ዘመቻ ጌዴዎን ክፍል አንድ
ዘመቻ ጌዴዎን በቤቱና በሕዝቡ ላይ በክፋትና በተንኮል በሚነሱ ሁሉ ተዋጊውና ድል አድራጊው እግዚአብሔር ብቻ መሆኑን የምንረዳበት ታሪክ ነው፡፡በዚሁ መጽሐፍ ላይ ሰፍሮ እንደምናገኘው ጌዴዎን በእስራኤላውያን ላይ በትዕቢትና ማንም ሊያሸንፈን አይችልም ባይነት የተነሱትን ምድያማውያንና አማሌቃውያን በመለከት፣በማሰሮና በመብራት ‹‹የእግዚአብሔር ኃይልና የጌዴዎን ጦር ደረሰብህ›› ብለው በመጮኸ ብቻ እስራኤላውያን ድል እንዲያደርጉ ከእግዚአብሔር መመሪያ የተቀበለ መስፍን ነው፡፡፡፡ለዘመቻ ጌድዎን የተነሱት የሰዎች ብዛት 22ሺህ ቢሆንም እግዚአብሔር ሊሠራባቸው የፈለገው ሦስት መቶ ሰው ብቻ ነው፡፡ፈሪና ቦቅቧቃዎችን ስላልስፈለገጉ በዚህ ላይ ደግሞ ፊሪ ሰው ስለ ወገኑም ሆነ ስለ ሀገሩ ፍቅር ስሌለው የማሸንፍ ወኔ ሊኖረው ስለማይችል 1ዮሐ4፡18 ይህ ዘመቻ ‹‹የፈራ ይመለስ›› በሚል አዋጅ እግዚአብሔር ሊሠራባቸው በፈለጋቸው 300 መቶ ሰዎች ብቻ ጦር ሳይመዘዝ የጌዴዎን ጦር የደረሰባቸው መስሎአቸው በራሳቸው ሾተል እርስ በእርሳቸው ተላልቀው የጠፉበት የእግዚብሔር ኃይል የተገለጠበት የድል ዘመቻ ነው፡፡
ዛሬም በዚህ በእኛ ዘመን በቤተክርስቲያን ውስጥ መሽገው ያሉ ሐሳውያንና ሲሞናውያንን ‹‹የእግዚአብሔር ኃይል የተዋሕዶ ልጆች መጡባችሁ ነቁባችሁ›› ብለን ኦሮቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን ለማፈራረስ የተሰለፉትን አካላት ንስሐ እስኪገቡ እምቢ ካሉ ደግሞ ከሐዋርያዊቷ ቤተክርስቲያን እስኪወጡ ድረስ የምንዋጋበት ጊዜው አሁን ይመስለኛል፡፡በሀገራችን ላይ ያለው ፈርጀ ብዙ ችግር ሳያንሰን ስለ ሆዳቸው ሙላትና ስለ ደረታቸው ቅላት በሚጨነቁ ውሪዎች ምዕመናን ቤተክርስቲያንን መጽናኛ፣ መጠጊያ አባቶችን የችግራቸው ተካፋይ እናዳይሆኑ በችግር ላይ ችግር እንዲጫንባቸው የአእምሮ ማረፊያና መጽናኛ እንዳያገኙ የዲያብሎስ መልእክተኞች አጥብቀውና ዓላማ ሰንቀው እየሠሩ ይገኛሉ፡፡
አብዛኛዎቻችን አርቆ አሳቢነት ከላያችን ተገፎ ጥቅመኝነት፣ ሐሜት፣ውሸትና አድመኝነት ሰልጥኖብን ክርስቶስ ለኃጢአተኞች መሞቱ ተረስቶ ኃጢአተኛ ከተገኘ ከመምከርና ከመመለስ ይልቅ ቤተ ክርስቲያን እንደገባ ከልብ ሰዎችን ማሳደድ ዋና መገለጫችን ሆኗል፡፡ ምክክራችንና ውሳኔያችን ከአራት ኪሎ ካፌዎችና ውስኪ ቤቶች አለማለፋቸው ደግሞ እጅግ የሚያሳዝንና የዝቅጠት ደረጃችንን ማሳያ ነው፡፡ወደድንም ጠላንም ዛሬ ሕዛባችን ላለበት የስነ ምግባር ጉድለት፣የሞራል ልዕልና እጦትና የእምነት ገድለት ቤተክርስቲያንና የቤተክርስቲያን ሰዎች ከተጠያቂነት ማምለጥ አንችልም፡፡አልታደልንም እንጂ ካለብን ትልቅ ኃላፊነት የተነሳ ኅብረተሰባችን የላቀና የበለጸገ ሀሳቦች ባለቤት በማድረግ ሲገባን ራሳችን ውሸተኞች አድመኞችና ሲሞናውያን ሆነን ሕዝቡንም የዚሁ ሰለባ በማድረግ ስለሃይማኖቱ ለዘብተኛ አቋም እንዲኖረው ብሎም የሃይማኖቱን ጉዳይ ለጆቢራዎችና ለቤተክህነቱ አይጦች አሳልፎ በመስጠት እጁን አጣምሮ እንዲቀመጥ ወኔው የተሰለበ አማኝ አንዲኖረን በማድረግ ተጠያቂ መሆን የሚገባን እኛው ነን፡፡ እኒህ ዓይነት ችግሮች ደግሞ በዘመቻ ካልሆነ ማስወገድ አይቻልም፡፡
ይህን ጽሑፍ ለማጻፍና ‹‹ዘመቻ ጌዴዎን›› መጀመር አለበት እንድል ያስቻሉኝንና ያነሳሱኝን ሁለት ምክንያቶች ልግለጥ፡-
፩. በአንዳንድ ‹‹ታዋቂ›› ሰባኪና ዘማሪ ወንድሞቻችን የሰርግ መርሐ ግብር ላይ የሚገኙ ታዳሚዎችን ላስተዋለ በትክክል ተደራጅተው ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ የሚንቀሳቀሱ መፍቀሬ ነዋይ ሲሞናውያን፣ ለቤተክርስቲያ ተቆርቋሪ መሳዮችና አስመሳዮች ሰውን ተሐድሶ እያሉ የሚያሸማቅቁ በተግባር ግን ራሳቸው ሊበራል ተሐድሶዋያን መኖራቸውን ለማረጋገጥ ጊዜ አይፈጅበትም፡፡ዝም ብላችሁ ጠጋ ብላችሁ ካዳመጣችሁ አባቶችን ለገብያ በማቅረብ ስለሚያገኙት ትርፍ ሲወያዩ፣ሲከራከሩ እና ሲጣሉ(በሽያጭ ዋጋ ማለቴ ነው) ስታዩ ልክ እንደ እኔ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ መግባታችሁ አይቀርም፡፡ በነገራችን ላይ በተለይ በቅርብ ጋብቻቸውን የፈጸሙ የእነዚህ ‹‹ታዋቂ›› ወንድሞቻችንን የሠርግንና የመልስን ቪዲዮ ወይም ፎቶ ካገኛችሁ ለቤተክርስቲያን ውደቀትም ይሁን ልማት የሚሠሩ ቡድኖችን በግልጽ ታዩበታላችሁ፡፡
፪.ሌላው ምክንያቴ በግንቦት ወር 2011 ዓ.ም እየተደረገ ያለውን የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ለግል ጥቅም ማጋበሻ እና ንጹሐን፣ ብጹአን ቅዱሳን አባቶችን ለማስፈራሪያነት በመጠቀም በተደራጀና ስልታዊ በሆነ መልኩ በመደራጀት አንዱ ወገን ሰዳቢ ከዚያው ቡድን ደግሞ ሌላው አስታራቂ ሆነው ገንዘብ ተቃባዮች እየተበራከቱ ስለመጡና በራዕ 13፡5 መሠረት ‹‹የስድብን አፍ›› ከአውሬው ተቀብለው እየተንቀሳቀሱ ያሉ አካላት መሳቂያ መሳለቂያ ሊያደርጉን ከምን ጊዜውም በላይ ተደራጅተው መንቀሳቀስ በመጀመራቸው ሥር ነቀል ዘመቻ ያስፈልጋል ብዬ በማመኔ ነው፡፡
ስለዚህ በመጀመሪያ ክፍል ጽሑፌ ሁለተኛውን ምክንያት ላብራራ እሞክራለሁ፡-
በነገራችን ላይ ‹‹ዘመቻ ጌዴዎን›› የሚያስፈልግበት ምክንያት እጅግ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ የክፍለ ሀገር ጉባኤያትን ጠልና ናቂዎች የሆኑ (በርግጥ እነሱ የገጠር የሚሉት ከእነሱ የተሻለ የሚያምንና ሃይማኖቱን የሚረዳ በመሆኑ ስብከታቸውና ዝማሬያቸውን ከእነሱ የእምነትና የዕውቀት ደረጃ በታች ስለሆነ የእነሱን ተረት ለመስማት ጊዜው ሊኖረው ባለመቻሉ ) ‹‹ታዋቂ›› ሰባክያንና ዘማርያ በአብዛኛው በጥቅም ላይፋቱ እርስ በእርስ የተሳሰሩ በመሆናቸው በዋነናነት ደግሞ ለሕዝቡም ይሁን ለቅድስት ቤተክርስቲያን ፍቅር ስሌላቸው ይፈራሉና እውነትን ቢናገሩና ቢሰብኩ ጥቅማቸው ስለሚቀርባቸው 1ዮሐ4፡18 ፍቅር የሌለው ሰው ደግሞ ፈሪና ለሆዱ አዳሪ በመሆኑ ‹‹የፈራ ይመለስ›› ብለናቸው በአባቶች ጸሎት ታግዘን ቀኖና ቤተክርስቲያንን ጠብቀን ኃይለ እግዚአብሔር ተደግፈን ለሰልፍ ልንወጣ ይገባናል፡፡
ስለ ተዋሕዶ ሃይማኖት መስፋፋትና መጠናከር ስለ ምዕመናን ድኅነት ከሚገዳቸው ለዚህ ዘመቻ ፈቃደኛ ከሆኑ አባቶች፣ ወንድሞችና እህቶች ምክክር መረዳት የቻልኩት ዐቢይ ነገር ሌሎች የእምነት ድርጅቶች በርካታ አስተዳደራዊ ሥነ ምግባራዊና ሃይማኖታዊ ችግር እያለባቸው የውስጥ ችግራቸውን በውስጥ እየፈቱ ባለበት ዘመን በእኛ በኦርቶዶክሳውያንን ቤት ግን እየሆነ ያለው ስም የማጥፋት ዘመቻና አስተዳደሯን የማዳከም ዘመቻ አይደለም በአማኞቻችን በከሀዲያን በአላውያን እንኳ ተፈጽሞ አያውቅም፡፡ዳሩ እነዚህ አካላት ጥንተ ታሪካቸው እንደሚያስረዳን ጉባኤ ቤት ያልዋሉ ያላደሩ ብቻ ሳይሆን በጉብኝት መልክ እንኳ ጎራ ብለው የማያውቁ ከመንገድ ተጠልፈው ከመንጋው የተቀላቀሉ የከሰሩ ነጋዴያን ናቸው፡፡ስለዚህ የዘመቻው መጀመሪያ በመንፈስ ቅዱስ ስለሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ ግንዛቤው፣ ዕውቀቱ ከምንም በላይ ደግሞ እምነቱ የሌላቸው ስለሆኑ ዘመናዊ የድምጽና የምስል መቅጃዎች በሲሞናውያን በኩል በማስገባት ቅዱስ ሲኖዶስ ብቻ አይቶና አመዛዝኖ ብያኔ ሊሰጥባቸው የሚገባቸውን አጀንዳዎችና ጉዳዮች ለአደባባይ መሳቂያና መሳለቂያ በማድረግ ሥጋዊና ቁሳዊ ፍልጎታቸውን እያሟሉ ባሉ የጡመራ መድረኮች(ብሎጎች) ይሆናል፡፡ ለዚህ ጽሑፍ ይህን ዕድል አግኝቶ የተመረጠው የጡመራ መድረክ ‹‹ሐራ ዘተዋሕዶ›› ነው፡፡
በዚህ የመጀመሪያ ክፍል ‹‹ሐራ ዘተዋሕዶ›› ለምን ዓላማ ተቋቋመ? ጸሐፊዎቹስ እነማን ናቸው? የሚለውን እንመለከታለን
‹‹ሐራ ዘተዋሕዶ›› ለምን ዓላማ ተቋቋመ?
በእነሱ የጡመራ ገጽ ላይ ይህ የጡመራ ገጽ ለምን ዓላማ እንደተቋቋመ እንዲህ በማለት ይገልጹታል ፡-
‹‹ሐራ ዘተዋሕዶ – የተዋሕዶ ሠራዊት፣ የተዋሕዶ ወታደር፣ የተዋሕዶ ጭፍራ ማለት ነው፡፡ ሐራ – ሐርነት፣ ነጻነት ያለው ማለት ነው፡፡ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን ትምህርትና ሥርዐት፣ ትውፊትና ታሪክ ለማጥፋት በውስጥና ከውጭ የሚንበለበሉትን የአፅራረ ቤተ ክርስቲያን ፍላጻ ለመመከት የእምነትን ጋሻ አንሥተን እንጦምራለን፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ብሔራዊ ክብርና ተቋማዊ ነጻነት በማንበር ሐዋርያዊ አገልግሎቷ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲጠናከርና እንዲስፋፋ የመረጃንና የዕውቀትን ሰይፍ በመያዝ እንጦምራለን፡፡ በአገልጋዮችና ምእመናን አዎንታዊ ተግባቦት ለተጨባጭ ለውጥ የሚያበቃ የመንፈስና የተግባር ተናሥኦት (Uprising) እንዲፋፋም እንጦምራለን፡፡ ስለዚህም ሐራውያን ለተዋሕዶ – የተዋሕዶ ሠራዊት፣ የተዋሕዶ ወታደሮች፣ የተዋሕዶ ጭፍሮች ነን፡፡››
እነሱ እንዲህ ነን ቢሉም መጋረጃው ሲገለጥ ታሪካቸውና ዓላማቸው ከዚህ በፍጹም ተቃራኒ ሆኖ እናገኛለን፡፡ ልብ ብሎ ላስተዋለው ዓለም በቴሊቪዥንና በፊልሞች የአውሬውን መንፈስ እያስተዋወቀች እንዳለው ሁሉ በዚህ የጡመራ መድረክም ምንም ዓይነት ሙያዊ ትንታኔ ሳያስፈልገው ከጥቅምት 12 ቀን 2002 ዓ.ም ጀምሮ ያለውን ጽሑፍ በአስተውሎት ለተመለከተ የአውሬውን መንፈስ እያለማመዱንና እያስተዋወቁን እንደሆነ፣ ከእምነት ትምህርቶች ይልቅ የምንፍቅና፣ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ጽሑፎች ይልቅ ፍጹም ኢ-ቀኖናዊ የሆኑ ጽሑፎችን በተደጋጋሚ ይጽፋል፤ ትውልዱ የቤተክርስቲያን ጉዳይ መቼም ቢሆን የማይስተካከል ነው ብሎ እንዲያስብና እንዲያምን፤ ገለልተኛና ለዘብተኛ ሆኖ እነሱ የፈለጉትን ማንገስ ያልፈለጉት መደቆስና ማኮሰስ የሚችሉ አይነኬ ናቸው ብሎ እንዲያስብ በምናባዊው ጭራቅ እንዲመስላቸው እነሱ ባሉበት ቦታ ሁሉ በለሆሳስና በጭንቀት እንዲያወራ አድርገን ያነገስናቸው የጥልቁ መልእክተኞች ናቸው፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነው ሐራውያን ከሐሳዊ መሲህ መገለጫዎች አንዱ የሆነውን ተሳዳቢነት ምዕመኑ እንዲለማመድ የቤተክርስቲያን አባቶችን ከብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጀምሮ እስከ አጥቢያ ምዕመን ድረስ ያሉትን መስደብ ማቃለል እንዲለማመድ እንዲሁም አማኙ ምን አባት አለ ብሎ ከንስሐና ከንስሐ አባት ውጪ እንዲኖር ማድረግ ኅቡዕ ዓላማቸው ነው፡፡ታዲያ ይኽ ለሐራውያ ምን ይጠቅማል ? ካላችሁኝማ በቃ ዋንኛ መተዳደሪያቸው ነው፡፡የአሠራር መንገዳቸው አንዱ ጋንታ የእገሌን ስም ላጥፋልህ ብሎ ብር ይቀበላል ሌላው ደግሞ ጸሐፊዎችን አግኝቼ ሁለተኛ እንዳይጽፉብህ ላድርግ ወይም አውግዝልሃለሁ ይላል፡፡ በቃ በአጠቃላይ ሐራ ዘተዋሕዶ ለምን ተቋቋመ ቢባል ሲሞናዊነትና ሐሳዊ መሲህነትን አለማምዶ ከቤተክርስቲያኒቱ የማይነጥፍ ሀብት ለግል ጥቅም ለማግበስበስና ቤተክርስቲያኒቱን ለማፈራረስ ነው፡፡ ሐራውያን በተጨባጭ ጸረ-ተሐድሶ እንደሆኑ ራሳቸውን ቢሰብኩንም እንደ አንድ ሊቅ ወንድሜ አገላለጥ በተጨባጭ ሊበራል ተሐድሶዎች ናቸው፡፡ ምክንያቱም ዋና ራዕያቸው ምዕመናን ከቤተክርስቲያን አባቶች ተለይቶ በእነሱ ዓይነት ጥቁር ራስ ጨዋዎች ስትመራ ማየትና ቤተክርስቲያኒቱን ሐዋርያዊት የሚያሰኛትን ከሐዋርያት ጀምሮ ሲወር ሲዋረድ እኛ ዘመን የደረሰውን ሥልጣነ ክህነት መክኖ ማየት ነው፡፡እዚህ ላይ ሐራ ከተቋቋመች ወዲህ ምን ምን ጻፈች የሚለውን በሠንጠረዥ ከማብራሪያ ጋር ወደ ፊትስለማቀርብ ተራ አሉባልታ እንደሆነ ትረዱልኛላችሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
ውድ አንባቢያን! በዚህ ክፍል ከሐራውያን መካከል የአንዱን እንደማሳያ በማቅረብ የሐራውያንን ማንነትና ጥንተ ታሪክ በመግለጥ መሠረተ ቢስ አሉባልታ አናፍሾች ፤ ሕዝብን አደናጋሪዎች መሆናቸውን የበለጠ ግልጽ ለማድረግ እሞክራለሁ፡፡ከሐራውያን ጋር የሚሰሩ እና በቤተክህነት መዋቅር ውስጥ ሆነው ከቤተክርስቲያን በሲሞናውነት የሚጠቀሙ ወንበዴዎችንና ቤተክርስቲያንን የወንበዴዎች ዋሻ ለማድረግ የተሰለፉ ወንበዴዎችን ጉዳይ እና ከፒያሳ ዶሮ ማነቂያ ወደ 5 ኪሎ በተዛዋወረውና ዋንኛ የመገበያያ ማዕከል ስለሆነው ኤፍሬም ውስኪ ቤት ጉዳይ ወደ ፊት በስፋት የምመለስበት ይሆናል፡፡
‹‹ሐራ ዘተዋሕዶ›› በእነማን ተቋቋመ?
‹‹ሐራ ዘተዋሕዶ›› ደጀ ሰላም የሚባለውን ብሎግ መዘጋት ተከትሎ የተቋቋመ ISIS(If you pay you are Safe; If not you can`t Survive›› የሚለውን ሲሞናዊ ዓላማ አንግቦ የተነሳ የመገበያያ(የነጋድያን) የጡመራ መድረክ ነው፡፡ በቃ በቤተክርስቲያን ሕይወትህ ወይም ሥራህ በተለይ ደመወዝ ከቤተክርስቲያን የሚከፈልህ ከሆንክና በተለይ ደግሞ ድቀት ከገጠመህ ፀረ-ገሪማውያ(ገሪማ ገረምከነ) ስለሆኑ፤ ተረጋግቶ በንስሐ ራስን ማረም በእነሱ ዘንድ ተቀባይነት ስለሌለው በሐራ ዘተዋሕዶ እንዳትብጠለጠል ከፈለግህ መክፈል አሊያም ወደድክም ጠላህም የማቅ ደጋፊ መሆን ብቻ ነው አማራጭህ! በነገራችን ላይ ይህ የመገበያያ ብሎግ በነገር አባታቸው በሁለ ገቡነና ራሱን በሾመው ‹‹የታሪክ ተመራማሪ፣ደራሲ፣ሀያሲ፣የሃይማኖት መምህር፣የተረት አባት፣የመንግሥት አማካሪ፣ፓለቲከኛ እና ወደ ፊት ምናልባት ታዋቂ ባለሐብትና ….›› በሆነው ግለሰብ መሪነትና አመካሪነት የተመሠረተ ነው፡፡ እናም አንዳንድ ያልነቁና ያልተረዱ የዋህ የማቅ አባላትንና ደጋፊዎችን የሚያታልሉት ከልብ ሳይሆን በአፍና በመጻፍ ስለ ማቅ ሲነሳ ለምን ይነካል ብሎ ፉከራና ሽለላ በማሳየት ነው፡፡ ይህን ለመረዳት የነገር አባታቸው ለምን እና እንዴት ከማቅ ወጣ? ብሎ ለጠየቀ መልሱ ቅርብ ነው፡፡ይኸው ግለሰብና ቡችሎቹ ማኅበሩን ከሦስቱም መንፈሳዊ ኮሌጆቻችን ደቀ መዛሙርት፣ከሊቃውንት አባቶች ከሰ/ት/ቤት አባላት የማኅበሩን ልሳን በመጠቀም በተደጋጋሚ ይሳደቡ፣ያጋጩ ያደባድቡና ያስወግዙ እንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡ በነገራችን ላይ ከዚህ ሰው ጋር ለመቆየትና ለመኖር የፈለገ ሰው በእሱ ሳንባ መተንፈስ በየሄድክበት ስሙ ተነሳም አልተነሳም ስለ እርሱ መስበክና መመስከር ግዴታ ነው፡፡ያለዚያ አንድ ታፔላ ተለጥፎልህ ስትብጠለጠል ስትሳደድ ትኖራለህ፡፡አሁን ግን ስለዚህ ሊበራል ጴንጤ የማወራበት ጊዜውና ተራው ስላልሆነ፤ በዚህ በዛሬው ጽሑፍ እሱ ካለፈበት የሕይወት መስመር ማለት ተንኮለኛነት፣ ተሳዳቢነትንና ሐሳዊነትን እንዲሁም ቤተክርስቲያን ውስጥ በተኩላነት የመኖርን አቅም እስኪያጎለብት ድረስ ተንከባክቦ ስላሳደገው ስለ አንዱ ቡችላ ላውጋችሁ፡፡
ይህ ቡችላ ሐራዊው አሉላ ጥላሁን(አብሮ የሚውላቸው ባልንጀሮቹ እጅግ ታዋቂነትን ባስገኘለት ሥራው ‹‹ዲጄው››ና ሰካራምነቱ ‹‹ጠጆ››…እያሉ ይጠሩታል)


ብዚ ጊዜ ወዳጆቹ አሉላ ብዙ እንዲያወረሰ ከፈለጉ የሚያቀርቡት ጠጅ ነው፡፡
ይህ ግለሰብ ከሐሮምያ ዪኒቨርስቲ በግብርና የመጀመሪያ ድግሪ እና ከአ.አ.ዩ በፍልስፍና ትምህርት የሁለተኛ ድግሪ ያገኘሲሆን(ወደፊት የሚጣራ ይሆናል) ለአቅመ ራስን መቻል እንዳይችልና በተላላኪነት እንዲኖር የተደረገ የመከነ ጎበዝ አርታኢ ነው፡፡ ይህ ወንድማችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አሳዳጊዎቹና አሳዳሪዎቹ ባለባቸው ‹‹የአማካሪነት›› እና የስላይድ ንግድ ሥራ ጫና ምክንያት ገሸሽ አድርገውት ስላሉ የእሱ ገብያ በሚደራበት የጥቅምትና የግንቦት ሲኖዶስ (ወደ ፊት ስብሰባው በዓመት 4ት ጊዜና ከዚያ በላይ እንዲሆን እንደሚጦምር ተስፋ አለኝ) ካልሆነ በስተቀር የእለት ጉርሱን በብድርና ጋባዥ በመፈለግ እንደሚኖር አውቃለሁ፡፡ ታዲያ ዲጄው ከወታደርነት ስኳድ ከተቀነሰ ጊዜ ጀምሮ ሱሱ አለቀው ብሎት ዛሬም አባቶችንና ወንድሞችን እየነጠሉ የመምታትና የማሸማቀቅ ሰትራትጂ በአግባቡ እየተጠቀመበት እና በዚሁ ለመተዳደር አማራጭ ያደረገ ይመስላል፡፡

ይህ ወንድማችን መቼም ያልሞከረው እና ያልገባበት መስክ ባለመኖሩ በአንድነት የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ አባል ሆኖ በነበረበት ጊዜ በሠራው መረጃ የማቀበልና የስለላ ተግባር ፓርቲውን ለማፈራረስ ባደረገው ሙከራ ተደጋጋሚ እስርና ከሀገር የመውጣት ክልከላ ደርሶበታል፡፡

አዲስ ሥራ ለመጀመርና የፖሊተካ ፓርቲ አባል ለመሆን በደጅ ጥናቱ ወቅት

ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ ከዲጄነቱ ጋር በተያያዘ የራስታን የኑሮ ዘይቤ የሚከተል እና በእነሱ መንገድ ለመኖር በተደጋጋሚ ጥረት እንደሚያደርግ በራሱ ብሎግ ላይ ተለጥፎ ከነበረው አሁን ግን ካነሳው መልእክት መረዳት ይቻላል፡፡

ዲጄነቱን የሚያውቁ ሰዎች በጃንሜዳ የድምጽ ችግር ገጥሞአቸው ለማስተካከል ሲውተረተር

እዚህ ላይ መነሳት ያለበት ጥያቄ የራሷ የታወቀና የተረዳ እምነት፣ ቀኖናና የአስተዳደር ዳኝነት ያላትን ሉዓላዊት ቤተክርስቲያን ለማፈራረስ፣ለማተራመስ፣እና አንድነቷን ለመፈታተን ሐራውያን ለምን እና በምን ዓላማ ተነሣሡ? ማን ቀጠራቸው? ቅኝ የገዛቸው ማነው? ለሚለው ጥያቄ መልስ ማግኘት እልህ አስጨራሽ ቢሆንም ለቅድስት ቤተክርስቲያን የወደፊት ህልውና የግድና ወሳኝ ነው፡፡ ይህ ወንድማችን ከማቅ ጋዜጣ አዘጋጅነትና ከማኅበሩ መደበኛ ሠራተኝነት ለምንና እንዴት ተባረረ? ዛሬስ መደበኛ ሥራና ደመወዝ የሌለው ሆኖ ሳለ በቅርብ ጊዜ የቤትና የመኪና ባለቤት ለመሆን በዝግጅት ላይ እንዳለና ሚስት ለማግባት የኢንተርኔት ቤት ደንበኛው በእጮኝነት ይዞ ለጋብቻ በዝግጅት ላይ መሆኑን በተለይ ትንሽ አልኮል(በተለይ ጠጅ) ሲቀማምስ አብሾ እንዳለበት ሰው እንዲለፈልፍና እንዲፎክር ያስቻለው ከማንና ከእነማን በሚያገኘው የገቢ ምንጭ ተማምኖ ነው? የሚሉት ጥያቄዎች የተሰማራበትን ዋናውን ዓላማ ለመረዳትና መፍትሔ ለማግኘት እንደሚረዳን አምናለሁ፡፡
ሐራዊው(ወታደሩ)፣ዲጄው፣ሰላዩና ፖለቲከኛው አሉላ ከ320 ሃያ ቅዱሳን በላይ ስንክሳር የተጻፈላቸው፣ድንጋይ ተንተርሰው፤ጤዛ ልሰው ግርማ ሌሊትን ጸብአ አጋንንት ታግሰው ስለ ሀገርና ስለ ዓለም ሰላም የሚያለቅሱ አባቶችና እናቶች መናንያን ያሉባትን ቅድስት ቤተክርስቲያን ሲዘልፍ፣ ሲሳደብና ሲያቃልል ምንም ሰው እንደሌለባት አድርጎ በድፍረትና በትዕቢት እንዲጽፍ ያስቻለው ከራስታዎች ጋር ባለው የቅርብ ግንኙነት የተለማመደው ጋንጃ ሳቢነቱና ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደገለጠው ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ ቤተክርስቲያንን ሲዋጋ የኖረው ዲያብሎስ ድፍረት እንደሰጠው እሙን ነው፡፡ይህ ምስኪን ወንድማችን ተረጋግቶ ቆሞ ለማወራት የሚቸገር በሙሉ መዳፉ ማንንም ለመጨበጥ የማይደፍር ከመሆኑም በላይ አንዳንድ ጊዜም እስከ መጦዝና አእምሮን የመሳት ሁኔታ እንደሚገጥመው በቅርብ የሚያውቁት አንዳንድ ወደጆቼ በቅርብ ጊዜ ያጫወቱኝን አስታውሳለሁ፡፡ አባቶቻችንም ከዚህ ጽሑፍ በኋላ ‹‹ዝንቱ ዘመድ ኢይወጽእ እንበለ ጾም ወጸሎት›› በሚለው አምላካዊ ቃል መሠረት በጸሎት እንደሚያግዙትና ከሱስና ከአጋንንት ቁራኝነት ነጻ እንደሚያወጡት ባለሙሉ ተስፋ ነኝ፡፡ ምክንያቱም ቤተክርስቲያን ስለሁሉም ነገር መፍትሔ ያላት ስንዱ እመቤትና ስለ ሁሉ መዳን ሁልጊዜ የምትጸልይ ስለሆነች፡፡ ወንድማችን አሁን እየተጓዘበት ያለው የዲያብሎስ መልእክተኛነት መረገም ነውና ቅድስት ቤተክርስቲያን ደግሞ በጸሎቷና በፍጹም ፍቅሯ ከወታደርነት፣ከዘማዊነትና ከነፍሰ ገዳይነት መልሳ ወደ ጵጵስና እና ወደ ፍጹምነት ማዕረግ እንዲደርሱ የረዳቻቸው በርካታ መሆናቸውን ተረድቶ ወደ ንስሐ እንደሚመለስና የቤተክርስቲያን ጸሎትም እንደሚረዳው ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
በቀጣይ
- ሐራዊው(ወታደሩ)፣ዲጄው፣ሰላዩና ፖለቲከኛው አሉላና ግብረ አበሮቹ በምን ሰንሰለት የሲኖዶስ ስብሰባዎችን ሙሉ መረጃ እንዴት እንደሚያስቀዱ፤
- እነማን አባቶችን በማን ከፋይነት እደተሰደቡ
- ከብጹአን አባቶች መካከል በእነማንና በምን መልኩ ይደገፋሉ
- በግንቦት 2011 ዓ.ም ለገበያ የቀረቡ ብጹአን አባቶችና የቡድኑ አባላት ስለሆኑ ብቻ ሰልፍ፣ ተቃውሞና የገዘፈ ችግር እያለባቸው ስለተንቆለጳጰሱ አባቶች እንዲሁም ሌሎች ወቅታዊ ርእሰ ጉዳዮችን ይዘን እንመለሳለን፡፡
ውድ አንባቢያን! የዚህ የጡመራ መድረክ ዋና ዓላማ ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ወደ ተሻለ ደረጃ ደርሳ የራሳን ጉዳይ ከሲሞናውያን እጅ ነጥቃ በራሷ ልጆችና በራሳ ሚዲያ ብቻ እየገለጠች ማየት በመሆኑ ማንኛውንም ምክር አስተያየትና ግሳጼ ለመቀበል ዝግጁ ነን፡፡
ለሁሉም አምላከ ቅዱሳን ይርዳን!
ቸር ሰንብቱ!
ተጻፈ በሳምኬት ዘሐመረ ብርሃን
ግንቦት 28 ቀን 2011 ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ