አስቀድመን በፌስ ቡክ ገጻችን ላይ አንድ ጥያቄ ጠይቀን ነበር፡፡ ይኸውም የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ወደ ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ለምን ተቀየረ? የሚል ጥያቄ ጠይቀን በጣም የሚገርማችሁ ማን መልስ ቢሰጥ ጥሩ ነው? ሞዐ ተዋሕዶ ነበር!!!ለቡ!!!
ለማንኛውም ከላይ ወደ አነሳሁት ርዕስ ልመለስ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚፈጠሩ ችግሮችን እንደ መልካምና ምቹ አጋጣሚ የሚጠቀሙ አሊያም ከችግሩ ፈጣሪዎች ጋር ቀድመው የተወያዩ በሚመስል መልኩ ችግር በተፈጠረ ማግስት የሚፈጠሩ ማኅበራትና ግበረ ኃይሎች ወይም ኅብረቶች(በነገራን ላይ #ኅብረት ዓይነተኛዋ የማጭበርበሪያ የዳቦ ስም ናት) በአብዛኛው ኢ-መዋቅራዊ ከመሆናቸው ባሻገር ከአብዛኛዎቹ ጀርባ ያሉት ግለሰቦች ተመሳሳይ መሆናቸው ከላይ ያነሳሁን ጥያቄ እንደጠይቅ አስገድዶኛል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ “ሕጋዊ በሆነ መንገድ የቤተ ክርስቲያንን መብት ለማስከበር ይሠራል፡፡” ብሎ ቃል እየገባ

እንዴት ልደግፍ? የእኔ ድርሻ ምንድነው? ምንተ ንግበር? ብሎ ከመጠየቅ ይልቅ ኃያላችንን ለማዳከም፣ የትኩረት አቅጣጫችን የተበታተነና ልክ እንደ ሉተራውያን በተለያየ ስም (መካነ ኢየሱስ፣ሙሉ ወንጌል፣ ቃለ ሕይወት፣ ጌጃ…) አንድ ሆነው ሲያበቁ ራሳቸውን በተለያየ ስያሜ እየሰየሙ የዋሕኑና ደጉን ምዕመን ማሰናከል ምን ይሉታል? እስካሁን ከዚህ በታች ከዘረዘርናቸው ማኅበራት፣ ኅብረት፣ ግብረ ኃይል ሂደት ሁላችንም መረዳት እንደምንችለው የስበት ማዕከላቸውና መዳረሻቸው ገንዘብ መሰብሰብና የግል ተከታይ(ቲፎዞ) ማፍራት ነው፡፡ ያለ ቅዱስ ሲኖስ ዕውቅናና ፈቃድ ማኅበራት፣ ኅብረት፣ ግብረ ኃይል እያሉ ማቋቋም ለቤተ ክርስቲያነቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳያል፡፡ እንዲሁም እኔ አውቅላችኋለሁ በሚል የትዕቢት ስሜት አንዱን አባት ተቆርቋሪ፤ ሌላው ለዘብተኛ፤ የተቀረውን ደግሞ ደንታ ቢስ ለማስመሰል የሚሠራውን እያንዳንዱን ሸፍጥ ታሪክ የመዘገበው ስለሆነ ዋጋ ሳያስከፍለን አይቀርም፡፡ በብፁዓን አባቶችም መካከል መለያያት ለመፍጠር የሚጠቀሙበት እንዲህ ዓይነቱ ስልት ያረጀ ያፈጀ ከመሆኑም ባሻገር የእግዚአብሔር ቃል ግን በመ. ምሳሌ 6፡ 16-19 “እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው ፤ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፤…በወንድማማች መካከል ጠብን የሚዘራ፤” እንዲል በዚህ መንገድ የሚጓዙ በአባታችን በእግዚአብሔር ዘንድ ጽዩፍ ስለሆኑ የ10፣ የ20፣ የ100 ዓመት ደረጃውን የጠበቀ ስልታዊ ዕቅድ ቢያቅዱ፤ ቀን ከሌሊት በትጋት ቢሠሩ እንኳ ወጤቱ ፍሬ አልባ መሆን ወይም መራራ ፍሬ ማፍራት ነው፡፡
ለምሳሌ የሕዝቡን ትኩሳት ተጠቅሞ ለምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ተብሎ የተቋቋመውን ሚዲያ ግለሰቦች እንደፈለጋቸው እንዲሆኑበት በላይክ፣ በሰብስክራይብ እና በሼር እንዲጠቀሙበት ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ብለው ሲሰይሙ ዝም ስላል ዛሬ ደግሞ ራሱን ልክ የቤተ ክርስቲያኒቱ ዋንኛ ተጠሪ አካል አድርጎ የምክክርና የጥናታዊ ጽሑፍ መድረክ ለመላው ኦርቶዶክሳውያን ማለት ምን ማለት ነው? ማነው መላ ኦርቶዶክሳዊያንን ጠሪ ያደረጋችሁ ? ማነው በእኛ ላይ የሾማችሁ? መድረኩ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችን የመመለስ ሓላፊነት አላችሁ? ለእናንተ ሲሆን ቀኖና ቤተ ክርስቲያን አይሠራም እንዴ? ጉባኤው በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት፣በጠቅላይ ቤተ ክህነት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፤በጠቅላይ ቤተ ክህነት እውቅና አለው? ፈቃድ ያለውን የቤተ ክርስቲያኒቱን ሚዲያ መጠቀም ለምን አልቻላችሁም? ዙሮ ዙሮ ከዩቲዩብ ለሚገኝ ድቃቂ ሳንቲም ብሎ ኢ-መዋቅራዊና ሁሉን አቀፍ ያልሆነው #ሞዐ ተዋሕዶ ላይ ከፊት የተሰለፉ ሰዎችን ለመስበርና ለማሰበር የሚደረገው ሩጫና ጥድፊያ ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝን ማስተዋል ይጠቅማል፡፡


በአጠቃላይ ባለፉት ሁለት እና ሦስት ዓመታት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ የተፈጠሩ መጠነ ሰፊ ችግሩችን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ለግለሰቦች የዕለት ጉርስ የዓመት ልብስ ከመጥቀም ባሻገር ይሄ ነው የሚባል ሁለንተናዊ ጥቅምና ለውጥ ያላመጡ ማኅበራት፤ኅብረት እና ግበረ ኃይሎች መካከል፡-
- ፈለገ ባኮስ የሰባክያን እና ዘማርያን ኅብረት
- የአዕላፋት ድምፅ የካህናትና ምዕመናን ተናሥዖት ኅብረት
- ሠለስቱ ምዕት የመንፈሳዊያን ማኅበራት ኅብረት
- የአስተዳዳሪዎች ኅብረት
- የወጣቶችና ጎልማሶች ማኅበራት ኅብረት
- የነገረ መለኮት ምሩቃን ማኅበር
- የሰ/ት/ቤቶች አንድነት
- ጴጥሮሳውያን የቤተ ክርስቲያን መብትና ክብር አስጠባቂ ማኅበራት ኅብረት
- ማኅበረ ካህናት ዘሰሜን አሜሪካ
- ማኅበረ ካህናት ዘዩኬና አየር ላንድ ሲሆኑ
- አሁን ደግሞ #ሞዐ ተዋሕዶ
- …ነገ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ችግር ሲፈጠር የሚፈጠሩ ይቀጥላሉ…
ከላይ የተዘረዘሩት እጅግ ጥቂቶቹ ሲሆኑ እነዚህ 99% እርስ በእርሳቸው በስውር መረብ የተሳሰሩ ናቸው፡፡ በእነዚህ ውስጥ ዋና ዋኛዎቹ ተዋንያን የራሳቸው ቋሚ ገቢ የሌላቸው፤ አለን የሚሉት ደግሞ በቃኝ የማያውቁ ሆድ አምላኩዎች ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የሁሉም መርሕ “የቤተ ክርስቲያንን መብት እናስከብራለን” ነው፡፡ የሚገርመው ነገር ደግሞ ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ማኅበር(ኅብረት) አንዲት ነገር ከለጠፈ ሳይጣራ፣ ሊሰጥ የሚችለው ጥቅም ፣ሊያስከትል የሚችለው ጉዳት ሳይጤን የእግር ኳስ ደጋፊ ይመስል እየተቀባበለ ይለጥፋል፡፡ ይሄ ከንቱነት ነው!!!
ሌላኛው ስጋቴ ማኅበረ ቅዱሳን እየቆየ ሲሄድ ዳንኤልና ግብረ አበሮቹ በሠሩት ሴራ ደመወዝዝ ከሚከፈላቸው መደበኛ የአድባራትና የገዳማት አገልጋዮች፣ ከሰባክያና ከሰ/ት/ቤት ጋር የመለያያት፣ያለመናበብ ብሎም የጥላቻ ስሜት እንደገጠመውና እንደተጋረጠበት ሁሉ የሞዐ ተዋሕዶ አጀማመርና አካሄድም ይሄንን ልዩነት የበለጠ የሚያሰፋው ካልሆነ በስተቀር የሚያጠብ ስላልሆነ ከተሳፈርንበት ጋላቢ ፈረስ ወረድ፤ ቆም ብለን ማሰብ አለብን!
በመጨረሻም በርካታ ተከታይ ያላቸው ሁለቱ ታላላቅ መምህራኖቻችን መ/ር ሰሎሞን ተስፋዬ እና ፍሬው አራት ዐይና የለጠፉትን በአጽንኦት ማየት የበርካታ ሰዎችን ስሜት ለመረዳት ይጠቅማልና ከታች ለጥፌዋለሁ፡፡


ስለ “ሞዐ ተዋሕዶ”ቆም! በደንብ ቆም! በትክክል ቆም! ተብሎ ይታሰብ!!!
ተጻፈ የካቲት 2014 ዓ.ም