገኝነት ነፃ ለመኾን እንደማይችሉ ያምናሉአቦይ ስብሐት ጎበዝ ነኽ አለኝ›› ያሉት ፓትርያርኩፓትርያርኩ ዛሬ በሕግ አፍራሽነት ይጠየቃሉ፣ የአ/አበባ ሀ/ስብከት በቀጣይ ብክነት ላይ – ፓትርያርኩን ሰርፕራይዝ እናድርጋቸውፓትርያርኩ:“እስከምሞት እዋጋዋለኹ፤ እጅ እግሩን አስረዋለኹ” ሲሉ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ዛቱፓትርያርኩ “ኃይል አለኝ” ሲሉ ዛቱፓትርያርኩ ተሸነፉ? “ሙስናን ተዉ፤ ማለት ከአንበሳ አፍ ሥጋ እንደ መንጠቅ ነው፤ አቅሙም ጉልበቱም የለንም” አሉፓትርያርኩ አላግባብ ያሳለፉትን ወቅቱን ያላገናዘበ ለውጥ አደናቃፊ እገዳ እንዲያነሡ ዋና ሥራ አስኪያጁ አሳሰቡ

  • አቡነ ጢሞቴዎስ፣አቡነ ሕዝቅኤል ፣አቡነ ያዕቆብ የደቡብ አፍሪካና የአትላንታው፣ አቡነ ኤውስጣቴዎስ ፣አቡነ ዳንኤል፣አቡነ እንድርያስ፣አቡነ ቶማስ፣አቡነ ፊልጶስ ዘፊላደልፊያ፣አቡነ በርናባስ፣ አቡነ መልኬጼዲቅ እና ሎሎችም ጭምር በሐራውያን ለገብያ ቀርበው ግብይት  ከተፈጸመባቸውና ኢቀኖናዊ መብጠልጠል ከደረሰባቸው አባቶች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው…
  • አቡነ እስጢፋኖስ፣አቡነ ማቴዎሰ፣አቡነ ሉቃስ፣አቡነ ሳዊሮስ እና አቡነ ዲዮስቆርዮስ ደግሞ በተደጋጋሚ ሙገሳና ድጋፍ፤ አንዳንዶቹ ደግሞ እንከን አልባ ተደረገው ከጸነገሩን አባቶች መካከል ይገኙበታል (አባቶች በሐራውያን ለመሰደብና ለመሞገስ መስፈርቱ ምን እንደሆነ አነስተኛ ጥናት በማድረግ ላይ ስለሆንን እንዳለቀ ይፋ ይሆናል)
  • አዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን ለሐራውያን ትልቁ የገብያና የመተዳደሪያ ማዕከላቸው ከመሆኑ አንጻር ጭር ሲል ጉሮሮአቸውም ስለሚዘጋ ማንም ይሾም ማን በወሬ ማተራመስ ትልቁ ተግባራቸው መሆኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡

አዚህ ላይ ስለ ቤተክርስቲያን አምላክ የምጠይቃችሁ ነገር ቢኖር የመጻፍ አቅሙና ጊዜው ያላችሁ የቅድስት ተዋሕዶ አገልጋዮች የኤፍሬም እሸቴ የግል ንብረቶች የሆኑትን ሦስቱን ብሎጎች ማለትም ደጀ ሰላም፣ አንድ አድርገንና ሐራ ዘተዋሕዶን ምን ርእሰ ጉዳዮችን አነሱ? ለቤተክርስቲያን ምን ፋይዳ አመጡ? ወይስ የበለጠ የጥርጣሬና የመለያየትን መንፈስ ዘሩብን? የሚሉትንና ተያያዥ ጥያቄዎችን በማንሳት ትንታኔ መሥራት ብትችሉ ለዘመቻ ጌዴዎን ታላቅ አስተዋጽኦ አበረከታችሁ ማለት ነው፡፡በእኔ በኩል የሐራውያንን ነገር በትኩረት ሳስብ እና ሐራዊ ታደሰ እንዴት ይህንን የስድብ መንፈስ ተዋረሰ ብየ ራሴን ስጠይቅ ሁለት ነገሮች በአእምሮዬ ይመላለሳሉ፡-

-ሀ-

በሉቃ8፡2 ላይ በመግደላዊት ማርያም ላይ አድረውባት ከነበሩትና ጌታችን ነጻ ካደረጋት ሰባት አጋንንት መካከል አንዱ የስድብ መንፈስ ነበር አንዲሁም በሐዋ16፡16-19 በተመዘገበው ታሪክ ላይ የመዋርተኝነትና የጥንቆላ መንፈስ ያደረባት ሴት ‹‹የመዳንን መንገድ የሚነግሩአችሁ እነዚህ ሰዎች የልዑል አምላክ ባሪያዎች ናቸው›› በማለት እየጮኸች የበለጠ ተከታይ ለማፍራት ባለመ አጋንንታዊ ዕቅድ እና በምትናገረው አዎንታዊ ቃል ለሐዋርያት አገልግሎት ተቆርቋሪ ለመምምሰል በትሞክርም ውስጧ ሸፍጥ ያለበት መሆኑ በመንፈስ ቅዱስ የተረዳው ቅዱስ ጳውሎስ ለክርስቶስ ወንጌል እንቅፋት የሆነውን የአስመሳይነት መንፈስ ገስጾ ከለየ በኋላ በማቴ12፡43 ላይ ‹‹ርኩስ መንፈስ ከሰው ከወጣ በኋላ ዕረፍትን ሲሻ ውኃ ወደ ሌለበት ምድረ በዳ የዞራል ግን አያገኝም፡፡…ከዚህ በኋላ ከርሱ የሚከፉ ሰባት አጋንንት ያመጣል…›› እንዲል እነዚህ ሁለት ሰዎች አጋንንት ከወጡላቸው በኋላ ማደሪያ አጥተው ሲንከራቱ ቆይተው በዚህ በእኛ ዘመን ቤተክርስቲያን ለማፈራረስና አገልጋዮቿን ለመለያየት ምቹ ማደሪያ ሆኖ ያገኙት ሐራዊ ታዴንና ግብረ አበሮቹን ይመስለኛል፡፡ ያለበለዚያ ግን ጤነኛ የሆነ ሰው የቤተክርስቲያን መሠረትና የሐዋርያት ተከታዮች የሆኑትን አባቶች በመሳደብ የወንጌል አገልግሎት እንቅፋት በመሆን ለመተዳደር አቅዶ ሊሠራ አይችልም፡፡ ስለዚህ ከዚህ ሐራዊ እነዚህ ርኩሳን መናፍስት እንዲርቁለት በጸሎት ልናስበው፣ልናስጠምቀው አሊያም አጋንንትን የማስወጣት ጸጋው ወደላቸው አባቶች ብንወስደው ይሻላል እላለሁ፡

-ለ-

እስትንፋሰ ዲያቢሎስ ሐራዊው ታደሰ ወርቁ ከዚህ በፊት በደጀ ሰላም አሁን ደግሞ በሐራ ዘተዋሕዶ ብሎግ ላይ ማን እንደቀጠረውና እንዳሰማራው ባላውቅም እነዚህን የስድብ ጽሑፎች በቤተክርስቲያኒቱ ሕጋዊ አካላት ላይ በመጻፍና በማጻፍ የተጠመደበት ሌላው ምክንያት እሱና ግብረ አበሮቹ በማቅ ላይ በፈጸሙት ስውር ሴራ ከተባረሩ በኋላ ዋንኛ ጉዳያቸው እና መተዳደሪያ ያደረጉት በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ ማኅበረ ቅዱሳንን አምርሮ ጠልነታቸውንና ማቅ መፍረስ አለበት የሚለውን የጥፋት ተልዕኮ መፈጸም ነው፡፡ ይህንን በሁለት ማሳያዎች ለማሳየት ልሞክር፡-

ማሳያ 1

ከላይ እንዳነሳሁት ሐራውያን ሰው ያወቃቸው ዛሬም የሚውቃቸው የማቅ ቀንደኛ ደጋፊና አባል እንደሆኑ አድርጎ ነው፡፡ ስለዚህ በአብዛኛው ሰው የሚረዳው ሐራ ወይም ደጀ ሰላም ተሳደበች ማለት ማቅ ተሳደበ ማለት ነው ብሎ ይረዳል፡፡ በዚህም ማንም አካል ክብሩ ሲነካ የሚታገስ የለምና ከቅዱስ ፓትርያኩ አስከ አጥቢያ እስካለው አገልጋይ፣ ሰ/ት/ቤት እና  ማህበራት  ማቅ ሰደበን አዋረደን ተሳለቀብን ብሎ እንዲያስብ በማድረግ ማህበሩን ከቤተክርስቲያኒቱ የመለየት የመጀመሪያ ዕቅዳቸው በከፊልም ቢሆን ተሳካ ማለት ነው፡፡ በእኔ እምነት ቅዱስ ፓትርያርኩ ‹‹ማህበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያንን በቅኝ ግዛት ይዟታል›› እስከ ማለት የደረሱት በእነዚህ ሐራውያን እኩይ ተግባር ምክንያት እንጂ ማህበሩን አውቀውት ነው የሚል ግምት የለኝም፡፡ በነገራችን ላይ ማህበሩ በእነዚህ የተኩላ ለምድ በለበሱ ማቅ ጠል ቡድኖች አቀነባባሪነት በሚፈጸመው እኩይ ሴራ ማህበሩ ከየአቅጣጫው በርካታ ወቀሳና ትችት ከደረሰበት በኋላ በሐምሌ 2001 ዓ.ም በሳተመው የስምዓ ጽድቅ ጋዜጣ የፊት ገጽ ላይ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን ‹ደጀ ሰላም› የተባለው ብሎግ ልሳኑ አለመሆኑን አስታወቀ›› ብሎ ማውጣቱ ለዚሁ ማሳያ ነው፡፡  

በዚሁ ጋዜጣ ገጽ 2 ላይ እንዲህ ይላል ‹‹…አቶ ዳንኤል ተስፋዬ እንደገለጹት ራሱን የማኅበረ ቅዱሳን ልሣን አድርጎ በማስተዋወቅ መግለጫዎችን የሚሰጠው ብሎግ ከማኅበሩ እውቅና ውጪ ነው፡፡ ብሎጉ አሁንም በማኅበሩ ስም መግለጫዎችን እያቀረበ እንደሚገኝ የጠቆሙት ዋና ጸሐፊው የማኅበሩ አለመሆኑን አሳውቀዋል አክለውም በዚህ ብሎግ ምንም ዓይነት መረጃ እንደማያስተላልፍ ገልጸዋል፡፡ ከማኅበሩ እውቅና ውጭ የሚንቀሳቀሰውን ይህን ብሎግ የማህበሩ አለመሆኑን ምዕመናን እንዲያውቁም ጸሐፊው አሳስበዋል፡፡

አያይዘውም እንዲህ ዓይነት ሓላፊነት የጎደለውና ምእመናንን ለማሳሳትና ቤተ ክርስቲያንን ለማወክ የሚደረጉ ሙከራዎችን ምእመናን ሊቃወሙ እንደሚገባቸውም ዋና ጸሐፊው ተናግረዋል፡፡››

በዚህ ያለተጠበቀ መግለጫ የተደናገጡት ሐራውያን የአሰላለፍ ለውጥ በማድረግ ከጥቅምት 2002 ዓ.ም ጀምሮ ሐራ ዘተዋሕዶ የሚል ሌላ የስድብ ብሎግ ከፍተው ብቅ ያሉት ለዚህ ነው፡፡ ማቅ እና እነዚህ ብሎጎች ተያይዘው የሚነሱበት ትልቁ ምክንያት ሁሉም ሐራውያን በአንድ ወቅት ከ‹‹አባ ተንኮሉ›› ጋር በመሆን በፈጸሙት ሴራ ምክንያት ተጠራርገው ከማቅ ከመውጣታቸው በፊት (እንዲህ እንደአሁኑ መራራ ፍሬዎች እና የእናት ጡት ነካሾች ከመሆናቸው በፊት) የማኅበሩ ጋዜጣና መጽሔት ዋናነና ምክትል አዘጋጆች እስከ መሆን በመድረሳቸው ነው፡፡

ዛሬም ማኅበሩ እነዚህ መሠሪዎችና ከጉያው የወጡ መራራ ፍሬዎች በተደጋጋሚ ካላጋለጠ በቀር ነቀርሳነታቸው ከማኅበሩ አልፎ ለቤተክርቲያን እንደሚተርፍና እየተረፈ ያለ መሆኑ የታወቀ ነው፡፡

ማሳያ 2

ታዴ በሃይማኖት ካባ በተሸፈነው ፖለቲካዊና ሲሞናዊ ማንነቱ ምክንያት ከማቅ ከወጣ በኋላ ቆሌ ስለራቀው ያልሞከረው የሥራ መስክ የለም ተንታኝ፣የታሪክ ተመራማሪ፣ሐያሲ፣ሰባኪ፣ዐቃቤ እምነት….በርግጥ ጥረቱን አደንቃለሁ፡፡በአብዛኛው ከፓትርያርክ ምርጫ ጋር በተያያዘ “ፋክት” በተሰኘው መጽሔት ቅፅ 2 ቁ.6 የሐምሌ እትም 2005 ዓ.ም ላይ “በቄሳራውያን መዳፍ ስር ያለ አስኬማ” በሚል ርዕስ  ፖለቲካዊ ጽሑፉ እንዲሁም በቀጣዩ ቁጥር 7 የነሐሴ 2005 ዓ.ም እትም ላይም  “የተቋማዊ ለውጥ ጅምሮች” በሚል ርእስ ባስነበበን ጽሑፍ ማቅ ‹‹ማህበሩ›› እያለ እንዲህ ተችቷል ፡-

  • እንደ ታደሰ አገላለጽ ማህበረ ቅዱሳን የሁለቱን ሲኖዶስ እርቀ ሰላም አሉታዊ እይታ እንዳለው ሲገልጥ አባቶች እርቅ ከፈፀሙና ወደአገር ቤት ከመጡ ችግር ይፈጠርብናል የሚል ስጋት እንዳለ ነው፡፡ከዚህ በተጨማሪ በአንድ በኩል ለሕዝባዊ ተቀባይነት እርቀ ሠላሙን እደግፈዋለሁ እያሉ በሌላ በኩል ደግሞ የእርቀ ሠላሙን ሂደት በውስጠዘ እያክፋፉ ድርድሩን ከድጡ ወደ ማጡ እንዲሆን አድርገውታል፡፡
  • የአ/አ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነትን ማቅ በተሐድሶ ሰበብ የቤተክርስቲያን ውስጥ ነውጥ አውጆ በነበረ ጊዜ ለረብሻው አሳድሟቸውና አሠማርቶአቸው እንደነበር ጠቁሟል፡፡
  • በወቅቱ ትልቁ የመንግስት ጥያቄና ትኩረት የሳበው የጥምቀት ተመላሽ ወጣቶችን ጉዳይ ማን አደራጃቸው? ከጀርባ ማነው የሚደግፋቸው? የሚለው ጥያቄ ስለነበር ይህ አጋጣሚ ተጠቅሞ ማህበሩን ከመንግሥት ጋር ለማነካስና ከላይ በማቅ ላይ ያቀዱትን ዕቅድ ለማስፈጸም እነዚህን ወጣቶች ማቅ እንዳደራጃቸው በድፍረት ጽፏል…

ምን አለፋችሁ ብቻ አልተሳካላቸውም እንጂ እንደ ሐራውያን ሕልምና ቅዠት እንዲሁም በብሉግና በጽሑፍ እንደሞከሩት የባንዳነት ፍልሚያ ቢሆን ኖሮ ማቅ እስከ አሁን ጠፍቶ ነበር፡፡


ወዳጄ ታዴ ከእንቅልፉ ሲነቃ ከእስትንፋሰ ዲያብሎስነት ወጥቶ ወደ ፊት ካልተቋረጠ አንድ ቀን የዓመቱ በጎ ሰው ተሸላሚ እንደሚሆን ተስፋዬ ጽኑ ነው!!!

ቸር ሰንብቱልኝ

ሳምኬት ነኝ!

ሐምሌ 4 ቀን 2011 ዓ.ም

ሐራ ዘተዋሕዶ የተዋሕዶ ነቀርሳ

ዘመቻ ጌዴዎን ክፍል ሁለት

ቀጥታ ወደ ክፍል ሁለት ከማግባቴ በፊት የባለፈውን ጽሑፍ መነሻ በማድረግ ብዥታ የተፈጠረባቸውን ሁለት ጉዳዮችን ማንሳት ወደድኩ፡-

ጉዳይ አንድ

ስለ ሐራዊ(ጨዋው)ና ዲጄው አሉላ ጥላሁን ባለፈው አንስቼላችሁ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ አንዳንድ እያስተዋልኳቸው ያሉ ነገሮች አሉ፡፡ ይህውም በጽሑፎቼ ስማቸውን የምጠቅሳቸውን ግለሰቦችን የማነሳበት ትልቁ ምክንያት ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ ከተሰለፉበት እኩይ ተልዕኮ እንዲታቀቡ ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ሐራዊ አስቀድሜ በነገርኳችሁ በስለላ የታገዘው የሴራ ፖለቲካ ሕይወቱ ምክንያት ብዙ ጊዜ በመታሰሩና ወደ የትኛውም ሀገር እንዳይወጣ እግድ የተጣለበት ከመሆኑ ባሻገር ቀውስነቱ ለወላጅ እናቱ ስለተረፈ ተከራይተውት ይኖሩበት ከነበረው ከራስ አምባ ቤቱ ከተባረሩ በኋላ በአሁኑ ሰዓት ፈረንሳይ ቤት ተከራይቶ የሚኖር ከንቱ ሰው ነው፡፡ ከማቅ ከተባረረም በኋላ ምንም ዓይነት ቋሚ መተዳደሪያ የሌለው ፣ማን እንደቀጠረው ባይታወቅም ዲጄው በተደጋጋሚ ሀገረ ስብከቶች ችግሮቻቸውን በራሳቸው እንዳይፈቱ የማበጣበጥ ሥራ የሚሰራ አካይስት ነው፡፡ለምሳሌ በምስራቅ ጎጃም በቅርቡ መሬት ላይ ካለው እውነታ ባላይ ለህዝብና ቤት ቆጠራ ጭምር ትኩረት እንዲያገኝ ያደረጉት የቅብዐትና የጸጋን ጉዳይ ሳይመነኩሱ ጳጳስ ከሆኑት ወገን ያልሆኑት የሊቁ አቡነ ማርቆስ ጉዳይ ብቻ በማስመሰል በምዕመናን መካከል እስከ ተኩስ የደረሰ ግጭት እንዲፈጠር ከፍተኛ ድርሻ የነበራቸው የዚሁ ብሎግ አባላትና ደጋፊዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ እነዚህን ጨዋዎች ከቤተክርስቲያን ደጀ ሰላምና አውደ ምህረት ገለል እንዲሉ በማድረግ እንጂ በጳውሎስ(መረዋ) ሠርግ ላይ የተደፋበት ጠጅ ሳያንስ ግንቦት 30 ቀን 2011 ዓ.ም በዚህ ሐራዊ ላይ በአምስት ኪሎው የኤፍሬም ውስኪ ቤት እንደተከሰተው ውስኪ ፊቱ ላይ በመድፋት አሊያም በቅርብ ብዙ አባቶችን ሸጦ በሰበሰበው ብር አገባለሁ ብሎ ደጋግሞ ሲያወራ በመሰማቱ በርካቶች በቤተክርስቲያንም ይሁን በአሸሼ ገዳሜ አደርገዋለሁ ብሎ ያሰበውን ሰርጉን እስቲ የትኛው ቤተክርስቲያንና ቦታ ላይ እንደሚያደርግ እናያለን!!! ብሎ በመዛት ለውጥ ይመጣል ብዬ አላስብም፡፡ ዴጄው አሉላ በተከለበሰበት ውስኪና ጠጅ እንዲሁም በዛቻዎቹ በመደንገጡ ከዚያን ቀን ጀምሮ የኢንተርኔት ቤት ደንበኛው ከሆነች እጮኛው ባልተናሰ መልኩ ወደ ሚወዳት ዳሽን ቢራ በትጋት ወደ መጋት ከመመለሱ በላይ በቁም የሚባትት ሁኗል፡፡ ይህን ጉዳይ ያነሳሁበት ዋና ዓላማ ሐራውያን(ጨዋዎች) በአብዛኛው የአእምሮ ቀውስ ተጠቂዎች(mental disorder) ያለባቸው በመሆኑ ውስኪም ይሁን ጠጅ በመድፋት ወይም አካላዊ ጥቃት በማድረስ እሊህን የተዋሕዶ ነቀርሳዎችን ማከም ስለማይቻል ሊረዳቸው ከቻለ ወደ አእምሮ ህሙማን ሆስፒታል አሳምነናቸው ብንወስዳቸው ዋጋ የሚገኝበት ከመሆኑ ባሻገር ቁጥራቸው እየተበራከተ ከመጡት ከሲሞናዊያን ቅድስት ቤተክርስቲያንን ለመታደግ እንደ አንድ እርምጃ ይሆናል ብዬ ስለማስብ ነው፡፡  

ጉዳይ ሁለት

አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች በተለይ ከማቅ ጋር ግንኙነት ያላችሁ፣ ደጋፊና አባላት የሆናችሁ በጣም ጥቂቶቻችሁ ከዚህ ቡድን ገጋር በኅቡዕ የምትሰሩ ደግሞ ለምን ተነቃብን ግማሾቻችሁ በዕውቀት ማነስ ምክንያት ግራ የተጋባችሁበት ነገር እንዳለ ስለተረዳሁ ይህንን ብዥታ ላጠራ እፈልጋለሁ፡፡

ለመሆኑ ማቅና ሐራ አንድ ናቸው ?

በፍጹም! እረ በጭራሽ! በየት በኩል!

ሐራ የቤተክርስቲያን ነቀርሳ፤ የአሁኑን ባላውቅም ማቅ ደግሞ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በሃሣብ ጸንሰው፥ በትምህርት ወልደው፥ በመንፈስ ቅዱስ እሳትነት ለኲሰው ለዚህ ያበቁት ማኅበር ነው። ይህ ማህበር በርካታ አንጸባራቂ ታሪኮችን ያስመዘገበ፤ በእነዚህ ስንኩላነ አእምሮ በሆኑ ነቀርሳዎች አመድ አፋሽና እጀ ሰባራ የሆነ፤ እንደ ሰደድ እሳት የተስፋፋ፤ በቀና የቤተክርስቲያ ልጆች አእምሮ ውስጥ የሚኖር የምናብ ማህበር እንጂ (ሐራውያንን ጨምሮ ብዙዎች ሞክረው ያላፈረሱት)  ቅድስት ማርያም የቆመ ሕንጻ ወይም የሐራውያን ማህበር አይደለም፡፡

ይሄንን ለማስረዳት ሁለት ነገሮችን በትኩረት ልንረዳቸው የሚገቡ ጉዳዮችን ላንሳ፡-

ትኩረት አንድ

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በመጋቢ 15 ቀን 2009 ዓ.ም በአብዛኛው የቤተክርስቲያን አይጦችንና ነቀዞችን ሰብስበው በጣም በቁጣና በብስጭት ሆነው ‹‹ቤተክርስቲያኒቱ በቅኝ ግዛት ተይዛለች… በማኅበረ ቅዱሳን ቅኝ ተይዛለች›› ያሉበትን ንግግር ሁላችንም ያደመጥን ይመስለኛል፡፡ቅዱስነታቸው፣በርካታ ቁጥር ያላቸው ብጹአን አባቶች፣ መነኮሳት፣የቤተክርስቲያን አገልጋዮች እና የመንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ማኅበሩን አምርረው የሚጠሉት አውቀውት ሳይሆን ወልዶ ያሳደጋቸው፤ አንቱታ ያስገኘላቸው፤ የማኅበሩን ሀብትና ንብረት ወደ ግል ንብረት በማዞር በዘረፉ ስንኩላነ አእምሮ በሆኑ እፉኝቶች ምክንያት ነው፡፡ የማኅበሩ አባላትማ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ብቁ፣ በሥነምግባር የታነጹና በሃይማኖት የበረቱ ዜጎች እንዲሆኑ በትጋትና በፍጹም ታማኝነት የሚሠሩ፤ የአገልግሎት ማከናወኛና የሕንጻ ግንባታ ቦታ መግዣና የመገንቢያ ገንዘብ እጥረት በተከሰተባቸው ጊዜያት፤ የአብነት ት/ት ቤቶች የመፈታት አደጋ በተጋረጠባቸው ጊዜያት፣ ሠርጋቸውን፣ የማስተርስ፣ የፒኤችዲ የትምህርት ፕሮግራማቸውን የሚሰርዙ ለማህበሩ ገቢ ብለው የትርፍ ሰዓት ሥራ የሚሰሩ፣ የሞቀ ቤታቸውን ጥለው አቧራ ላይ መሬት ላይ እየተኙ ጉልበታቸውን፣ ገንዘባቸውን ጊዜያቸው ሰጥተው የሚያገለግሉ ናቸው!!!

ሐራዎች እነሱ ከሌሉ ማኅበሩ እንደሚፈርስ ወሬ በመንዛት በአባላቱ መካከልም የፍርሃትና የጭንቀት መንፈስ ቢዘሩም ጤነኞቹ እነ ዶ/ር ዘርዓየሁ ስሜ ግን ይህን ጉዳይ አጥብቀው የሚቃወሙ ናቸው፡፡በአንድ ወቅት የማኅበሩ ሰብሳቢ የነበሩት ቀሲስ ዶ/ር ሰሙ ምትኩ በአዲስ አበባ ከሚታተመው የቀለም ቀንድ ሳምንታዊ ጋዜጣ ጋር በማኅበሩ አገልግሎት፤ በቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ኹኔታና ተያያዥ ጉዳዮች በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳንን የወለደው፥ ‹እኔ ለቤተ ክርስቲያኔ ምን ማድረግ እችላለኹ?› የሚለው ሐሳብ ነው፤ይጥፋ የሚሉት የጥቅም ጋብቻ የፈጸሙ አማሳኞችና የተሐድሶ መናፍቃን ናቸው›› ያሉት ለዚህ ማሳያ ነው፡፡

ትኩረት ሁለት

ከጥቂት ሳምንታት በፊት በፍትሕ መጽሔት በውስጥ የሽፋን ገጽ  ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን ወይስ ማህበረ ሰይጣን?›› የሚለው መጽሐፍ ከተዋወቀ በኋላ በዚሁ መጽሔት በ1ኛ ዓመት ቁጥር 12 እትም ላይ በፕሮቴስታንት እምነት ተከታዩ ብርሃኑ ደቦጭ ለምን ሂስ  እንዲጻፍ ተፈለገ?(በሰላ ሂሱ እጅግ የማከብረው ብርሃኑ እንዲህ ዓይነት የወረደ ጽሑፍ ሲጽፍ አይቼ ስለማላውቅ ነው) ማን ለምን ዓላማ ጽፎ ሰጠው?  የሚሉት ጥያቄዎች አእምሮዬ ላይ ተመላለሱ እኔም እንዴት?ለምን?እነማን? የሚሉት ጥያቄዎች ራሴን መጠየቅ ጀመርኩ፣ ለካ ጉዳዩ ሌላ ኖሯል ያኔ የአዲስ ነገር ጋዜጠኞች በወያኔ ጂሐዲስቶች ሲሳደዱ ከሐራውያን ጋር የቀረበና የጠበቀ ግንኙነት ያለው አንዱ የሐራውያን ወዳጅ ብርሃኑን ከእስር አድኖት ኖሮ ያቺን እንደ ውለታ ቆጥሮ  እንዳጻፈው ለማረጋገጥ ችዬአለሁ(ያላዋቂ ሳሚ… እንዲሉ በእኔ እምነት በዚህ ጽሑፉ የመልስ ምት መሆኑ ቀርቶ እንዲያውም የበለጠ መጽሐፉን ያስተዋወቁት ይመስለኛል)፡፡ በነገራችን ላይ የመጽሐፉ ጸሐፊ(ስትራቴጅስቱ ማለቴ ነው) ከመንግሥት አከላት ጋር ቅርበት ባላቸው ጉምቱ አክራሪ የመናፍቃን ቡድን እንደሚደገፍ በተደጋጋሚ ተዋሕዶን የማፍረስ ሥልጠና እየሰጠ እንዳለ፣ የወጣቶች የመናፍቃን ህብረት ወኪል መሆኑን ለመረዳት ችዬአለሁ፡፡ የሆነ ሆኖ ይህን መጽሐፍ ጨምሮ በእኩያን የተጻፉ ማቅ የተብጠለጠለበት እነ ይነጋልየለውጥ ያለህ እና የመሳሰሉትን መጻሕፍት እንዲጽፉ ፣የተቃውሞ ሰልፎች  እንዲደረጉ  እና  ማህበሩ ጥርስ ውስጥ እንዲገባ ያደረጉት የእናት ጡት ነካሾቹ ራሳቸው ሐራውያን መሆናቸውን በመጽሐፎቹ ውስጥ ከተካተተው የጎደፈ ስምና ታሪካቸው መረዳት ይቻላል፡፡

ስለዚህ ሐራውያን የማኅበሩን ካባ የደረቡ ነገር ግን ውስጣቸው ማቅን አምርሮ የሚጠሉ በረቀቀ መንገድ (conspiracy) የሚኖሩ ቆርጠው ካልተጣሉ በስተቀር ለመፈወስ ፈቃደኛ ያልሆኑ የተዋሕዶ ነቀርሳዎች ናቸው፡፡

ይቅርታ ወደ ዋናው ርእሴ ሳልገባ አደከምኳችሁ፡፡ ምን ይደረግ የሐራውያን ደባ ተከድኖ ይብሰል ተብሎ የኖረ ስለሆነ በቀላሉ ተነግሮና ተጽፎ ሰለማያልቅ ነው፡፡

‹‹ሐራ ዘተዋሕዶ›› በእነማን ተቋቋመ?

በዘመቻ ጌድዮን በክፍል አንድ ላይ ከጸሐፊዎቹ አንዱን ተመልክተናል ከዚህ በኋላ ባሉት ክፍሎች የዚህ ብሎግ ባለቤት ማነው? እነማን ይሳተፉበታል? ስብስቡ በከፊል እነማንን ይይዛል? ጸሐፊዎቹ እየታወቁ የፈለጉትን ሲያሞካሹ ያልፈለጉትን ሲሰድቡና ሲያንቋሽሹ ለምን ዝም ተባሉ? የሚሉትን ጥያቄዎችንና ተያያዥ ጉዳዮችን ለመዳሳሰስ እሞክራለሁ፡፡

መቼም ዘመቻ አያሳርፍም አይደል ሐራውያን መቼም የማያሳስቱንና የማያሰሩን ኃጢአት የለም፡፡ ሲፈልጋቻው ሰድበው ተሳዳቢ፣ ሐሜተኛ ውሸታም…አድርገውናል፡፡ መጀመሪያ ሐራ ምን ማለት እንደ ሆነ ለምን መዝገበ ቃላት አላይም ብዬ መፈለግ ጀመርኩ፡፡ የአቡሃ ለሐሰት ልጆች ናቸውና ያገኘሁትና እነሱን የሚገልጻቸው ትክክለኛ የሐራ ትርጓሜ በአለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት ገጽ 464 ላይ ሐራ ማለት ጨዋ(ያልተማረ)፤ሐራዊ ደግሞ የጨዋ ወገን(ያልተማረ ወገን) ብሎ ይፈታዋል፡፡ ጭፍራም ቢሉ ከግብራቸው አንጻር የዲያብሎስ እንጂ የቅድስት ተዋሕዶ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ስለዚህ ሐራ ዘተዋሕዶ ማለት መሠረታዊ የሚባል እንኳ የሚባል የቤተክርስቲያን ዕውቀት ሳይኖራቸው ስለቤተክርስቲያኒቱ የሚጽፉ የጨዋዎች(ያልተማሩ) የአእምሮ ስንኩላን የሆኑ የዲያብሎስ ጭፍሮች ስብስብ ነው፡፡አበው ስም ይመርህ ኀበ ግብሩ ይሉሃል ይሄ ነው፡፡

ለመሆኑ የሐራ ዘተዋሕዶ ብሎግ ባለቤት ማነው?

ከዚህ በፊት ያሉትንና ቤተክርስቲያንን ለመሳደቢያ አባቶችንና አገልጋዮችን ለማዋረጃና ለማሸማቀቂያ ብሎም ለማስገበሪያ የሚውሉ እንደ ደጀ ሰላም፣ አንድ አድርገን የመሳሱት የጡመራ መድረኮች በቤተክርስቲያን ላይ ነቀርሳ አድርጎ የተከለው ማነው? ከጥቅምት 12 ቀን 2002 ዓ.ም ጀምሮ ሐራ ዘተዋሕዶን ያቋቋመው(host ያደረገው)ና ለሦስት ጸሐፍት ምሥጢራዊ መግቢያ ቁልፍ(password) የሰጠው የዚህ ስድ ብሎግ ባለቤትና መሥራች የማቁ መሥራች ‹‹ቀሲስ›› ኤፍሬም እሸቴ ነው፡፡

ይህ ሰውና ግብረ አበሮቹ አንድን ጳጳስ ወይም የቤተክርስቲያን አገልጋይ በራስ ቁጥጥር ስር ለማዋል ከፈለግህ መፍትሔው መስደብ፣ ማሰደብና ማሸማቀቅ ብቻ የሚለው ዋና መርሀቸው ነው፡፡ እስቲ አንድ ማሳያ ላቅርብ በደጀ ሰላም ብሎግ ጥቅምት 4/2003 ዓ.ም በጻፉት ጽሑፍ፡-

‹‹አቡነ ፋኑኤል የእብሪታቸውን ልክ ምናልባትም የእምነታቸውን ጤናማነት በውል በሚያሳይ አኳኋን…‹‹እንኳንስ ለሰው ይቅርና የምትችሉ ከሆነ ለመድኃኔዓለም ብታመለክቱ እኔ አልፈራም፡፡››…የአቡነ ፋኑኤል (የቀድሞው አባ መላኩ) ብልሽት የአሁን ሳይሆን የሊቃነ ጳጳሳቱ ልብስ ሰፊ ሳሉ ጀምሯቸው በሀገረ አሜሪካ ሥር የሰደደ መሆኑን ያስታውሳሉ፡፡… ‹‹በሙግት መኖር እንደሆነ የኖርኩበት ነው፤ ሲሻችሁ በቺቺ መጫረስ ትችላላችሁ፤ በቺቺ ተጫረሱና እኔ ከአሸናፊው ጋራ እሆናለሁ›› ማለት የለመደባቸው ማኬቬሊያዊው አቡነ ፋኑኤል ከዜግነታዊ ማንነታቸው አንሥቶ ክስ ያልተለያቸው ናቸው …‹‹ይሞታል ወይ ታዲያ! ስለ ራሴም ዝና እናገራለሁ፤ እኔ አሜሪካ ሄጄ በሊሞዚን መሽሞንሞን እችላለሁ፤ በችግር የምትቆራመደው አንተ ነህ!!›› በማለታቸው የማያፍሩ ናቸው፡….‹‹በሐዋሳ የካህናት ማሠልጠኛ ውስጥ ለምረዳቸው አሳዳጊ አልባ ሕፃናት አውለዋለሁ›› በሚል ብር እንደሚሰበስቡ ተነግሯል፡፡ ዶላሩን ለማጋበስ የማስመሰያ ቪዲዮ እያቀናበረ የሚረዳቸውም…ቤታቸውን ዘግተው ስለ ቤተ ክርስቲያን ችግር የሚንከራተቱ የሐዋሳ ምእመናን ተወካዮች እግራቸው ሥር ወድቀው በልቅሶ ቢለምኗቸው፣ ‹‹ዘወር በል፤ በልቅሶ የሚሆን ነገር የለም፤ የአዋሳን ምእመን እንዲህ የሚያደርገው’ኮ ወንጌል overdose ሆኖበት ነው›› በማለት የግብረ በላዎቻቸውን ድምፅ የሚያሰማ ኀይለ ቃል ተጠቅመዋል፡፡‹‹የሕዝቡን ጫጫታ እንደ ሳውንድ ትራክ ተጠቅመን ሥራችንን ሠርተናል›› በማለት መሣለቃቸው ተሰምቷል፡፡…በወቅቱ አቡነ ፋኑኤል በአደባባዩ እንዲህ ብለው ነበር – ‹‹መንግሥት የራሱን ወታደር አሠማርቶ እነዚህን ሰዎች (የሐዋሳ የፍትሕ እና ልማት ኮሚቴ አባላት) የማይቆጣጠር ከሆነ እኔ የራሴን ሚልሻ እመለምላለሁ፡፡››

እና የመሳሰሉ ርካሽ ክብረ ነክ ቃላት በተደጋጋሚ ሲጽፍባቸው የነበሩትን አባት ንስሐ ገብቶ ይሁን አይሁን ባላውቅም በኋላም ከነ ልጁ ሥልጣነ ክህነት የሰጡትን ከባቴ አበሳ የሆኑትን የሰሜን አሜሪካ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፋኑኤልን ይዛችሁ ስለ እኩይ ተግባሩ አናግሩት፡፡ እርግጠኛ ነኝ አይክዳችሁም፡፡

የሰደባቸውን ያህል አንበርክከው አገኘሁህ በሚመስል አስተያየት ሥልጣነ ቅስና በሾሙት ወቅት…የጊዜ እንጂ የሰው ጀግና የለውም አይደል የሚባል…አሁን ማ የኤፍሬም ቅኝቱ ሁሉ አቡነ ፋኑኤል ፋኑኤል… ሆኗል፡፡

በነገራችን ላይ ኤፍሬምን ከአዲስ አበባ ወደ አሜሪካ ይዛው የገባችው መርከብ የአ.አ.ዩ ተማሪዎች ከቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን መታፈስን ተከትሎ በሚያዝያ ወር 1993 ዓ.ም በስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ላይ የጻፋት ጽሑፍ ነች

እኔ ግን ሁል ጊዜ ጥያቄ የሚፈጥርብኝና በጣም ግራ የሚገባኝ በ1982 ዓ.ም ከነበረበት የጫትና የሲጋራ ሱስ እንዲላቀቅና ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ጋር ንስሐ እንዲገባ ያስተማሩትን አባቶችና ወንድሞች ለመዝለፍ፤ ሳትጸየፍ ከነ ሱሱ ተቀብላ እስከ ቅስና ማዕረግ እንዲደርስ ያደረገችውን ቅድስት ቤተክርስቲያንን በአደባባይ ለማዋረድ ለምን ፈለገ? ባለውለታው ማቅን ለምን ቤተ ክርስቲያን እንደገባ ውሻ ለምን እንዲታይ አደረገ? የሚሉት ጥያቄዎች ናቸው፡፡

በእርግጥ ኤፍሬም ምንም እንኳ አሜሪካ ስለሆነ ሆስት ያድርገው እንጂ ብሎጉን የመቆጣጠር ኃለፊነት በዋናነት የተረከበው የሁሉም ሐራውያን የነገር አባት ተኩላውና መሠሪው ዳንኤል ክብሪት(ክስረት) ነው፡፡ የእርሱን ጉዳይ በጊዜው የምመጣበት ሲሆን  እኔ በርግጥ ደጋግሞ ባሳተማቸው ከመናፍቃን ከካቶሊክና ከሌሎች ዓለማውያን የተውጣጡ የተረት መጻሕፍቶቹ ላይ ስለ ወያኔ የግፍ አገዛዝ የማይጽፈው በአንድ ወቅት እኔው እራሴ ለአንድ ጉዳይ መስቀል አደባባይ ከሚገኘው አቦይ ስብሐት ቢሮ ተገኝቼ በጆሮዬ እንደሰማሁት ‹‹እኛንም በጠበጣችሁን፣ሰላም ነሳችሁን፣ ይሄን ውሻ ሰውዬም(ፓትርያርኩ) ብንነግረው አልሰማ አለ፣ ቤተክርስቲያን መፍረስ ነበረባት፣ ዳሩ ምን ዋጋ አለው ኩሽና እንኳን ሲፈርስ ብዙ ጥንቃቄ ይፈልጋል….›› የሚሉ ከበረሃ ጀምሮ ቤተክርስቲያንን የማፈራረስና የመከፋፈል ዕቅድ፣እኩይ ራዕይና ሰይጣናዊ ምኞቱ ያነገቡ የህወሓት መሪዎች ተከታይና ደጋፊ የሆነችውና ቀጥቅጣ የምትገዛው የአሁኗ ባለቤቱ አጠገቡ ስላለች ይመስለኝ ነበር፡፡ ከድርጅቱ መሥራቾች አንዱ  የሆኑት ዶ/ር አረጋዊ በርሔ ለዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ በሚል ርእስ ሠርተውት ኋላ ወደ መጽሐፍ በቀየሩት “The Origin of TPLF”  በሚለው የጥናት ጽሑፉ ላይ

‹‹የቤተ ክርስቲያኗ ሥልጣን (በትግራይ የነበረውን) ለማድቀቅ ሲባል በስብሃት ነጋ የሚመራ የስለላ ቡድን ተቋቋመ፡፡ ይህ ቡድንም ደብረ ዳሞን ጨምሮ በትግራይ ውስጥ ባሉ ገዳማት አባላቱን መነኰሳት በማስመሰል፣ የገዳማቱን እንቅስቃሴ በህወሓት ፍላጎት ሥር የማስገዛት ሥራ ሠርቷል›› በገጽ 317 ላይ ገልጧል፡፡

ድርጅቱ ሙሉ በሙሉ ሃይማኖትን ጠቅልሎ ለመያዝ የተነሣበትን ገፊ ምክንያትም እንዲኽ በማለት አብራርተዋል፡

‹‹ቤተ ክርስቲያኗ ተከታዮቿን፣ ለነበረው የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲገዙ ከማስተማር በዘለለ የብሔራዊ ንቃት(ማንነት) ማስተማርያም ነበረች፡፡ለህወሓት እንቅስቃሴ ዕንቅፋት እንደነበረች ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህም ቤተ ክርስቲያኒቱን በህወሓት ዓላማ ሥር ለማሳደር ፍላጎት ነበር፤ በዚህ የተነሣም የእርስዋን ተጽዕኖ ለማግለል ጥልቅ ርምጃ ወስደዋል፡፡›› /ገጽ 315 – 316/ / አረጋዊ ‹‹ጥልቅ ርምጃዎች›› ብለው ከጠቀሳቸው መካከል አንደኛው ‹‹ለአጥቢያ ቀሳውስቱ ኮንፈረንስ በማዘጋጀት፣ በትግራይ ውስጥ ያሉትን አብያተ ክርስቲያን ለብቻ ነጥሎ ህወሓት በሚያራምደው የትግራይ ብሔርተኝነት ሥር ማካተት›› እንደነበረ በዚኹ መጽሐፍ ጠቅሷል፡፡

እኔ ባለኝ መረጃ መሠረት ደግሞ አቦይ ስብሐት ነጋ ራሱ ከወሰዳቸው ጥልቅ እርምጃዎች አንዱ የለውጥ እንቅፋት ናቸው ያላቸውን በርካታ ንፁሐን የትግራይ ካህናትንና አገልጋዮች መጨፍጨፍ ነው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ኢሕአዴግ አንድን አካል(ስብስብ) በአደባባይ ከነቀፈ ከዚያ ስብስብ መካከል በስውር አብረውት እየሰሩ ያሉ አካላት እንዳሉ መጠርጠር እንዳለብኝ የተረዳሁት ዘግይቼ ነው፡፡

በዚህም መሠረት ሕወሓቶች አንዱና ዋንኛ ዕቅድ አድርገው የያዙትን ራዕይ ማለትም  የተካፋፈለች ቤተ ክርስቲያን፣ አቋም አልባ ጳጳሳት እና አንድነት የሌላቸው አገልጋዮች አንዲኖራት ለማድረግ ሕወሓት መራሹ መንግሥት አስርጎ የማቅ አባላት ካደረጋቸው አባላት በተጨማሪ ተመራጭ ካደረጋቸው ብሎጎች አንዱ ሐራና ታላቅ እህት ብሎጎቿ መሆናቸውን ወስጠ ምስጢራቸውን የሚያውቅ አንድ ወዳጃቸው በቅርብ አጫውቶኛል፡፡

ታዲያ አድር ባዩና አስመሳዩ ወንድሜ ኤፍሬም እሸቴ በቃሉ፣ እንዲሁም እንደ መስቀል ወፍ ብቅ በሚሉና በአሜሪካ በሕልውና ለመቆየት ወሳኝ ከሆኑት ጉዳዮች አንዱ የሆነውን ሕወሓት መራሹን መንግሥት መሳደብና መንቀፍ የሚለውን መርህ ተግባራዊ ለማድረግ ሲሞካክር ሳየው አሳዝኖኝ ከንፈሬን መምጠጤ አልቀረም፡፡

ይህ ፎቶ ማክሰኞ ሚያዚያ 9/2004 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ለምክር ቤቱ “መንግሥት በሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ አልገባም” ብለው ባቀረቡበት ወቅት “አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የአክራሪነት ዝንባሌ ይታይባቸዋል ላሉት ንግር መልስ በሰጠበት ወቅት የለጠፈው ነው፡፡

አንደው ግን ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የደከሙባቸው ልጆቻቸው እንዲህ መክነው ሲቀሩ ምን ይሉ ይሆን?

በቀጣይ ክፍል ስለሌሎቹ ሐራውያን አስተዋውቃችኋለሁ

የፈራ ይመለስ!

ሳምኬት ነኝ

ቸር ሰንብቱ!

ሰኔ 25/2011 ዓ.ም

‹‹ዘመቻ ጌዴዎን›› መጽ. መሳ. ምዕራፍ ፯

ዘመቻ ጌዴዎን ክፍል አንድ

ዘመቻ ጌዴዎን በቤቱና በሕዝቡ ላይ በክፋትና በተንኮል በሚነሱ ሁሉ ተዋጊውና ድል አድራጊው እግዚአብሔር ብቻ መሆኑን የምንረዳበት ታሪክ ነው፡፡በዚሁ መጽሐፍ ላይ ሰፍሮ እንደምናገኘው ጌዴዎን በእስራኤላውያን ላይ በትዕቢትና ማንም ሊያሸንፈን አይችልም ባይነት የተነሱትን ምድያማውያንና አማሌቃውያን በመለከት፣በማሰሮና በመብራት ‹‹የእግዚአብሔር ኃይልና የጌዴዎን ጦር ደረሰብህ›› ብለው በመጮኸ ብቻ እስራኤላውያን ድል እንዲያደርጉ ከእግዚአብሔር መመሪያ የተቀበለ መስፍን ነው፡፡፡፡ለዘመቻ ጌድዎን የተነሱት የሰዎች ብዛት 22ሺህ ቢሆንም  እግዚአብሔር ሊሠራባቸው የፈለገው ሦስት መቶ ሰው ብቻ ነው፡፡ፈሪና ቦቅቧቃዎችን ስላልስፈለገጉ  በዚህ ላይ ደግሞ ፊሪ ሰው ስለ ወገኑም ሆነ ስለ ሀገሩ ፍቅር ስሌለው የማሸንፍ ወኔ ሊኖረው ስለማይችል 1ዮሐ4፡18 ይህ ዘመቻ ‹‹የፈራ ይመለስ›› በሚል አዋጅ እግዚአብሔር ሊሠራባቸው በፈለጋቸው 300 መቶ ሰዎች ብቻ ጦር ሳይመዘዝ የጌዴዎን ጦር የደረሰባቸው መስሎአቸው በራሳቸው ሾተል እርስ በእርሳቸው ተላልቀው የጠፉበት የእግዚብሔር ኃይል የተገለጠበት የድል ዘመቻ ነው፡፡

ዛሬም በዚህ በእኛ ዘመን በቤተክርስቲያን ውስጥ መሽገው ያሉ ሐሳውያንና ሲሞናውያንን ‹‹የእግዚአብሔር ኃይል የተዋሕዶ ልጆች መጡባችሁ ነቁባችሁ›› ብለን ኦሮቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን ለማፈራረስ የተሰለፉትን አካላት ንስሐ እስኪገቡ እምቢ ካሉ ደግሞ ከሐዋርያዊቷ ቤተክርስቲያን እስኪወጡ ድረስ የምንዋጋበት ጊዜው አሁን ይመስለኛል፡፡በሀገራችን ላይ ያለው ፈርጀ ብዙ ችግር ሳያንሰን ስለ ሆዳቸው ሙላትና ስለ ደረታቸው ቅላት በሚጨነቁ ውሪዎች ምዕመናን ቤተክርስቲያንን መጽናኛ፣ መጠጊያ አባቶችን የችግራቸው ተካፋይ እናዳይሆኑ በችግር ላይ ችግር እንዲጫንባቸው የአእምሮ ማረፊያና መጽናኛ እንዳያገኙ የዲያብሎስ መልእክተኞች አጥብቀውና ዓላማ ሰንቀው እየሠሩ ይገኛሉ፡፡

አብዛኛዎቻችን አርቆ አሳቢነት ከላያችን ተገፎ ጥቅመኝነት፣ ሐሜት፣ውሸትና አድመኝነት ሰልጥኖብን ክርስቶስ ለኃጢአተኞች መሞቱ ተረስቶ ኃጢአተኛ ከተገኘ ከመምከርና ከመመለስ ይልቅ ቤተ ክርስቲያን እንደገባ ከልብ ሰዎችን ማሳደድ ዋና መገለጫችን ሆኗል፡፡ ምክክራችንና ውሳኔያችን ከአራት ኪሎ ካፌዎችና ውስኪ ቤቶች አለማለፋቸው ደግሞ እጅግ የሚያሳዝንና የዝቅጠት ደረጃችንን ማሳያ ነው፡፡ወደድንም ጠላንም ዛሬ ሕዛባችን ላለበት የስነ ምግባር ጉድለት፣የሞራል ልዕልና እጦትና የእምነት ገድለት ቤተክርስቲያንና የቤተክርስቲያን ሰዎች ከተጠያቂነት ማምለጥ አንችልም፡፡አልታደልንም እንጂ ካለብን ትልቅ ኃላፊነት የተነሳ ኅብረተሰባችን የላቀና የበለጸገ ሀሳቦች ባለቤት በማድረግ ሲገባን ራሳችን ውሸተኞች አድመኞችና ሲሞናውያን ሆነን ሕዝቡንም የዚሁ ሰለባ በማድረግ ስለሃይማኖቱ ለዘብተኛ አቋም እንዲኖረው ብሎም የሃይማኖቱን ጉዳይ ለጆቢራዎችና ለቤተክህነቱ አይጦች አሳልፎ በመስጠት እጁን አጣምሮ እንዲቀመጥ ወኔው የተሰለበ አማኝ አንዲኖረን በማድረግ ተጠያቂ መሆን የሚገባን እኛው ነን፡፡ እኒህ ዓይነት ችግሮች ደግሞ በዘመቻ ካልሆነ ማስወገድ አይቻልም፡፡

ይህን ጽሑፍ ለማጻፍና ‹‹ዘመቻ ጌዴዎን›› መጀመር አለበት እንድል ያስቻሉኝንና ያነሳሱኝን  ሁለት ምክንያቶች ልግለጥ፡-

፩. በአንዳንድ ‹‹ታዋቂ›› ሰባኪና ዘማሪ ወንድሞቻችን የሰርግ መርሐ ግብር ላይ የሚገኙ ታዳሚዎችን ላስተዋለ በትክክል ተደራጅተው ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ የሚንቀሳቀሱ መፍቀሬ ነዋይ ሲሞናውያን፣ ለቤተክርስቲያ ተቆርቋሪ መሳዮችና አስመሳዮች ሰውን ተሐድሶ እያሉ የሚያሸማቅቁ በተግባር ግን ራሳቸው ሊበራል ተሐድሶዋያን መኖራቸውን ለማረጋገጥ ጊዜ አይፈጅበትም፡፡ዝም ብላችሁ ጠጋ ብላችሁ ካዳመጣችሁ አባቶችን ለገብያ በማቅረብ ስለሚያገኙት ትርፍ ሲወያዩ፣ሲከራከሩ እና ሲጣሉ(በሽያጭ ዋጋ ማለቴ ነው) ስታዩ ልክ እንደ እኔ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ መግባታችሁ አይቀርም፡፡ በነገራችን ላይ በተለይ በቅርብ ጋብቻቸውን የፈጸሙ የእነዚህ ‹‹ታዋቂ›› ወንድሞቻችንን የሠርግንና የመልስን ቪዲዮ ወይም ፎቶ ካገኛችሁ ለቤተክርስቲያን ውደቀትም ይሁን ልማት የሚሠሩ ቡድኖችን በግልጽ ታዩበታላችሁ፡፡

.ሌላው ምክንያቴ በግንቦት ወር 2011 ዓ.ም እየተደረገ ያለውን የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ለግል ጥቅም ማጋበሻ እና ንጹሐን፣ ብጹአን ቅዱሳን አባቶችን ለማስፈራሪያነት በመጠቀም በተደራጀና ስልታዊ በሆነ መልኩ በመደራጀት አንዱ ወገን ሰዳቢ ከዚያው ቡድን ደግሞ ሌላው አስታራቂ ሆነው ገንዘብ ተቃባዮች እየተበራከቱ ስለመጡና በራዕ 13፡5 መሠረት ‹‹የስድብን አፍ›› ከአውሬው ተቀብለው እየተንቀሳቀሱ ያሉ አካላት መሳቂያ መሳለቂያ ሊያደርጉን ከምን ጊዜውም በላይ ተደራጅተው መንቀሳቀስ በመጀመራቸው ሥር ነቀል ዘመቻ ያስፈልጋል ብዬ በማመኔ ነው፡፡

ስለዚህ በመጀመሪያ ክፍል ጽሑፌ ሁለተኛውን ምክንያት ላብራራ እሞክራለሁ፡-

በነገራችን ላይ ‹‹ዘመቻ ጌዴዎን›› የሚያስፈልግበት ምክንያት እጅግ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ የክፍለ ሀገር ጉባኤያትን ጠልና ናቂዎች የሆኑ (በርግጥ እነሱ የገጠር የሚሉት ከእነሱ የተሻለ የሚያምንና  ሃይማኖቱን የሚረዳ በመሆኑ ስብከታቸውና ዝማሬያቸውን ከእነሱ የእምነትና የዕውቀት ደረጃ በታች ስለሆነ የእነሱን ተረት ለመስማት ጊዜው ሊኖረው ባለመቻሉ  )  ‹‹ታዋቂ›› ሰባክያንና ዘማርያ በአብዛኛው በጥቅም ላይፋቱ እርስ በእርስ የተሳሰሩ በመሆናቸው በዋነናነት ደግሞ ለሕዝቡም ይሁን ለቅድስት ቤተክርስቲያን ፍቅር ስሌላቸው ይፈራሉና እውነትን ቢናገሩና ቢሰብኩ ጥቅማቸው ስለሚቀርባቸው 1ዮሐ4፡18 ፍቅር የሌለው ሰው ደግሞ ፈሪና ለሆዱ አዳሪ በመሆኑ ‹‹የፈራ ይመለስ›› ብለናቸው በአባቶች ጸሎት ታግዘን ቀኖና ቤተክርስቲያንን ጠብቀን ኃይለ እግዚአብሔር ተደግፈን ለሰልፍ ልንወጣ ይገባናል፡፡

ስለ ተዋሕዶ ሃይማኖት መስፋፋትና መጠናከር ስለ ምዕመናን ድኅነት ከሚገዳቸው ለዚህ ዘመቻ ፈቃደኛ ከሆኑ አባቶች፣ ወንድሞችና እህቶች ምክክር መረዳት የቻልኩት ዐቢይ ነገር  ሌሎች የእምነት ድርጅቶች በርካታ አስተዳደራዊ ሥነ ምግባራዊና ሃይማኖታዊ ችግር እያለባቸው የውስጥ ችግራቸውን በውስጥ እየፈቱ ባለበት ዘመን በእኛ በኦርቶዶክሳውያንን ቤት ግን እየሆነ ያለው ስም የማጥፋት ዘመቻና አስተዳደሯን የማዳከም ዘመቻ አይደለም በአማኞቻችን በከሀዲያን በአላውያን እንኳ ተፈጽሞ አያውቅም፡፡ዳሩ እነዚህ አካላት ጥንተ ታሪካቸው  እንደሚያስረዳን ጉባኤ ቤት ያልዋሉ ያላደሩ ብቻ ሳይሆን በጉብኝት መልክ እንኳ ጎራ ብለው የማያውቁ ከመንገድ ተጠልፈው ከመንጋው የተቀላቀሉ የከሰሩ ነጋዴያን ናቸው፡፡ስለዚህ የዘመቻው መጀመሪያ በመንፈስ ቅዱስ ስለሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ ግንዛቤው፣ ዕውቀቱ ከምንም በላይ ደግሞ እምነቱ የሌላቸው ስለሆኑ ዘመናዊ የድምጽና የምስል መቅጃዎች በሲሞናውያን በኩል በማስገባት ቅዱስ ሲኖዶስ ብቻ አይቶና አመዛዝኖ ብያኔ ሊሰጥባቸው የሚገባቸውን አጀንዳዎችና ጉዳዮች ለአደባባይ መሳቂያና መሳለቂያ በማድረግ ሥጋዊና ቁሳዊ ፍልጎታቸውን እያሟሉ ባሉ የጡመራ መድረኮች(ብሎጎች) ይሆናል፡፡ ለዚህ ጽሑፍ ይህን ዕድል አግኝቶ የተመረጠው የጡመራ መድረክ ‹‹ሐራ ዘተዋሕዶ›› ነው፡፡

በዚህ የመጀመሪያ ክፍል ‹‹ሐራ ዘተዋሕዶ›› ለምን ዓላማ ተቋቋመ? ጸሐፊዎቹስ እነማን ናቸው? የሚለውን እንመለከታለን

‹‹ሐራ ዘተዋሕዶ›› ለምን ዓላማ ተቋቋመ?

በእነሱ የጡመራ ገጽ ላይ ይህ የጡመራ ገጽ ለምን ዓላማ እንደተቋቋመ እንዲህ በማለት ይገልጹታል ፡-

‹‹ሐራ ዘተዋሕዶ – የተዋሕዶ ሠራዊት፣ የተዋሕዶ ወታደር፣ የተዋሕዶ ጭፍራ ማለት ነው፡፡ ሐራ – ሐርነት፣ ነጻነት ያለው ማለት ነው፡፡ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን ትምህርትና ሥርዐት፣ ትውፊትና ታሪክ ለማጥፋት በውስጥና ከውጭ የሚንበለበሉትን የአፅራረ ቤተ ክርስቲያን ፍላጻ ለመመከት የእምነትን ጋሻ አንሥተን እንጦምራለን፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ብሔራዊ ክብርና ተቋማዊ ነጻነት በማንበር ሐዋርያዊ አገልግሎቷ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲጠናከርና እንዲስፋፋ የመረጃንና የዕውቀትን ሰይፍ በመያዝ እንጦምራለን፡፡ በአገልጋዮችና ምእመናን አዎንታዊ ተግባቦት ለተጨባጭ ለውጥ የሚያበቃ የመንፈስና የተግባር ተናሥኦት (Uprising) እንዲፋፋም እንጦምራለን፡፡ ስለዚህም ሐራውያን ለተዋሕዶ – የተዋሕዶ ሠራዊት፣ የተዋሕዶ ወታደሮች፣ የተዋሕዶ ጭፍሮች ነን፡፡››

እነሱ እንዲህ ነን ቢሉም መጋረጃው ሲገለጥ ታሪካቸውና ዓላማቸው ከዚህ በፍጹም ተቃራኒ ሆኖ እናገኛለን፡፡ ልብ ብሎ ላስተዋለው ዓለም በቴሊቪዥንና በፊልሞች የአውሬውን መንፈስ እያስተዋወቀች እንዳለው ሁሉ በዚህ የጡመራ መድረክም ምንም ዓይነት ሙያዊ ትንታኔ ሳያስፈልገው ከጥቅምት 12 ቀን 2002 ዓ.ም ጀምሮ ያለውን ጽሑፍ በአስተውሎት ለተመለከተ የአውሬውን መንፈስ እያለማመዱንና እያስተዋወቁን እንደሆነ፣ ከእምነት ትምህርቶች ይልቅ የምንፍቅና፣ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ጽሑፎች ይልቅ ፍጹም ኢ-ቀኖናዊ የሆኑ ጽሑፎችን በተደጋጋሚ ይጽፋል፤ ትውልዱ የቤተክርስቲያን ጉዳይ መቼም ቢሆን የማይስተካከል ነው ብሎ እንዲያስብና እንዲያምን፤ ገለልተኛና ለዘብተኛ ሆኖ እነሱ የፈለጉትን ማንገስ ያልፈለጉት መደቆስና ማኮሰስ የሚችሉ አይነኬ ናቸው ብሎ እንዲያስብ በምናባዊው ጭራቅ እንዲመስላቸው እነሱ ባሉበት ቦታ ሁሉ በለሆሳስና በጭንቀት እንዲያወራ አድርገን ያነገስናቸው የጥልቁ መልእክተኞች ናቸው፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነው ሐራውያን ከሐሳዊ መሲህ መገለጫዎች አንዱ የሆነውን ተሳዳቢነት ምዕመኑ እንዲለማመድ የቤተክርስቲያን አባቶችን  ከብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጀምሮ እስከ አጥቢያ ምዕመን ድረስ ያሉትን መስደብ ማቃለል እንዲለማመድ እንዲሁም አማኙ ምን አባት አለ ብሎ ከንስሐና ከንስሐ አባት ውጪ እንዲኖር ማድረግ ኅቡዕ ዓላማቸው ነው፡፡ታዲያ ይኽ ለሐራውያ ምን ይጠቅማል ? ካላችሁኝማ በቃ ዋንኛ መተዳደሪያቸው ነው፡፡የአሠራር መንገዳቸው አንዱ ጋንታ የእገሌን ስም ላጥፋልህ ብሎ ብር ይቀበላል ሌላው ደግሞ ጸሐፊዎችን አግኝቼ ሁለተኛ እንዳይጽፉብህ ላድርግ ወይም አውግዝልሃለሁ ይላል፡፡ በቃ በአጠቃላይ ሐራ ዘተዋሕዶ ለምን ተቋቋመ ቢባል ሲሞናዊነትና ሐሳዊ መሲህነትን አለማምዶ ከቤተክርስቲያኒቱ የማይነጥፍ ሀብት ለግል ጥቅም ለማግበስበስና ቤተክርስቲያኒቱን ለማፈራረስ ነው፡፡ ሐራውያን በተጨባጭ ጸረ-ተሐድሶ እንደሆኑ ራሳቸውን ቢሰብኩንም እንደ አንድ ሊቅ ወንድሜ አገላለጥ በተጨባጭ ሊበራል ተሐድሶዎች ናቸው፡፡ ምክንያቱም ዋና ራዕያቸው ምዕመናን ከቤተክርስቲያን አባቶች ተለይቶ በእነሱ ዓይነት ጥቁር ራስ ጨዋዎች ስትመራ ማየትና ቤተክርስቲያኒቱን ሐዋርያዊት የሚያሰኛትን ከሐዋርያት ጀምሮ ሲወር ሲዋረድ እኛ ዘመን  የደረሰውን ሥልጣነ ክህነት መክኖ ማየት ነው፡፡እዚህ ላይ ሐራ ከተቋቋመች ወዲህ ምን ምን ጻፈች የሚለውን  በሠንጠረዥ ከማብራሪያ ጋር ወደ ፊትስለማቀርብ ተራ አሉባልታ እንደሆነ ትረዱልኛላችሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ውድ አንባቢያን! በዚህ ክፍል ከሐራውያን መካከል የአንዱን እንደማሳያ በማቅረብ የሐራውያንን ማንነትና ጥንተ ታሪክ በመግለጥ መሠረተ ቢስ አሉባልታ አናፍሾች ፤ ሕዝብን አደናጋሪዎች መሆናቸውን የበለጠ ግልጽ ለማድረግ እሞክራለሁ፡፡ከሐራውያን ጋር የሚሰሩ እና በቤተክህነት መዋቅር ውስጥ ሆነው ከቤተክርስቲያን በሲሞናውነት የሚጠቀሙ ወንበዴዎችንና ቤተክርስቲያንን የወንበዴዎች ዋሻ ለማድረግ የተሰለፉ ወንበዴዎችን ጉዳይ እና ከፒያሳ ዶሮ ማነቂያ ወደ 5 ኪሎ በተዛዋወረውና ዋንኛ የመገበያያ ማዕከል ስለሆነው ኤፍሬም ውስኪ ቤት ጉዳይ ወደ ፊት በስፋት የምመለስበት ይሆናል፡፡

‹‹ሐራ ዘተዋሕዶ›› በእነማን ተቋቋመ?

‹‹ሐራ ዘተዋሕዶ›› ደጀ ሰላም የሚባለውን ብሎግ መዘጋት ተከትሎ የተቋቋመ ISIS(If you pay you are Safe; If not you can`t Survive›› የሚለውን ሲሞናዊ ዓላማ አንግቦ የተነሳ የመገበያያ(የነጋድያን) የጡመራ መድረክ ነው፡፡ በቃ በቤተክርስቲያን ሕይወትህ ወይም ሥራህ በተለይ ደመወዝ ከቤተክርስቲያን የሚከፈልህ ከሆንክና በተለይ ደግሞ ድቀት ከገጠመህ ፀረ-ገሪማውያ(ገሪማ ገረምከነ) ስለሆኑ፤ ተረጋግቶ በንስሐ ራስን ማረም በእነሱ ዘንድ ተቀባይነት ስለሌለው   በሐራ ዘተዋሕዶ እንዳትብጠለጠል ከፈለግህ መክፈል አሊያም ወደድክም ጠላህም የማቅ ደጋፊ መሆን ብቻ ነው አማራጭህ! በነገራችን ላይ ይህ የመገበያያ ብሎግ በነገር አባታቸው በሁለ ገቡነና ራሱን በሾመው ‹‹የታሪክ ተመራማሪ፣ደራሲ፣ሀያሲ፣የሃይማኖት መምህር፣የተረት አባት፣የመንግሥት አማካሪ፣ፓለቲከኛ እና ወደ ፊት ምናልባት ታዋቂ ባለሐብትና ….›› በሆነው ግለሰብ መሪነትና አመካሪነት የተመሠረተ ነው፡፡ እናም አንዳንድ ያልነቁና ያልተረዱ የዋህ የማቅ አባላትንና ደጋፊዎችን የሚያታልሉት ከልብ ሳይሆን በአፍና በመጻፍ ስለ ማቅ ሲነሳ ለምን ይነካል ብሎ ፉከራና ሽለላ በማሳየት ነው፡፡ ይህን ለመረዳት የነገር አባታቸው ለምን እና እንዴት ከማቅ ወጣ? ብሎ ለጠየቀ መልሱ ቅርብ ነው፡፡ይኸው ግለሰብና ቡችሎቹ ማኅበሩን ከሦስቱም መንፈሳዊ ኮሌጆቻችን ደቀ መዛሙርት፣ከሊቃውንት አባቶች ከሰ/ት/ቤት አባላት የማኅበሩን ልሳን በመጠቀም በተደጋጋሚ ይሳደቡ፣ያጋጩ ያደባድቡና ያስወግዙ እንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡ በነገራችን ላይ ከዚህ ሰው ጋር ለመቆየትና ለመኖር የፈለገ ሰው በእሱ ሳንባ መተንፈስ በየሄድክበት ስሙ ተነሳም አልተነሳም ስለ እርሱ መስበክና መመስከር ግዴታ ነው፡፡ያለዚያ አንድ ታፔላ ተለጥፎልህ ስትብጠለጠል ስትሳደድ ትኖራለህ፡፡አሁን ግን ስለዚህ ሊበራል ጴንጤ የማወራበት ጊዜውና ተራው ስላልሆነ፤ በዚህ በዛሬው ጽሑፍ እሱ  ካለፈበት የሕይወት መስመር ማለት ተንኮለኛነት፣ ተሳዳቢነትንና ሐሳዊነትን እንዲሁም ቤተክርስቲያን ውስጥ በተኩላነት የመኖርን አቅም እስኪያጎለብት ድረስ ተንከባክቦ ስላሳደገው ስለ አንዱ ቡችላ ላውጋችሁ፡፡

ይህ ቡችላ ሐራዊው አሉላ ጥላሁን(አብሮ የሚውላቸው ባልንጀሮቹ እጅግ ታዋቂነትን ባስገኘለት ሥራው ‹‹ዲጄው››ና ሰካራምነቱ ‹‹ጠጆ››…እያሉ ይጠሩታል)

ይህ ግለሰብ ከሐሮምያ ዪኒቨርስቲ በግብርና የመጀመሪያ ድግሪ እና ከአ.አ.ዩ በፍልስፍና ትምህርት የሁለተኛ ድግሪ ያገኘሲሆን(ወደፊት የሚጣራ ይሆናል) ለአቅመ ራስን መቻል እንዳይችልና በተላላኪነት እንዲኖር የተደረገ የመከነ ጎበዝ አርታኢ ነው፡፡ ይህ ወንድማችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አሳዳጊዎቹና አሳዳሪዎቹ ባለባቸው ‹‹የአማካሪነት›› እና የስላይድ ንግድ ሥራ ጫና ምክንያት ገሸሽ አድርገውት ስላሉ የእሱ ገብያ በሚደራበት የጥቅምትና የግንቦት ሲኖዶስ (ወደ ፊት ስብሰባው በዓመት 4ት ጊዜና ከዚያ በላይ እንዲሆን እንደሚጦምር ተስፋ አለኝ) ካልሆነ በስተቀር የእለት ጉርሱን በብድርና ጋባዥ በመፈለግ እንደሚኖር አውቃለሁ፡፡ ታዲያ ዲጄው ከወታደርነት ስኳድ ከተቀነሰ ጊዜ ጀምሮ ሱሱ አለቀው ብሎት ዛሬም አባቶችንና ወንድሞችን እየነጠሉ የመምታትና የማሸማቀቅ ሰትራትጂ በአግባቡ እየተጠቀመበት እና በዚሁ ለመተዳደር አማራጭ ያደረገ ይመስላል፡፡

ይህ ወንድማችን መቼም ያልሞከረው እና ያልገባበት መስክ ባለመኖሩ በአንድነት የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ አባል ሆኖ በነበረበት ጊዜ በሠራው መረጃ የማቀበልና የስለላ ተግባር ፓርቲውን ለማፈራረስ ባደረገው ሙከራ ተደጋጋሚ እስርና  ከሀገር የመውጣት ክልከላ ደርሶበታል፡፡

አዲስ ሥራ ለመጀመርና የፖሊተካ ፓርቲ አባል ለመሆን በደጅ ጥናቱ ወቅት

በስለላ ሥራ ላይ

ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ ከዲጄነቱ ጋር በተያያዘ የራስታን የኑሮ ዘይቤ የሚከተል እና በእነሱ መንገድ ለመኖር በተደጋጋሚ ጥረት እንደሚያደርግ በራሱ ብሎግ ላይ ተለጥፎ ከነበረው አሁን ግን ካነሳው መልእክት መረዳት ይቻላል፡፡

ዲጄነቱን የሚያውቁ ሰዎች በጃንሜዳ የድምጽ ችግር ገጥሞአቸው ለማስተካከል ሲውተረተር

meskel Squre(1997) …Experiencing His Majesty

እዚህ ላይ መነሳት ያለበት ጥያቄ የራሷ የታወቀና የተረዳ እምነት፣ ቀኖናና የአስተዳደር ዳኝነት ያላትን ሉዓላዊት ቤተክርስቲያን ለማፈራረስ፣ለማተራመስ፣እና አንድነቷን ለመፈታተን  ሐራውያን ለምን እና በምን ዓላማ ተነሣሡ? ማን ቀጠራቸው? ቅኝ የገዛቸው ማነው? ለሚለው ጥያቄ መልስ ማግኘት እልህ አስጨራሽ ቢሆንም ለቅድስት ቤተክርስቲያን የወደፊት ህልውና የግድና ወሳኝ ነው፡፡ ይህ ወንድማችን ከማቅ ጋዜጣ አዘጋጅነትና ከማኅበሩ መደበኛ ሠራተኝነት ለምንና እንዴት ተባረረ? ዛሬስ መደበኛ ሥራና ደመወዝ የሌለው ሆኖ ሳለ በቅርብ ጊዜ የቤትና የመኪና ባለቤት ለመሆን በዝግጅት ላይ እንዳለና ሚስት ለማግባት የኢንተርኔት ቤት ደንበኛው በእጮኝነት ይዞ ለጋብቻ በዝግጅት ላይ መሆኑን በተለይ ትንሽ አልኮል(በተለይ ጠጅ)  ሲቀማምስ አብሾ እንዳለበት ሰው እንዲለፈልፍና እንዲፎክር ያስቻለው ከማንና ከእነማን በሚያገኘው የገቢ ምንጭ ተማምኖ ነው? የሚሉት ጥያቄዎች የተሰማራበትን ዋናውን ዓላማ ለመረዳትና መፍትሔ ለማግኘት እንደሚረዳን አምናለሁ፡፡

ሐራዊው(ወታደሩ)፣ዲጄው፣ሰላዩና ፖለቲከኛው አሉላ ከ320 ሃያ ቅዱሳን በላይ ስንክሳር የተጻፈላቸው፣ድንጋይ ተንተርሰው፤ጤዛ ልሰው ግርማ ሌሊትን ጸብአ አጋንንት ታግሰው ስለ ሀገርና ስለ ዓለም ሰላም የሚያለቅሱ አባቶችና እናቶች መናንያን ያሉባትን ቅድስት ቤተክርስቲያን ሲዘልፍ፣ ሲሳደብና ሲያቃልል ምንም ሰው እንደሌለባት አድርጎ በድፍረትና በትዕቢት እንዲጽፍ ያስቻለው ከራስታዎች ጋር ባለው የቅርብ ግንኙነት የተለማመደው ጋንጃ ሳቢነቱና ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደገለጠው ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ ቤተክርስቲያንን ሲዋጋ የኖረው ዲያብሎስ ድፍረት እንደሰጠው እሙን ነው፡፡ይህ ምስኪን ወንድማችን ተረጋግቶ ቆሞ ለማወራት የሚቸገር በሙሉ መዳፉ ማንንም ለመጨበጥ የማይደፍር ከመሆኑም በላይ አንዳንድ ጊዜም እስከ መጦዝና አእምሮን የመሳት ሁኔታ እንደሚገጥመው በቅርብ የሚያውቁት አንዳንድ ወደጆቼ በቅርብ ጊዜ ያጫወቱኝን አስታውሳለሁ፡፡ አባቶቻችንም ከዚህ ጽሑፍ በኋላ ‹‹ዝንቱ ዘመድ ኢይወጽእ እንበለ ጾም ወጸሎት›› በሚለው አምላካዊ ቃል መሠረት በጸሎት እንደሚያግዙትና ከሱስና ከአጋንንት ቁራኝነት ነጻ እንደሚያወጡት ባለሙሉ ተስፋ ነኝ፡፡ ምክንያቱም ቤተክርስቲያን ስለሁሉም ነገር መፍትሔ ያላት ስንዱ እመቤትና ስለ ሁሉ መዳን ሁልጊዜ የምትጸልይ ስለሆነች፡፡ ወንድማችን አሁን እየተጓዘበት ያለው የዲያብሎስ መልእክተኛነት መረገም ነውና ቅድስት ቤተክርስቲያን ደግሞ በጸሎቷና በፍጹም ፍቅሯ ከወታደርነት፣ከዘማዊነትና ከነፍሰ ገዳይነት መልሳ ወደ ጵጵስና እና ወደ ፍጹምነት ማዕረግ እንዲደርሱ የረዳቻቸው በርካታ መሆናቸውን ተረድቶ ወደ ንስሐ እንደሚመለስና የቤተክርስቲያን ጸሎትም እንደሚረዳው ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

በቀጣይ

  • ሐራዊው(ወታደሩ)፣ዲጄው፣ሰላዩና ፖለቲከኛው አሉላና ግብረ አበሮቹ በምን ሰንሰለት የሲኖዶስ ስብሰባዎችን ሙሉ መረጃ እንዴት እንደሚያስቀዱ፤
  • እነማን አባቶችን በማን ከፋይነት እደተሰደቡ
  • ከብጹአን አባቶች መካከል በእነማንና በምን መልኩ ይደገፋሉ
  • በግንቦት 2011 ዓ.ም ለገበያ የቀረቡ ብጹአን አባቶችና የቡድኑ አባላት ስለሆኑ ብቻ ሰልፍ፣ ተቃውሞና የገዘፈ ችግር እያለባቸው ስለተንቆለጳጰሱ አባቶች እንዲሁም ሌሎች ወቅታዊ ርእሰ ጉዳዮችን ይዘን እንመለሳለን፡፡

ውድ አንባቢያን! የዚህ የጡመራ መድረክ ዋና ዓላማ ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ወደ ተሻለ ደረጃ ደርሳ የራሳን ጉዳይ ከሲሞናውያን እጅ ነጥቃ በራሷ ልጆችና በራሳ ሚዲያ ብቻ እየገለጠች ማየት በመሆኑ ማንኛውንም ምክር አስተያየትና ግሳጼ ለመቀበል ዝግጁ ነን፡፡

ለሁሉም አምላከ ቅዱሳን ይርዳን!

ቸር ሰንብቱ!

ተጻፈ በሳምኬት ዘሐመረ ብርሃን

ግንቦት 28 ቀን 2011 ዓ.ም 

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

እስከ መቼ ቤተክርስትያን በ ‘ሐራ ዘተዋህዶ’ ድህረ ገጽ ትታመስ? ክፍል ፩

ውድ የተዋህዶ ምእመናን እንደሚታወቀው ጥንታዊቷ የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ከተጋረጡባት አሳሳቢ ችግሮች አንዱ በቤተክርስትያን ውስጥ ቁጭ ብለው ፣ በቤተክርስትያን ውስጥ ያለውን አስተዳደራዊ ድክመትና ግልጽ የሆነ የመረጃ ፍሰት አለመኖር እንድ ጥሩ እድል በመጠቀም፣ በምንም አይነት መስፈርት የቤተክርስትያን ልሳን እንዲሆኑ ህጋዊም ሆነ ሃይማኖታዊ ፍቃድ ሳይኖራቸው ለድብቅ አላማቸው ማሳኪያ የሆኑ ዜናዎችን እውነቱን ከውሸቱ በመድበላለቅ ለህዝበ ክርስትያኑ የተዛባ የመረጃ ምንጭ በመሆን የአባቶችን ስም ሲያንቋሽሹ ፤ የቤተክርስትያንን ስምና መዋቅራዊ አሰራር ሲያዋርዱ ማየት የዘወትር ክስተት ሆኖ ማየት የተለመደ ሆኗል።

ከነዚህም ከላይ ከተጠቀሱት የተዛባ የመረጃ ምንጮች / Fake News or Distorted News/ ዋነኛ ሆኖ ቤተክርስትያንን ባሁኑ ሰዐት እያመሳት ያለው ‘ሐራ ዘተዋህዶ’ የተሰኘው ድህረ ገጽ ሲሆን ፤ በቀጣይ ጽሁፋችን ይህን ድህረ ገጽ ከጀርባ ሆኖ በሚስጥር ማን እንደሚያንቀሳቅሰው፤ በግለሰብ ደረጃ እነማን እንደሚሳተፉበትና ያላቸውን ድብቅ አጀንዳ በቀጣይ በዝርዝር የምንመለስበት ይሆናል።