ውድ የተዋህዶ ምእመናን እንደሚታወቀው ጥንታዊቷ የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ከተጋረጡባት አሳሳቢ ችግሮች አንዱ በቤተክርስትያን ውስጥ ቁጭ ብለው ፣ በቤተክርስትያን ውስጥ ያለውን አስተዳደራዊ ድክመትና ግልጽ የሆነ የመረጃ ፍሰት አለመኖር እንድ ጥሩ እድል በመጠቀም፣ በምንም አይነት መስፈርት የቤተክርስትያን ልሳን እንዲሆኑ ህጋዊም ሆነ ሃይማኖታዊ ፍቃድ ሳይኖራቸው ለድብቅ አላማቸው ማሳኪያ የሆኑ ዜናዎችን እውነቱን ከውሸቱ በመድበላለቅ ለህዝበ ክርስትያኑ የተዛባ የመረጃ ምንጭ በመሆን የአባቶችን ስም ሲያንቋሽሹ ፤ የቤተክርስትያንን ስምና መዋቅራዊ አሰራር ሲያዋርዱ ማየት የዘወትር ክስተት ሆኖ ማየት የተለመደ ሆኗል።
ከነዚህም ከላይ ከተጠቀሱት የተዛባ የመረጃ ምንጮች / Fake News or Distorted News/ ዋነኛ ሆኖ ቤተክርስትያንን ባሁኑ ሰዐት እያመሳት ያለው ‘ሐራ ዘተዋህዶ’ የተሰኘው ድህረ ገጽ ሲሆን ፤ በቀጣይ ጽሁፋችን ይህን ድህረ ገጽ ከጀርባ ሆኖ በሚስጥር ማን እንደሚያንቀሳቅሰው፤ በግለሰብ ደረጃ እነማን እንደሚሳተፉበትና ያላቸውን ድብቅ አጀንዳ በቀጣይ በዝርዝር የምንመለስበት ይሆናል።