ዘመቻ ጌዲዎን 4

የተራቡና የማይጠግቡ ጅቦች በደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያን


በዛሬው ዘመቻ ጌድዎን ክፍል ላቅርብላችሁ የወደድኩት ጉዳይ በት.ኤር 19፡3 ላይ ‹‹…የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡-የሰማውን ሰው ጆሮ ጭው የሚያደርግ ክፉ ነገር እነሆ በዚህ ስፍራ አመጣለሁ፡፡›› እንዲል በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ላይ በደፋሮቹና እምነት አልባዎቹ የተራቡ ጅቦች መሪነት የደረሰው ግፍና የተቀነባበረው ሴራ ጆሮዬን ጭው ስላደረገውና ስላስደነገጠኝ እንዲሁም በአሁኑ ሰዓት ቅድስት ቤተክርስቲያን እየተጓዘች ያለችበትን የኋሊት ጉዞና የደረስንበትን የሃይማኖት፣የቀኖና የሕገ ቤተክርስቲያን ጥሰት እንዲሁም የሥነ ምግባርና የሞራል ዝቅጠትና ውድቀት ደረጃ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ በመሆኑ ማነህ ወዳጄ! የተኛህ ንቃ ለማለት ጽፌዋለሁ፡፡

ይህ ጽሑፍ ስድስት ንኡስ ርእሶች ማለትም

  • ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የነበራቸው ድርሻ
  • በሊቀ ጳጳስ አቡነ ሳዊሮስ የሚመራው ክንፍና በአቡነ ቴዎፍሎስ የሚመራው ቡድን
  • በደቡብ አፍሪካ የጆሐንስበርግ ቅድስት ሥላሴ ከሳሾች
  • በደቡብ አፍሪካ አጣሪ ሆነው ተመደበው ስለነበሩ ግለሰቦች ማንነት
  • ሐራ ዘተዋሕዶ በደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያንና በሊቀ ጳጳሱ ላይ ያደረገችው ዘመቻ
  • ማጠቃለያ

ያሉት ሲሆን በእርጋታ እንድታነቡ እጋብዛለሁ

መልካም ንባብ!!!

በየትኛውም የመገናኛ ብዙኃን፣የምስል ወድምጽ እንዲሁም የህትመት ሚዲያ ስለቤተክርስቲያን የተጻፉ ጽሑፎችን ከመከታተልና ከመመረጅ በላይ የሚያስደስተኝ ነገር የለም፡፡ ታዲያ ያሄ የያዘኝ አባዜ አንድ ቅዳሜ ላይ በብስለቱና በአስተዋይነቱ በሀገር ደረጃ አጅግ ከምናከብራቸው ታላላቅ ኢትዮጵያውያን ጋር በትጋትና በታማኝነት በመስራት የሚታወቀው ጋዜጠኛና ጸሐፊው ተረፈ ወርቁ(ዲ/ን) ግዮን መጽሔት ቅፅ 2 ቁጥር 64 ሐምሌ 2011 ዓ.ም  እና ቁጥር 61 ሰኔ 2011 ዓ.ም ‹‹የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በደቡብ አፍሪካ ከትናንትና እስከ ዛሬ›› በሚል ርእስ በሁለት እትሞች የዳበረ፣ ጥልቅና ብስል ጽሑፍ በደቡብ አፍሪካ ስላለችው የኢትዮጵያ ቤ/ክን በአግባቡ አስቃኝቶናል፡፡ የእኔ አእምሮ ደግሞ ጥያቄ ከመጠየቅ አይቦዝንምና ዲ/ን ተረፈ ወርቁ በዚህ ጊዜ ለምን ስለዚህ ርእሰ ጉዳይ ማንሳት ፈለገ? ሀገረ ስብከቱና ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ያዕቆብ አሁን በምን ሁኔታ ላይ ናቸው? …የሚሉና በርካታ ጥያቄዎች አእምሮዬን ያናውጡት ጀመር፡፡ አሳ ጎርጓሪ …እንደሚባለው ለካ ጉዳዩ ሌላ ነው….

  • ሊቀ ጳጳሱ በዘረኞችና በጥቅመኞች መረብ ተጠልፈው በተረፈ ይሁዳውያን ተሽጠው፣ ከአዲስ አበባ እንዳይወጡ ተደርጎ፤ የደቡብ አፍሪካን ቤተክርስቲያን በአሜሪካ እንደለመዱት የግል ንብረት (PRIVATE LIMITED COMPANY) ለማድረግ ባሰፈሰፉ አካላት፤ በእስትንፋሰ ዲያብሎሱ ታደሰ ወርቁ አርቃቂነትና ፀሐፊነት በተዘጋጀው ባለ 58 ገጽ ኢሰብአዊ ሪፖርት ፣ በተራቡ ጅቦች በአሥር አለቃ ፋንታሁን ሙጬ አቅራቢነት በአዲሱ አሳማ አብርሃም ገረመው ቃለ አቀባይነት፤በዲጄው አሉላ ብሎግ ለጣፊነት፣ በእነ አቡነ ሳዊሮስ ሴራ ጠንሳሽነት፣ እንዲሁም በቅርብ አባ ቶማስ በሚባሉ መነኩሴ ድብደባ የደረሰባቸው የረቀቀ ሴራ (Conspiracy Expert)  አቡነ ቴዎፍሎስ(በቀድሞው አባ ጽጌ ደገፋው) የግል ቤተክርስቲያን በየአህጉሩ የመያዝ ፍላጎት እንዲሁም በጥቃቅን ነፍሳት ተባባሪነት ሊቀ ጳጳሱ ሰው ስለሌላቸው ብቻበይፋ ከሚታወቁት የጳጳሳት ቡድን መካከል የአንዱም አባል በላመሆናቸው ምክንያት በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት እስከ ጥቅምት ሲኖዶስ ከኢትዮጵያ እንዳይወጡ መደረጉን ስሰማ ደግሞ ጉዳዩን በጥልቀት እንዳየውና ነገር አለ!…እንድል አደረገኝ ፡፡

ወደ ዋናው ጽሑፍ ከመግባቴ በፊት ለንጽጽር እንዲመች በ”ዜን” መጽሔት፣ ቅጽ 1 ቁጥር 3 ሰኔ 2002 ዓ/ም ‹‹ጅብ ( ዥብ)›› ተብሎ የወጣውን ጽሑፍ ማየት እኔ ሰለማስነብባችሁ የተራቡ የሰው ጅቦች ለመረዳት ይጠቅማልና እነሆ፡-

‹‹ጅብ የሚለው ቃል ዐዲስ አማርኛ መዝገበ ቃላት ሲፈታው ” የአውሬ ሥም የውሻ ፣ የድብ ፣ የተኩላ ፣ የቀበሮ ፣ ዓይነት … በማሽተት አውቆ ወገኖቹን የሚጠራ ፣ በደን የሚኖር የአህያ ጠላት ….” ይለዋል።…እንደሚታወቀው ጅብ ስጋ በል እንስሳ ነው። የሚበላው ሲያጣ ግን አትክልትና ፍራፍሬ ቢሆን ይቀማምሳል። በአደን ወቅት በብድንም በተናጠልም ያጠቃሉ ፤ በብዙ ተረቶቻችን ላይ ጅቦች ፈሪ ተደርገው ይሳላሉ ይህ የተሳሳተ ግምት ነው ጅብ የሚመገበው ምግብ እጥረት ካጋጠመው ከአንበሳም መንጋ ቢሆን አስጥለው ይመገባሉ።…ጅቦች ስሪያ ሚፈፅሙት በብድን ነው። አንዷን ሴት ጅብ እየተፈራረቁ ይሰርሯታል። ይህንን ለማድረግ ግን ጉልበተኛ ፣ ታጋይ ና ጠንካራ ካልሆነ አንድ ወንድ ጅብ እንዳማረው ይቀራል። ሴቷ ጅብ ለተገናኛት ሁሉ እርካታን የምትቸር ናት።…በድምፃቸው መልዕክት መለዋወጥ ሲችሉ ከዱር እንስሳት ከልብ ከት ከት ብሎ በመሳቅ ብቸኞቹ ናቸው። ጅብ 16 ሰዓት በትጋት ሲያድን ቆይቶ የተቀረውን ሰዓት ከሰው እይታ ከለል ብሎ ያርፋል።…››

እዚህ ላይ ሁለት ጉዳዮችን ልብ ብላችሁ እንድታነቡ ተማጽኖዬ ላቅርብ፡-

ጉዳይ 1፡- ጅብ የሚለው ቃል አነሱን አምባ መጠጊያ አድርገው ቤተክርስቲያንና ልጆቿን ለሚቦጠብጡ ለግል ጥቅማቸውና ብልጽግናቸው የሚሯሯጡ ሆዳሞች እንጂ ቅዱሳንና ብጹአን አባቶችን አይመለከትም፡፡

ጉዳይ 2፡- የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ያዕቆብ ብጹዕነታቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ የተፈጸመባቸውን ኢሰብአዊ፣የዘረኞችና የመንጋ ሴረኞች ርብርብ ካዳመጡ በኋላ ‹‹ በኀጢአት ከማንም አልበልጥም፤ በጽድቅም ከማንም አልበልጥም እኔ ሰው ነኝ! መድኃኔዓለም አይደለሁም፤ እኔ አሁን የምናገረው ስለ ደቡብ አፍሪካ ምደባ አይደለም፤ እኔ የቅዱስ ፓትያርኩን  እግር እያጠብኩ መኖር እችላለሁ፡፡ የተፈፀመብኝ ድርጊትም ይሁን ሪፖርቱ ኢ-ሰብአዊ ነው፡፡  ››  እንዳሉት ብፁዕነታቸው እንደ ማንኛውም ሰው አስተዳደራዊ ድክመት ሊታይባቸው ይችላል፡፡ ነገር ግን እንኳን በነፍስ ግድያ ሊጠረጠሩ ወደ ኋላ ሄጄ ግለ ታሪካቸውን ለማጥናት እንደሞከርኩት ‹‹ዜና ቤተክርስቲያን›› ሐምሌና ነሐሴ 1998 ዓ.ም ባሳተመው ጋዜጣ ላይ ብጹእነታቸው ገና በአዲስ አበባ እንደ ዛሬው በአጀብ የሚጓዙ ሰባክያን ባልነበሩበት ዘመን ከ25-45 ኪ.ሜ በእግራቸው እየተጓዙ በአዳሜ ቱሉ፣በጨፌ ጂላ፣ቡልቡላ፣ቡታ ጅራ እና የዝዋይ አጎራባች በታዎች ምዕመናን በተዋሕዶ እምነት እንዲጸኑ አደርገዋል ከዚህ በተጨማሪ በኢአማንያን በተከበቡ ሁለት ከተሞች የሰ/ትቤት የማደራጃ ኮርስ ሰጥተዋል፣ በርካታ ሰ/ት/ቤቶች አንዲቋቋሙ የአንበሳውን ድርሻ ተወጥተዋል፡፡ ባዶ እግራቸውንና በብስክሌት እየተጓዙ ስብከተ ወንጌል ያስፋፉ፤የዓውደ ምሕረት የወንጌል ት/ት ባልተስፋፋበት ጊዜ እንኳን ነፍሰ ገዳይና አስገዳይ ለሆነው ዲያብሎስ ጭንቅ የሆኑ፣ ልጅ አልባ፣ ጤናና ሰላም አልባ ለነበሩ ሰዎች መፍትሔ ከመሆን ውጪ እንደሌሎቹ የግል ሀብት፣ ንብረት(መኪና፣ፎቅ…) ምቾትና ድሎት ሳይፈልጉ ለሕዝብ የኖሩና የሚኖሩ ከአዋቂው ጋር እንደ አዋቂ፣ ከወጣቱ ጋር እንደ ወጣት፣ ከሕጻናት ጋር ዝቅ ብለው ለሰው እንጂ ለራሳቸው የማይኖሩ አባት መሆናቸውን ለረጅም አመታት የሚያውቋቸው የደቡብ አፍሪካ ምዕመናን ጭምር ለዚህ ምስክር መሆናቸውን ተረድቻለሁ፡፡ የእኔ ጽሑፍ ዓላማ ግን የእሳቸውን በጎ ሥራ እያነሱ ማሞጋገስ ሳይሆን ድክመቶቹን ሁሉ እሳቸው ላይ በመደፍደፍ በደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያን ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ምዕመኑ ያለ አባትና አጽናኝ እንዲኖር በምንም መልክ ከእርሳቸው ጋር የማይገናኙ ጉዳዮችን በማቀናጀት በእነ ሆድ አምላኩ የደረሰውን ግፍ በማሳየትና መፍትሔ ለማምጣት ነው፡፡

የኢትዮጵያውያን ኑሮ በደቡብ አፍሪካ

ደቡብ አፍሪካ በጣም መልካም፣በሥነ ምግባር የታነጹ ዜጎች ባለቤትና ለሚሠራና ለሚተጋ ሰው በልፋቱ መጠን ዋጋ የምትከፍል ሀገር ናት፡፡ ደቡብ አፍሪካ የሁሉም አፍሪካውያን እናት በመሆን ከዚህም በተጨማሪ ለያዥ ለገናዥ እጅግ ፈታኝ የሆኑ ወንበዴዎችንና ዘራፊዎችን ተሸክማ ሁሉንም በህግና በሥርዓት ለመመለስና ለማስተናገድ የምትጥር ሀገር ናት፡፡

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያውን በደቡብ አፍሪካ ምን ዓይነት የስጋት የጭንቀትና የፍርሃት ሕይወት ተጋፍጠው እየኖሩ እንዳለ ለመረዳት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ቴሌቭዝን(ኢቢሲ) የካቲት 11 ቀን 2011 ዓ.ም ‹‹ስደት፣ ተስፋ፣ ሞት…›› በማለት ያቀረበውን ዘጋቢ ፊልም ማየቱ በቂ ነው፡፡ በተለይ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ቀደሞም ቢሆን ከኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ጋር ተያይዞ ለቤት ኪራይና ለልጆች የትምህርት ቤት ክፍያ እንኳ ለመክፈል የሚቸገሩ በበዙበት፤ ሰሞኑን የተከሰተው አስደንጋጭና ልብን በኃዘን የሚሰብር ዜና በዚያ ላሉ ወገኖቻችን የበለጠ ሕይወትን ውስብስብ እንደሚያደርገው እሙን ነው፡፡ በደቡብ አፍሪካ ያሉ ምዕመናን ዕለት ዕለት ከሚገጥማቸውና ከሚደርስባቸው የውንብድና ተግባር ጋር በተያያዘ …እኔ ደግሞ መቼ ይሆን ተራዬ ደርሶ የምዘረፈው? የምደበደበው? ወደ ሀገሬስ የሚመለሰው አካሌ ወይስ በድኔ? እያሉ በጭንቀትና በሰቀቀን የሚኖሩ ቢሆኑም ብቸኛ አምባቸው፣ መጠጊያቸውና መጽናኛቸው ቅድሰት ቤተክርስቲያን ብቻ በመሆኗ እነሱ ይቸገራሉ እንጂ ቤተክርስቲያን ተቸግራ ማየት የማይፈልጉ ናቸው፡፡የአንዳንድ አድርባይ ቄሶችና በየመጠጥ ቤቱ የመንድር ሴት ይመስል ወሬና ተንኮል እየፈበረኩ ከሚያመሹ መሸተኞች በቀር በደቡብ አፍሪካ ሴቶቹ በጣም ምስጉን ትጉህ የሥራ ሰዎች ሲሆኑ በተለይ በtown ያሉ ወንዶች ግን በአብዛኛው መንደርተኛና ሀሜተኞች ናቸው ተብለው ይታማሉ ::የደቡብ አፍሪካ ምዕመናን ቅድስት ቤተክርስቲያን የሕልውናቸው መሠረት መሆኗን በአግባቡ የተገነዘቡ በመሆናቸው የቤተክርስቲያን አገልግሎት ከሚጓደል የቤተሰባቸውን ኑሮ መጓደል የሚመርጡ፤ በሸፍጥና በተንኮል ቤተክርስቲያንን ለሚበድሉ ደግሞ ልክ የሚያስገቡ ቆራጦች መሆናቸውን የኢትዮጵያ ቤ/ክን በተሐድሶ በተናወጠችበት ጊዜያት እንኳ የስላይድ ነጋዴው የእነ እስትንፋሰ ዲያብሎሱ ታደሰ ወርቁ ቧልትና ቀልድ ሳያስፈልጋቸው ጸረ-ማርያሞችንና ፖለቲከኞችን ተጋፍጠውና አሸንፈው ከዘመን ቀድመው በጽናት የቆሙ የተዋሕዶ የቁርጥ ቀን ልጆች ናቸው፡፡

ታዲያ ዘርፈ ብዙ ማኅበራዊና ኢከኖሚያዊ ችግር ያለበትን ምዕመን ቤተክርስቲያን እንኳ መጥቶ እንዳይጽናና ለግል ጥቅም ሲባል በሬ ወለደ ዓይነት ወሬ እየፈጠሩ የግል ጥቅምና ፍላጎትን የምዕመናንን ጉዳይ አድርጎ ማቅረብና በውጪ ያለችዋን ቤተክርስቲያን ሰላማዊ አገልግሎት መበጥበጥ መናፍቃንና አሕዛብ በቤተክርስቲያን እያደረሱ ካሉት ተጽእኖ ቢበልጥ እንጂ ያንሳል እንዴ? ከዚህ በላይስ ምን ግፍ አለ?

ለመሆኑ በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንና ምዕመናን ላይ እየደረሰ ላለው በደል እነማን ምን አስተዋጽኦ አላቸው?

  1. ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

በመሠረቱ ቅዱስነታቸው የደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያንን በወሬና በክስ ካልሆነ በስተቀር በተግባር አያውቋትም፡፡ጳጳሱን ለመከታተል እንዲያመቻቸው ናዝሬት ማርያም ከሰባት ዓመት በላይ አንዳች የልማት ሥራ ሳያከናውኑ ቀጥታ ወደ ደቡብ አፍሪካ የሄዱት ሰርጎ ገቡ፣ ተመሳስሎ ነዋሪና የንስሐ ልጆች ብር ስልቻ የሆኑት  የመንደራቸውን ሰው ያለ አቅማቸው በሥራ አስኪያጅነት ቢያስቀምጡም፤ የእነ አቡነ ሳዊሮስ ሴራና ውትወታ እንዳለ ሆኖ የቅዱስነታው ትልቁ ጉዳይ ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ያዕቆብ እንጂ የደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያን ወይም ምዕመናን እንዳይደሉ ከብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ በርካታ ምዕመናን የተረዱት ጉዳይ ነው፡፡ በርካታ ሰዎች ከሚፈጽሙት ተግባር በመነሳት እንዳለመታደል ሆኖ ቅዱስነታቸውን ቂመኛ ናቸው ይሏቸዋል፡፡ ለዚህም  በግልም ይሁን እንደ ተቋም(ደብር፣ገዳም…) ከደረሰባቸው ችግር ስለ ቂመኝነታቸው ብዙ ቢወራም እኔ ግን ሁለት የቅርብ ጊዜ ምሳሌዎችን ላሳይ፡-

ማሳያ 1፡-የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ባደረጉት ሰላማዊና ኮሌጁ የትምህርትና የምርምር ማዕከል ይሁን እንቅስቃሴና ሂደት ክብሬንና ሥልጣኔ ተጋፍተዋል በሚል ሰበብ ቂም ስለያዙባቸው የትኛውም ፓትርያርክ አድርጎት የማያውቀውንና መንፈሳዊ ኮሌጁ ከ900 በላይ ተማሪዎች ባስመረቀበት የ2011 ዓ.ም የምርቃት መርሐ ግብር ላይ ቂም ስለያዙ ብቻ አለመገኘታቸው እጅግ አሳፋሪ ተግባርና ከዚሁ ከቂመኛ ጠባያቸው የመነጨ እንደሆነ በርካቶች ከምርቃት በፊትና በኋላ ሲያወሩ ሰምቻለሁ! በዚህም የተበሳጩ በርካታ ተማሪዎች ከምርቃቱ በኋላ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ መኖሪያ ቤት ሄደው ይመርቁን ማለታቸው ሰምቻለሁ እነዚህንም ፎቶዎች አይቻለሁ፡፡

አንዳንዶች መደበኛ አገልጋዮች በመሆናቸው የቅዱስነታቸው በትር እንዳይወርድባቸው ፊታቸውን መሸፈን አስፈልጓል

ማሳያ 2፡- የቀድሞው ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ዲዮስቆርዮስ ጋር በተለያዩ ጊዜያት ተፈጥረው በነበሩት አለመግባበት ቂም ስለያዙ ልክ መውረዳቸውን ተከትለው እየጠዘጠዟቸው መሆኑን ራሳቸው አቡነ ዲዮስቆርዮስ በየጳጳሳቱ ቤት፣ በቤተክህነቱ የተለያ መምሪያዎች ከበተኑት ደብዳቤ በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡

ታዲያ ቅዱስነታቸው ገና የካቲት ላይ ተሹመው ግንቦት ላይ ባልዋሉበትና ባላደሩበት የተሳሳተ መረጃ ይዘው አቡነ ያዕቆብ በማኅበረ ቅዱሳን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ስለ ማኅበሩ ምስረታና የእሳቸውን አስተዋጽኦ መናገራቸውን ተከትሎ እሳቸው ማኅበረ ቅዱሳን ናቸው፣ እኔ ፓትርያርክ እንዳልሆን ጥረት አደርገዋል፣ ይንቀኛል፣ የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ደጋፊ…እና የመሳሰሉትን ተልካሻ ምክንያቶች አጠገባቸው ሁነው ገድለ ዲያብሎስ በሚጽፉና በረከሰ ማንነታቸውን አባቶችን በማጋጨት እራሳቸው የግጭቱ አጣሪ በመሆን በሚኖሩ ሆድ አደር ጅቦት ተሳስተው ባገኙት አጋጣሚ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ያዕቆብን መበቀል ይፈልጋሉ እየተባሉ መታማታቸው አልቀረም፡፡ በግንቦት የ2011 ቅዱስ ሲኖዶስ ላይም የደቡብ አፍሪካ ጉዳይ ሲነሳ የሐሰት ክስ መሆኑን እያወቁ በተመሳሳይ ወቅት ክስ ያለባችው ስድስት ሊቃነ ጳጳሳት ጉዳይ ምንም ትኩረት ሳይሰጡ ለይተው የብፁዕነታቸውን የሥራ ሞራል ለመንካት አስበው ‹‹እስከ ጥቅምት ሲኖዶስ ድረስ እዚሁ ኢትዮጵያ ይቆዩ››እንደገና ይጣራ..››. የሚለውን ሀሳብ ይዘው በጽኑ ሲሞግቱ የነበረ ሲሆን በዚህም ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት ከላይ ያነሳሁትን ሀሳብ በሚያጠናክር መልኩ በትዝብት ከመመልከት በላይ አንዳንዶች በይፋ ከብጹነታቸው ጋር የግል ችግር አልዎት እንዴ? ብለው እስከ መጠየቅ ደርሰዋል፡፡

በእኔ እምነት ግን ቅዱስነታቸው አቡነ ያዕቆብ ላይ የመረረ የጥላቻ አቋም አንዲኖራቸው ያደረጋቸውና በየጊዜው ከሚነሱ ከሳሾች ጋር ተባባሪ የሚሆኑበት ምክንያት አቡነ ጳውሎስ ላይ የነበራቸውን ቂም ለመወጣት ብቸኛና ቻይ ሆነው ያገኙት ሰው አቡነ ያዕቆብ ስለሆኑ ይመስለኛል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አንዳንድ ብጹአን አባቶች በጋራም በተናጥል ቅዱስነታቸውን ለምን አይተዋቸውም? ብለው በጠየቋቸው ሰዓት እሳቸው ማኅበረ ቅዱሳን ናቸው  ነበር መልሳቸው፡፡

ዙሮ ዙሮ ይህ አካሄድ ቤተክርስቲያንን የሚጎዳ በመሆኑ ሁለቱ አባቶች ገድለ ዲያብሎስ ጸሐፊዎችና ተርጓሚዎችን፣ነጭ ውሸት አውሪዎችንና ክፉ አማካሪዎችን ከአጠገባቸው አርቀው ከራሳቸው ክብርና ሥልጣን ይልቅ በዚህ ውዝግብ መካከል ነቢዩ በትን.ኤር23፡1‹‹የማሰማርያዬን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮውላቸው!›› እንዳለው ለምዕመናኑ ሲባል ተቀራርበው ቢወያዩ በቀላሉ መፍትሔ ይመጣል ባይ ነኝ፡፡

2. በሊቀ ጳጳስ አቡነ ሳዊሮስ የሚመራው ክንፍ

ከአቶሚክ ቦንብ በላይ አጥፊ ተግባራትን በሌሎች ሀገረ ስብከቶች ጣልቃ በመግባት በሥልጣን ዘመናቸው ያከናወኑትና ቅዱስ ሲኖዶስን በጸሐፊነት ሲያገለግሉ የቆዩት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሳዊሮስ ደቡብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ላይ ልባቸው ተተክሎ ከቀረ አራት ዓመታት በላይ አለፉ፡፡ ብጹዕነታቸው የዛሬ አራት አመት በፊት ችግር ተፈጠረ ተብሎ ቅዱስ ሲኖዶስ እሳቸውን፣ ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤልንና አባ ቃለ ጽድቅን ለአጣሪነት በመደበበት ወቅት የጆበርግና የፕሪቶሪያ ጮሌዎች አጣሪ ቡድኑ አንድ ከሆነ ተንኮላቸው ሊነቃባቸውና ሊጋለጥ መሆኑን ስለተረዱ የአቡነ ሳዊሮስን የንዋይ ፍቅር ካጠኑ በኋላ አበል በሚል ሰበብ ከአቡነ ሕዝቅኤል ደብቀው 17 ሺህ ራንድ እና መጠኑ ያልታወቀ ዶላር በፖስታ አድርገው በእጅ መንሻ መልክ ያበረክታሉ፡፡ ሌላው የሴራ ቡድን ደግሞ ወሬውን ከእነ መረጃው አቡነ ሕዝቅኤል ጆሮና እጅ ይደርሳል ብጹዕነታቸው ድርጊታቸው አሳፋሪ ከብጹዕነታቸው የማይጠበቅ በመሆኑ ሊወቅሷቸው ቢሞክሩም ለምን ነቁብኝ ብለው ተጣልተዋቸው ማጣራቱን ሳይፈጽሙ እጅ መንሻ የተቀበሉበትን የሀሰት ክሶች ሰብስበው ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ፡፡ አቡነ ሕዝቅኤልና አባ ቃለ ጽድቅ ማጣራቱን ፈጽመው ዘግይተው ተመለሱ፡፡ በዚህም የተነሳ እስከ ዛሬ ድረስ ሁለቱ ሊቃነ ጳጳሳት አይነጋገሩም፡፡ አቡነ ሳዊሮስም ከዚያች ጊዜ ጀምሮ በጸሐፊነታቸውና በቲም ዲዮስቆርዮስ የተሸፈነላቸውን የተመደቡበትን ሀገረ ስብከታቸውን ፈርጀ ብዙ ድክመትና ጉድለትና የካህናት በደል ወደ ጎን በመተው በደቡብ አፍሪካ ተመድቦ ለመስራት ብዙ ደክመዋል፡፡ለቤተክህነቱ የማይጠግቡ የተራቡ ጅቦች በርካታ መዋዕለ ንዋይ አፍሰዋል፡፡የመረጃ ምንጬቼ የሚያደርጉትን የስልክ ልውውጥ መነሻ በማድረግ ልክ እንደ አባ ጥዑመልሳን አዳነ ዋና እስኪሆኑ ድረስ ራሳቸውን ም/ሊቀጳጳስ አድርገዋል፡፡ቢሳካላቸውስ ኖሮ? ልክ እንደ ኢትዮጵያ ምዕመናን ደቡብ አፍሪካውያንን በሴራ መምራት ይቻል ይሆን? ደግሞ ሁሉንም ጉዳይ ትተነው አሁን እዚያስ ቢመደቡ እንዴት አድርገው ተግባብተው ሊሠሩ አስበው ይሆን? እንጃ! ግን አይታወቅም አስተርጓሚ ቀጥረው ይሰሩ ይሆናል!

ሊቀ ጳጳሱ አሁን ይረዱ አይረዱ አላውቅም እንጂ እስከ ቅርብ ጊዜ ለሀገረ ስብከትዎ እንዲህ መታወክ ተጠያቂው አቡነ ሳዊሮስ ናቸው ሲባሉ አረ በፍጹም ሊሆን አይችልም እሳቸው ለእኔ ተከራካሪ ናቸው ይሉ እንደነበር አንድ ወደጃቸው አጫውቶኛል፡፡ ዳሩ ብጹዕነታቸው ሁሉን አክባሪ እንጂ በማንም ግለሰብና ሀገረ ስበከት ጉዳይ ጣልቃ ገብተው እንደማያውቁ፣ በሲኖዶስ ስብሰባ ላይ እንኳ ወሳኝ ጉዳይ ካልሆነ በቀር ከመናገር መስማትን የሚመርጡ መሆናቸውን ከበርካታ ሊቃነ ጳጳሳት መረዳት ችያለሁ፡፡ በአሁኑ የግንቦት ስብሰባ ላይ አልተሳካም እንጂ ተሳክቶ አቡነ ያዕቆብ ከሀገረ ስብከታቸው ቢነሱ ኖሮ፤ አነስተኛ ደመወዝና መተዳደሪያ አጥተው በየአህጉረ ስብከቱ የሚንከራተቱ ሊቃውንት ባሉባት ቤተክርስቲያን ሌሎች በደብዳቤ ያልተሾመባቸውን የብር ማግበስበሻ ስልቶቹን ትቼ የትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት ሥራ አስኪያጅና የወለቴ  ማዕዶተ ዮርዳኖስ ቅዱስ ዮሐንስ እና አባ ኪሮስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪነትን ደርቦ ሁለት ደመወዝ ጠቅልሎ የሚበላውን መልአከ መዊዕ ሳሙኤል እሸቱ(ሳሚ ሮቶ) ቤተክህነቱ አከባቢ በደቡብ አፍሪካ ጉዳይ የሽብርና የፕሮፖጋንዳ ወሬን በመንዛት ውጤታማ የነበረውን  ሰሳመሚ ሮቶን ቢሳካ ኖሮ የደቡብ አፍሪካ ሥራ እስኪያጅ ለማድረግ በወሬና በተግባር በመንቀሳቀስ ብዙ ዋጋ ከፍለዋል፡፡

መልአከ መዊዕ ሳሙኤል እሸቱ(ሳሚ ሮቶ)

እነዚህ አካላት ከዚህ ሁሉ ጥልፍልፍ ሴራ አለመሳካት በኋላ ሳይመደቡና በማይመለከታቸው ጉዳይ ጅብ በቀደደው እንዲሉ… ወደ ፊት በዝርዝር የማቀርብላችሁ ሲሆን ሩዋንዳ ቤተክርስቲያን በጋራ ሄደው የፈጸሙት ነገር ለዚሁ የሴራ አብሮነት አንዱ ማሳያ ነው፡፡

የሴራ ቡድኑ አባላት በዩጋንዳ

ከአዲስ አበባው የአቡነ ሳዊሮስ ክንፍ ጋር ትስስር ያላቸው የደቡብ አፍሪካ ጁሐንስበርግና ፕሪቶሪያ ከሳሾች

ሀ. አቶ ገዛኸኝ አበበ

ይህ ግለሰብ የኮ/ል መንግሥቱ ኃ/ማርያም የእህት ልጅ ሲሆን ከአጎቱ ያልተናነሳ ግፍና በደል በመሥራት ላይ እያለ በድንገት የተከሰተውን የመንግሥት ለውጥ ተከትሎ መጀመሪያ ወደ ኬንያ የገባ ሲሆን ኬንያ በነበረበት ወቅት በስኳድነቱ በበርካታ ወንጀሎች እጁ የተጨማለቀና በኋላም የአንድ ወዳጁን የዙምባቡዌ ቪዛ ከፓስፖርቱ ላይ ገንጥሎ የራሱ ፓስፖርት ላይ በመለጠፍ በማጭበርበር ወደ ቤ/ክን በመጠለያነት ገብቶ ነፍሱን ካዳነ በኋላ የራሱን ስራ ወደ ሌላ ማላከክ እይዘዋለሁ ብሎ እስቦ የነበረውን የመንግሥት ከፍተኛ ሥልጣን በለውጡ ምክንያት በማጣቱ ጅብ በማያውቁት ሀገር….እንዲሉ ራሱን ንስሐ የገባ በማስመሰል ኢትዮጵያ ላይ ያለውን የሥልጣን ጥማት ለማሳካት ምቹ አውድ ሆና የታየችው ቤ/ክን ስለሆነች በውስጡ የተቀበረውን ወያኔን ያለማሸነፍ ንዴት ቤተክርስቲያን ላይ ማፍሰስ አለበት እንዴ? ይሄ መታረም ያለበት ነው፡፡ ደግሞም ያስጠለለችውን ቤ/ክን ውለታ ረስቶ በአባቶችና በአገልጋዮች ላይ ሁከትና ያለመረጋጋት በመፍጠር መኖር ነውር ከመሆኑም በላይ እጅግ አሳፋሪ ድርጊት ነው፡፡ ደግሞስ ጀግና ከሆነ ወያኔ ሲያበረው የት ነበር? ስኳዱ ገዛኸኝ ብዙም ያልዳበረችውንና በቂ ገቢ ያላመጣችለትን የሒሳብ መዝገብ አያያዝ(አካውንቲንግ) ትምህርት መነሻ በማድረግ የሀገረ ስብከቱ እና የፕሪቶሪያ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ሒሳብ ሹም እስከ መሆን የደረሰ ይሁዳዊ ሥልጣን አግኝቶ ነበር፡፡ በኋላ ላይ የሀገረ ስብከቱ ሥራአስኪያጅ የነበሩት ፕ/ር ዘሪሁን የፕሪቶሪያ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረትን ሒሳብ ለሳርስ(SARS) መቅረብ ስላለበት ይመርመር ሲባል ከዚያ ግዜ ጀምሮ ረብሻና ብጥብጥ እንደጀመረ አንድ እውነተኛ የማቅ አባል የሆነ ወዳጄ አጫውቶኛል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ  በወቅቱ የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳዳሪ የነበሩትን ቆሞስ አባ ገ/ሥላሴ መርሻ የነበራቸው ጽኑ ቤተክርስቲያናዊ አቋም ስላልተመቸው ያለውን ወታደራዊ ልምድ በመጠቀም የአንድ ቄስ ሚስት የሆነችውን ሴት በማግባባት ዘመናዊ ካሜራ አዘጋጅቶ ገብታ እሳቸው ቤት ሊደፍሩኝ ነው ብላ እንድትጮኸ፤ በቤተክርስቲያኑ ዙሪያ ደግሞ ፖሊስ አዘጋጅቶ ዲፖርት ለማድረግ ዝግጅት በማድረግ የግፍ ድራማውን ሊሰራ ሲሉ ለቤተክርስቲያን ቢሰራ፣ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ ቢያወራ የማየይሰለቸውና የማይደክመው ደቡብ አፍሪካዊ ቄስ ቶምሰን(ተ/ሚካኤል) ጉዳዩን በቅርበት ይከታተል ስለነበረ በወቅቱ ለዓለም ሃይማኖቶች ምክር ቤት ጉባኤ ለንደን ከነበሩት ከብጹዕ አቡነ ያዕቆብ ጋር በስልክ በመነጋገር መነኩሴውን ዲፖርት ከመደረግ ያተርፏቸዋል፡፡ በኋላ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ዳኛው ለመሆኑ ድርጊቱ የተፈጸመው የት ቦታ? ብሎ ጠየቅ ለከሳሾችና ለኦፐሬሽኑ መሪ አቶ ገዛኸኝ አስደንጭ ጥያቄ ነበር፡፡ ዳኛው መልሱን መነሻ በማድረግ ወደ እሳቸው ቤት የሄደችው እሳ ከሆነች መነኩሴውን መጠየቅ አንችልም በማለት እኩይ ዕቅዳቸውን ሁሉ አከሸፈባቸው፡፡ በነገራችን ላይ ይሄ ተልእኮ  ተሳክቶ ቢሆን ሁለት ግብ ነበረው አንደኛ አባን ገ/ሥላሴን አባሮ ያለምንም ተቀናቃኝ ቦታውን መቆጣጠር ሁለተኛው ደግሞ እንድትጮኸ የታዘዘችው መሪ ተዋናይ የሚያስቸግራቸው ቄስ ሚስት ስለነበረች ሥልጣንህ ፈርሷል ብሎ ማሳደድ ነበር፡፡

አቶ ገዘኸኝ እነ ሙጬ(ጅቦ) ‹‹ለማጣራት›› ደ/አፍሪካ በነበሩበት ወቅት ማታ ማታ በተከታታይ አንዳንዴ ከአቡነ ሳዊሮስ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከአቡነ ቴዎፍሎስ ጋር ያደርጉት በነበረው የስልክ ኮንፈረንስ ላይ ለመገኘት ዘወትር ማታ ማታ በድብቅ ወደ ጆበርግ ሥላሴ ይጓዝ እንደነበረ ከቦታው የደረሰኝ መረጃ ያረጋግጣል፡፡

እንግዲህ ምዕመናን የአዲስ አበባ አብያተክርስቲያናት በሰንበት ተማሪዎችና በምዕመናን ጥረት ከጡረተኛና በተለይ አምባገነን ከሆኑ ማርክሲስት የወታደር ቤት የሰበካ ጉባኤ አባላት ነጻ በመውጣት ላይ እንዳለች የደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያንም ንስሐ በገቡ በቅዱስ ቁርባን በተወሰኑ ከአድሎአዊነት በጸዱ የሰበካ ጉባኤ አባላት የመመራት እድል እንዲገጥማት ምኞቴ ነው፡፡

 ለ. ‹‹ዲ/ን›› ንዋይ ገሠሠ

ንዋይ ወደ ደቡብ አፍሪካ ከመምጣቱ በፊት የUN የሱዳን ቡድን ውስጥ የነበረ የጤና መኮንንና በማቅ ስም ከሚነግዱ ጥቂት መሥራች አባላት መካከል አንዱ ነው፡፡ በተለይ እሱ ያለበት የፕሪቶሪያ ሐመረ ኖኅ ኪዳነምሕረት እሱ ከመምጣቱ በፊት ምንም ዓይነት ኮሽታ የማይሰማባትና የተረጋጋ አገልግሎት የሚፈጸምባት ቦታ ሁና ቆይታለች፡፡ ንዋይን የሚያውቁት ሰዎች የውሃ ውስጥ አረንጓዴ እባብ ነው ይሉታል፡፡ ንዋይ ሰበካ ጉባኤ በነበረበት ዘመን ከ9 ወር የሙዳየ ምጽዋት ቆጠራ የተገኘው አጠቃላይ ገንዘብ 35 ሺህ ራንድ ብቻ ነበር፡፡ የዚህ ትልቁ ምክንያት ደግሞ አሜሪካ የሚገኙት የግብር አጋሮቹ እንደሚያደርጉት ለገጠሪቱ አብያተክርስቲያን፣ አድባራትና ገዳማት መርጃ የሚሆን አሥራት እየተቀበሉ ዋጥ ስልቅጥ ማድረግ ነው፡፡ በዚህ ምክንያትም የፕሪቶሪያ ቤተክርስቲያን ራሷን መቻል አቅቷት ከሀገረ ስበከቱ ድጎማ እስከ መደረግ ደረሳለች፡፡

ሐራውያን በሊቀ ጳጳሱና በደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያን ላይ እንዲጽፉና እንዲሳደቡ ከ3ሺህ ዶላር ያላነሰ አሰባስቦ ለዲጄው ለአሉላ የከፈለ ይሄው ግልሰብ ነው፡፡ ይሄ ብር እንግዲህ የእነ አባ አእምሮን ክፍያ ሳይጨምር ነው፡፡ ንዋይ ከሚስቱ በኩል በየጊዜው የሚደርስበትን ቁጣና ድብደባ የሚመወጣው ቤተክርስቲያን ላይ ነው(ፕሮጄክሽን መሆኑ ነው)፡፡ በነገራችን ላይ ሚስቱ አባ ጥዑመልሳን አዳነን በጣም ስላናደዳት በአደባበይ በጥፊ የላሰች ወለተ ሄሮዳድያ ናት፡፡

ንዋይ የደቡብ አፍሪካው ነውጥ አልበቃው ብሎ የአምባሳደር አለምፀሐይ መሠረትን የዩጋንዳ ሹመት ተከትሎ ቢሄድም እዚያ ያለው ምዕመንና ካህን አንድ በመሆኑ ያቀደው እኩይ ዓላማ ሳይሳካለት አፍሮ ተመልሷል(ፕሪቶሪያዎች አንድ ሰሞን ጠፍቶባችሁ የነበረው ለዚህ ነው) ፡፡ አዲስ አበባ የሚኖር አንድ የሁለታችን ወደጅ እንዳረጋገጠልኝ ጊዜ እየጠበቀ የሚነሳ መጠነኛ የአእምሮ ቀውስ እንዳለበት ነግሮኛል፡፡ ምህረቱን እንዲልክለት ምኞቴ ነው፡፡

3. በደቡብ አፍሪካ የጆሐንስበርግ ቅድስት ሥላሴ ከሳሾች

የሊቀ ጳጳስ አቡነ ያዕቆብ ዋና ከሳሾች የሆኑት አስተዳድረዋቸው የማያውቁትና የማያውቋቸው በስደተኛው ሲኖዶስ ‹‹ሥር›› በስም እንጂ በተግባር ያልነበሩ አካላት ናቸው፡፡ በእኔ እምነት ይህ ክስ ኢፍትሐዊ(አድሎአዊ) የሚሆንበት ትልቁ ምክንያት ብጹእነታቸውን መክሰስ የሚችሉት ካወቁዋቸውና ከእነሱ ጋር ከሰሩ በኋላ ነበር፡፡ ባልዋሉበት ባላደሩበት ባላስተዳደሩት እንዴት ተጠያቂ ሊሆኑ ቻሉ? ይሄ እኮ ማለት በሱዳን አስተዳደራዊ ጉዳይ የኢትዮጵያን መንግሥት እንደመጠየቅ ያለ ነው፡፡

በነገራችን ላይ የሁለቱ ሲኖዶሶች አንድነት አብዛኛው የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች ቢያስደስትም የጆሐንስበርግ ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክንን የግል ንብረት አድርገው ለሚተዳደሩት ለእነ አባ አእምሮ ታከለ፣ ለእነ መቶ አለቃ ንብረትና ግብረ አበሮቻቸው አስደንጋጭ መርዶና ባልተዘጋጁበት ወቅት የመጣ ትልቅ ዱብዕዳ  ነው ምክንያቱስ? ቢባል ቤተክርስቲያኑ ወደ ህጋዊ አካሄድ ገባ ማለት ጉሮሮአቸው ተዘጋ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ መከፈል ያለበት ዋጋ ሁሉ ተከፍሎ ቤ/ክኑ የግል ንብረት እንደሆነ መቆየት አለበት፡፡

 የጆሐንስበርግ ቅድስት ሥላሴ ካቴደራል የማን ነው?መሪዎቹስ እነማን ናቸው?

ይህ ካቴደራል በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሥር ያለ ተብሎ ለስሙ ይጠራ እንጂ በቅዱስነታቸው ጨርሶ የማይታወቅ በአብዛኛው የአንድ ዘር ስብስብ የተያዘ የግል ይዞታ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ይህ ቤ/ክን አስራት በኩራት፣ፈሰስ፣ሰበካ ጉባኤ ጨርሶ የሚሉት ቃላት ላለፉት በርካታ አመታት ተሰምተው አይታወቁበትም፡፡ ቤ/ክኑን  በግል ንብረትነት የያዙትና በግል እያስፈራሩ የሚኖረው በኢትዮጵያ ምድር የተወለዱ ደራጎኖች እነ መቶ አለቃ ንብረት ጌታነህ እና ከ6 ዓመታት በላይ ሊቀመንበር የሆነው አቶ ገበየሁ ባሕሩ ናቸው፡፡ አባ አእምሮ ደግሞ ኢትዮጵያ ሳለ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስቀጥራችኋለሁ እያለ የስንቱን ምስኪን ካህንና አገልጋይ ቤት፣ ከብትና ንብረት አሽጦ በድንበር በኩል ወደ ደቡብ አፍሪካ ከገባ በኋላ ለእነ ንብረት ምቹ የዲያብሎስ ፈረስ ሆኖ ስላገኙት በአግባቡ እየተጠቀሙበት ይገኛል፡፡ የጆሐንስበርግ ቅድስት ሥላሴ ካቴደራል የሚመሩ ሰዎች የቆሸሸ ስብእና እንመልከት፡-

ሀ. አባ አእምሮ ታከለ

በተለይ የዩቲዩቡን ቃለ ምልልስ ጊዜ ኖሮአችሁ ብታደምጡ ሰለ ሰውዬው የበለጠ ትረዳላችሁ

እኚህን ‹‹መነኩሴ›› የማውቃቸው ገና መርካቶ ራጉኤል ስብከተ ወንጌል ውስጥ እያሉ ነበር፡፡ ከዚያም በፋንታሁን ሙጬ የሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ዘመን የላፍቶ ሚካኤል አስተዳዳሪ ሆነው ይሾማሉ፡፡ ያው አዲስ አበባ ላይ ለመሾም የመጀመሪያ መስፍረት ብር(አሁን ካልጨመረ ለአስተዳደሪነት 100ሺህ-200ሺህ) ሁለተኛው ደግሞ  አፈ ቀላጤ መሆን ብቻ ነው፡፡ እዚህ ላይ ልብ እንድትሉልኝ የምፈልገው አንዳንዶች ሙጬና አባ አእምሮ ዝምድና አላቸው ይላሉ እነ የማውቀው ግን አባ እእምሮን ያሾማቸው ዘራቸው ወይም የቤ/ክን ዕውቀታቸው ሳይሆን ብራቸው፣ የመክፈል አቅማቸው ብቻ ነው፡፡ አንዳንዶች አባ አእምሮን በሰራው እኩይ ተግባር ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ መመለስ እንደማይችል ይገልጻሉ፡፡ ምንም እንኳን ዛሬ ከባለቤት አልባው ቤ/ክን በገፍ በተዘረፈው ገንዘብ ቢወዳጁም እጅና ጓንት ቢሆኑም የትላንቶቹ ደጀ ሰላማውያን የዛሬዎቹ ሐራዎች ከዚህ በፊት በደጀ ሰላም ብሎጋቸው ጁን 23፣ 2012 በሙስና የሚታሙት የላፍቶ ደ/ትጉሃን ቅ/ሚካኤል አስተዳዳሪ አባ አእምሮ ታከለ የአ/አ ሀ/ስብከት ም/ሥ አስኪያጅ ኾና ተሾሙ›› በሚለው ርእሰ አንቀጽ ሥር

‹‹ላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተዘዋውረው በአስተዳዳሪነት ከተሾሙ ሁለት ዓመታትን ብቻ ነው ያስቆጠሩት – አባ አእምሮ ታከለ ፡፡ በሁለት ዓመት የደብሩ ቆይታቸው ግን ካራታቸው በመዝገብ ላይ ያልሰፈረ የወርቅ እና የውጭ ምንዛሬ ስርቆትን ጨምሮ ለተፈጸሙ ሕገ ወጥ የነዋየ ቅድሳት ሽያጭ እና የሙዳይ ምጽዋት ቆጠራ እንዲሁም ያለ ደረሰኝ ገቢ የመሰብሰብ ድርጊቶች ዋነኛ ተጠያቂ መኾናቸው በሰፊው ይነገራል። በደብሩ የአንድ ወገን የጎጠኝነት አስተሳሰብ እንዲስፋፋና ሌሎች በርካታ አስተዳደራዊ ችግሮችም እንዲከሠቱ ምክንያት የመኾናቸው ጉዳይ አደባባይ የወጣ ምስጢር መኾኑን ብዙዎች ይመሰክራሉ። በድንገት ተነሥተው ከሄዱበት ገዳም በጣም በአጭር ጊዜ ውስጥ ምንኩስና ከተቀበሉ በኋላ ብዙም ሳይቆዩ የላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ የኾኑት አባ አእምሮ÷ ይህን ሹመት ለማግኘት ለቀድሞዎቹ የሀ/ስብከቱ አስተዳደር ሓላፊዎች እስከ 2ዐ ሺሕ ብር ገደማ መማለጃ መስጠታቸው ተጠቁሟል፡፡ አባ አእምሮን በቅርበት የሚያውቋቸው ሰዎች ሰውዬው ገንዘብ አምላኩቤት ለመሥራትና መኪና ለመግዛት የሚቋምጡ፣ የመጠጥ ሱስ እና ከምንኩስና ሕይወት ይኹን ከጥሩ ምእመን ጋራ የማይጣጣሙ እኵይ ጠባዕያትን የተላበሱ ስለመኾናቸው ይመሰክሩባቸዋል፡፡…››

እንግዲህ አባ አእምሮ በላፍቶ ሚካኤል በደብሩ በታሪክ ተሠርቶ ታይቶ የማይታወቅ ትልቅ ውንብድና ከሰሩ በኋላ ባልታወቀ ሁኔታ(በእኔ እምነት ምናልባት በዘረፋና በተንኮል ሊቅነታቸው ሊሆን ይችላል)  ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ም/ሥራ አስኪያጅ ሁነው ይሾማሉ፡፡

ይህ ሰዓት ደግሞ አስር አለቃ ፋንታሁን ሙጬ በቅዱስ ሲኖዶስ ወሳኔ መሠረት ይከሰስ የተባለበት ጊዜ ነበር፡፡ የትላንቶቹ ደጀ ሰላማውያን የዛሬዎቹ ሐራዎች ከዚህ በፊት በደጀ ሰላም ብሎጋቸው በNov 2010 << የሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ ሹመት እያነጋገረ ነው >> በሚል ርእስ ሥር

‹‹የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን በተመለከተ በቅዱስ ሲኖዶስ የተሠየመው አጣሪ ኮሚቴ ለጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ባቀረበው ሪፖርት እንዲሁም በ29ው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ስብሰባ ላይ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሪፖርት ውስጥ ተካትቶ በቀረበው የቁጥጥር አገልግሎት ሪፖርት ቃለ ዓዋዲውን ተከትሎ ከመሥራት እና መልካም አስተዳደርን ከማስፈን አኳያ በተገኘባቸው ከፍተኛ ግድፈት የተነሣ ከሥራ አስኪያጅነት ሐላፊነታቸው እንዲወገዱ፣ የፈጸሟቸው በደሎች ሁሉ ተጣርቶ በሕግ እንዲጠየቁ የተወሰነባቸው ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ማዕርግ የልማት ጉዳዮች ዘርፍ ሥራ አስኪያጅ ሆነው መሾማቸው ጥያቄዎችን እያስነሣ ይገኛል፤ በቤተ ክርስቲያኒቱ ወቅታዊ ችግሮች ዙሪያ በምእመኑ ዘንድ አንድ አቋም እና ግንዛቤ እየተፈጠረ የመጣበትን አትኩሮት ለማስቀየስ የሚደረግ ጥረት አካል ተደርጎም ተወስዷል፡፡›› ሙሉውን ከብሎጉ ያንብቡ!

እዚህም ላይ ታዲያ ጮሌው አባ አእምሮ ትልቅ ውለታ ሠራለት፡፡ ሙጬን ከሳሽ መሆን የሚችለው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ነበር፡፡ የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ አጀንዳውን ይዞ በሚነጋገርበት ጊዜ አባ አእምሮ ይሄ ክስ እኮ ሙጬን ብቻ አይመለከትም ሁሉንም የአስተዳደር አካላት የሚመለከት ነው ብንተወው ይሻላል ብሎ በማስፈራሪያ ጭምር ይናገራል፡፡ በዘረፋው ላይ የተነካኩት አብዛኛው የአስተዳደር ጉባኤ አባላት ያላዩትን ነገር ስላሳያቸው በማመስገን የውሾን ነገር ያነሳ…ብለው ተማምለው የአጀንዳውን ግብአተ መሬት አከናወኑ፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አባ አእምሮና ሙጬ በፍቅርና በጥቅም ትስስር ከነፉ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ፋንታሁን ሙጬ አባ አእምሮን በማንኛውም ጉዳይ መተባበር ግዴታው ነው፡፡ ለዚህም ይመስላል በእነ አቡነ ሳዊሮስ የደቡብ አፍሪካ ጉዳይ ከግብ እንዲያደርስ ሙጬ የተመረጠው፡፡ የቤተክርስቲያን ራስ ክርስቶስ ግን ተንኮላቸውንና ሴራቸውን በሙሉ አከሸፈባቸው፡፡ በነገራችን ላይ አባ አእምሮ ከሊቀ ጳጳስ አባ ያዕቆብ ጋር ምንም ዓይነት ጠብም ይሁን ንግግር የላቸውም አያዉቃቸውም፡፡ በቃ ወደ ካናዳ እና አሜሪካ ለመሸጋገር ከፍተኛ ምኞትና ህልም እንዲሳካ ከፈለጉ ለአቡነ ቴዎፍሎስ ይህን ሴራ በስኬት መውጣት እንዳለባቸው መመሪያ ስለተሰጣቸው ነው፡፡

ለ. አቶ ገበየሁ ባሕሩ

ይህ ግለሰብ ‹‹የሰበካ ጉባኤው›› ሊቀመንበር ከሆነ ወደ አስር አመታት ሊጠጋው የደረሰ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ከቤተክርስቲያኒቱ በዘረፈው ገንዘብ የሁለት ግሮሰሪ ባለቤት ሁናል፡፡ኢትዮጵያ ላይ ደግሞ ፎቅ በማስገንባት ላይ ነው፡፡በጭራሽ ሕጋዊ አሠራር በቤተክርስቲኒቱ እንዳይኖር የሚፈለገው ይህ ግለሰብ ያለ ማኅበረ ምዕመናኑ ጥቆማና ፈቃድ ለእኩይ ተግባሩ የሚመቹትን ሰዎች (ሄኖክና የሺን) በደብዳቤ ጥሪ የሰበካ ጉባኤ አካል እንዳሉ ለማስመሰል ምዕመናኑን እያታለለ ይገኛል፡፡

ሐ. መቶ አለቃ ንብረት ጌታነህ

ይህ ግለሰብ የሥላሴ ቤተክርስቲያን ካዝና(ባንክ ቤት) ሲሆን የትኛው ገቢ ይሁን ወጪ በእርሱ በኩል ካላለፈ ሊበላህ ይደርሳል፡፡ በሽጉጥ ያስፈራራሃል ያሳድድሃል ብቻ ምን አለፋችሁ ገንዘብ ከፈለክ ለእሱ መገዛት ብቻ ነው ምርጫህ፡፡ 45 ሺሕ ራንድ ይከራይ የነበረውን ሕንጻ በተቆጣጣሪነት በንጽሕና ያገለግል የነበረውን አቶ ሕሊና ለገሰ አላስበላ ብሎ ስላስቸገረው ብቻ ካባረረ በኋላ የዚህን ኪራይ ብር እየተቀበለ አከፋፋይ የነበረው ይኸው ሰው ነው፡፡ በነገራችን ላይ ብሩን በልተው በልተው ግራ ሲገባቸው አጣሪዎች ወደ ደቡብ አፍሪካ በመጡ ወቅት ከነ ሙጬ ጋር ይመካከሩና አባ አእምሮ አንድ ነገር በዓውደ ምሕረት ላይ እንዲናገሩ ያደርጋሉ ‹‹… የዚህ ሕንጻ ተከራዮች ገቢ የለንም እያሉ ነው፤ ለአንድ ኢትዮጵያዊ ተከራይ ሰጥተነው 20 ሺህም ያግኝ 10ሺህ ለቤ/ክኑ እኩል ያካፍላል…›› እያሉ ሲናገሩ ሕንጻውን በእጅ አዙር ሸጠው ወደ አሜሪካ ለመጓዝ አስበው መሆኑን የነቁት በተለይ ማኅበረ ተክለ ሃይማኖቶች ‹‹…እርስዎ ሰውዬ በጣም ተንኮለኛና ክፉ ሰው ነዎት፣እኛ ከእርሶ ጋር አንኖርም…››ብለው ስላስደነገጧቸው ቆሌያቸው ተገፈው ነው ያሉት፡፡ በእነ መቶ አለቃ ንብረት እየሰለጠኑ ያሉት ታዳጊ በዝባዦች እነ ነጻነት፣ ዳኜ የመሳሰሉት ወጣቶች ከቤተክርስቲያኒቱ ብር እየተሰጣቸው የፈለጉትን ይመልሳሉ ያልፈለጉትን ያስቀራሉ፡፡ ምን አለፋችሁ የቤተክርስቲያኒቱን ብር መነገጃ አድርገውታል፡፡ አሁን በቅርብ ጊዜ ከታምሩ አበበ ጋር ለክሱ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ እንኳ ወጪያቸው ሙሉ ለሙሉ የተሸፈነው ከቤተክርስቲያን ወጪ ተደርጎ ነው፡፡ ይህንን እዚያ ካሉ አገልጋዮች ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

መ. አቶ ታምሩ አበበ

አቶ ታምሩ ተቃዋሚ መስሎ የኖረና እሱ ባለበት አካባቢ ባለ የፖለቲካ ቡድን ሰብሳቢ ቢሆንም ራሱን የደቡብ አፍሪካ የኮሚኒዩቲ ሰብሳቢ አድርጎ የሾመ፣ምንም አይነት መተዳደሪያ የሌለው ከእነ ንብረት ወርሃዊ ክፍያ እየተከፈለው የሚኖር እግዚአብሔር የሰጠውን የንስሐ ዕድሜ በአግባቡ መጠቀም ያልቻለ ከንቱ ሰው ነው፡፡ ይህ ግለሰብ ትክክለኛው የደቡብ አፍሪካ የኮሚኒቲ ሰብሳቢ ፕ/ር ሙላቱ ፍቃዱ መሆኑን ቢያውቅም የቤተክርስቲን ጠላቶችን ሐራውያን እነ አሉላን ተጠቅሞ በተረቀቀለት ማታለያ የኮሚኒዩቲ ደብዳቤ ላይ የፈረመ ነው፡፡

በመሠረቱ ማንም ሰው የትኛውንም የፖለቲካ አቋም መያዝ መከተል መብቱ ነው፡፡ ቤ/ክንንና ምዕመናን ግን ለፖለቲካ እኩይ ዓላማ መጠቀሚያ ለማድረግ መሞከር ያረጀ ያፈጀ አካሄድ ነው፡፡ አቶ ታምሩ የደቡብ አፍሪካ ምዕመናን እንደሚያውቁት ምንም እንኳን እነ ንብረት  እንደ መደበኛ አገልጋይ ደመወዝ ቢከፍሉትም በተደጋጋሚ ቤተሰቡን ማስተዳደር ልጆቹን ማስተማር ባለመቻሉ እየተለመነለት እንደሚኖር አገር ያወቀው ፀሐይ የሚቀው ጉዳይ ነው፡፡ አቶ ታምሩ የተሾመበት ሴራ በመክሸፉ ወደ ደቡብ አፍሪካ መመለስ ጨንቆት ይህንን ጽሑፍ እስከ ጻፍኩበት ጊዜ ድረስ አዲስ አበባ ውስጥ ከእነ አባ አእምሮ በሚደረግለት ድጎማ እንደሚኖር ለማወቅ ችያለሁ፡፡

በነገራችን ላይ አቶ ታምሩ ቅዱስ ፓትርያርኩን እንዲያገኝ ያመቻቸለት ‹‹ወንዱ እጅጋየሁ እየተባለ የሚጠራው›› አቶ ቴዎድሮስ ሞላ(ቴዲ ሞላ) የመርካቶው አራጣ አበዳሪና ተበዳሪ የቅድስት ቤተክርስቲያን መዋቅር ውስጥ ለመግባትና ታዋቂነትን ለማግኘት ሲል በአሁኑ ሰዓት ሁለት መኪናዎቹን ሸጦ ያሉትን ስልኮች ዘግቶ ከደረሰበት ኪሳራ ለማገገም ሲል ራሱን የአቡነ ማትያስ ዋና የግል አማካሪ እንደሆነ አድርጎ የሚያስወራ ነው፡፡ ይህ ግለሰብ በስመ መርካቶ ነጋዴነት ቤተክህነት ገብቶ (በአብዛኛው አባቶች ብር ሲያዩ መቼም ብር እንደሚሉ ስላጠና) አሳክማለሁ፣ የቤት እቃ አሟላለሁ፣ ቅዱስነታቸው በየቦታው ሲዘዋወሩ የሚሰጧቸውን የስጦታ ዕቃዎች እኔ እገዛለሁ እያለ ቤተሰቡን ችግር ላይ ጥሎ ከክስረቱ ለማገገም መርካቶ ራጉኤልና የተለያዩ አብያተክርስቲያናት ላይ የሱቅ ባለቤት የሆነ በቤተክርስቲያን ላይ የተሰማራ ደላላ ነው፡፡ ቴዲ ሞላ በአሁኑ ሰዓት ከደህና የንግድ ሥራውና ውጤታማ የመርካቶ ራጉኤል አገልግሎቱ ተለይቶ በአራጣ የተበደረውን ብድርና በየቦታው ያሉትን ዕቁቦች መክፈል ባለመቻሉ እኔ የማውቃቸውን ሁለት ዘመናዊ መኪናዎች ሽጦ፣ በጤንነቱም ላይ ከባድ የሆነ የዲስክ መንሸራተት ደርሶበት ራሱን የቤተክህነቱ ፈላጭ ቆራጭ፣አድራጊ ፈጣሪና ያደገበትን የበለጸገበትን መርካቶና አከባቢውን ለቆ የወንበዴዎች ዋሻ ቤተክህነቱን ተጠግቶ የሚኖር የከሠረ ነጋዴ ነው፡፡ አቶ ቴዲ ቤተክህነት ውስጥ እያጭበረበረ ካለበት ህቡዕ ደሞዝተኛነትና የድለላ ሥራዎቹን ከቤተክህነቱ መዋቅር ውስጥ ገለል ካላለ ስለ እርሱ ጉዳይ በቀጣይ በዝርዝር በመረጃ አስደግፌ የምመለስበት ይሆናል፡፡

ሠ. ‹‹ቀሲስ›› በቀለ

እኚህ ቄስ ለባለ 58 ገጹ ሪፖርት መስረጃነት እንደ ዋና ተደርገው የቀረቡና ከ9 ዓመታት በላይ ያለትዳር አጋር የቆዩና በዚህ ጽሑፍ ለማካተት ልቡናዬ ያልፈቀደውን እኩይ ተግባራት የፈጸሙ ናቸው፡፡ ከአባ አእምሮ ጋር የልብ ወዳጅ ያህል ቅርበት ያለው አንድ ደቡብ አፍሪካ ያለ ወዳጄ እንደ ነገረኝ ከሆነ በፈጸመውም የማጭበርበር ሥራ ምዕመናን አንቀው ይዘው ሲጠይቁት መቼ ነው አቡነ ያዕቆብ ያስደበደቡህ? ብለው ሲያፋጥጡት አውነቱን አባ አእምሮ የሐሰት ምስክር መሆን ይችል ዘንድ 40 ሺህ ራንድ እንደከፈሉት እውነቱን አስወጥተውታል፡፡ ይህ ድርጊቱ ከተሰማ በኋላ በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ምዕመናን በመሰባሰበብ ክስ የመሰረቱበት ሲሆን በፈጸመው የሐሰት ምስክርነት ምክንያት በካህናትና በምዕመናን አንድነት አይንህን ለአፈር እንደተባለ ለማረጋገጥ ችዬአለሁ፡፡ ሊቀ ጳጳሱም ቢሆኑ እስከ ዛሬ ድረስ ያለ ሚስት እየኖረ ከሆነ ሥልጣነ ክህነቱን መያዝ ይገባቸው ነበር ብዬ አምናለሁ፡፡ የአቶ በቀለን መከሰስ ሳነሳ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ያዕቆብ በእነ ሙጬ ላይ በስም አጥፊነት ለምን ክስ አይመሰርቱም? ብዬ አንድ ወዳጃቸውን ብጥይቀው የሰጠኝ መልስ የሚከተለው ነው‹‹የተፈጸመባቸውን ድርጊት ኢሰብአዊ አስመልክቶ በርካታ ወዳጆችና የሕግ ባለሙያዎች በዚህ ጉዳይ ውክልና ይስጡንና እንክሰሳቸው ብለው ቢጠይቋቸውም የብፁእነታቸው መልስ ግን…ይሄንን ጉዳይ ለመድኃኔዓለም አሳልፌ ስለሰጠሁ በዓለማዊ ፍርድ ቤት ክስ በመካሰስ ቤተክርስቲያኔን አላዋርድም›› ነበር መልሳቸው ብሎኛል፡፡ በእኔ እምነት ግን እንዲህ ማን ይነካናል ብለው በትዕቢት ለተወጠሩ አሳማዎች ክሱ ከአስፈላጊ በላይ ነው ባይ ነኝ፡፡

በተዘዋዋሪ መንገድ የደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያን እንዳትረጋጋ ያደረጉ ብፁአን አባቶች

ሀ. የካሊፎርንያ ኔቫዳና አሪዞና ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ቴዎፍሎስ

በምንኩስና ስማቸው አባ ጽጌ ድንግል ደገፋው የደቡብ ጎንደር መነኮሳትን ብቻ በመሾም ይታወቅ ከነበረውን የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ  ሲኖዶስ መካከል ሾልከው ከገቡ ጎጃሜ መካከል አንዱ ናቸው፡፡ ብጹዕነታቸው በአሜሪካ ወደ ሎስ አንጀለስ ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላለፉት 22 ዓመታት አገልግለዋል ። ለዚህም የረዳቸው የአደባባይ ንግግር ያይደል የጠረጴዛ ላይ የጥልቅ ሴራዎች(Conspiracy) ሊቅ በመሆናቸው እንደሆነ በቅርብ የሚያውቋቸው አባቶችና ወንድሞች ገልጸውልኛል፡፡ እኚህ አባት በቅርብ አባ ቶማስ የሚባል መነኩሴ እጅግ ተበሳጭቶ ከደበደባቸው ውጪ በአደባባይ ሲናገሩ ድምጻቸው አይሰማም፡፡ ይህን የበለጠ ለመረዳት በውጪው ሲኖዶስ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ በነበሩበት ወቅት ማኅበረ ቅዱሳን ጠልነታቸውን የገለጹበትን የጻፉትን ደብዳቤ ማንበብ በቂ ሊሆን ይችላል፡፡

ታዲያ ብጹዕ አቡነ ቴዎፍሎስ ያለ ግል ቤተክርስቲያን የአሜሪካ ኑሮ ስለሰለቻቸው ደቡብ አፍሪካ በመጀመሪያ የአሁኑ የሲኖዶስ ጸሐፊ አቡነ ዮሴፍን በመቀጠልም ራሳቸው የደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያንን መውረስ ነበር እቅዳቸው፡፡ ለዚህ ምስክር የሚሆነው አጣሪዎቹ እነ ሙጬ ደቡብ አፍሪካ የነበረው የማያቋርጥ የስልክ ምልልስ፣ የእስትንፋሰ ዲያብሎሱን የታደሰ ወርቁን ጽሑፍ በማረም እንዲሁም በቅዱስ ሲኖዶ ስብሰባ ላይ የደቡብ አፍሪካ ጉዳይ በአግባቡ ታዮቶ መወሰን አለበት ብለው በርካታ ብጹአን አባቶች ቢያቀርቡም አቡነ ቴዎፍሎስ ግን እንዴት የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መልሱ ይታያል? በመንፈስቅዱስ የሚመራ ጉባኤ እንዴት ውሳኔውን ይቀለብሳል? ብለው ሀሳብ በመስጠት ነገሩን የበለጠ ውስብስብ በማደረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አደርገዋል፡፡ በቅዱስ ሲኖዶስ ታሪክ እንኳን ገና በቃለ ጉባኤ ሰፍሮ ያለተፈረመ ቀርቶ የተፈረሙ በርካታ ቃለ ጉባኤያት ተግባራዊ የማይሆንበት ቤት መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አቡነ ኤልያስና በጵጵስና አሿሿማቸው ላይ ጥያቄ እየተነሳባቸው ካሉ የስውዲኑ ብጹዕ አቡነ ሕርያቆስ ሌላኛው የደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያን ሰላምና መረጋገት እንዳይኖራት ጥረት ከሚያደርጉ ያለ ሀገረ ስብከታቸው ጣልቃ ከሚገቡ አባቶች መካከል ይገኙበታል፡፡ በአቡነ ሕርያቆስ አሿሿማቸውላይ እየተነሳ ያለው ጥያቄ በእኔ እምነት የስርዓተ ቤተክርስቲያንን ጠንቅቆ ያለማወቅ ነው ባይ ነኝ፡፡ ከዚህ ይልቅ ለእኔ ትልቁ ጉዳይና ጥያቄ አንድ መነኮስ ትልቁና የመጨረሻው የሥልጣነ ክህነት ማዕረግ ጵጵስና ከደረሰ በኋላ እንዴት አንድ ተራ ምዕመን የማይሰራውን ሴራ ለመስራት ይተጋል? የሚለው ነው

ለ. ብጹዕ አቡነ ሉቃስ

የሴቲት ሁመራና የሰሜን አፍሪካ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሉቃስ የደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያንን አጥብቀው እንዲከታተሉ ምክንያት የሆነው ም/ሊቀጳጳስ ነኝ ባዩ እና ከደቡብ አፍሪካ በበርካታ ክሶችና ቅሌት የተባረረው አባ ጥዕመልሳን የሚያቀርብላቸውን እኩይ ወሬና በራሱም ይሁን በንስሐ ልጆቹ በኩል የሚያቀርብላቸው ገጸ በረከት ስላታለላቸው ነው፡፡ አባ ጥዑም ደቡብ አፍሪካ ከተመደቡ ጀምሮ ከአዋሳ ጀምሮ ባላቸው መተሳሰር ምክንያት የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊነታቸውን በመጠቀም ከአባ ጥዑመ ልሳን ጋር በመሆን አቡነ ያዕቆብን ለማስነሳት ከፍተኛ ትግል አድርገዋል፡፡ በወቅቱም አቡነ ያዕቆብ ጳጳሳትን ወደ ብጹዕነታቸው በመላክ ከሀገረ ስበከታቸው ላይ እጃቸውን እንዲያነሱ እንዳሰሰቧቸውና በእምቢተኝነት እስከአሁን እንደቀጠሉ ለማወቅ ችያለሁ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አቡነ ሉቃስ በቻሉት ሁሉ ከአቡነ ያዕቆብ ተቃራኒ መቆም ሥራቸው  ሆነ፡፡ በ2011 ዓ.ም የግንቦቱ ሲኖዶስ እነ ታምሩ አበበ ክሱን ከዳር ለማድረስ ይሰበሰቡ የነበሩት በአቡነ ሉቃስ ቤት ሲሆን ተከታታይ ስብሰባቸው ግን በአንድ አስደንጋጭ ክስተት ምክንያት መቀጠል አልቻሉም፡፡ ይኸውም የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ሳይጠናቀቅ  አቡነ ሉቃስ ድንገት ይታመሙና ወደ ላንድማርክ ሆስፒታል ይገባሉ፡፡ ሒኪሞቹ የብጹዕነታቸው ሕመም ጋግሪን መሆኑን ይነግሯቸዋል፡፡ በኋላም አንድ እግራቸውን መቁረጥ ግድ ሆነና ተቆረጠ፡፡ ይህን አጋጣሚ ስሰማ እጅግ ከመደንገጤም በላይ በቃ ለዚሁ ነው የምንፋጀው? የምንገፋፋው? ማለቴ አልቀረም፡፡ያው ሁሉም ቀሪ ኃላፊ ነው፡፡ መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ከላይ እስከ ታች ላለነው ልብ ይስጠን፡፡

እዚህ ላይ ልብ ያለው ልብ ይበል! አነዚህ ሰዎች ይህን ሁሉ ርብርብ ያደረጉበት ትልቁ ምክንያት የደቡብ አፍሪካ ቤተክርስቲያ በአቡነ ያዕቆብ ወደ ሕጋዊ መስመር ከገባ በቃ ቤተክርስቲያንን የግል መተዳደሪያ፣መነገጃ ማድረግ ሊቀር ስለሆነ ነው፡፡ ጎበዝ ይሄ እኮ የሕልውናቸው ጉዳይ ነው፡፡ ስለዚህ የእነዚህ እኩያን ትልቁ ስሜታቸውና ፍላጎታቸው የራሳቸውን ሰው ማስመደብና በልተው የማያስበሉትን በእነሱ አስተሳሰብ ሞኝ የሆኑትን አባት  ማስነሳትና በሀገረ አሜሪካ እንዳሉት ግብር ከፋይ የግል ይዞታ አብያተክርስቲያናት ማድረግ  ነው፡፡ ይህ ካልተሳካ ደግሞ በኢትዮጵያ በኩል ባለው ቡድን ቤተክርስቲያኑቱን ያለ ርኅራኄ መዝረፍ ማዘረፍ ነበር፡፡

4. በደቡብ አፍሪካ አጣሪ ሆነው ተመደበው ስለነበሩ ግለሰቦች ማንነት

ይቀጥላል…

ውድ አንባብያን! በቀረው የሱባኤ ጊዜ በደቡብ አፍሪካ ያሉ የኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ ምዕመናንን የገጠማቸውን ፈተና ሁሉ ያርቅላቸው ዘንድ በጸሎት እንድናስባቸው አደራ እላለሁ!

ተጻፈ ነሐሴ 08 ቀን 2011 ዓ.ም

Leave a comment