ዘመቻ ጌዴዎን ክፍል ሁለት
ቀጥታ ወደ ክፍል ሁለት ከማግባቴ በፊት የባለፈውን ጽሑፍ መነሻ በማድረግ ብዥታ የተፈጠረባቸውን ሁለት ጉዳዮችን ማንሳት ወደድኩ፡-
ጉዳይ አንድ
ስለ ሐራዊ(ጨዋው)ና ዲጄው አሉላ ጥላሁን ባለፈው አንስቼላችሁ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ አንዳንድ እያስተዋልኳቸው ያሉ ነገሮች አሉ፡፡ ይህውም በጽሑፎቼ ስማቸውን የምጠቅሳቸውን ግለሰቦችን የማነሳበት ትልቁ ምክንያት ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ ከተሰለፉበት እኩይ ተልዕኮ እንዲታቀቡ ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ሐራዊ አስቀድሜ በነገርኳችሁ በስለላ የታገዘው የሴራ ፖለቲካ ሕይወቱ ምክንያት ብዙ ጊዜ በመታሰሩና ወደ የትኛውም ሀገር እንዳይወጣ እግድ የተጣለበት ከመሆኑ ባሻገር ቀውስነቱ ለወላጅ እናቱ ስለተረፈ ተከራይተውት ይኖሩበት ከነበረው ከራስ አምባ ቤቱ ከተባረሩ በኋላ በአሁኑ ሰዓት ፈረንሳይ ቤት ተከራይቶ የሚኖር ከንቱ ሰው ነው፡፡ ከማቅ ከተባረረም በኋላ ምንም ዓይነት ቋሚ መተዳደሪያ የሌለው ፣ማን እንደቀጠረው ባይታወቅም ዲጄው በተደጋጋሚ ሀገረ ስብከቶች ችግሮቻቸውን በራሳቸው እንዳይፈቱ የማበጣበጥ ሥራ የሚሰራ አካይስት ነው፡፡ለምሳሌ በምስራቅ ጎጃም በቅርቡ መሬት ላይ ካለው እውነታ ባላይ ለህዝብና ቤት ቆጠራ ጭምር ትኩረት እንዲያገኝ ያደረጉት የቅብዐትና የጸጋን ጉዳይ ሳይመነኩሱ ጳጳስ ከሆኑት ወገን ያልሆኑት የሊቁ አቡነ ማርቆስ ጉዳይ ብቻ በማስመሰል በምዕመናን መካከል እስከ ተኩስ የደረሰ ግጭት እንዲፈጠር ከፍተኛ ድርሻ የነበራቸው የዚሁ ብሎግ አባላትና ደጋፊዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ እነዚህን ጨዋዎች ከቤተክርስቲያን ደጀ ሰላምና አውደ ምህረት ገለል እንዲሉ በማድረግ እንጂ በጳውሎስ(መረዋ) ሠርግ ላይ የተደፋበት ጠጅ ሳያንስ ግንቦት 30 ቀን 2011 ዓ.ም በዚህ ሐራዊ ላይ በአምስት ኪሎው የኤፍሬም ውስኪ ቤት እንደተከሰተው ውስኪ ፊቱ ላይ በመድፋት አሊያም በቅርብ ብዙ አባቶችን ሸጦ በሰበሰበው ብር አገባለሁ ብሎ ደጋግሞ ሲያወራ በመሰማቱ በርካቶች በቤተክርስቲያንም ይሁን በአሸሼ ገዳሜ አደርገዋለሁ ብሎ ያሰበውን ሰርጉን እስቲ የትኛው ቤተክርስቲያንና ቦታ ላይ እንደሚያደርግ እናያለን!!! ብሎ በመዛት ለውጥ ይመጣል ብዬ አላስብም፡፡ ዴጄው አሉላ በተከለበሰበት ውስኪና ጠጅ እንዲሁም በዛቻዎቹ በመደንገጡ ከዚያን ቀን ጀምሮ የኢንተርኔት ቤት ደንበኛው ከሆነች እጮኛው ባልተናሰ መልኩ ወደ ሚወዳት ዳሽን ቢራ በትጋት ወደ መጋት ከመመለሱ በላይ በቁም የሚባትት ሁኗል፡፡ ይህን ጉዳይ ያነሳሁበት ዋና ዓላማ ሐራውያን(ጨዋዎች) በአብዛኛው የአእምሮ ቀውስ ተጠቂዎች(mental disorder) ያለባቸው በመሆኑ ውስኪም ይሁን ጠጅ በመድፋት ወይም አካላዊ ጥቃት በማድረስ እሊህን የተዋሕዶ ነቀርሳዎችን ማከም ስለማይቻል ሊረዳቸው ከቻለ ወደ አእምሮ ህሙማን ሆስፒታል አሳምነናቸው ብንወስዳቸው ዋጋ የሚገኝበት ከመሆኑ ባሻገር ቁጥራቸው እየተበራከተ ከመጡት ከሲሞናዊያን ቅድስት ቤተክርስቲያንን ለመታደግ እንደ አንድ እርምጃ ይሆናል ብዬ ስለማስብ ነው፡፡
ጉዳይ ሁለት
አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች በተለይ ከማቅ ጋር ግንኙነት ያላችሁ፣ ደጋፊና አባላት የሆናችሁ በጣም ጥቂቶቻችሁ ከዚህ ቡድን ገጋር በኅቡዕ የምትሰሩ ደግሞ ለምን ተነቃብን ግማሾቻችሁ በዕውቀት ማነስ ምክንያት ግራ የተጋባችሁበት ነገር እንዳለ ስለተረዳሁ ይህንን ብዥታ ላጠራ እፈልጋለሁ፡፡
ለመሆኑ ማቅና ሐራ አንድ ናቸው ?
በፍጹም! እረ በጭራሽ! በየት በኩል!
ሐራ የቤተክርስቲያን ነቀርሳ፤ የአሁኑን ባላውቅም ማቅ ደግሞ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በሃሣብ ጸንሰው፥ በትምህርት ወልደው፥ በመንፈስ ቅዱስ እሳትነት ለኲሰው ለዚህ ያበቁት ማኅበር ነው። ይህ ማህበር በርካታ አንጸባራቂ ታሪኮችን ያስመዘገበ፤ በእነዚህ ስንኩላነ አእምሮ በሆኑ ነቀርሳዎች አመድ አፋሽና እጀ ሰባራ የሆነ፤ እንደ ሰደድ እሳት የተስፋፋ፤ በቀና የቤተክርስቲያ ልጆች አእምሮ ውስጥ የሚኖር የምናብ ማህበር እንጂ (ሐራውያንን ጨምሮ ብዙዎች ሞክረው ያላፈረሱት) ቅድስት ማርያም የቆመ ሕንጻ ወይም የሐራውያን ማህበር አይደለም፡፡
ይሄንን ለማስረዳት ሁለት ነገሮችን በትኩረት ልንረዳቸው የሚገቡ ጉዳዮችን ላንሳ፡-
ትኩረት አንድ
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በመጋቢ 15 ቀን 2009 ዓ.ም በአብዛኛው የቤተክርስቲያን አይጦችንና ነቀዞችን ሰብስበው በጣም በቁጣና በብስጭት ሆነው ‹‹ቤተክርስቲያኒቱ በቅኝ ግዛት ተይዛለች… በማኅበረ ቅዱሳን ቅኝ ተይዛለች›› ያሉበትን ንግግር ሁላችንም ያደመጥን ይመስለኛል፡፡ቅዱስነታቸው፣በርካታ ቁጥር ያላቸው ብጹአን አባቶች፣ መነኮሳት፣የቤተክርስቲያን አገልጋዮች እና የመንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ማኅበሩን አምርረው የሚጠሉት አውቀውት ሳይሆን ወልዶ ያሳደጋቸው፤ አንቱታ ያስገኘላቸው፤ የማኅበሩን ሀብትና ንብረት ወደ ግል ንብረት በማዞር በዘረፉ ስንኩላነ አእምሮ በሆኑ እፉኝቶች ምክንያት ነው፡፡ የማኅበሩ አባላትማ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ብቁ፣ በሥነምግባር የታነጹና በሃይማኖት የበረቱ ዜጎች እንዲሆኑ በትጋትና በፍጹም ታማኝነት የሚሠሩ፤ የአገልግሎት ማከናወኛና የሕንጻ ግንባታ ቦታ መግዣና የመገንቢያ ገንዘብ እጥረት በተከሰተባቸው ጊዜያት፤ የአብነት ት/ት ቤቶች የመፈታት አደጋ በተጋረጠባቸው ጊዜያት፣ ሠርጋቸውን፣ የማስተርስ፣ የፒኤችዲ የትምህርት ፕሮግራማቸውን የሚሰርዙ ለማህበሩ ገቢ ብለው የትርፍ ሰዓት ሥራ የሚሰሩ፣ የሞቀ ቤታቸውን ጥለው አቧራ ላይ መሬት ላይ እየተኙ ጉልበታቸውን፣ ገንዘባቸውን ጊዜያቸው ሰጥተው የሚያገለግሉ ናቸው!!!
ሐራዎች እነሱ ከሌሉ ማኅበሩ እንደሚፈርስ ወሬ በመንዛት በአባላቱ መካከልም የፍርሃትና የጭንቀት መንፈስ ቢዘሩም ጤነኞቹ እነ ዶ/ር ዘርዓየሁ ስሜ ግን ይህን ጉዳይ አጥብቀው የሚቃወሙ ናቸው፡፡በአንድ ወቅት የማኅበሩ ሰብሳቢ የነበሩት ቀሲስ ዶ/ር ሰሙ ምትኩ በአዲስ አበባ ከሚታተመው የቀለም ቀንድ ሳምንታዊ ጋዜጣ ጋር በማኅበሩ አገልግሎት፤ በቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ኹኔታና ተያያዥ ጉዳዮች በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳንን የወለደው፥ ‹እኔ ለቤተ ክርስቲያኔ ምን ማድረግ እችላለኹ?› የሚለው ሐሳብ ነው፤ይጥፋ የሚሉት የጥቅም ጋብቻ የፈጸሙ አማሳኞችና የተሐድሶ መናፍቃን ናቸው›› ያሉት ለዚህ ማሳያ ነው፡፡
ትኩረት ሁለት
ከጥቂት ሳምንታት በፊት በፍትሕ መጽሔት በውስጥ የሽፋን ገጽ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን ወይስ ማህበረ ሰይጣን?›› የሚለው መጽሐፍ ከተዋወቀ በኋላ በዚሁ መጽሔት በ1ኛ ዓመት ቁጥር 12 እትም ላይ በፕሮቴስታንት እምነት ተከታዩ ብርሃኑ ደቦጭ ለምን ሂስ እንዲጻፍ ተፈለገ?(በሰላ ሂሱ እጅግ የማከብረው ብርሃኑ እንዲህ ዓይነት የወረደ ጽሑፍ ሲጽፍ አይቼ ስለማላውቅ ነው) ማን ለምን ዓላማ ጽፎ ሰጠው? የሚሉት ጥያቄዎች አእምሮዬ ላይ ተመላለሱ እኔም እንዴት?ለምን?እነማን? የሚሉት ጥያቄዎች ራሴን መጠየቅ ጀመርኩ፣ ለካ ጉዳዩ ሌላ ኖሯል ያኔ የአዲስ ነገር ጋዜጠኞች በወያኔ ጂሐዲስቶች ሲሳደዱ ከሐራውያን ጋር የቀረበና የጠበቀ ግንኙነት ያለው አንዱ የሐራውያን ወዳጅ ብርሃኑን ከእስር አድኖት ኖሮ ያቺን እንደ ውለታ ቆጥሮ እንዳጻፈው ለማረጋገጥ ችዬአለሁ(ያላዋቂ ሳሚ… እንዲሉ በእኔ እምነት በዚህ ጽሑፉ የመልስ ምት መሆኑ ቀርቶ እንዲያውም የበለጠ መጽሐፉን ያስተዋወቁት ይመስለኛል)፡፡ በነገራችን ላይ የመጽሐፉ ጸሐፊ(ስትራቴጅስቱ ማለቴ ነው) ከመንግሥት አከላት ጋር ቅርበት ባላቸው ጉምቱ አክራሪ የመናፍቃን ቡድን እንደሚደገፍ በተደጋጋሚ ተዋሕዶን የማፍረስ ሥልጠና እየሰጠ እንዳለ፣ የወጣቶች የመናፍቃን ህብረት ወኪል መሆኑን ለመረዳት ችዬአለሁ፡፡ የሆነ ሆኖ ይህን መጽሐፍ ጨምሮ በእኩያን የተጻፉ ማቅ የተብጠለጠለበት እነ ይነጋል፣ የለውጥ ያለህ እና የመሳሰሉትን መጻሕፍት እንዲጽፉ ፣የተቃውሞ ሰልፎች እንዲደረጉ እና ማህበሩ ጥርስ ውስጥ እንዲገባ ያደረጉት የእናት ጡት ነካሾቹ ራሳቸው ሐራውያን መሆናቸውን በመጽሐፎቹ ውስጥ ከተካተተው የጎደፈ ስምና ታሪካቸው መረዳት ይቻላል፡፡




ስለዚህ ሐራውያን የማኅበሩን ካባ የደረቡ ነገር ግን ውስጣቸው ማቅን አምርሮ የሚጠሉ በረቀቀ መንገድ (conspiracy) የሚኖሩ ቆርጠው ካልተጣሉ በስተቀር ለመፈወስ ፈቃደኛ ያልሆኑ የተዋሕዶ ነቀርሳዎች ናቸው፡፡
ይቅርታ ወደ ዋናው ርእሴ ሳልገባ አደከምኳችሁ፡፡ ምን ይደረግ የሐራውያን ደባ ተከድኖ ይብሰል ተብሎ የኖረ ስለሆነ በቀላሉ ተነግሮና ተጽፎ ሰለማያልቅ ነው፡፡
‹‹ሐራ ዘተዋሕዶ›› በእነማን ተቋቋመ?
በዘመቻ ጌድዮን በክፍል አንድ ላይ ከጸሐፊዎቹ አንዱን ተመልክተናል ከዚህ በኋላ ባሉት ክፍሎች የዚህ ብሎግ ባለቤት ማነው? እነማን ይሳተፉበታል? ስብስቡ በከፊል እነማንን ይይዛል? ጸሐፊዎቹ እየታወቁ የፈለጉትን ሲያሞካሹ ያልፈለጉትን ሲሰድቡና ሲያንቋሽሹ ለምን ዝም ተባሉ? የሚሉትን ጥያቄዎችንና ተያያዥ ጉዳዮችን ለመዳሳሰስ እሞክራለሁ፡፡
መቼም ዘመቻ አያሳርፍም አይደል ሐራውያን መቼም የማያሳስቱንና የማያሰሩን ኃጢአት የለም፡፡ ሲፈልጋቻው ሰድበው ተሳዳቢ፣ ሐሜተኛ ውሸታም…አድርገውናል፡፡ መጀመሪያ ሐራ ምን ማለት እንደ ሆነ ለምን መዝገበ ቃላት አላይም ብዬ መፈለግ ጀመርኩ፡፡ የአቡሃ ለሐሰት ልጆች ናቸውና ያገኘሁትና እነሱን የሚገልጻቸው ትክክለኛ የሐራ ትርጓሜ በአለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት ገጽ 464 ላይ ሐራ ማለት ጨዋ(ያልተማረ)፤ሐራዊ ደግሞ የጨዋ ወገን(ያልተማረ ወገን) ብሎ ይፈታዋል፡፡ ጭፍራም ቢሉ ከግብራቸው አንጻር የዲያብሎስ እንጂ የቅድስት ተዋሕዶ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ስለዚህ ሐራ ዘተዋሕዶ ማለት መሠረታዊ የሚባል እንኳ የሚባል የቤተክርስቲያን ዕውቀት ሳይኖራቸው ስለቤተክርስቲያኒቱ የሚጽፉ የጨዋዎች(ያልተማሩ) የአእምሮ ስንኩላን የሆኑ የዲያብሎስ ጭፍሮች ስብስብ ነው፡፡አበው ስም ይመርህ ኀበ ግብሩ ይሉሃል ይሄ ነው፡፡
ለመሆኑ የሐራ ዘተዋሕዶ ብሎግ ባለቤት ማነው?
ከዚህ በፊት ያሉትንና ቤተክርስቲያንን ለመሳደቢያ አባቶችንና አገልጋዮችን ለማዋረጃና ለማሸማቀቂያ ብሎም ለማስገበሪያ የሚውሉ እንደ ደጀ ሰላም፣ አንድ አድርገን የመሳሱት የጡመራ መድረኮች በቤተክርስቲያን ላይ ነቀርሳ አድርጎ የተከለው ማነው? ከጥቅምት 12 ቀን 2002 ዓ.ም ጀምሮ ሐራ ዘተዋሕዶን ያቋቋመው(host ያደረገው)ና ለሦስት ጸሐፍት ምሥጢራዊ መግቢያ ቁልፍ(password) የሰጠው የዚህ ስድ ብሎግ ባለቤትና መሥራች የማቁ መሥራች ‹‹ቀሲስ›› ኤፍሬም እሸቴ ነው፡፡


ይህ ሰውና ግብረ አበሮቹ አንድን ጳጳስ ወይም የቤተክርስቲያን አገልጋይ በራስ ቁጥጥር ስር ለማዋል ከፈለግህ መፍትሔው መስደብ፣ ማሰደብና ማሸማቀቅ ብቻ የሚለው ዋና መርሀቸው ነው፡፡ እስቲ አንድ ማሳያ ላቅርብ በደጀ ሰላም ብሎግ ጥቅምት 4/2003 ዓ.ም በጻፉት ጽሑፍ፡-
‹‹አቡነ ፋኑኤል የእብሪታቸውን ልክ ምናልባትም የእምነታቸውን ጤናማነት በውል በሚያሳይ አኳኋን…‹‹እንኳንስ ለሰው ይቅርና የምትችሉ ከሆነ ለመድኃኔዓለም ብታመለክቱ እኔ አልፈራም፡፡››…የአቡነ ፋኑኤል (የቀድሞው አባ መላኩ) ብልሽት የአሁን ሳይሆን የሊቃነ ጳጳሳቱ ልብስ ሰፊ ሳሉ ጀምሯቸው በሀገረ አሜሪካ ሥር የሰደደ መሆኑን ያስታውሳሉ፡፡… ‹‹በሙግት መኖር እንደሆነ የኖርኩበት ነው፤ ሲሻችሁ በቺቺ መጫረስ ትችላላችሁ፤ በቺቺ ተጫረሱና እኔ ከአሸናፊው ጋራ እሆናለሁ›› ማለት የለመደባቸው ማኬቬሊያዊው አቡነ ፋኑኤል ከዜግነታዊ ማንነታቸው አንሥቶ ክስ ያልተለያቸው ናቸው …‹‹ይሞታል ወይ ታዲያ! ስለ ራሴም ዝና እናገራለሁ፤ እኔ አሜሪካ ሄጄ በሊሞዚን መሽሞንሞን እችላለሁ፤ በችግር የምትቆራመደው አንተ ነህ!!›› በማለታቸው የማያፍሩ ናቸው፡….‹‹በሐዋሳ የካህናት ማሠልጠኛ ውስጥ ለምረዳቸው አሳዳጊ አልባ ሕፃናት አውለዋለሁ›› በሚል ብር እንደሚሰበስቡ ተነግሯል፡፡ ዶላሩን ለማጋበስ የማስመሰያ ቪዲዮ እያቀናበረ የሚረዳቸውም…ቤታቸውን ዘግተው ስለ ቤተ ክርስቲያን ችግር የሚንከራተቱ የሐዋሳ ምእመናን ተወካዮች እግራቸው ሥር ወድቀው በልቅሶ ቢለምኗቸው፣ ‹‹ዘወር በል፤ በልቅሶ የሚሆን ነገር የለም፤ የአዋሳን ምእመን እንዲህ የሚያደርገው’ኮ ወንጌል overdose ሆኖበት ነው›› በማለት የግብረ በላዎቻቸውን ድምፅ የሚያሰማ ኀይለ ቃል ተጠቅመዋል፡፡‹‹የሕዝቡን ጫጫታ እንደ ሳውንድ ትራክ ተጠቅመን ሥራችንን ሠርተናል›› በማለት መሣለቃቸው ተሰምቷል፡፡…በወቅቱ አቡነ ፋኑኤል በአደባባዩ እንዲህ ብለው ነበር – ‹‹መንግሥት የራሱን ወታደር አሠማርቶ እነዚህን ሰዎች (የሐዋሳ የፍትሕ እና ልማት ኮሚቴ አባላት) የማይቆጣጠር ከሆነ እኔ የራሴን ሚልሻ እመለምላለሁ፡፡››
እና የመሳሰሉ ርካሽ ክብረ ነክ ቃላት በተደጋጋሚ ሲጽፍባቸው የነበሩትን አባት ንስሐ ገብቶ ይሁን አይሁን ባላውቅም በኋላም ከነ ልጁ ሥልጣነ ክህነት የሰጡትን ከባቴ አበሳ የሆኑትን የሰሜን አሜሪካ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፋኑኤልን ይዛችሁ ስለ እኩይ ተግባሩ አናግሩት፡፡ እርግጠኛ ነኝ አይክዳችሁም፡፡

በነገራችን ላይ ኤፍሬምን ከአዲስ አበባ ወደ አሜሪካ ይዛው የገባችው መርከብ የአ.አ.ዩ ተማሪዎች ከቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን መታፈስን ተከትሎ በሚያዝያ ወር 1993 ዓ.ም በስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ላይ የጻፋት ጽሑፍ ነች

እኔ ግን ሁል ጊዜ ጥያቄ የሚፈጥርብኝና በጣም ግራ የሚገባኝ በ1982 ዓ.ም ከነበረበት የጫትና የሲጋራ ሱስ እንዲላቀቅና ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ጋር ንስሐ እንዲገባ ያስተማሩትን አባቶችና ወንድሞች ለመዝለፍ፤ ሳትጸየፍ ከነ ሱሱ ተቀብላ እስከ ቅስና ማዕረግ እንዲደርስ ያደረገችውን ቅድስት ቤተክርስቲያንን በአደባባይ ለማዋረድ ለምን ፈለገ? ባለውለታው ማቅን ለምን ቤተ ክርስቲያን እንደገባ ውሻ ለምን እንዲታይ አደረገ? የሚሉት ጥያቄዎች ናቸው፡፡
በእርግጥ ኤፍሬም ምንም እንኳ አሜሪካ ስለሆነ ሆስት ያድርገው እንጂ ብሎጉን የመቆጣጠር ኃለፊነት በዋናነት የተረከበው የሁሉም ሐራውያን የነገር አባት ተኩላውና መሠሪው ዳንኤል ክብሪት(ክስረት) ነው፡፡ የእርሱን ጉዳይ በጊዜው የምመጣበት ሲሆን እኔ በርግጥ ደጋግሞ ባሳተማቸው ከመናፍቃን ከካቶሊክና ከሌሎች ዓለማውያን የተውጣጡ የተረት መጻሕፍቶቹ ላይ ስለ ወያኔ የግፍ አገዛዝ የማይጽፈው በአንድ ወቅት እኔው እራሴ ለአንድ ጉዳይ መስቀል አደባባይ ከሚገኘው አቦይ ስብሐት ቢሮ ተገኝቼ በጆሮዬ እንደሰማሁት ‹‹እኛንም በጠበጣችሁን፣ሰላም ነሳችሁን፣ ይሄን ውሻ ሰውዬም(ፓትርያርኩ) ብንነግረው አልሰማ አለ፣ ቤተክርስቲያን መፍረስ ነበረባት፣ ዳሩ ምን ዋጋ አለው ኩሽና እንኳን ሲፈርስ ብዙ ጥንቃቄ ይፈልጋል….›› የሚሉ ከበረሃ ጀምሮ ቤተክርስቲያንን የማፈራረስና የመከፋፈል ዕቅድ፣እኩይ ራዕይና ሰይጣናዊ ምኞቱ ያነገቡ የህወሓት መሪዎች ተከታይና ደጋፊ የሆነችውና ቀጥቅጣ የምትገዛው የአሁኗ ባለቤቱ አጠገቡ ስላለች ይመስለኝ ነበር፡፡ ከድርጅቱ መሥራቾች አንዱ የሆኑት ዶ/ር አረጋዊ በርሔ ለዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ በሚል ርእስ ሠርተውት ኋላ ወደ መጽሐፍ በቀየሩት “The Origin of TPLF” በሚለው የጥናት ጽሑፉ ላይ
‹‹የቤተ ክርስቲያኗ ሥልጣን (በትግራይ የነበረውን) ለማድቀቅ ሲባል በስብሃት ነጋ የሚመራ የስለላ ቡድን ተቋቋመ፡፡ ይህ ቡድንም ደብረ ዳሞን ጨምሮ በትግራይ ውስጥ ባሉ ገዳማት አባላቱን መነኰሳት በማስመሰል፣ የገዳማቱን እንቅስቃሴ በህወሓት ፍላጎት ሥር የማስገዛት ሥራ ሠርቷል›› በገጽ 317 ላይ ገልጧል፡፡
ድርጅቱ ሙሉ በሙሉ ሃይማኖትን ጠቅልሎ ለመያዝ የተነሣበትን ገፊ ምክንያትም እንዲኽ በማለት አብራርተዋል፡–
‹‹ቤተ ክርስቲያኗ ተከታዮቿን፣ ለነበረው የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲገዙ ከማስተማር በዘለለ የብሔራዊ ንቃት(ማንነት) ማስተማርያም ነበረች፡፡ …ለህወሓት እንቅስቃሴ ዕንቅፋት እንደነበረች ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህም ቤተ ክርስቲያኒቱን በህወሓት ዓላማ ሥር ለማሳደር ፍላጎት ነበር፤ በዚህ የተነሣም የእርስዋን ተጽዕኖ ለማግለል ጥልቅ ርምጃ ወስደዋል፡፡›› /ገጽ 315 – 316/ ዶ/ር አረጋዊ ‹‹ጥልቅ ርምጃዎች›› ብለው ከጠቀሳቸው መካከል አንደኛው ‹‹ለአጥቢያ ቀሳውስቱ ኮንፈረንስ በማዘጋጀት፣ በትግራይ ውስጥ ያሉትን አብያተ ክርስቲያን ለብቻ ነጥሎ ህወሓት በሚያራምደው የትግራይ ብሔርተኝነት ሥር ማካተት›› እንደነበረ በዚኹ መጽሐፍ ጠቅሷል፡፡
እኔ ባለኝ መረጃ መሠረት ደግሞ አቦይ ስብሐት ነጋ ራሱ ከወሰዳቸው ጥልቅ እርምጃዎች አንዱ የለውጥ እንቅፋት ናቸው ያላቸውን በርካታ ንፁሐን የትግራይ ካህናትንና አገልጋዮች መጨፍጨፍ ነው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ኢሕአዴግ አንድን አካል(ስብስብ) በአደባባይ ከነቀፈ ከዚያ ስብስብ መካከል በስውር አብረውት እየሰሩ ያሉ አካላት እንዳሉ መጠርጠር እንዳለብኝ የተረዳሁት ዘግይቼ ነው፡፡
በዚህም መሠረት ሕወሓቶች አንዱና ዋንኛ ዕቅድ አድርገው የያዙትን ራዕይ ማለትም የተካፋፈለች ቤተ ክርስቲያን፣ አቋም አልባ ጳጳሳት እና አንድነት የሌላቸው አገልጋዮች አንዲኖራት ለማድረግ ሕወሓት መራሹ መንግሥት አስርጎ የማቅ አባላት ካደረጋቸው አባላት በተጨማሪ ተመራጭ ካደረጋቸው ብሎጎች አንዱ ሐራና ታላቅ እህት ብሎጎቿ መሆናቸውን ወስጠ ምስጢራቸውን የሚያውቅ አንድ ወዳጃቸው በቅርብ አጫውቶኛል፡፡
ታዲያ አድር ባዩና አስመሳዩ ወንድሜ ኤፍሬም እሸቴ በቃሉ፣ እንዲሁም እንደ መስቀል ወፍ ብቅ በሚሉና በአሜሪካ በሕልውና ለመቆየት ወሳኝ ከሆኑት ጉዳዮች አንዱ የሆነውን ሕወሓት መራሹን መንግሥት መሳደብና መንቀፍ የሚለውን መርህ ተግባራዊ ለማድረግ ሲሞካክር ሳየው አሳዝኖኝ ከንፈሬን መምጠጤ አልቀረም፡፡

አንደው ግን ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የደከሙባቸው ልጆቻቸው እንዲህ መክነው ሲቀሩ ምን ይሉ ይሆን?
በቀጣይ ክፍል ስለሌሎቹ ሐራውያን አስተዋውቃችኋለሁ
የፈራ ይመለስ!
ሳምኬት ነኝ
ቸር ሰንብቱ!
ሰኔ 25/2011 ዓ.ም