ዘመዴ መስከረም 5 ቀን 2013 ዓ.ም በለቀቀው 55ኛው የYouTube ‹‹የበረኸኞቹ መልእክት›› ላይ የቤተክርስቲያን አራሙቻዎችና ነቀርሳዎች የሆኑ አይነኬዎችን ነጭ ነጩን ነግሮ እኛም የማጽዳት ዘመቻውን እንድንቀላቀል ጠንከር ያለ ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያ አስተላልፏል፡፡ እግዚአብሔር በክብር ላይ ክብርን ያድልህ!! ድሮም በየገዳማቱ ለበረከትና አባቶች ለመርዳት ሲንከራተት የኖረ፤ እውነተኛ አባቶችን ከልቡ የሚወድ፤ በታላላቅ የጸሎት አባቶችም የተቀባ የቤተክርስቲያን የቁርጥ ቀን ልጅን ከእነዚህ ከግብዞች፣ከሌቦች፣ከመዓተኞች፣ከቤቱ ሸክሞች፣ከሃይማኖት አሰዳቢዎች ተርታ አሰልፎ ለማየት መሞከር የማይታሰብ ነበር፡፡ በእውነት ዘመዴ እነዚህ አይነኬ ነን ባዮች፣ የቤተክርስቲያን ምስጦች በመገሰጽህ ሁሌም እንደምኮራብህ ዛሬም እጅግ ኮራሁብህ!!!
መቼም የፌስቡኩን መንደር የተቆጣጠሩት፤ አየሩን የሞሉት የእነዚህ አስመሳዮችና ጭፍን ደጋፊዎች ተራ ተራውን፤ ገበሬ አስደንግጡን፣ ገንዘብ የሚሰበሰብበትን ብቻ እየፈለጉ የሚለጥፉ እንጂ እንዲህ ጠፈፍ ያለውን ነጭ ነጩን እውነት መግለጥ ስለሚያንገሸግሻቸውና ስለሚያቅለሸልሻቸው በፌስቡክና በድህረ ገጻችን ላይ ይህን ጮማ እና አንጀት ቅቤ የሚያርስ ፤ሰው ሁሉ የYouTube ‹‹የበረኸኞቹ መልእክት›› እንዲያደምጠው የሚመራ ጽሑፍ ጽፈናል፡፡
አንዳንዶች hameretewahido.com ድረ ገጽ ላይ በማኅበሩ ካባ ተደብቀው ስለሚያጭበረብሩ ሰዎች የተጻፈውን ተመልክታችሁ የተንጫጫችሁ ነበራችሁ፡፡ እኛ ድሮም የምንለው፣የምንፈልገውና የምንደግፈው ማኅበረ ቅዱሳን የጥንቶቹንና መንፈሳውያኑን ፤ያለመታከትና ያለ ሥጋዊ ጥቅም የሚወጡ፣የሚወርዱ፣ የሚደክሙት፣ ደፋ ቀና የሚሉትን እንጂ ለቤተክርስቲያኒቱ የብጥብጥ፣የዝርፊያና የውንብድና መዋቅር የሚዘረጉትን አይደለም፡፡ ዘመዴ እንዳለው እነዚህ አራሙቻዎች ራሳቸውን ካላረሙ ነቅሎ መጣል ያስፈልጋል፡፡
ዘመዴ 1፡55፡52 በሚወስደው ሁሉም ሰው ተረጋግቶ ሊያደምጠው በሚገባውና እንኳን ለተናጋሪው ለሰሚው ቁና ቁና የሚያስተነፍሰውን ጭንቅላት ሊያፈነዳ የሚደረሰውን ‹‹የበረኸኞቹ መልእክት›› ማዳመጥ እጅግ ወሳኝ ነው፡፡ አስቲ ዘመዴ በቪዲዮው ማገባደጃ ላይ ስለ እነዚህ አራሙቻዎች፣ ምስጦች፣ ግብዞች፣ሌቦች፣ መዓተኞች፣ የቤቱ ሸክሞች፣ ሃይማኖት አሰዳቢዎች…ምን እንዳለ በወፍ በረር ከንግግሩ የወሰድኩትን ላስነብባችሁ፡፡
ውድ አንባብያን 55ኛውን የዘመዴ የYouTube ‹‹የበረኸኞቹ መልእክት›› ከታላቅ ተማጽኖ ጋር እንዲያደምጡ ላልሰማ እንዲያሰሙ አደራ ለማለት እንወዳለን!!!! አደራ!!!አደራ!!!አደራ!!!ዘመዴ እንዲህ ይላል፡-

40 ሚሊዮኑ ለተጎዱ ሰዎች ይከፋፈል ተብሎ ነበረ፡፡ ነገር ግን በሻሸመኔም፣ በባሌም፣ በሐረርጌም፣ በአሩሲም ያሉት ስደተኞች የተጠየቅነው የባንክ አካውንት የለም የደረሰን ብር የለም ከየትና እንዴት ተብሎ ወጣ እንደተባለ አናውቅም ብለዋል፡፡ ኮሚቴው ቀርቦ ለሕዝብ ያስረዳ ሰውዬው ሳይፈርም ሰውዬው ሳያውቅ ሳይጠየቅ ስደተኞቹ ሳይነገራቸው የባንክ ቡክ ተዘጋጅቷል 40 ሚሊዮን ብር ሊከፋፈሉ ነው ማለት ይሄ ነውር ነው!!! ይሄ ግፍ ነው!! ይሄ ሌብነት ነው!!!ይሄ ወራዳነት ነው!!! ታላላቅ የተባላችሁ ሰዎች ቀርባችሁ አስረዱ ሻሸመኔ አሁንም ለቅሶ ላይ ናቸው፡፡ ግማሹ ወደ ጠበል ግማሹ ወደ ሰው ቤት እየሄደ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን ያሉት የሚያውቁት ነገር የለም፡፡ዘመድኩን በቀለ ለምኗል በቴሌቪዥን ሲነገር ሰምተናል ያየነው ነገር የለም ብለዋል፡፡ እግዚአብሔር ይፍረድ!!! ዝም ብትሉ እኔ ዝም አልልም!!! ሦስት አካላትን በስም ጠርቼ እናገራለሁ፡-
- የጴጥሮሳውያን ኅብረት የምትባል በቀሲስ ሙሉቀን የምትመራ ኃይል፤ የመስከረም 4ቱን ሰልፍ የጠመዳችሁ፣ ሙሴ የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ባል እዚህ ውስጥ ለምን እንደገባህ አናውቅም አናውቅህም ውጣ !!! ቀሲስ ሙሉቀን የምትባል ከዚህ ሴራ ውጣ! እናንት የመስከረም አራቱን ሰልፍ ያጨናገፋችሁ…ከአቡነ ዮሴፍ ጋር ከሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ጋር ቢሮ ተሰጥቷችሁ የምትሸርቡትን ሴራ እግዚአብሔር ያፈርሰዋል!!! ጴጥሮሳውያን የሚባል አስመላሽ ኮሚቴ የመብት አስከባሪ ኮሚቴ የሚባል ነውረኛ!!! ቤተክርስቲያንን አሳልፎ የሚሰጥ፤ ሻጭ፣ አውደልዳይ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ዳንኤል ክብረት እንድትጽፍልኝ እንድትደውልልኝ አልፈልግም ተሸክመሃቸው ዙር!!! አሉላ ሰሎሞን እንድትጽፍልኝ እንድትደውልልኝ አልፈልግም ተሸክመሃቸው ዙር!!! ታደሰ ወርቁ እንድትጽፍልኝ እንድትደውልልኝ አልፈልግም ተሸክመሃቸው ዙር!!! ጴጥሮሳውያን ኅብረት የምትባል ግን እጅህን ከቤተክርስቲያን ላይ አንሳ!!!…ምድረ ሌባ ሁላ ዘራፊ ሁላ እንደቋመጣችሁ ይቀራል ማለት ነው፡፡


- አቶ አንተነህ አቢሲኒያ ባንክ የነበርከው…እዚህ ዐቢይ ኮሚቴ ውስጥ በየት በኩል መጥተህ እንደገባህ አናውቅም ውጣ! አቢሲኒያ ባንክ እዚያው የሠራህውን ግፍ እዚያው ጨርስ፡፡ ውጣ! አናውቅህም ውጣ!!!
- አቶ ፋንታሁን ሙጬ ዕድሜ ልክህን ቤተ ክርስቲያንን እንዳደማህ አትኑር ውጣ!!!…ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ ከሕዝብ የተሰበሰበውን ልብስ፤ንብረት ሸጥሽው? የት አደረሽው? ለጥቅምሽ አዋልሽው የት አገባሽው? ቤተ ክህነት ገብቶ ተቀምጧል የተቸገሩት ባሌ ነው ያሉት፤ የተቸገሩት አሩሲ ነው ያሉት ሞዴስ የላቸውም፡፡ ዳይፐር የላቸውም፡፡ በሽተኞች ናቸው፡፡ ህጻናቱ ብርድ ላይ ናቸው፡፡ አምባሳደር ፍጹም የኢትዮጵያ አምባሰደር በአሜሪካ የኢትዮጵያ አየር መንገድን አስፈቅደው ከቀረጥ ነጻ የገባውን ከፋንታሁን ሙጬ ጋር ተደራድረሽ ምንድነው ያደረግሽው? ወጥተሽ ለሕዝቡ አስረጂ! …ለሕዝቡ ይድረስ! ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ ችግር ካለ ችግሩን ተናገሪ!… ንብረቱ ኢትዮጵያ ከደረሰ ወር አለፈው፡፡ ችግረኞቹ አልደረሳቸውም፡፡ ምክንያቱ ምንድነው? ተናገሪ!…
የጴጥሮሳውያን ኅበረት የሚባል ተሞዳሟጅ የታከለ ኡማ አቃጣሪ የነበረ፤ በጥቅም ታስረው ቤተክርስቲያንን አሳልፎ የሰጠ፤ ፌክ ካህናት ሦስቱም ፤ቤተክርቲያንን አንገቷን እንድታቀረቅር ያደረጉ በዚህ ምክንያት ከመንግሥት ሹመኞች ጥቅማ ጥቅም የተሰጣቸው፤ የዘመኑ የቤተክህነት ሮናልዶዎች፤ ቅዱሳን ፓትርያርኮቹን ሊያለያዩ የተሾሙ የተቀመጡ፤ መርዞች፤ አንዴ እዚህ አንዴ እዚያ የሚያጫውቱ ተጠንቀቁ!!!…
40 ሚሊዮኑ ለባለጉዳተኞቹ ይድረስ…እኔ ኃላፊነት አለብኝ! አልቅሼ፣ አንቅልፍ አጥቼ፣ በጫካ፣ በመቃብር፣ በወንዝ በጀርመን ተንከራትቼ የለመንኩት ገንዘብ ነው፡፡ ይሄ ገንዘብ መንገድ ላይ እምዿ ቀሊጦ ብሎ እንዲቀር አልፈልግም!!!…ምሥራቅ ሐረርጌ አንድ ብር አልደረሳቸውም፡፡ ምዕራብ ሐረርጌ አንድ ብር አልደረሳቸውም፡፡ በቤተክርስቲያን ተጠልለው ያሉት የባንክ ቡክ ወጥቶላቸዋል፤ 37 ሚሊዮን ብር ወጥቷል የተባለው የት? ከየት? እንዴት? የእነማን? የለም!!! አልዋሽም !ምን አገባኝና ለየትኛው ዕድሜዬ ብዬ አልዋሽም፡፡ ታላላቅ ሰዎች እነ አቶ ትእዛዙ፣ እነ አቶ ብርሃን፣ እነ ወ/ሮ ኤልሳ የምትባሉ ተጠንቀቁ! ለራሳችሁ ስም ስትሉ ተጠንቀቁ!!! እውነት እንዲሠራ ግፉ!!! በዚህ ዓይነት አይደለም መዓት፤ አይደለም መቅሰፍት ሌላም ይገባን ነበር!…
ጴጥሮሳውያን የሚባል ማንም አይደለም…ጴጥሮሳውያን ውስጥ ያሉ በሙሉ የማኅበረ ቅዱሳን ልጆች ናቸው…ድጋሜ እናገራለሁ አሉላ ጥላሁን ወዳጄ ነህ፤ ወንድሜነህ እንዳትደውልልኝ!!! በሕዝብ ሁሉ ፊት ነው የምነግርህ እንዳትደውልልኝ! ስትደውልልኝ ደግሞ ያበጠ ነገር ይፈነዳል! ታደሰ ወርቁ ተሳስተህ እንዳትደውል! ስልክህን የማላነሳው ስለመላናግርህ ነው፡፡ሰለማልፈልግህ ነው፡፡ ጴጥሮሳውያን ኅብረቶች ነን የምትሉ በሙሉ ማለት ነው እንዳትደውሉ፡፡ አልፈልግም የማንንም መስማት አልፈልግም!!!… አንድ ሰው ስለ ጴጥሮሳውያን ኅብረት ቢያወራኝ አይመለከተኝም፡፡ ብሎክ ነው የማደርገው!!! ባለፈው ሽማግሌዎች ደውላችሁ ነው ያስቆማችሁኝ፡፡ ዳንኤል ክብረት እሪ ብለህ ነው ያስቆምከኝ፡፡ እነዚህ ነውረኞች!!! ባክህ ተዋቸው ዘመዴ ብለህ፡፡ የምተውበት ምክንያት ለካስ ለሌላ ጉዳይ ነው!!!…አንኗኗራትም ወይ ቤተክርስቲያኒቷ፤ ወይ እናንተ፤ ወይ እኛ አብረን እንጠፋታለን!!! እንዲሁ ተከድኖ ይብሰል የሚባል ነገር የለም፡፡ ፋንታሁን ሙጬ በፈጠረህ አምላክ ቤተክርስቲያኒቷን ዘላለም ስታደማት አትኑር! ከወ/ሮ እጅጋየሁ ጋር ሆነህ ስታደማት ኖርክ፤ ከነ በጋሻው ጋር ሆነህ ስታደማት ኖርክ፤ አሁን ደግሞ አታድማት ፋንታሁን ሙጬ በፈጠረህ አምላክ ተዋት! ተፋታት በቃ ቤተክርስቲያንን!!!
ፋንቱ ወልዴ.. የአሜሪካን ሕዝብ እኔ ነኝ የለመንኩት ፤ ክቡር አምባሰደሩን እኔ ነኝ የጠየኩት ቤተ ያሬድ ላይ ፤ መርካቶ ወስደሽ ሽጠሸውም ከሆነ ንገሪን፤ በየቀኑ እደውላለሁ አልደረሰንም ነው እያሉ ነው፡፡ ቤተ ክህነት ስደውል አለ ተቀምጧል እያሉኝ ነው፤ አረሳስታችሁ ልትሸጡት ነው፤ አዳዲስ ልብስ ነው፤ የሕጻናት ልብስ ነው፤ዳይፐር ነው፤ ሞዴስ ነው፤ ቤታቸው ንብረታቸው ተቃጥሎ ሜዳ ላይ ለወደቁት የአሜሪካ ሕዝብ የሰጠው ነው፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በነጻ ያስገባው ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ያለቀረጥ ያስገባው ነው፡፡ ክቡር አምባሳደሩን አቶ ፍጹምን እግዚአብሔር ይስጠው ረጅም ዕድሜ ይስጠው!!! የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኩራታችንን እግዚአብሔር ይስጠው!!! በጉምሩክ ላይ የሚሰሩትን እግዚአብሔር ይስጣቸው!!! ነገር ግን የእኛዎቹ ጉዶች ጉደኞች እናንተ መዓት ጠሪዎች የቤቱ ሸክሞች ሃይማኖት አሰዳቢዎች…መናጢ ሁላ፣ መናኛ ሁላ፣ተጠግተህ አንተ በደም ገንዘብ ልትከብር ትፈልጋለህ አፈር ብላ አትከብራትም…ሌቦች መዓተኞች የእናንተ መዓት ነው ይሄንን ሁላ የሚያመጣው…ለክሬ ነው የምሰራው ለማዕተቤ ነው የምሠራው ለየትኛው ዕድሜዬ ብዬ..
የቀረውን ከቪዲዮው ይከታተሉ
መስከረም 8 ቀን 2013 ዓ.ም