ዘመቻ ጌዴዎን ክፍል ሦስት
እጅግ ጨዋ ስለሆነው ስለ ታደሰ መጻፍ ከመጀመሬ በፊት በጣም ሲያስጨንቀኝ የነበረው ነገር በምን ቃል፣ በምን መንገድ ልገልጸው እችላለሁ የሚለው ነበር፡፡ የቤተክርስቲያንን ትምህርት ባለማወቅ ፍጹም ጨዋ (ያለተማረ)ና የዳንኤል ቶፋ(የሌላን ሰው ሥራ ወክሎ የሚሰራ) የሆነውን ይህን ሐራዊ ለመግለጥ ግሩም ግብርከ የሚያስብል አንድ አስገራሚ ፍጥረት አገኘሁኝ፡፡ ይኸውም በአለማችን እጅግ አስፈሪውና በብዛት በደቡብ አሜሪካ (በተለይ በኮሎምቢያ) የሚገኘው ስኮፖላሚን (Scopolamine) ወይም በተለምዶ እስትንፋሰ ዲያ ብ ሎስ (Devil’s Breath) በመባል የሚታወቀው ተክል(ዕፅ) ነው፡፡



ከላይ የመምትመለከቱት ሦስተኛው እፀ ፋሪስ(አስተናግር) ነው፡፡ አበባው እንዳያምታታችሁ ነው እዚህ ጋር የገባው፡፡ ሁለቱ ግን እስትንፋሰ ዲያብሎስ በአበባ እና በፍሬ ጊዜ ነው
ይህን ዕፅ የወሰደ ሰው ሲንቀሳቀስ ስናየው ፍጹም ጤነኛ፣ የተረጋጋ፣ እና በሙሉ አዕምሮው የሚያስብ ይመስላል።ምንም ዓይነት የመጦዝ ወይም ራስን የመሳት ስሜት አይታይበትም፡፡ ነገር ግን እውነታው ከዚህ የራቀ ነው።የዚህን ዕፅ ፍሬ ዱቄት በአፍንጫቸው በኩል ውልብ ያለባት ሰዎች ፈረንጆቹ እንደሚሉት በደመ ነፍስ የሚንቀሳቀስ፣ ፍጹም ታዛዥ (Zombie) ሁነው ይታያሉ። ዕጹን ላቀመሰው ሰው ፍጹም ታዛዥ ሆኖ መከተል ብቻ ነው። እቤት እንሂድ እሺ፣ ወደ ባንክ እንሂድ እሺ፣ አልጋ ላይ እንተኛ እሺ፣ መኪናህን ስጠኝ እሺ፣ ያለህን ንብረት በሙሉ ስጠኝ እሺ፣ ሚስትህን ልተኛት እሺ፣ ባልሽን ልተኛው እሺ፣ ገደል ልክተትህ እሺ…እሺ…እሺ…ብቻ። ብቻ ምን አለፋችሁ የሚታዘዘውን ትዕዛዝ ሁሉ በሙሉ ፈቃደኝነትና ትብብር መፈጸም ብቻ ነው። ይህን ሁሉ ሲያደርጉ ራስን መሳት ብሎ ነገር የለም። ፍጹም ጤነኛ። ብቻ አድርግ የተባለውን ሁሉ ማድረግ ነው። በሌላ አገላለጽ ሰውየው ጤነኛ ያልሆነ ወይም አዕምሮው የተወሰደበት ወይም እንዳይሰራ የተደረገበት ነገር ግን ጤነኛ የሚመስልና የሚጠየቀውን በፍጹም አዛኝነትና ታዛዥነት የሚፈጽም ማለት ነው። ፈረንጆቹ ሲገልጹት “scary hallucinations which even induce a dangerous, zombie-like state” ይሉታል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ በሀገሪቱ መዲና በአዲስ አበባ ተመሳሳይ ነገሮች እየተፈጠሩ እንዳሉ ሰምተናል።በቅርብ የምናውቀው ሰውም ለፍቶ ያጠራቀመውን 80 ሺህ ብር እራሱ ወደ ባንክ በባጃጅ ወስዶ፣ ከባንክ አውጥቶ እንደሰጠ እናውቃለን። የሚያስታውሰው የሆነ ሰው አፍንጫውን እንዳሸተተው ብቻ ነው። ከዚያ ውጪ ዘግይቶ የተገነዘበው የባንክ አካውንቱ ባዶ መሆኑን ብቻ ነው። ተመሳሳይ ሌላ ታሪክ እንጨምር። አዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በአንዱ የሚሰራ የሆነ ሰውም የሆኑ ሰዎች ሰላምታ ሰጥተውት እንደተሳሳሙ ያስታውሳል፤ ነገር ግን ሞባይሉን፣ ላፕቶፑን፣ ዋሌቱን፣ ብቻ በወቅቱ ይዞት የነበረውን ሁሉ እራሱ አውጥቶ እንደሰጠም ሰምተናል። ታሪኩ ብዙ ነው። የሰማችሁ ወይም የደረሰባችሁ ታውቁታላችሁ።
በዚህ እጅግ አስፈሪ በሆነ ዕጽ የተጠቁት እንደሚያስረዱት ከሆነ አንዳንዶቹ ከምግባቸው ውስጥ፣ ሌሎቹ ከሚጠጡት ነገር ውስጥ ብን ተደርጎባቸው፣ አሊያም በመልከ መልካም ሴቶች እሽት በስሱ ሳይታወቃቸው አፍንጫቸውን በመሳም ወይም በማሻሸት እንዲስቡ ተደርገዋል። ሌሎቹ ደግሞ ሳያስቡት ዕጹ ባለበት ጥጥ ድንገት አላፊ ሰው አፋቸውን ወይም አፍንጫቸውን ጠረግ አድርጎ እንዳለፈ ብቻ ነው የሚያውቁት። ከዚያ በኋላ ስለሆነው ነገር የሚያውቁት ነገር አይኖርም። ከዕጹ ተገዢነት ሲነቁ ታዲያ በራሳቸው ፈቃድ ተደፍረው፣ ገንዛባቸውን እራሳቸው ከባንክ አውጥተው ሰጥተው፣ የቤታቸውን ዕቃ ራሳቸው መኪና ተከራይተውና ራሳቸው ጭነው ለማያውቋቸው ሰዎች አስረክበው እንደነበረ ያውቃሉ። ታዲያ ምን ዋጋ አለው፤ ስለተፈጠረው ሁኔታ ምንም የሚያስታውሱት ነገር የለም። ሰዎቹን እንኳን አያስታውሱም። ብቻ ንብረታቸው የለም አለያም አካላዊ ጥቃት ደርሶባቸዋል።
ታዲያ ሐራዊ የዳንኤል ክስረት ቡችላ ታደሰ እና እስትንፋሰ ዲያብሎስ ምን አገናኛቸው ነው ጥያቄው?

ከላይ ከተገለጠው ከዕፁ ጠባይ በመነሳት እናንተ እንዴት እንደምትረዱት ባላውቅም እኔ ግን በደንብ የማውቀው ወዳጄ ታዴና እስትንፋሰ ዲያብሎስ በሁለት መልክ ይመሳሰሉብኛል፡፡
መመሳሰል ፩. በቁሙ
የእስትንፋሰ ዲያብሎስ ተክልን ማንኛውም ሰው አበባውን ሲመለከተው፤ ወደ አፍንጫው አስጠግቶ ሲያሸተው እንዲሁም የአበባው ውበት ለሰውም ይሁን ለንቦች ተስማሚ መዓዛ ያለውን ይህን ተክል በምንም ዓይነት እንዲህ የአደንዛዥና ሀቅልን ሰላቢ ፍሬ ባለቤት ይሆናል ብሎ ለማሰብ ይከብዳል፡፡ ልክ እንደ ዕፁ ሁሉ ሐራዊው ታዴ አንገቱን እያቅለሰለሰ፣ ነጭ ነጠላ ለብሶ በተቀደሰው አደባባይ ቆሞ ለእኩይ ዓላማና ለንግዱ ሥራ ያመቸው ዘንድ ‹‹ተሐድሶ››፣ ‹‹አጽራረ ቤተክርስቲያን››፣ ‹‹ሐራ ጥቃ››…እያለ እና ከመዝገበ ቃላት በተውሶ ያገኛቸውን ቃላት በተንሸራታች ጽሑፎች(Business Slide) ሲገልጥላችሁ እንዴት ዓይነት በቤተክርስቲያን ፍቅር የተቃጠለ የመናፍቃን ጠላት ነው ማለታችሁ አይቀርም፡፡ ጉዳዩ ግን ሌላ ነው ጨዋው ታዴ በማቅ ላይ በፈጸማቸው እኩይ ተግባራት ምክንያት ከተባረረ በኋላ ለእንጀራ ሲል ውሎው ከሲሞናውያን፤ አዳሩ ደግሞ እሱን አስመስሎና አሳህሎ ከወለደው ከግብር አባቱ ጋር ሆነ፡፡ ስለዚህ በቁሙ እስትንፋሰ ዲያብሎስ ያልኩበት ምክንያት ይህ ሐራዊ በተቀነባበሩና በሐሰት በተሞሉ የሐሰት ሰነዶች ያለ ማጣራት አባቶችን እገሌ ይወገዝ፣ እገሌ ይባረር፣ እገሌ ከሹመት ይሻር እና የመሳሰሉትን ምክረ ሀሳብ አቅርቦ የችኮላና አስተውሎት የጎደለው ውሳኔ እንዲወስኑ ያፈዘዛቸውና ያደነገዛቸው ጊዜ በርካታ ነው፡፡ በነገራችን ላይ አብዛኛውን ጊዜ አባቶቻችን የሚነቁትና የሚደነገጡት አንድን ሰው ካወገዙና ከለዩ በኋላ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በእንተ ስማ ለማርያም ብለው ዋጋ ከፍለው በትጋት ከተሠማሩባትና ካደጉባት ከእናት ቤተ ክርስቲያን አስወጥቶ ባዶ እጃቸውን አስቀርቶ ጎዳና ተዳዳሪ ያደረጋቸው ፣ ትውልደ አራዊት በሆኑ በመናፍቃን ያስበላቸው፣ ልክ እንደ ዮዲት ጉዲት ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመበቀል እንዲነሳሱ ያቆሰላቸው በርካቶች ናቸው፡፡ ስለዚህ ይህ ሐራዊ በቁሙ እስትንፋሰ ዲያብሎስ ነው ብንል ያንስበታል እንጂ አይበዛበትም!!!
መመሳሰል 2. በተጠቃሚነት
ከዚህ ማስፈንጠሪያ ላይ እንደምትመለከቱት (https://www.youtube.com/watch?v=ToQ8PWYnu04) አንዴ በዚህ ሱስ(ሰውን አፍዝዞ በመዝረፍ) ከተለከፋችሁ ለነፍስ ግድያ እንኳ ወደ ኋላ አትሉም፡፡ ይህን ሐራዊ የዚህ ዕፅ ሱሰኛ እንደሆነ እንድጠረጥር ያደረገኝ ነገር ምን መሰላችሁ ከሐራዊው ታደሰ ጋር ለማውራት እድል የገጠማቸው ሁሉ በተደጋጋሚ የሚነግራቸው አቡነ እገሌ፣አባ እገሌ፣ቄስ እገሌ…በቃ ሁሉንም በቁጥጥር ስር ማዋል እንደሚችል ሲናገር መስማት የተለመደ ነው፡፡ እኔም በተለያዩ አጋጣሚዎች አዲስ አበባም ይሁን ክፍለ ሀገር በአገልግሎት(እሱ ለገለጣ) በተገናኘንበት ጊዜያት የተረዳሁት ጉዳይ በቃ ታዴ እንኳን ለመሳተፍ ለማውራት እንኳ በሩቅ ከሚፈራቸው ከቅዳሴና ከማኅሌት አገልግሎቶች ውጪ ሁሉን አዋቂ እንደሆነ ፋታ በሌለው ወሬው ሲነግራችሁ አጃኢብ! ማለታችሁ አይቀርም፡፡ ከሁሉ በላይ ያስደነገጠኝና እኔም በተግባር ማረጋገጥ የቻልኩት ነገር በተለይ አቡነ ዲዮስቆርዮስና አቡነ ሳዊሮስ በሐራውያን ቁጥጥሩ ሥር ስለ መሆናቸው ‹‹እኛ ያለ እነሱ ፤ እነሱ ያለ እኛ ሕልውና የለንም›› እያለ ሲያወራ የሰማሁበት ቀን ነው፡፡ ምናልባት ይህንኑ ዕፅ እየተጠቀመ አደንዝዟቸው ይሆን እንዴ? እንጃለቱ! እንዲህስ አያድርግብን!!! ከዚህም በተጨማሪ በስህተት እንኳ በቤተክርስቲያን ጉባኤ ቤቶች አልፎ የማያውቀው ሐራዊው ታደሰ የቤተክርስቲያን አለቆች ሰባኪያነ ወንጌል አበክረው የሚያውቋቸውን፤ ምንም ሕጸጽ የማይገኝባቸውን አገልጋዮች በፊት ለፊታቸው ተሐድሶ መናፍቅ ሲል ደንዝዘው ያለተቃውሞ የሚሰሙት በእስትንፋሰ ዲያብሎስ አደንዝዟቸው ሊሆን እንደሚችል መጠርጠር የጀመርኩት ግን መቼም በ‹‹ቅድሰት ሀገር›› አራት ኪሎ የማይታይና የማይሰማ ነገር ምን አለ? ዕፁን አራት ኪሎ አለሌና ጨዋ ሰባክያን ዘማርያንና አዝማሪያን በሚሰባሰቡባቸው ቦታዎች በማየቴ ደግሞ ጠላታችሁ ድንግጥ ይበልና እስካሁን ድንጋጤዬ አልለቀቀኝም፡፡


ሮሚና ካፌና ቱሪስት ሆቴል ጎን ይህ ዕፅ መገኘቱ ምን እንድምታ ይኖረው ይሆን? እኔጃ! እኔ ግን አእምሮዬ በበርካታ ጥያቄዎችና ጥርጣሬዎች ተወጥሯል!!!
በዚሁ አጋጣሚ ሐራውያንን ጨምሮ የማታውቁት ሰው ሻይ ቡና ቢጋብዛችሁ ባትቀበሉ ይመረጣል፤ ከተቀበላችሁም በምንም ተዐምር ምግባችሁን ወይም መጠጣችሁን ትታችሁ ሽንት ቤት ወይም ስልክ ብላችሁ አትውጡ። ሽንት ቤት መሄድ ካለባችሁ ብርጭቋችሁን ባዶ አድርጋችሁ መሆኑን አረጋግጡ። ከተረሳም ስትመለሱ አትጠጡት። ቢቻል ከማናውቃቸው፣ እንደነ ታዴ ካሉ ጮሌዎችና ከማናምናቸው ጋር ባንዝናና ይመረጣል። ለማንኛውም ንቁና ጠንቃቃ መሆን ሁሌም አይጎዳም!!!
እናላችሁ እኔና ታዴ ከረጅም ጊዜ በፊት በመተዋወቃችን እንዲሁም አብረን በማገልገላችን ምክንያት እጅጉን አጃጅሎኝ እንደኖረ የገባኝ ዘግይቶ ነው(ይቅርታ ነገር ቶሎ ስለማይገባኝ ነው)፡፡ ባለፈው ጊዜ አንኳ ትዝ ይላችሁ የለ? መቼ ነበር? ጊዜው ተዘነጋኝ…ታዴ መቼም የራሱን ሊበራል ተሐድሶነት ይረሳና ብዙ ጊዜ ወጥ ረገጥ ይሆናል፡፡ ታዲያ በዚህ ድርጊቱ የተበሳጩ እስካሁን ማንነታቸውን በውል ያላወቅናቸው ደብዳቢዎች ሲፈነካክቱት የእጁን አገኘ! ገና ይቀረዋል! ሲሉ በእርሱ ምክንያት ከብዙ ሰው ተጣላቼ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ ታዴ ከዚያ የዋህ ማንነት ወጥቶ ወደ ፋሽሽታዊነት ተቀይሮ በሐራ ዘተዋሕዶ ላይ ዲጄው አሉላን በፒያሳው ኢንተርኔት ቤት ለጣፊ(blog poster) አድርጎ በቅብዐተ ተንኮል ከሾመው በኋላ ከጥቅምት 2002 ዓ.ም ጀምሮ በተለይ፡-
ከመስከረም 2006 ዓ.ም እስከ መጋቢት 2011 ዓ.ም ቅዱስ ፓትርያርኩን ብቻ የሚመለከቱ 50 ጉዳዮችን የለጠፉ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 46ቱ ምዕመናን በቤተክርስቲያኒቱ የበላይ አካላት ላይ ፍጹም ጥላቻ እንዲኖራቸውና አባቶችን በንቀት እንዲመለከቱ የሚያደርጉ ናቸው፡፡ በውስጥ ያሉትን ጸያፍ እና ከአንድ ተራ አሳዳጊ የበደለው ከሚባል ሰው እንኳ የማንሰማቸውን የእርኩሳን መናፈስት ልጆች መሆናቸውን የሚገልጡ ቃላት ትቼ ጥቂቶቹ እንዲህ ይላሉ ተጽዕኖ አልባ መሪ፣ የመነጋገርና የመደራደር አቅም የሌላቸው፣ ፓትርያርኩ ከመንግሥት ጥገኝነት ነፃ ለመኾን እንደማይችሉ ያምናሉ፣ አቦይ ስብሐት ጎበዝ ነኽ አለኝ›› ያሉት ፓትርያርኩ፣ ፓትርያርኩ ዛሬ በሕግ አፍራሽነት ይጠየቃሉ፣ የአ/አበባ ሀ/ስብከት በቀጣይ ብክነት ላይ – ፓትርያርኩን ሰርፕራይዝ እናድርጋቸው፣ ፓትርያርኩ:“እስከምሞት እዋጋዋለኹ፤ እጅ እግሩን አስረዋለኹ” ሲሉ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ዛቱ፣ ፓትርያርኩ “ኃይል አለኝ” ሲሉ ዛቱ፣ ፓትርያርኩ ተሸነፉ? “ሙስናን ተዉ፤ ማለት ከአንበሳ አፍ ሥጋ እንደ መንጠቅ ነው፤ አቅሙም ጉልበቱም የለንም” አሉ፣ ፓትርያርኩ አላግባብ ያሳለፉትን ወቅቱን ያላገናዘበ ለውጥ አደናቃፊ እገዳ እንዲያነሡ ዋና ሥራ አስኪያጁ አሳሰቡ…
- አቡነ ጢሞቴዎስ፣አቡነ ሕዝቅኤል ፣አቡነ ያዕቆብ የደቡብ አፍሪካና የአትላንታው፣ አቡነ ኤውስጣቴዎስ ፣አቡነ ዳንኤል፣አቡነ እንድርያስ፣አቡነ ቶማስ፣አቡነ ፊልጶስ ዘፊላደልፊያ፣አቡነ በርናባስ፣ አቡነ መልኬጼዲቅ እና ሎሎችም ጭምር በሐራውያን ለገብያ ቀርበው ግብይት ከተፈጸመባቸውና ኢቀኖናዊ መብጠልጠል ከደረሰባቸው አባቶች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው…
- አቡነ እስጢፋኖስ፣አቡነ ማቴዎሰ፣አቡነ ሉቃስ፣አቡነ ሳዊሮስ እና አቡነ ዲዮስቆርዮስ ደግሞ በተደጋጋሚ ሙገሳና ድጋፍ፤ አንዳንዶቹ ደግሞ እንከን አልባ ተደረገው ከጸነገሩን አባቶች መካከል ይገኙበታል (አባቶች በሐራውያን ለመሰደብና ለመሞገስ መስፈርቱ ምን እንደሆነ አነስተኛ ጥናት በማድረግ ላይ ስለሆንን እንዳለቀ ይፋ ይሆናል)
- አዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን ለሐራውያን ትልቁ የገብያና የመተዳደሪያ ማዕከላቸው ከመሆኑ አንጻር ጭር ሲል ጉሮሮአቸውም ስለሚዘጋ ማንም ይሾም ማን በወሬ ማተራመስ ትልቁ ተግባራቸው መሆኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡
አዚህ ላይ ስለ ቤተክርስቲያን አምላክ የምጠይቃችሁ ነገር ቢኖር የመጻፍ አቅሙና ጊዜው ያላችሁ የቅድስት ተዋሕዶ አገልጋዮች የኤፍሬም እሸቴ የግል ንብረቶች የሆኑትን ሦስቱን ብሎጎች ማለትም ደጀ ሰላም፣ አንድ አድርገንና ሐራ ዘተዋሕዶን ምን ርእሰ ጉዳዮችን አነሱ? ለቤተክርስቲያን ምን ፋይዳ አመጡ? ወይስ የበለጠ የጥርጣሬና የመለያየትን መንፈስ ዘሩብን? የሚሉትንና ተያያዥ ጥያቄዎችን በማንሳት ትንታኔ መሥራት ብትችሉ ለዘመቻ ጌዴዎን ታላቅ አስተዋጽኦ አበረከታችሁ ማለት ነው፡፡በእኔ በኩል የሐራውያንን ነገር በትኩረት ሳስብ እና ሐራዊ ታደሰ እንዴት ይህንን የስድብ መንፈስ ተዋረሰ ብየ ራሴን ስጠይቅ ሁለት ነገሮች በአእምሮዬ ይመላለሳሉ፡-
-ሀ-
በሉቃ8፡2 ላይ በመግደላዊት ማርያም ላይ አድረውባት ከነበሩትና ጌታችን ነጻ ካደረጋት ሰባት አጋንንት መካከል አንዱ የስድብ መንፈስ ነበር፤ አንዲሁም በሐዋ16፡16-19 በተመዘገበው ታሪክ ላይ የመዋርተኝነትና የጥንቆላ መንፈስ ያደረባት ሴት ‹‹የመዳንን መንገድ የሚነግሩአችሁ እነዚህ ሰዎች የልዑል አምላክ ባሪያዎች ናቸው›› በማለት እየጮኸች የበለጠ ተከታይ ለማፍራት ባለመ አጋንንታዊ ዕቅድ እና በምትናገረው አዎንታዊ ቃል ለሐዋርያት አገልግሎት ተቆርቋሪ ለመምምሰል በትሞክርም ውስጧ ሸፍጥ ያለበት መሆኑ በመንፈስ ቅዱስ የተረዳው ቅዱስ ጳውሎስ ለክርስቶስ ወንጌል እንቅፋት የሆነውን የአስመሳይነት መንፈስ ገስጾ ከለየ በኋላ በማቴ12፡43 ላይ ‹‹ርኩስ መንፈስ ከሰው ከወጣ በኋላ ዕረፍትን ሲሻ ውኃ ወደ ሌለበት ምድረ በዳ የዞራል ግን አያገኝም፡፡…ከዚህ በኋላ ከርሱ የሚከፉ ሰባት አጋንንት ያመጣል…›› እንዲል እነዚህ ሁለት ሰዎች አጋንንት ከወጡላቸው በኋላ ማደሪያ አጥተው ሲንከራቱ ቆይተው በዚህ በእኛ ዘመን ቤተክርስቲያን ለማፈራረስና አገልጋዮቿን ለመለያየት ምቹ ማደሪያ ሆኖ ያገኙት ሐራዊ ታዴንና ግብረ አበሮቹን ይመስለኛል፡፡ ያለበለዚያ ግን ጤነኛ የሆነ ሰው የቤተክርስቲያን መሠረትና የሐዋርያት ተከታዮች የሆኑትን አባቶች በመሳደብ የወንጌል አገልግሎት እንቅፋት በመሆን ለመተዳደር አቅዶ ሊሠራ አይችልም፡፡ ስለዚህ ከዚህ ሐራዊ እነዚህ ርኩሳን መናፍስት እንዲርቁለት በጸሎት ልናስበው፣ልናስጠምቀው አሊያም አጋንንትን የማስወጣት ጸጋው ወደላቸው አባቶች ብንወስደው ይሻላል እላለሁ፡፡
-ለ-
እስትንፋሰ ዲያቢሎስ ሐራዊው ታደሰ ወርቁ ከዚህ በፊት በደጀ ሰላም አሁን ደግሞ በሐራ ዘተዋሕዶ ብሎግ ላይ ማን እንደቀጠረውና እንዳሰማራው ባላውቅም እነዚህን የስድብ ጽሑፎች በቤተክርስቲያኒቱ ሕጋዊ አካላት ላይ በመጻፍና በማጻፍ የተጠመደበት ሌላው ምክንያት እሱና ግብረ አበሮቹ በማቅ ላይ በፈጸሙት ስውር ሴራ ከተባረሩ በኋላ ዋንኛ ጉዳያቸው እና መተዳደሪያ ያደረጉት በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ ማኅበረ ቅዱሳንን አምርሮ ጠልነታቸውንና ማቅ መፍረስ አለበት የሚለውን የጥፋት ተልዕኮ መፈጸም ነው፡፡ ይህንን በሁለት ማሳያዎች ለማሳየት ልሞክር፡-
ማሳያ 1
ከላይ እንዳነሳሁት ሐራውያን ሰው ያወቃቸው ዛሬም የሚውቃቸው የማቅ ቀንደኛ ደጋፊና አባል እንደሆኑ አድርጎ ነው፡፡ ስለዚህ በአብዛኛው ሰው የሚረዳው ሐራ ወይም ደጀ ሰላም ተሳደበች ማለት ማቅ ተሳደበ ማለት ነው ብሎ ይረዳል፡፡ በዚህም ማንም አካል ክብሩ ሲነካ የሚታገስ የለምና ከቅዱስ ፓትርያኩ አስከ አጥቢያ እስካለው አገልጋይ፣ ሰ/ት/ቤት እና ማህበራት ማቅ ሰደበን አዋረደን ተሳለቀብን ብሎ እንዲያስብ በማድረግ ማህበሩን ከቤተክርስቲያኒቱ የመለየት የመጀመሪያ ዕቅዳቸው በከፊልም ቢሆን ተሳካ ማለት ነው፡፡ በእኔ እምነት ቅዱስ ፓትርያርኩ ‹‹ማህበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያንን በቅኝ ግዛት ይዟታል›› እስከ ማለት የደረሱት በእነዚህ ሐራውያን እኩይ ተግባር ምክንያት እንጂ ማህበሩን አውቀውት ነው የሚል ግምት የለኝም፡፡ በነገራችን ላይ ማህበሩ በእነዚህ የተኩላ ለምድ በለበሱ ማቅ ጠል ቡድኖች አቀነባባሪነት በሚፈጸመው እኩይ ሴራ ማህበሩ ከየአቅጣጫው በርካታ ወቀሳና ትችት ከደረሰበት በኋላ በሐምሌ 2001 ዓ.ም በሳተመው የስምዓ ጽድቅ ጋዜጣ የፊት ገጽ ላይ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን ‹ደጀ ሰላም› የተባለው ብሎግ ልሳኑ አለመሆኑን አስታወቀ›› ብሎ ማውጣቱ ለዚሁ ማሳያ ነው፡፡

በዚሁ ጋዜጣ ገጽ 2 ላይ እንዲህ ይላል ‹‹…አቶ ዳንኤል ተስፋዬ እንደገለጹት ራሱን የማኅበረ ቅዱሳን ልሣን አድርጎ በማስተዋወቅ መግለጫዎችን የሚሰጠው ብሎግ ከማኅበሩ እውቅና ውጪ ነው፡፡ ብሎጉ አሁንም በማኅበሩ ስም መግለጫዎችን እያቀረበ እንደሚገኝ የጠቆሙት ዋና ጸሐፊው የማኅበሩ አለመሆኑን አሳውቀዋል አክለውም በዚህ ብሎግ ምንም ዓይነት መረጃ እንደማያስተላልፍ ገልጸዋል፡፡ ከማኅበሩ እውቅና ውጭ የሚንቀሳቀሰውን ይህን ብሎግ የማህበሩ አለመሆኑን ምዕመናን እንዲያውቁም ጸሐፊው አሳስበዋል፡፡
አያይዘውም እንዲህ ዓይነት ሓላፊነት የጎደለውና ምእመናንን ለማሳሳትና ቤተ ክርስቲያንን ለማወክ የሚደረጉ ሙከራዎችን ምእመናን ሊቃወሙ እንደሚገባቸውም ዋና ጸሐፊው ተናግረዋል፡፡››
በዚህ ያለተጠበቀ መግለጫ የተደናገጡት ሐራውያን የአሰላለፍ ለውጥ በማድረግ ከጥቅምት 2002 ዓ.ም ጀምሮ ሐራ ዘተዋሕዶ የሚል ሌላ የስድብ ብሎግ ከፍተው ብቅ ያሉት ለዚህ ነው፡፡ ማቅ እና እነዚህ ብሎጎች ተያይዘው የሚነሱበት ትልቁ ምክንያት ሁሉም ሐራውያን በአንድ ወቅት ከ‹‹አባ ተንኮሉ›› ጋር በመሆን በፈጸሙት ሴራ ምክንያት ተጠራርገው ከማቅ ከመውጣታቸው በፊት (እንዲህ እንደአሁኑ መራራ ፍሬዎች እና የእናት ጡት ነካሾች ከመሆናቸው በፊት) የማኅበሩ ጋዜጣና መጽሔት ዋናነና ምክትል አዘጋጆች እስከ መሆን በመድረሳቸው ነው፡፡
ዛሬም ማኅበሩ እነዚህ መሠሪዎችና ከጉያው የወጡ መራራ ፍሬዎች በተደጋጋሚ ካላጋለጠ በቀር ነቀርሳነታቸው ከማኅበሩ አልፎ ለቤተክርቲያን እንደሚተርፍና እየተረፈ ያለ መሆኑ የታወቀ ነው፡፡
ማሳያ 2
ታዴ በሃይማኖት ካባ በተሸፈነው ፖለቲካዊና ሲሞናዊ ማንነቱ ምክንያት ከማቅ ከወጣ በኋላ ቆሌ ስለራቀው ያልሞከረው የሥራ መስክ የለም ተንታኝ፣የታሪክ ተመራማሪ፣ሐያሲ፣ሰባኪ፣ዐቃቤ እምነት….በርግጥ ጥረቱን አደንቃለሁ፡፡በአብዛኛው ከፓትርያርክ ምርጫ ጋር በተያያዘ “ፋክት” በተሰኘው መጽሔት ቅፅ 2 ቁ.6 የሐምሌ እትም 2005 ዓ.ም ላይ “በቄሳራውያን መዳፍ ስር ያለ አስኬማ” በሚል ርዕስ ፖለቲካዊ ጽሑፉ እንዲሁም በቀጣዩ ቁጥር 7 የነሐሴ 2005 ዓ.ም እትም ላይም “የተቋማዊ ለውጥ ጅምሮች” በሚል ርእስ ባስነበበን ጽሑፍ ማቅ ‹‹ማህበሩ›› እያለ እንዲህ ተችቷል ፡-
- እንደ ታደሰ አገላለጽ ማህበረ ቅዱሳን የሁለቱን ሲኖዶስ እርቀ ሰላም አሉታዊ እይታ እንዳለው ሲገልጥ አባቶች እርቅ ከፈፀሙና ወደአገር ቤት ከመጡ ችግር ይፈጠርብናል የሚል ስጋት እንዳለ ነው፡፡ከዚህ በተጨማሪ በአንድ በኩል ለሕዝባዊ ተቀባይነት እርቀ ሠላሙን እደግፈዋለሁ እያሉ በሌላ በኩል ደግሞ የእርቀ ሠላሙን ሂደት በውስጠዘ እያክፋፉ ድርድሩን ከድጡ ወደ ማጡ እንዲሆን አድርገውታል፡፡
- የአ/አ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነትን ማቅ በተሐድሶ ሰበብ የቤተክርስቲያን ውስጥ ነውጥ አውጆ በነበረ ጊዜ ለረብሻው አሳድሟቸውና አሠማርቶአቸው እንደነበር ጠቁሟል፡፡
- በወቅቱ ትልቁ የመንግስት ጥያቄና ትኩረት የሳበው የጥምቀት ተመላሽ ወጣቶችን ጉዳይ ማን አደራጃቸው? ከጀርባ ማነው የሚደግፋቸው? የሚለው ጥያቄ ስለነበር ይህ አጋጣሚ ተጠቅሞ ማህበሩን ከመንግሥት ጋር ለማነካስና ከላይ በማቅ ላይ ያቀዱትን ዕቅድ ለማስፈጸም እነዚህን ወጣቶች ማቅ እንዳደራጃቸው በድፍረት ጽፏል…
ምን አለፋችሁ ብቻ አልተሳካላቸውም እንጂ እንደ ሐራውያን ሕልምና ቅዠት እንዲሁም በብሉግና በጽሑፍ እንደሞከሩት የባንዳነት ፍልሚያ ቢሆን ኖሮ ማቅ እስከ አሁን ጠፍቶ ነበር፡፡

ወዳጄ ታዴ ከእንቅልፉ ሲነቃ ከእስትንፋሰ ዲያብሎስነት ወጥቶ ወደ ፊት ካልተቋረጠ አንድ ቀን የዓመቱ በጎ ሰው ተሸላሚ እንደሚሆን ተስፋዬ ጽኑ ነው!!!
ቸር ሰንብቱልኝ
ሳምኬት ነኝ!
ሐምሌ 4 ቀን 2011 ዓ.ም